Netsanet: Juli 2014

Donnerstag, 31. Juli 2014

የአዲስጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ተጨማሪ የ5 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባት

July31/2014

• መኖሪያ ቤቷ በፖሊስ ተበርብሯል

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአንዋር መስጂድ በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የታሰረችው የአዲስጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ሐሙስ ሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም ሜክሲኮ በሚገኘው በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምድብ ችሎት ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር ቀርባለች።

ምርመራውን በማጣራት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ባለፈው ሳምንት የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት ወደአዚዛ መኖሪያ ቤት ተጉዞ ብርበራ ማድረጉ ታውቋል። በዚህ ብርበራ ፖሊስ አዚዛን በጥርጣሬ ከያዘበት ጉዳይ ጋር ተያያዠነት ያለው ማስረጃ እንዳላገኘ ነው ፎቶ ጋዜጠኛዋ የተናገረችው።

ጉዳዩን በማጣራት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ክፍል አዚዛን ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ያቀረባት ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችለው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ግን አምስት ቀን ብቻ በመፍቀድ ለማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አዚዛና ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች እንዲቀርቡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በዕለቱ የተጠርጣሪዎቹን የፍርድ ሂደት ለመከታተል በርካታ ግለሰቦችና ቤተሰቦቻቸው የተገኙ ቢሆንም ችሎቱ ግን በዝግ ተካሂዷል።
ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሰየማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ችሎት አርፍዶ ነበር የተሰየመው።ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ በፍርድ ቤቱ ከመፈቀዱ በቀር አዚዛ በችሎቱ የተጠየቀችው ነገር እንዳልነበር ነው የተናገረችው።

በስፍራው ለስራ ከመገኘቴ በቀር በፖሊስ ሊያሳስረኝ የሚያስችል ምንም የወንጀል ድርጊት አልፈፀምኩም የምትለው ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሃመድ ምንም አይነት ጥፋት ለመፈጸሟ ማስረጃ ባይቀርብባትም ፖሊስ ለቀጣይ 5 ቀናት በእስር ላይ እንድትቆይ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።

አዚዛ እስካሁን በፖሊስ የቀረበባት እና የተጠረጠረችበትን ጥፋት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለመኖሩ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው የጊዜ ቀጠሮ በነጻ ሊያሰናብታት አለያም በዋስ ሊፈታት እንደሚችል ያላትን ተስፋ ለባልደረቦቿ ተናግራለች።

አዚዛ በሚቀጥለው ቀጠሮ ፍርድ ቤት ስትቀርብ የእስር ቆይታዋ 18 ቀናት ይሆናል ማለት ነው።

Addis Guday's photo.

እኛም የሚሊዮኖች አካል ነን። የአንድነት ጉዳይ ያገባናል – ግርማ ካሳ


Commentኢንጂነር ዘለቀ ረዲ፣  ጊዜያቸዉን ወስደው ፣ በአንድነት ዉስጥ እየታየ ያለዉን በሌሎች ድርጅቶች ያልተለመደ፣ ዲሞክራሲያዊ ፉክክርን በመቀላቀል፣ የድርሻቸዉን ለማበርከት በርካታ ጽሁፎችን አስነብበዉናል። ለዚህም ያለኝን ምስጋና እና አድናቆት መግለጽ እወዳለሁ። ከርሳቸው ጋር በግል የተለዋወጥናቸው ሐሳቦች እንደተጠበቁ ፣ በአደባባይ ፣ በፌስ ቡክ ላቀረቡልኝ አንዳንድ ጥያቄዎች ግን ፣ እኔም በአደባባይ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ።
«ምርጫ በአንድነት ዉስጥ ፤ ለአቶ በላይ ፍቃደ ድጋፌን እሰጣለሁ» በሚል ርእስ፣  የመምረጥ መብት ባይኖረኝም፣ እንደ ደጋፊ ሐሳቤን የመግለጽ መብቴን ተጠቅሜ ፣ አቶ በላይን ኢንዶርስ ማድረጌ ይታወሳል።
«በላይ ጠንካራ መሆኑን እንዴት አወቁ ? በእርግጥ እርስዎ አሁን የያዙትን አቋም ቀደም ብለን እኛም ይዘን ነበር። ሆኖም በላይ ምክትል ሆኖ ከተመረጠ በኋላ፣ እኔ ሐሳቤን አንስቻለሁ። የተወሰኑትም እንዲሁ አደርገዋል። ምክንያቱም በስሩ የነበሩትን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የፖለቲካ ጉዳዮችን አንቀሳቅሶ መስራት አልቻለም። ለዚህም ይህ ትንሽ ነገር መምራት ካልቻለ ግዙፉን የአንድነት ፓርቲ ይመራዋል የሚል እምነት የለኝም። የእርስዎ ግምገማም መነሻዉን ባውቀው ደስ ባለኝ ነበር» ሲሉ ኢንጂነር  ዘለቀ ጥያቄ አቅርበዉልኛል።
በጣም ጥሩ፣ ወቅታዊና መጠየቅ ያለበትን  ጥያቄ ነው የጠየቁኝ። ኢንጂነር ዘለቀ ፣  ከስድስት ወራት በፊት፣ በላይ ብቃት አለው የሚል እምነት እንደነበራቸው አልሸሸጉም። «ምክትል ሊቀመንበር ከሆነ ጀምሮ ግን፣ ስራዉን አልሰራም» በሚል ነው ትችታቸው።
በላይን  ያለመምረጥም ሆነ፣ በላይ እንዳይመረጥ የመቀስቀስ ሙሉ መብት አላቸው። አቶ በላይ አንድ ትልቅ ድርጅት ለመምራት ራሱን እጩ ካደረገ፣ ጠንካራ ጥያቄዎች ሊቀርቡለት፣ ሊተች ይገባል። ኢንጂነር ግዛቸውም እንደዚሁ።
ኢንጂነር ዘለቀ፣  ከአንድነት ፓርቲ ጋር የተዋሃደው፣ የቀድሞ የብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ነበሩ። ሁለቱ ፓርቲዎች ሲዋሃዱ፣ ዉህዱን ፓርቲ ለመምራት እጩ ሆነው ከቀረቡ ሶስት እጩዎች መካከል አንዱ ነበሩ። የአዲስ አበባ ምክር ቤት አመራር የነበሩ ዶር ንጋት፣ የተከበሩ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ሁለተኛውና ሶስተኛ እጪዎች ነበሩ። በወቅቱ ኢንጂነር ግዛቸው «ፖለቲካ በቃኝ!  በመምህርነት አገሬን አገለግላለሁ» በሚል እራሳቸውን ያገለሉበትም ወቅት ነበር።
ዶር ነጋሶ ጊዳዳ  በጠቅላላ ጉባኤው ሲመረጡ ፣ ኢንጂነር ዘለቀ ፣ ከአንድ ተፎካካሪ የሚጠበቅ ግሩም ንግግር በማድረግ ከዶር ነጋሶ ጋር አብረው በጋራ እንደሚሰሩ አሳወቁ። በዶር ነጋሶ ካቢኔ ዉስጥም በመመረጥ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆነው መስራት ጀመሩ። እንግዲህ አንባቢያን ተመልከቱልኝ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ያለዉን የዲሞክራሲ ባህል።
የትም ቦታ በሥራ ላይ መጋጨት፣ አለመስማማት አለ። ይሄ ደግሞ ብዙ ሊያስገርመን አይገባም። ያዉም ደግሞ አባላት አስተያየታቸዉን በግልጽ መናገር በሚችሉበት ድርጅት ዉስጥ ፣ ግጭቶች የተለመዱ ናቸው። የግድ አለመስማማቶች መፈጠር አለባቸው። ችግር የሚሆነው አለመስማማቶች፣ ወደ እህልና ግትርነት አምርተው መከፋፈልን ሲፈጥሩ ነው እንጂ። (ኢሕአዴግ ዉስጥ አለመስማማት ሲኖር የበላይ ሆኖ የሚወጣው ቡድን ሌላዉን ወይ እሥር ቤት፣ ወይም ስደት፣ ወይም ካለው ሃላፊነት አባሮ መዋረድ ልማድ እንደሆነ የምታወቅ ነው። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እንደ ሮቦት በሉ የተባሉትን ማለት፣  ጻፉ የተባሉት መጻፍ፣ ግደሉ፣ ደብድቡ ሲባሉ ሕሊናቸዉን እና ኃይማኖታቸውን ሸጠው ሲገድሉና ሲደበድቡ ነው የምናውቀው።)
ኢንጂነር ዘለቀ በሥራ አስፈጻሚው ዉስጥ ሲሰሩ ከዶር ነጋሶ ጋር የመስማማት ችግር አጋጠማቸው። ከድርጅት ጉዳይ ሃላፊነታቸው ተነሱ። ነገር ግን ኢንጂነር ዘለቀ፣  አኩርፈው ፓርቲዉን ጥለው አልሄዱም። በምክር ቤት አባልነት አንድነትን ማገልገል ቀጠሉ።
ከስድስት ወራት በፊት አንድነት ፓርቲ መሪዉን እንደገና የሚመርጥበት ጊዜ መጣ። ዶር ነጋሶ ፣ የእድሜ ጉዳይ አይፈቅድልኝም በሚልና ሌሎች ምክንያቶች እንደማይወዳደሩ አሳወቁ። ሶስት እጩዎች ቀረቡ። የፓርላማ አባልና በወቅቱ የፓርቲው ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በወቅቱ የፋይናንስ ሃላፊ አቶ ተክሌ በቀለ እንዲሁም «ከፖለቲካ ወጥቻለሁ። በቃኝ » ብለው የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው።

