ህወሓት፣ በቀን ገቢ ግምት ግብር ከፋዮች ላይ ያሰበው መጠነ ሰፊ ዘረፋ ላይ በደረሰበት ሰፊ ተቃውሞ ሳቢያ ቀላል የማይባል ኪሳራ ደርሶበታል። በዚህም ምክንያት የማፈግፈግ ምልክቶችን አሳይቷል። ማፈግፈግ የሥርዓቱ ጊዜዓዊ ማምለጫ ነው፤ ሁኔታዎች ሲረጋጉ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም። እንዲያውም ሌሎች ተጨማሪ የዝርፊያ መስሮችን መክፈቱን የማይቀር ነው።
አሁን ተግባራዊ መሆን የጀመረ ድሆችን ይበልጥ የማደህያ አንድ መጠነ ሰፊ ፕሮጀክት እነሆ። በወሊሶ ከተማ የቀበሌ ቤቶች ኪራይ በአንድ ጊዜ ከ 40 - 50 ጊዜ እጥፍ መጨመሩ ኢሳት ገልፆ ነበር።
እንዲህ ዓይቱ ጭማሪ በወሊሶ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኦሮሚያ ከተሞች ወስጥ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኗል።. ለምሳል፣ በወር 10 ብር ይከፈልበት የነበረ ዛኒጋባ ብር 500 እንዲከፈልበት፤ መክፈል የማይችሉ ቤቶቹን እንዲለቁ እንዲደረግ ተወስኗል።
ይህ ውሳኔ በኦሮሚያ ላይ ተወስኖ የሚቀር አይደለም፤ የኦሮሚያው አፈፃፀም ታይቶ ወደሌሎች ክልሎችም መዛመቱ የማይቀር ነው። ስለሆነም ካሁኑ ተቃውሞዓችን አገራዊ መሆን ይኖርበታል።
መጪው 2010 "ለማይወክለን አገዛዝ ግብር ብቻ ሳይሆን ማናቸውንም ክፍያ አንፈፅምም" የሚባልበት ዓመት መሆን ይኖርበታል።
መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ወታደሮችና ፓሊሶች "አንገዛም፣ አንታዘዝም፣ አንከፍልም፣ አንሠራም……" ለማለት ይዘጋጁ።
ጊዜው "የእምቢ አልገዛም! " "የእምቢ አልከፍልም! " ነው።