በወቅቱ አገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ ያሉ በርካታ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች፣ አቶ በላይ ፍቃደ፣ ደርጅቱን እንዲመራ፣  እንዲወዳደር ጥያቄ አቀረቡለት። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው  ሳይቀሩ «በላይ ድርጅቱን ለመምራት ብቃት፣ ብቻ ሳይሆን እውቀትና ብስለት ያለው ወጣት አመራር ነው » ሲሉ፣  በላይ ቢወዳደር እርሳቸው ወደ ዉድድሩ ይገቡ እንዳልነበረና ድጋፋቸውን ለበላይ እንደሚሰጡ ይናገሩ ነበር። በላይ «አንድ የአንድነት ተራ አባል፣ ከሊቀመንበሩ ያልተናነሰ መስራት የሚችል ነው። እኔ አገሬን እና ፓርቲዬን ለማገልገል የግድ ሊቀመንበር መሆን የለብኝም»  የሚል አስተሳሰብ ያለው፣ ለስልጣን እና ለወንበር የማይሸቀዳደም፣  እርጋታና ትህትና የተሞላበት ሰው ነው። በመሆኑም ኢንጂነር ግዛቸው ሁሉ ጠይቀዉት፣ ለመወዳደር ፍቃደኛ አለመሆኑ፣ የሚያሳየው የዚህን ሰው ትህትና ነው።
የማታ ማታ ኢንጂነር ግዛቸው የአንድነት ሊቀመንበር ሆነው ይመረጣሉ። አቶ በላይ ፍቃደን  እንዲሁም ከርሳቸው ጋር የተወዳደሩትን አቶ ተክሌ በቀለን ምክትል ሊቀመናብርት አድርገው በመምረጥ ስራ ይጀመራሉ። እርስ በርስ ሲፎካከሩ የነበሩ እንደገና አብረው መስራት ጀመሩ ማለት ነው።
ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ባዋቀሩት ካቢኔ  ከተካተቱት መካከል፣ በዶር ነጋሶ ከሥራ አስፈጻሚ እንዲወጡ የተደረጉት፣ በጠቅላላ ጉባኤውም የምክር ቤት አባል ሆነው በድጋሚ የተመረጡት፣  ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ይገኙበታል። ኢንጂነር ዘለቀ፣ በጣም ቁልፍና  ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ሃላፊነት ይሰጣቸዋል። የዉጭ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ሆነው በኢንጂነር ግዛቸው ይሾማሉ። ከስራቸው ዉስጥ በዉጭ ያሉ የድጋፍ ማህበራትን ማሰባሰብና የበለጠ ማደራጀት አንዱና ዋናው ነበር።
የመኢአድ እና የአንድነት ዉህደት ሲጠናቀቅ አዲስ አመራር መኖር ስላለበት፣ የአንድነት ምርጫ በተደረገ በስድስት ወራቱ፣  እንደገና ምርጫ ማድረጉ የግድ ሆነ።
ዉጭ ባሉ ደጋፊዎች ዘንድ አዲስ አመራር የማግኘት ትልቅ ፍላጎትና ጉጉት አለ። ይሄም ኢንጂነር ግዛቸው ላይ ካለ ተቃዉሞ ሳይሆን፣ ኢንጂነሩ ከዘጠና ሰባት ጀምሮ የነበሩ እንደመሆናቸው፣ በቅንጅት ከዚያም አንድነት ዉስጥ ለነበሩ መከፋፈሎች  ተጠያቂ የሚያደርጓቸው ኢትዮጵያዉያን ጥቂት ባለመሆናቸው፣ በአጭሩ ኮንትሮቨርሻል መሪ በመሆናቸው፣ ለዉህዱ ፓርቲና ለትግሉ ከርሳቸው ሌላ አዲስ አመራር  ቢኖር በጣም ጠቃሚ ነው ከሚል አስተሳሰብ ነው።
በዚህም ምክንያት አንድነትም ሆነ ዉህዱ ፓርቲ በውጭ ያሉ ደጋፊዎቹን ከማብዛት አንጻር፣ አቶ በላይ ከስድስት ወራት በፊት የነበረዉን ዉሳኔ ከልሶ፣ እንዲወዳደር ዉጭ ያለው ደጋፊ ግፊት ማድረግ ጀመረ። ይሄ ደግሞ በየትም ዴሞክራሲ ያለ አሰራር ነው። (ትዝ ይለኛል እዚህ አሜሪካ አገር ጀነራል ኮሊን ፓወል፣ ለፕሬዘዳንት እንዲወዳደር፣  ብዙ ግፊት ከየአቅጣጫው ይቀርብለት እንደነበረ)
አገር ቤትም፣ አቶ በላይን በቅርበት የሚያወቁ፣ የጊዜዉን አሳሳቢነት፣ የትግሉን ወሳኝነት በማስመር፣  በነርሱ ዘንድ ያለዉን የአገር ቤት ሁኔታ ጠረቤዛ ላይ በማስቀመጥ፣  የድርሻቸውን ከፍተኛ ግፊት አደረጉ። አቶ በላይ፣ ሊቀመንበር ባይሆንም፣ ለአገሩና ለሕዝቡ ድሮም ሲሰራ የነበረ እንደመሆኑ፣ ፍቃደኛ ሆኖ፣ ሁኔታዎችን አመቻችቶ እጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ቀረበ። ይሄም ለብዙዎቻችን መልካም ዜና ሆነ።
«አንዳንዶች ያኔ አልወዳደርም ብሎ አሁን ለመወዳደር ለምን ፈለገ ?» የሚል ጥያቄ አቶ በላይ ላይ ያነሱ አሉ። እንግዲህ መልሱን ከዚህ ጽሁፍ የሚያገኙ ይመስለኛል። ደግሞ እነዚህ ሰዎች፣  ለአቶ በላይ ይሄን አይነት ጥያቄ ሲያቀርቡ  «ኢንጂነር ግዛቸው ፖለቲካ በቃኝ ብለው በነበረበት ጊዜ፣ ከየት መጡ ሳይባል፣  እንደገና ሲወዳደሩ፣  «ለምን ? ምን ተገኝቶ ?» ብለው ጠይቀዋል ወይ ?  አንዳንድ አስተያየቶች ስንሰጥ፣  ትንሽ ደብል ስታንዳርድ ባይኖረን ጥሩ ነው።
ኢንጂነር ግዛቸው ራሳቸውም በተደጋጋሚ እንዳስረዱት ለሊቀመንበርነት ከስድስት ወራት በፊት የተወዳደሩት፣ ብዙዎች እንዲወዳደር ስለጠየቋቸውና ግፊት ስላደረጉባቸው እንደሆነ ገልጸዋል። « እኔ ተለምኜ ነው። አልፈልግም ነበር» ነበር ያሉት። እዚህ ላይ ምን ችግር የለኝም። ልክ ኢንጂነር ግዛቸው እንዳደርጉት፣ አሁን አቶ በላይ፣  ከደጋፊዎቻቸው የሚቀርብላቸውን ጥያቄ አስተናግደው ፣ ለመወዳደር ቢወስኑ ምኑ ላይ ነው ሐጢያቱ ? አስቡት ኢንጂነር ግዛቸው ከፖለቲካ ዉጭ ሆነው ሳለ ነው በአንዴ ዘለው ሐሳባቸው ቀይረው፣ ሊቀመንበር ለመሆን ብቅ ያሉት። አቶ በላይ ግን  አሁን የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር ነው። ከምክትል ሊቀመንበርነት ወደ ሊቀመንበርነት ለመሸጋገር ነው ራሱን እጩ ያደረገው።
አቶ በላይ እጩ ሆነ እንደቀረበ፣ የአብዛኞቻችን ግምት፣ ከጥቂት ወራት በፊት፣  ስለ አቶ በላይ የተናገሩትን ቃል አክብረው፣ ኢንጂነር ግዛቸው የዶር ነጋሶን ፈለግ በመከተል ራሳቸዉን ከእጩነት ያወጣሉ የሚል ነበር። ነገር ግን እንደገመትነው አልሆነም። ኢንጂነሩ ቃላቸውን ገልብጠው፣ ራሳቸውን ለእጩነት አቀረቡ። ያ ብቻ አይደለም፣ «በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ከስድስት ወራት በፊት ምርጫ ስለተደረገ ፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሳይወዳደሩ በቀጥታ ነው ማለፍ ያለባቸው» የሚል ክርክር ይዘው የተወሰኑቱ፣  ያለ ምርጫ ኢንጂነር ግዛቸውን ለማስመረጥ ዘመቻ ጀመሩ። እነዚህ ወገኖች ያለ ኢንጂነር ግዛቸው ውስጣዊ ስምምነት፣ ኢንጂነር ግዛቸው ያለምርጫ እንዲሾሙ ለማድረግ ይከራከራሉ ብዬ አላስብም። በሌላ አባባል፣ ኢንጂነር ግዛቸው ራሳቸው፣ ሳይመረጡ በቀጥታ ለማለፍ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል ብዬ አስባለሁ።
ከነዚህ የ«ኢንጂነር ግዛቸው ይመረጡ» ዘምቻ አጧጧፊዎች አንዱ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ናቸው። ኢንጂነር ዘለቀ ፣ ኢንጂነር ግዛቸውን ለማስመረጥ በሚጽፉት፣ በሚያደርጉት እንቅስቃሴውች ሁሉ ምንም ቅሬታ የለኝም። ኢንጂነር ግዛቸው እንዲመረጡ በሥራ አስፈጻሚ ዉስጥ፣ በብሄራዊ ምክር ቤቱ፣  በጠቅላላ ጉባኤው እንዲሁም በአደባባይ የመቀስቀስ፣ የመሟገት ሙሉ መብት አላቸው። መብታቸውን ተጠቅመው፣ የዲሞክራሲ ባህሉን ለማሳደግ ለሚያደርጉት ጥረት አመሰግናቸዋለሁ።
እንደ ማንኛዉ የምርጫ ዉድድር፣ የምንደገፈውን ለማስመረጥ ስንል ፣ የማንደግፈው ለምን መመረጥ እንደሌለበት ማሳየቱ የተለመደና ብዙ ችግር የማይፈጠር ነው። ኢንጂነር ዘለቀም፣ ኢንጂነር ግዛቸው እንዲመረጡላቸው ፣ አቶ በላይ ለምን መመረጥ እንደሌለበት ያመላክታል የሚሉትን የራሳቸውን ምክንያቶች በማቅረብ፣  አቶ በላይ ብቃት የላቸዉም የሚለውን መከራከሪያቸውን ለመሸጥ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተገቢና ዴሞክራሲያዊ ነው።  አቶ በላይ ሆነ ደጋፊዎቻቸው፣ የአቶ ዘለቀን ትችና አስተያየት በመረጃና በሐሳብ መመከት እንጂ፣  ቅር መሰኘት ያለባቸው አይመስለኝም። እኔም፣ አቶ በላይን ኢንዶርስ እንደማድረጌ፣  ለምን የኢንጂነር ዘለቀ ረዲ መከራከሪያ ነጥብ፣  ዉሃ እንደማይቋጥር ለማሳየት ልሞከር። የኢንጂነር ዘለቀን ረዲ ሐሳቦች በሐሳቦች ለመመከት ማለት ነው።  (አስቡት እንግዲህ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንዲህ ባለ ሁኔታ ነው በሐሳብ በመፋጨት የሰለጠነ ፖለቲካ እያሳዩን ያሉት)
ኢንጂነር ዘለቀ፣ ስለ አቶ በላይ የብቃት ጉድለት ሲናገሩ፣ በአቶ በላይ ሥር ያሉ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የፖለቲካ ዘርፍ ኮሚቴዎች ሥራ አልሰሩም ከሚል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ኮሚቴዎች ሥራ እየሰሩ ነው የሚል እምነት አለኝ። ኮሚቴዎች ባላቸው አነስተኛ ሪሶርስ፣  የተቻላቸውን እያደረጉ እንደሆነ የሚገልጹ አንዳንድ መረጃዎች አሉኝ። ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሳይሆን፣ አንድነት ከኢሕአዴግ ለምን እንደሚሻል የሚገልጹ አማራጭ ፖሊሲ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያሉ እንደሆነ ሰምቻለሁ። እንዲህ አይነቶቹን ሰነድ ማዘጋጀት ጊዜ ይወስዳል። ተራ ደብዳቤ አይደለም። ምሁራንን ማማከር፣ ምርምሮች ማድረግ፣ ነገሮችን ከሁሉም አቅጣጫዎች መመልክት ያስፈልጋል። (በቅርቡ የነዚህ ኮሜቴዎች የሥራ ዉጤት፣ በአዲሱ የውህዱ ፓርቲ አመራር ዘንድ ቀርቦ፣ ዉይይቶች ተደርጎበት ፣ ተሻሽሎ፣  ይፋ ሲሆን የምናየው ይሆናል)
አልሰሩም ብለን ደግሞ ብንቀበልም እንኳን ፣ የነዚህ ኮሚቴዎች ሃላፊዎችን የሾሙት ኢንጂነር ግዛቸው መሆናቸዉን መርሳት የለብንም። በአቶ በላይ የተሾሙ አይደሉም። ለኮሚቴዎቹ ድክመት ሃላፊነት መዉሰድ ያለባቸው ኢንጂነር ግዛቸው ናቸው። ኢንጂነር ዘለቀ አላስተዋሉትም እንጂ ትችት ያቀረቡት ኢንጂነር ግዛቸው ላይ ነው።
ሌላው ኢንጂነር ዘለቀ  በአቶ በላይ ስር ናቸው ያሏቸውን የኢኮኖሚ፣ የማህበረሰባዊና የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚቴዎች እንደጠቀሱት፣ ሌሎች እንደ ዉጭ ጉዳይ ያሉ ኮሚቴዎችን ቢጠቅሱ ጥሩ ይሆንም ነበር። እስከሚገባኝ ድረስ የዉጭ ጉዳይ ኮሚቴው፣ የሚጠበቅበትን ሥራ ሰርቷል ማለት አይቻልም። የዚህ ኮሚቴ ሃላፊ ደግሞ ፣ አቶ በላይን ሥራዉን አልሰራም ብለው የሚጽፉት ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ናቸው።
አንድ ጠንካራ የአንድነት ደጋፊ ስለ ኢንጂነር ዘለቀ ሲጽፉ « ኢንጂነር ዘለቀ የዉጭ ጉዳይ ሃላፊነት ስራቸውን ትንሽ አይደለም ምንም አልሰሩም» ነበር ያሉት። እኝህ ደጋፊ ሲያክልም «ታዲያ እርሳቸው ምንም ሳይሰሩ ፣ ስንት ሥራ የሰራዉን፣ በወሬና በአሉባላታ ሳይሆ በስራዉ ዉጭ ሆነ አገር ውስጥ ባሉ ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ ያለውን ፣ አንጋፋ የአንድነት አመራርን በአደባባይ ብቃት የለዉም ማለት ነውር ነው» ሲሉ ኢንጂነር ዘለቀ ስለ አቶ በላይ በሰጡት አስተያየት እንደማይስማሙ ገልጸዋል።
አቶ በላይ ፍቃደን፣ ለአንድነት ቅርበት የሌላቸው ወገኖች ላያውቋቸው ይችላሉ። የአንድነት አባላት፣ ደጋፊዎች፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል በቅርበት የሚከታተሉ ግን፣  አቶ በላይን በደንብ ያወቁታል። በተለይም ዉጭ አገር ባሉ የአንድነት ደግፊዎች ዘንድ አቶ በላይ እጅግ በጣም ተወዳጅ ነው።
አቶ በላይ ከሰሩት ጥቂቶቹን  ላካፍላችሁ ( ሌሎች የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ከተሰጡ አስተያየቶች ቀንጨብጨብ አድርጌ)
አቶ አንዱዓለም ወደ ቃሊት ከመወሰዱ በፊት ፣ የአንድነት ፎርም የሚባል ዝግጅት በየጊዜው ይቀርብ ነበር። በዚህ ፎረም፣  በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ዉስጥ የተለያዩ እንግዶች እየተጋበዙ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ሃተታ ያቀርቡ ነበር። ከዉጭ አገርም በስካይፕ ምሁራን እየቀረቡ የሰላማዊው ትግል የሚያደግበትን የተለያዩ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል። የዚህ የአንድነት ፎረም ጀማሪና ዋና አዘጋጅ  አቶ አንዱዓለም አና አቶ በላይ ነበሩ። በዚህ ፎረም ከዉጭ እንደ ዶር መሳይ ከበደ፣ ዶር አክሎግ ቢራራ፣ ፕሮፌሰር ሰይድ፣ አቶ ብርሃነ መዋ፣ ጠበቃ ፍጹም አለሙ፣ አቶ ግርማ ሞገስ የመሳሰሉ ቀርበው የፖለቲካ ሃተታ አቀርበዋል። ከአገር ዉስጥም እንደ እስክንደር ነጋ፣ አሁን በ እሥር ቤት የሚገኙ ዞን ዘጠኖች  የመሳሰሉ ቀርበው ስልጣና ሰጥተዋል።
ሁላችንም መቼም የአንድነት ልሳን የነበረችውን የፍኖት ጋዜጣ እናስታወሳታለን። ይች ጋዜጣ መዉጣት እንድትጀመር  በዋናነት ያደረገው በላይ ፍቃዱ ነው። የጋዜጣው የኢዴቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢም ሆኖ አግልግሏል። ጋዜጣው በወያኔ መታተም ሳትችል ስትቀር ፣ አንድነት የራሱ ማተሚያ እንዲኖረው ለማድረግ ፣ ለዚህ ጉዳይ ከተቋቋመው የፍኖት ግብረ ኃይል ጋር በመተባባበር ገንዘብ እንዲሰበሰብ አድርጎ፣ የማተሚያ መሳሪያዉ ተገዝቷል። በኢትዮጱያ የመብራት ችግር ስለሌለና አገዝዙ የአንድነት ጽ/ቤትን የኤሌትሪክ መስመር ሆን ብሎ ብዙ ጊዜ ስለሚቆርጥ፣ ለማተሚያ ሥራ ጅኔሬተር በመግዛት የሕትመት ሥራው የሚጀመርበት ሥራ ለማፋጠን ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
የአምስቱ አመት ፓላን በሚል ሰፊ ሰነድ መዘጋጀቱ ይታወቃል። ይህ ሰነድ ለድጋፍ ድርጅቶች ተልኮም አንብበነዋል። ይህን ሰነድ ካዘጋጁት ወገኖች መካከል አንዱ አቶ በላይ ነው። (ምናልባትም ኢንጂነር ዘለቀ ያኔ የአንድነት አመራር ስላልነበሩ ላያውቁት ይችሉ ይሆናል)
የአንድነት ፓርቲ ተቀባይነት ከፍ ካደረጉት እንቅስቃሴዎች መካከል በዋናነት እና በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ነው። ይህ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ፣  ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ከፖለቲካው ወጥቻለሁ ባሉበት ወቅት፣ የተከበሩ ዶር ነጋሶ አንድነትን ሲመሩ ፣ የተጀመረ እንቅስቃሴ ነው። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት የተሰኘዉን የመጀመሪያዉ ዙር እንቅስቃሴ ፣  ከሚመሩትና ከሚያስተባብሩት አመራር አባላት መካከል በዋናነት የሚቀመጠው በላይ ነበር።
የተለያዩ ጉዳዮች ሲነሱ፣ በራዲዮኖች ፣ ቴሌቭዥኖች፣  ፓልቶክ ክፍሎች በመቅረብ፣ የአንድነት ደጋፊዎች በሚያዘጋጁት ዝግጅቶች ላይ በስካይፕ በመገኘት፣ የአንድነት ራእይና ተልእኮ በሚገባ የገለጹ፣  ጠንካራ የአመራር አባል ናቸው። እስቲ አቶ በላይ አንድ ወቅት ፣ አሁን በማእከላዊ ከሚገኘው፣ ሌላው አንጋፋ የአንድነት አመራር ጋር በኢሳት ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እንስማ። ረጋ ያለ፣ ማሳመን የሚችል፣ የሚናገረዉን የሚያወቅ አመራር እንደሆነ እናያለን።
እንደ እኔ ግምት፣  ትግሉ በአሁኑ ወቅት አዲስ ፣ የበሰለ፣ ባጌጅ የሌው አመራር ይፈልጋል። ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ እየተመለስን መጎተት አንፈልግም። በድጋሚ የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ድምጻቸውን ለአቶ በላይ ፍቃደ እንዲሰጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
አገር ውስጥ ባሉ በከፊል ፣ ዉጭ ባሉ ደጋፊዎች ዩናኒመስሊ ማለት ይቻላል የማይደገፉ፣ ኮንትሮቨርሻል የሆኑ ሊቀመንበር መርጠው፣  አንድነት ሆነ ዉህዱ ፓርቲ ትግሉን ወደፊት ለማስኬድ ያለዉን ብቃት እንዳያሽመደምዱ እመክራለሁ።
እኔም ሆንኩኝ ሌላው ተራ ደጋፊ፣ አስተያየት መስጠት እንጂ መራጮች አይደለንም። የአንድነት፣ የዉህዱ ፓርቲ፣ የትግሉን አቅጣጫ የሚወስኑት አገር ቤት ያሉት፣  የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች የሆኑት እንደ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ናቸው። በሥራቸው አልገባንም። እነርሱን ለማዘዝና ለመጫን መብትም የለንም፤ አልሞከርንምም። ነገር ግን  አንድነት፣  የሚሊዮኖች ንቅናቄ የሚመራ፣  ሚሊዮኖች እያሰባሰበ ያለ እንደመሆኑ፣  «እኛም የሚሊዮኖች አካል ነን። የአንድነት ጉዳይ ያገባናል» በሚል ነው አስተያየት የምንሰጠው።
በዚህም አጋጣሚ፣ ኢንጂነር ግዛቸው ከዚህ በፊት የተናገሩትን  ቃል አክብረው፣ አመራሩን ለአዲሶች በማስረከብ የዶር ነጋሶን ጊዳዳ ፣ የዶር ኃይሉ አርአያን፣ የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ .. ፈለግ እንዲከተሉ በድጋሚ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ሦስት የኢቴቪ ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሥራቸው ለቀቁ Thee ETV senior officials resigned

በ ፍሬው አበበ (ሰንደቅ ጋዜጣ)
በርካታ ጋዜጠኞች በለውጡ ደስተኞች ሆነዋል
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (የቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት) ሦስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቅርቡ ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የወቅታዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ አሸብር ጌትነት፣ የትምህርታዊ ፕሮግራሞች ክፍል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ተመስገን ገ/ህይወት፣ የመዝናኛ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ፍቅር ይልቃል በወራት ልዩነት ድርጅቱን መልቀቃቸው ታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ከጥር ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ከኃላፊነታቸው ተነስተው በኢቴቪ ከተሾሙ በኋላ የድርጅቱን የአሠራር ሥርዓት ለማስተካከል የወሰዱት ጠንካራ እርምጃዎች በኃላፊዎቹ እንዳልተወደደ ምንጮች ተናግረዋል።
በኢቴቪ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የሚደረጉ የውጪ አገር ጉዞዎች በጥቂት ግለሰቦች ሞኖፖሊ ብቻ ተይዞ የቆየ ሲሆን፤ አዲሱ ዳይሬክተር ይህን አሰራር በመሰረዝ የሚመለከታቸው ሪፖርተሮች በየተራ ተመድበው እንዲሰሩበት ማድረጋቸው፣ አንዳንድ ኃላፊዎች የጥቅም ግጭት በሚያስከትል መልኩ ኢቴቪ ውስጥ እየሰሩ በግል ድርጅታቸው አማካይነት ሥራዎችን ለመወዳደር ማመልከታቸውና ይህም ተቀባይነት ማጣቱ፣ እንዲሁም ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍት የነበሩ አሰራሮች እየተዘጉ መምጣታቸው ኃላፊዎቹን ሳያበሳጭ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
አንድ የድርጅቱ ባልደረባ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገረው፤ አዲሱ ማኔጅመንት ሥር ነቀል ለውጥ እያደረገ መምጣቱ በአብዛኛዎቹ ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ዘንድ ድጋፍ ማግኘቱን ተናግረዋል። አንዳንድ ኃላፊዎች ያለ ችሎታቸው ጭምር ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታ እንደነበርና ይህም በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ይህ ሁኔታ አሁን እንዲስተካከል መደረጉ አስደስቶናል ብለዋል። በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ውስጥ የሚካሄደው ለውጥ በዚሁ ከቀጠለ በቀጣይ ሕዝባዊ ሚዲያ ለመፍጠር የሚያስችል ይሆናል ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝን በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
    ባለፈው ሰኔ ወር አጋማሽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ እንዲያድግ የሚደነግገውን አዋጅ ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል።

Mittwoch, 30. Juli 2014

የግል ሚዲያው “በፀረ ሽብር ህግ” ሊበላ ይሆን? [ኣቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ]

July 30/2014
የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ፡፡ የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም፡፡ በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር፡፡ ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል፡፡ የዘጋቢ ፊልሞቹ ዋና ግብ “የኢህአዴግን አብዮታዊ ዲሞክራሲን መንገድ አምነው ያልገበሩ የግል የሚዲያ ተቋማትን ለማጥፋት ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡” የግል ሚዲያውን ማጥፊያ መንገዶች ሁሉን አቀፍ ናቸው፡፡ በዋነኝነት ኤኮኖሚያዊ የሚባለው ሲሆን ይህም በምንም ሁኔታ ከመንግስት ወይም “ከልማታዊ ባለሀብቶች” ገንዘብ እንዳያገኙ ማድረግ ሲሆን ከአንባቢ የሚሰበሰቡትንም ገንዝብ ለእዕትመቱ ቀጣይነት እንዳይመች የሚቻለውን ቀዳዳ ሁሉ መዝጋት፤ ይህ የማይሳካ ቢሆን በአሰተዳደራዊ ዘርፍ እንዲወሰድ የተቀመጠው ፍርድ ቤትን በመጠቀም ጋዜጠኞችን ማስር ነው፡፡ ይህ በመጨረሻ የተቀመጠው አማራጭ የውጭ ሀይሎች የማይቀበሉትም ቢሆን መጠቀም ሲያስፈልግ መጠቀም ግድ ነው፡፡ ይህ ሃሳብ የኔ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ አይደለም፡፡ አቶ መለስ ዜናው አዘጋጅተውት ኢህአዴግ የሚባለው ፓርቲ እንደ መርዕ ተቀብሎት አሁን በአቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የገዢነት ዘመንም የሚቀጥል የሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር የራዕይ ክፍል ነው፡፡ ይህን ራዕይ አላስቀጥልም ሚዲያ በዓለም ተቀባይነት ባለው መስፈርት አራተኛ መንግሰት እንዲሆን አደርጋለሁ ይሉናል ብለን ብንጠብቅም ሊሆን የቻለ ነገር የለም፡፡
ለዚህም ማሳያው ባለፈው ሳምንት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ ክሱም በቀጣይ ዝም ብሎ ተራ ክስ እንደማይሆን ምልክቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዜጎችን አሸባሪ በማለት ክስ በመመስረት ታዋቂ የሆኑት ግለሰብ በዋና ተዋናኝነት የቀረቡበት ሲሆን ይህ ዘጋቢ ፊልምም ለቀጣይ ለሚያዘጋጁት ክስ መንደርደሪያ ሊሆናቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ በሽብርተኝነት የሚከሰሱ ሚዲያዎችና አምደኞች እንደሚኖሩ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እዚህ አካባቢ እስክንድር፣ ርዕዮት፣ ውብሸት ሰለባ የሆኑለት የግል ሚዲያ ተሳትፎና ሃሳብን የመግልፅ ነፃነት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ሀቃቢ ህጉ ከሰጡት አሰተያየት ሳይሆን ስንት ሰው ከሰው ወህኒ የወረወሩበትን አዋጅ ሰም በትክክል መጥራት አለመቻላቸው ነው፡፡ ለነገሩ “የሽብር ህጉ” እያሉ ሲጠሩት ትክክለኛ የተፃፈ ስሙ ባይሆንም እውነተኛ ምግባሩን ግን መግለፁን አልዘነጋሁትም፡፡ በተደጋጋሚ “የሽብር ህጉ” እያሉ ሲጠሩት አዘጋጁ ጋዜጠኛም አውቆ መሆን ይኖርበታል ይህን ክፍል ማስተካከል ያልቻለው፡፡ የውስጥ አርበኝነት ይሆን ብለን ታዝበን ከማለፍ አንባቢም ልብ ካላለው ለማስታወስ ብዬ ነው፡፡ ይህ “የሽብር” ያሉትን ህግ መቼ እንደምንገላገለው ባናውቅም ግብሩ ግን አሸባሪነት መሆኑ ተገልፆልናል፡፡
የብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ ቀደም ሲልም ከበላያቸው ለስሙ ኃለፊ የነበረ ቢሆንም በመሰሪያ ቤታቸው አድርጊ ፈጣሪ እንደ ነበሩ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ እርሳቸው ከሰጡት ውስጥ ድንቅ የሆነብኝ ግን 45 ሺ ታትሞ ሁለትና ሶሰት ሺ ነው የሚሸጠው የሚለው ክፍል ነው፡፡ ከዚህ ቀጣይ ያለው ነገር ግልፅ ነው፡፡ ክቡርነታቸው እንደነገሩን እነዚህ ጋዜጦች የሚደጉማቸው አንድ ኃይል አለ የሚል ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ አምደኛ ሆኜ እንኳን አንድ መፅሄት በነፃ እንደማልወስድ እግረ መንገዴን ብነግራቸው ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ቅዳሜ ሳልገዛ ካመለጠኝ እሁድ ከገበያ ላይ እንደማላገኝው ልባቸው ያውቀዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለብሮድክሳት ባለስልጣኝ ሃላፊ ሁለት ሺ ኮፒ ለኢህአዴግ አባላትም እንደማይበቃ አልተረዱትም፡፡ በዚህ ክፍል አንባቢ እንዲረዳልኝ የምፈልገው አንድ እውነት ከሻቢያ፣ ከግብፅ፣ ከግንቦት ሰባት፣ ወይም አንድ የውጭ ሀይል የሚል ክስ ታሳቢ መደረጉ ነው፡፡ ክሱ ልክ መሆኑ አያስጨንቃቸውም ማንን ፈርተው ልክ እንዲሆን ይጨነቃሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ስንወያይ አንድ ወዳጄ ያለኝን ማንሳት ይጠቅማል፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተሰብ ዘመድ የሚባል የላቸውም ወይ? ይታዘበናል አይሉም ወይ? ነው ያለኝ፡፡ እኔም ደገምኩት አፈርኩ ለእናንተ ስል ብዬ፡፡
ለነገሩ እነዚህ ጋዜጦች በዚህን ያህል ዝቅተኛ ኮፒ የሚሸጡ ከሆነ መንግሰት የሚባል አካል ለምን ተሸበረ? ለምንስ ዘጋቢ ፊልም መስራ አሰፈለገው? ብለንም ልንጠይቅ እንገደዳለን፡፡ ሌላው ጥያቄ ደግሞ እነዚህ የውጭ የሚባሉ ሀይሎች የማይሸጥ ጋዜጣና መፅሔት ታትሞ ቢቀመጥ የሚያስቡተን ሀገር የመበተን ሴራ እንዴት ይሳካል ብለው ነው ድጋፋቸውን የሚቀጥሉት? ብለን ጠይቀን እንለፍ፡፡
ሌላው አስቂኝ ክስ ደግሞ “አሻጥረኛ አከፋፋዮች” የሚለው ነው፡፡ አቶ ሽመልስ ከማል አዲሰ ዘመን ከገበያ ልትወጣ የተቃረበችው በእነዚህ አሻጥረኛ አከፋፋዮች ሴራ እንደሆነ ምክር ቤት ቀርበው ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢዲስ ዘመንን ይዘት ማስተካከል ሲያቅታቸው የመጣላቸው ሰብብ አድርገን መውሰድ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ዋናው ግብ አከፋፋዮችን በይፋ በማውገዝ ለቀጣይ እርምጃ ማዘጋጀት ነው፡፡ እነዚህ አከፋፋዮችን ማጥፋት ደግሞ የግል ሚዲያ ዕትመቶች ወደ ህዝብ እንዳይቀርብ ማድረጊያ ወሳኝ መንገድ ተብሎ እየታሰበ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የዚህ ክስ ተጋሪ የሆኑት አቶ እውነቱ በለጠ የኮሚኒኬሽን ሚኒሰቴር ዴህታ ናቸው፡፡ የአቶ ሽመልስን አሳበ በመጋራት በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ተመሳሳይ ሃሳብ አንፀባርቀዋል፡፡ ሰለዚህ የመንግሰት ኮሚኒከሽን ሚኒሰትር መሰሪያ ቤት የግል ሚዲያውን የሚያሽከረክሩት ዋናኛ ሞተሮች “አሻጥረኛ አከፋፋዮች ናቸው የሚል ስምምነት ላይ መድረሱን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ከዚያስ …… ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡
እነዚህ ከላይ የተቀሰኳቸው ሁለት የመንግሰት ተቋማት በግብ ከመስማማታቸው ውጭ የሚያቀርቡት ሃሳብ ግን ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆነ አይረዱትም፡፡ በእነዚህ ሁለት የመንግሰት ተቋማት ውስጥ የግል ሚዲያውን በማጥፋት ዙሪያ ስምምነት አለ፤ ሁለቱም በየፈርጃቸው ግን ሊወስዱ ያሰቡት መንገድ የተለያየ እና የሚቃረን ነው፡፡ የብሮድካስት ባለስልጣን ዕትመቶቹ አይሸጡም፤ እነዚህ ሚዲያዎች በውጭ ሀይል ድጋፍና ዕርዳት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩት ይላል፡፡ የመንግሰት ኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ደግሞ እነዚህ የግል ሚዲያዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲታተሙ እና እንዲሰራጩ የሚያደርጉት አከፋፋዮች ናቸው፡፡ የመንግሰት ልሳን እንዳይሽጥ በማድረግ ጭምር እያሉን ነው፡፡
አቶ ብርሃኑ አዴሎ “በፀረ ሽብር አዋጅ” ዝግጅት ወቅት የነበራች የሞቀ እና ሰሜት የተሞላበት ተሳትፎ ታይቶ ለዘጋቢ ፊልም መቅረባቸው አንዱ ቢሆንም የሀቃቢ ህጉን በዘጋቢ ፊልም ላይ ያደረጉትን ንቁ ተሳትፎ ወስደን ጉዳዮን ስናየው በቀጣይ ክሱ “የሽብርተኝነት” እንደሚሆን መጠርጠር ብቻ ሳይሆን መዘጋጀትም ይኖርብናል፡፡ እግረ መንገዳቸው ግን አማረልኝ ብለው ያነሱትን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ቋሚ አምደኛ መሆን ትክክልም ተገቢም እንዳልሆነ ለማስረዳት የሄዱበት ርቀት ነው፡፡ ዝም ብሎ ለማስታወስ ያህል በአዲስ ነገር ጋዜጣ የኢህአዴግ አባል የሆነ ቋሚ አምደኛ ነበር፡፡ ይህ ጋዜጣ ግን በመንግሰት ጥርስ ተነክሶበት ከገበያ የወጣ፤ ምርጥ ልጆቹም የተሰደዱበት ነው፡፡ በአቶ ብርሃኑ አዴሎ አመክንዮ ከሄድን ኢህአዴግና አዲሰ ነገር ግንኙነት ነበራችው ልንል ነው? እኔ በምፅፍበጽ ፋክት መፅሄት ላይ አባል የሆኑኩበትን ፓርቲ እያብጠለጠሉ ይፅፋሉ፤ በግሌ የፖለቲካ አቋሜንም ሆነ ማህበራዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ምልከታዬን አሰፍራለሁ አቶ ብርሃኑን ጨምሮ ብዙ እንባቢዎች እንዳሉኝ ከሚደርሰኝ መረጃ አውቃለሁ፡፡ ይህ እኔ አባል የሆኑኩበት ፓርቲና ሚዲያውን ምን ያገናኛቸዋል፡፡ አንድ እውነት ግን አለ፡፡ ይህውም የህዝብ ሚዲያዎች በኢህአዴግ ታግተው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እኩይ አስተሳሰብ ማረጋቢያ የሆኑ ሲሆን የተገፉት ደግሞ አማራጭ አሳቦችን ለማቅረብ አሁን የግል ሚዲያዎች ምቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ብዙ ሚሊዮን ተመልካች እንዳለው እናውቃለን፡፡ እድሉን ብናገኝ ከ20 ሺ ኮፒ በላይ በሳምንት ከማይታተሙ መፅሄቶች ይልቅ ኢቲቪን እንመርጥ ነበር፡፡ የተዘረፈው የህዝብ ሚዲያ ለህዝብ ጥቅም የሚውልበት ቀን እሰኪደርስ ግን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ይህ ምርጫ ሳይሆን ተገደን የገባንበት ነው፡፡ የግሉ ሚዲያ ለጊዜው የተገፉትን መወከሉ ስህተት የለበትም፡፡ ይልቁንም ሊበረታት የሚገባው ነው፡፡
ኢህአዴግ የህዝብ ውሳኔ የማይቀበል ፓርቲ እንደሆነ ዋነኛ ማሳያ ሊሆን የሚችለው አሁን በግል ሚዲያዎች ላይ የያዘው አቋም ነው፡፡ ያለምንም ጥርጥር አሁን በገበያ ላይ ያሉት ዕትመቶች በገበያ ላይ እንዲኖር የኑሮ ሸክሙን አቻችሎ በውድ ጋዜጣና መፅሄት የሚገዛ ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ደግሞ ለግል ሚዲያው የድጋፍ ድምፅ እየሰጠ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ የማይፈልገውን መፅሄት በገንዘቡ ገዝቶ ቤቱ የሚገባ ጅል አይደለም፡፡ አንዳንዱ መፅሄት ሲገዛ ለታሪክ ጭምር የሚቀመጥ ብሎ ነው፡፡ ኢህአዴግ በዚህ ጉልበቱ ይህን የህዝብ ድምፅ ሊያሸንፍለት የሚችል ሚዲያ ሊያዘጋጅ አልቻለም፡፡ ስለዚህ አሁን የያዘው መንገድ እነዚህን የህዝብ ድምፆች ለማፈን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ የህዝብ ድምፆች ደግሞ እንዲታፈኑ የተፈለገው ከቀጣይ ሁለት ሺ ሁለት ምርጫ ጋር ተዳምሮ ካደረበት ስጋት የሚመነጭ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አሁን በቅርቡ የሚደረገው የደሞዝ ጭማሪ የግል ሚዲያዎችን ተገዢነት እንደሚጨምረው ይገመታል፡፡ ምክንያቱም ብዙ የመንግሰት ሰራተኞች ሊኖራቸው የሚፈልጉትን መፅሄት መግዛት ባለመቻላቸው በማንበብ ብቻ ተገድበው ነበር የሚል እምነት ስለአለኝ ነው፡፡
ቸር ይግጠመን

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሕወሓት መንግስት በአንዳርጋቸው ላይ ላወጣው ቪዲዮ ምላሽ ሰጡ

July29/2014

የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሕወሓት መንግስት ከ3 ቀን በፊት በቲቪ በማሳየት ላቀረበው ቪድዮ ምላሽ ሰጡ። ቪድዮው የተዘጋጀው የሰውን አንገት ለማስደፋትና ለፕሮፓጋንዳ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ብርሃኑ በአቶ አንዳርጋቸው እጅ ምንም ዓይነት ምስጢሮች እንደሌሎ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ሰጥተውታል ለተባለው ፓስወርድም “የኦፕሬሽናል ጉዳዮችን የያዘ ፓስወርድ አይደለም፤” ያሉት ዶ/ር አንዳርጋቸው የሰጠው ፓስወርድ የተለያዩ ጥናቶችን የያዘ እንጂ ወያኔ ቢያገኘውም ባያገኘውም ምንም የሚጎዳ ነገር አይደለም ብለዋል። ዶ/ሩ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በኢሳት ቲቪ የተነጋገሩበት ቪድዮ ይኸው።

Dienstag, 29. Juli 2014

ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ አገር ጥሎ ተሰደደ

July29/2014
“በደህንነቶች የሚደርስብኝን ጫና መቋቋም አልቻልኩም”
በ“ሰንደቅ” ጋዜጣ ላይ ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አዘጋጅነት ድረስ የሰራውና በቅርቡ የተመሰረተው “የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ” የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ አገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት ጀምሮ የደህንነት ኃይሎች ሲያደርጉበት የነበረውን ክትትል ተቋቁሞ ስራውን ሲሰራ እንደነበር የጠቆሙት ምንጮች፤ ዘንድሮ ከጥቅምት ወር ጀምሮ አዲስ በተመሰረተው የጋዜጠኞች ማህበር (ኢጋመ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ግን የደህንነቶቹ ክትትልና ወከባ እረፍት እንደነሳው ተናግረዋል፡፡ የማህበሩን መመስረት አስመልክቶ ከማህበሩ ፕሬዚዳንት ከጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ ጋር ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ቃለ-ምልልስ ከሰጠ በኋላ በደህንነት ሰዎች መዋከቡ እንደተባባሰ የገለፁት ምንጮች፤እነዚሁ ደህንነቶች የሚሰራበት ተቋም ድረስ በመሄድ ስለማህበሩ መረጃ እንዲሰጥ አሊያም ማህበሩን እንዲለቅ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡትና በዚህም ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ከማህበሩ ለመራቅ መገደዱን ጠቁመዋል፡፡ 
ዘንድሮ በመጋቢት ወር ላይ በኬኒያ ናይሮቢ ለጋዜጠኞች በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ተካፍሎ ከተመለሰ በኋላ ከሌሎች የኢጋመ አመራር አባላት ጋር በ “አርቲክል 19” የሰለጠነ በማስመሰል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሽብርተኝነት ከተወነጀሉት መካከል አንዱ ሆኖ መውጣቱ ስጋቱን ይበልጥ እንዳባባሰበት የገለፁት ምንጮች፤ በደረሰበት ከፍተኛ ጫናም ለአጭር ጊዜ ከማህበሩ ጋር የነበረውን ግንኙነት አቋርጦ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ 
በቅርቡ ደግሞ ማህበሩ ያካሄደውን ውይይት ተከትሎ የማያውቃቸው ሰዎች “በዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ላይ እንድትመሰክር እናደርጋለን፤ ካልሆነም መታሰረህ አይቀርም” በሚል እንዳስፈራሩት ምንጮች ጠቁመው፤ በዚህም የተነሳ አገሩን ጥሎ መሰደዱን ገልፀዋል፡፡ 
የጋዜጠኛ ዘሪሁንን መሰደድ በተመለከተ ያነጋገርነው የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ፤ ጋዜጠኛው መሰደዱንም ሆነ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እንደማያውቅ ጠቁሞ፤ ከ10 ቀን በላይ በስራ ገበታው ላይ ባለመገኘቱና ስልኩ ዝግ በመሆኑ፤ ወደ ስራ ገበታው እንዲመለስ የሚገልጽ ደብዳቤ በዝግጅት ክፍሉ መለጠፉን ተናግሯል፡፡ 
ጋዜጠኛ ዘሪሁን ምንም ሳይናገር አድራሻውን በመሰወሩ፣ ሲጨነቁ መሰንበታቸውን ዋና አዘጋጁና የሥራ ባልደረቦቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

Montag, 28. Juli 2014

ኦሮሞ እና እስልምና በ“ሕዳሴ አብዮት” መስመር (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

July28/2014


በወርሃ-ግንቦት ላይ ለዘመናት የተንሰራፋውን ሀገራዊ ደዌ ይፈውሳል ብዬ ተስፋ ስለማደርግበት “የሕዳሴ አብዮት” በሶስት ተከታታይ ክፍሎች ለመዳሰስ መሞከሬ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ መጪው የ “ሕዳሴ አብዮታችን” መፍትሔ ሊሰጥባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መሀል በዋነኝነት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማሕበረሰብ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የመብት ጥያቄን በተመለከተ በጥቅሉ ጠቃቅሼው አልፌ ነበር፡፡ ሆኖም ‘ሰፋ ብሎ ቢዳሰስ’ የሚሉ በተለያየ መንገድ የሚቀርቡ ጎትጓች ድምፆች መበራከታቸው የመነሻ ሃሳቡን ፈታ አድርጌ እንዳቀርብ አስገድዶኛል፤ እንግዲህ ይህ ጭብጥም የዛው ተከታይ መሆኑ ይሰመርልኝ፡፡

የኦሮሞ ጥያቄ'

በኢትዮጵያችን ከሚገኙ በርካታ ብሔሮች መካከል አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው ኦሮምኛ ተናጋሪው ቢሆንም፣ ለዘመናት ይደርሱበት ከነበሩ ሥርዓታዊ በደሎች እና የባሕል ጭፍለቃዎች ዛሬም በምልአት ነፃ እንዳልወጣ በቂ ማሳያዎች አሉ፡፡ በ1960ዎቹ አጋማሽ የአገሪቷ አደባባዮች የዘመኑን መንፈስ በተረዱ ቁጡ ወጣቶች መጥለቅለቁን ተከትሎ፣ ‹በንጉሣዊው አገዛዝ ግብዓተ-መሬት ላይ የመጨረሻዋን ድንጋይ ለማስቀመጥ› በሚል ሰበብ ቤተ-መንግስቱን መቆጣጠር የቻለው ወታደራዊው ደርግ፣ ህልቆ መሳፍርት በሌለው መስዋዕትነት የተገኘውን ወርቃማ ዕድል ከጅማሮው አጨናፍጎታል፡፡ በግልባጩ አብዮቱን ካጋሙት ገፊ-ምክንያቶች ዋንኞቹ ለሆኑት የብሔርና የሕዝባዊ መንግስት ምስረታ ጥያቄዎች፣ መፍትሄ ይስጥ አይስጥ እስኪረጋገጥ ድረስ መታገስ ያልፈለገው ህወሓት፣ ጉዳዩ በደም መፋሰስ ብቻ እንደሚፈታ አውጆ ጫካ ሲገባ አዲሱ መንግስት ገና የ6 ወር ጨቅላ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ይሁንና ታሪክ በአስከፊ መልኩ ራሱን ሲደግም ያስተዋልነው ወታደራዊውን መንግስት መንፈቅ-ዓመት ያህል እንኳ መታገስ ያልፈቀደው ይህ ቡድን፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ሳይሰጥ ከሁለት አስርታት በላይ ያለመንግራገጭ በሥልጣን ለመቆየት ባለመቸገሩ ነው፤ ርግጥ የእኔ ትውልድም የእድሜውን እኩሌታ በትግስት መጠበቁ የአደባባይ እውነታ ቢሆንም፣ ተጨማሪ የቻይነት ዓመታት ይኖራሉ ብዬ ግን አላስብም፤ አብዮቱን ምኩንያዊ የሚያደርገውም ይህ ነው፡፡

…እነሆም ከአራት አስርታት በላይ ሲንከባለሉ የቆዩት የኦሮሞ ጥያቄዎች በ“ሕዳሴ አብዮት” ይፈቱ ዘንዳ፣ ሊተኩርባቸው የሚገቡ አንኳር አጀንዳዎችን በሁለት አውድ ከፍለን እንመለከታለን፡፡


ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ጥያቄዎቹን ከወረቀት ድንጋጌ (ከአፋዊነት) እና ከፕሮፓጋንዳ ሽንገላ ባለፈ፣ እውነተኛ መፍትሔ በሚያስገኝ መልኩ እልባት ሊያበጅላቸው አልፈቀደም፤ ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ‹‹አነበርኩት›› የሚለው ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም የይስሙላ ስለመሆኑ ለመገንዘብ፣ ዛሬም ከደርዝን በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች የራስ አስተዳደር ጥያቄን አንግበው በትግል መድረክ መገኘታቸውን ማየቱ በቂ ነው፡፡ የክልሉ ‹‹ገዥ›› እንደሆነ የሚነገርለት ኦህዴድም ቢሆን፣ የህወሓቱ የአማርኛ ክንፍ እንደሆነው ብአዴን ሁሉ፣ የኦሮምኛ ክንፍ ከመሆን አለማለፉን፣ የብሔሩ ልሂቃንን ጨምሮ የፌደራል ሥርዓቱን አወቃቀር ያጠኑ በርካታ ምሁራን ማስረጃ እያጣቀሱ ያጋለጡት እውነታ ነው፡፡ ሕዝቡም በየጊዜውና በየአጋጣሚው የሚያነሳው ጥያቄ አሁንም ተግ አለማለቱ የልሂቃኑ ማስረጃ መሬት መርገጡን ያስረዳል፡፡ በቅርቡ አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ስለሕጋዊነቱ በድፍረት የደሰኮረለት የማስተር ፕላኑ ጥያቄ በኃይል መጨፍለቅም በገዥው በኩል ሕገ-መንግስቱ አፈር ለብሶ እንዳበቃለት ተናግሮ አልፏል፡፡በተጓዳኝ የክልሉ ነዋሪ በተፈጥሮ ሀብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆንና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይኖር ከመደረጉ ባሻገር፤ ከሕዝቡ ቁጥር ብዛት አኳያ ኦሮምኛ በሁለተኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋነት እንዲያገለግል ኦህዴድ ተፅእኖ የሚፈጥር አልሆነም፤ ሌላው ቀርቶ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያነሱ ፖለቲከኞች ‹‹ኦነግ›› ተብለው የምድር ፍዳቸውን ሲቀበሉ የታደጋቸው የለም፡፡ የዚህ እኩይ ድርጊት ተጠያቂም ጉልበተኛው ህወሓት ብቻ ነው ማለት ገራገርነት ይመስለኛል፤ የገዛ ወገኑን አሳልፎ የሰጠው ኦህዴድም ጭምር የድርሻውን መውሰዱ አይቀሬ ነውና፡፡ ይህም ሆኖ ከአንዳንድ ምልክቶች በመነሳት ጥያቄዎቹ መልስ እስካላገኙ ድረስ፣ የቱንም ያህል የእስር ቤት ደጃፎች ከዚህም በላይ ቢጨናነቁ፣ የቱንም ያህል የእስረኞቹ ሰቆቃ እያደር ቢበረታ ከእንግዲህ በኦሮሚያ ምድር በፍርሃት ዝም-ጭጭ ብሎ የሚተኛ ሊኖር እንደማይችል ዛሬ ላይ ቆሞ መናገሩ ‹‹ሟርተኛ›› አያስብልም፡፡


የኦሮምኛ ተናጋሪውን ያደረ ቅራኔ በመፍታት የአንድነት ዘብ ለማድረግ፣ የሀገሪቱ ታሪክ እና ባሕል በዳግም ብያኔ መታደሱ ግድ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የክልሉ ማሕበረሰብ በዘመናዊው መንግስት ምስረታም ሆነ ከባእድ ወረራ መታደጉ ላይ ታላቅ አበርክቶ ቢኖረውም፣ በሀገሪቷ ታሪክ ውስጥ ሚናው ደብዝዞ መገለፁ ጎምዛዛ እውነት ነው፤ የቋንቋው ተናጋሪ ያልሆነው አብዛኛው ኢትዮጵያዊም ይህንን አምኖ ሊያርመው ቀርቶ፣ እውቅና ሊሰጠው እንኳ አለመፍቀዱ፣ ጉዳዩን ወደሰሞነኛው ‹‹ውጡ ከሀገራችን›› አይነቱ አስደንጋጭ ኩነት ገፍቶታል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው በጥቂት የብሔሩ ልሂቃን የሚንፀባረቀው (ሀገርን ለፍርሰት ሊያጋልጥ የሚችለው) ሸውራራ የታሪክ አረዳድን እና የቅኝ አገዛዝ ትርክትን ማጥራት ሌላው ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል፤ ምክንያቱም ከጥያቄው ጋር ተያይዘው የሚነሱ የተቃውሞ ድምፆች ማጠንጠኛ ‹ባሳለፍነው መቶ ዓመት ለቅኝ አገዛዝ ተዳርገናል፣ ሥርዓታዊ በሆነ መዋቅር የሥልጣን ባይተዋር ሆነን ቆይተናል፣ ከሌላው ሕዝብም በተለየ መልኩ ከሰብአዊ ፍጡር በታች ተቆጠረን ተረግጠናል…› የሚል መንፈስ እንዲይዝ እየተለጠጠ ነው፡፡ ይህ የታሪክ ትንተና ስሁት መሆኑን የምንረዳው በየትኛውም መንግስታዊ ሥልጣን ጊዜ (ሀገሪቱ በጦር መሪዎችም ሆነ በነገሥታቱ ጠንካራ መዳፍ ስር በተያዘችበት ዘመን) በግንባር ቀደምትነት በመንበሩ ላይ ይፈራረቁ ከነበሩት አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪዎች የማይተናነስ እኩል ሚና እንደነበራቸው የቋንቋው ተናጋሪ ምሁራን በማስረጃ አስደግፈው ባዘጋጇቸው ድርሳኖቻቸው ያተቱትን ስናስተውል ነው፡፡

ለማሳያም ‹‹የጎንደር ዘመን›› ተብሎ ከሚጠቀሰው (እ.ኤ.አ ከ1636-1769 ዓ.ም ድረስ የዘለቀው) ማዕከላዊ መንግስት ውድቀት በኋላ የተተካውና ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› እየተባለ የሚጠራው አገራዊ የአስተዳደር ዘይቤ ጠንሳሽና ተግባሪ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደነበሩ ማስታወሱ በቂ ነው፡፡ በወቅቱ የመንግስቱ መቀመጫ ከሰሜን ጎንደር ወደ ደብረታቦር የተዘዋወረ ሲሆን፣ የግዛት ወሰኑ ደግሞ ጎንደርን፣ ወሎን፣ ጎጃምን፣ ከፊል ሸዋንና ትግራይን የሚያካትት እንደነበር መዛግብቱ ያወሳሉ፡፡ በዘመኑ ሥልጣኑን የጠቀለሉትና ‹‹የጁ (ወራ-ሼክ) ስርወ-መንግስት›› በሚል ስም የሚጠሩት የአሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደነበሩ የብሔሩ ምሁራን ነግረውናል፡፡ እያገባደድነው ባለው በዚህ ዓመት ‹‹የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች›› በሚል ርዕስ ዳጎስ ያለ ጥራዝ ያሳተሙት ታቦር ዋሚ ‹‹በኢትዮጵያ ታሪክ ዘገባዎች አላግባብ ዘመነ መሳፍንት ሲባል የቆየው የየጁ ዘመንና ታሪካዊ ሚና›› በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በርካታ መጽሐፍትና የጥናት ጽሑፎችን በመጥቀስ ሥልጣኑ በኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እጅ እንደነበረ በስፋት አብራርተዋል፡፡ ታቦር በትርክታቸው ‹‹የጁ ከሰሜን ኢትዮጵያ የኦሮሞ ነገዶች አንዱ እንደሆነና ቀስ በቀስም ይህ ስም የጎሳው ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ የሰፈረበት አካባቢ ጭምር መጠሪያ እንደሆነ በርካታ ጸሐፍት ይመሰክራሉ›› (ገፅ 287) ሲሉ በአባሪ ማስረጃዎች አስደግፈው አቅርበዋል፡፡ ሥርወ-መንግስቱ በሥልጣን ላይ የቆየበት ጊዜያትንም ‹‹ከጎንደር ዘመነ-መንግስት ማብቂያ እስከ አፄ ቴዎድሮስ መነሳት ድረስ የነበሩትን ዓመታት ሁሉ ያካትታል›› (ገፅ 293) በማለት ገልፀውታል፤ ይህንን በአሃዝ እናስቀምጠው ብንል ደግሞ ወደ 86 ዓመት ገደማ ልንቆጥር እንገደዳለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ‹‹የኦሮሞ ታሪክ›› የተሰኘው መጽሐፍ ጸሐፊ እሸቱ ኢረና ዲባባም መከራከሪያውን እንዲህ ሲሉ ያጠናክሩታል፡- ‹‹ጎንደር የሃበሻ መንግስት (አቢሲኒያ)ማዕከል በነበረችበት ወቅት የኦሮሞ ህዝብ በአካባቢው ሰፍሮ ይኖር እንደነበረና ወሳኝ ሚና ለረጅም ጊዜ ነበረው፤ እ.ኤ.አ. ከ1853-1854 በጎንደር በእስር ላይ የነበረው ጀርመናዊ ሰዓሊ በሰራቸው ምስሎች ኦሮሞ በወቅቱ በአካባቢው ገዢ እንደነበር እርሱም ከአካባቢው ኦሮሞ ሴት እንዳገባ፤ ምስልዋንም ሰርቶ እነዚህ የስዕል ስራዎቹ እ.ኤ.አ. በ1868 ዓ.ም በለንደን ከተማ በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወጥቶ ይገኛል፡፡ በአካባቢው ሰፍረው ይኖሩ ከነበሩት የኦሮሞ ጎሳዎች ውስጥ የቦረና ኦሮሞ አንዱ መሆኑን ኤች ሙሬይ በ1830ዎቹ ባሳተመው ጽሑፍ ውስጥ ከጠቀሰ በኋላ ኦሮሞ እንደ ሕዝብ በደንቢያ በጎጃም፣ በዳሞትና በአንጎት አካባቢዎች ሰፍሮ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡›› (ገፅ 83-84)

 ራሱ የክልሉ መንግስትም፣ በባሕልና ቱሪዝም ቢሮው በኩል  ‹‹የኦሮሞ ታሪክ እስከ አስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን›› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፍ ‹‹…‹ወራ- ሼክ› የሚለው የቤተሰቡ መጠሪያ በየጁ ኦሮሞዎች ዘንድ ታላቅ ዝና ከማግኘቱም በላይ በአጠቃላይ የየጁ ኦሮሞዎች ቀደምት መንግስት መነሻ ወይም አባት ተደርጎ እስከመቆጠር ደረሰ ይባላል›› (ገፅ 281) ሲል ገልጿል፡፡

በግልባጩ የአፄ ምኒሊክ ፈረስ ሐረርና አርሲ መርገጡን ‹‹የቅኝ-ግዛት ወረራ›› አድርገው የሚያቀርቡ ዘመነኛ ‹‹ፖለቲከኞች››፣ ይህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ ለመቀበል ቀርቶ ለመስማት አይፈቅዱም፡፡ የጠቀስኳቸው ድርሳናትም የሚነግሩን ኦሮሞ ከሌላው ብሔር ጋር ትንቅንቅ ገጥሞ በለስ ቀንቶት ድል ባደረገ ቁጥር መንግስታዊ ሥልጣን መጠቅለሉን ብቻ አይደለም፤ በሀገሪቱ ታሪክ ጭቆና እንጂ ቅኝ አገዛዝ የሚባል ነገር አለመኖሩንም ጭምር ነው፡፡ ከኤርትራ እስከ ሞያሌ፤ ከጋምቤላ እስከ ሶማሌ በተዘረጋው ሰፊ የኢትዮጵያ ግዛት ላይ በተደጋጋሚ ከተቃጡ የባዕዳን ወረራዎች በቀር፣ ቅኝ-ገዢም ሆነ ቅኝ-ተገዢዎች ስለመኖራቸው የሚያትት አንድም የታሪክ መረጃ ተፈልጎ ታጥቷል፡፡ መቼም ‹‹ድሮ ነፃ ሀገር ነበረን›› በሚል ዛሬ ላይ የመገንጠልን ጥያቄ ሲያነሱ፤ አሊያም አንድ ብሔርን በነፍጠኛነትና በወራሪነት ሲኮንኑ የምናደምጣቸው ጠርዘኛ ልሂቃን ‹የኦሮሚያ የግዛት ወሰን ጎንደርን እና ትግራይን ያጠቃልል ነበር› ስለማለታቸው ሰምተን አናውቅም፡፡ መቀመጫውን ደብረታቦር ላይ አድርጎ ከትግራይ እስከ ሸዋ ያስተዳድር የነበረ ሥርወ-መንግስት፣ የበለጠ ጉልበተኛ ተነስቶበት፣ በተራው ከመንበሩ በኃይል ሲገለበጥ ቅኝ-አገዛዝና ኢ-ሰብአዊ ብሎ ለመኮነን መሞከሩ ውሃ የሚያነሳ ሙግት ሊሆን አይችልም፡፡ እዚህ ጋ ሊዘነጋ የማይገባው ጉዳይ፣ በተለይም ከአፄ ምኒሊክ መንገሥ ወዲህ የኦሮሞ ማሕበረሰብ ቋንቋውን ጨምሮ የባሕል እሴቶቹ ተውጠው፣ የአገሪቱ ወካይ እንዳይሆኑ መጨፍለቃቸውን ነው፤ እንደምሳሌም የገዳ ሥርዓት ምንም እንኳ ሁሉንም የቋንቋው ተናጋሪ ያቀፈ ባይሆንም (የ‹‹ጊቤ ግዛት›› ተብለው የሚታወቁት፡- ጅማ፣ ሊሙ፣ ጎማ፣ ጉማ እና ጌራ ከገዳ ይልቅ በንጉሣዊ ሥርዓት ሲተዳደሩ፤ ወለጋና ኢሊባቡርን የመሳሰሉ አካባቢዎችም በ‹‹ሞቲ›› ይመሩ ስለነበር) የአክሱም ሐውልትን ወይም የጎንደር ግንብን ያህል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቦታ አለማግኘቱ አይካድም፡፡ እንዲሁም በሌላ ቋንቋ ተናጋሪው ዘንድ ‹‹ጣኦት ማምለክ›› ተደርጎ የሚቆጠረው የኢሬቻ ክብረ-በዓል አረዳድ ስሁት ስለመሆኑ ቢረፍድም የመስከሩ ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡ ይህ የምስጋና ሥነ-ስርዓት በአገሪቱ ታሪክ ተገቢውን የክብር ስፍራ ሳያገኝ መገፋቱን በማመን፣ ሚዛንን ማስተካከል ግድ ይላል፡፡ በጥቅሉ ምግቡ፣ አለባበሱ፣ ሙዚቃውና መሰል እሴቶቹ በትልቁ የታሪካችን ገፅ በበቂ ደረጃ አለመወከላቸውን ዛሬም ለማድበስበስ መሞከሩ መፍትሔውን ከማራቅ፤ አሊያም ልዩነትን ከማስፋት ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ መቼም በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ ቡድኖች መኖራቸው ደብቀን የምናስቀረው ሚስጥር አይደለም፤ ከኦሮሚያ እስኪ ኦጋዴን፤ ከጋምቤላ እስከ ቤንሻንጉል ድረስ ይህን ለማስፈፀም የሚተጉ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋልና፡፡ በርግጥ እነዚህ ኃይሎች የቆሙበት መሰረት ማሕበረሰቡን የሚወክል ነው ወይስ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ብቻ የሚያረካ? የሚለው ገና ያልጠራ፣ አሁንም አጥጋቢ መልስ ያላገኘ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ፖለቲካዊው ፍላጎት ማሕበራዊ ውሉን የዋጠው ይመስላል፡፡

ኤርትራን ያጣንበት ምክንያትም ከዚህ ብዙም እንደማይርቅ ጥርጥር የለውም፡፡ አሁንም የዚህን ጥያቄ ውል ከሳትን ሌላ የምናጣው ክፍለ-አካል መኖሩ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህም ነው በ‹‹ሕዳሴው አብዮት›› እንደ አዲስ በምትገነባው ኢትዮጵያችን ጥያቄዎቹ በቀዳሚነት ምላሽ ሊያገኙ ይገባል ብዬ የምከራከረው፡፡ በለውጡም፣ እነዚህ ጎታች የፖለቲካ አቋሞች እና አቀንቃኞቹ ዘላቂ መፍትሔ አግኝተው የአንድነት ዘመን አብሳሪ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም፡፡

በተቀረ በኦሮሞ ላይ አንድ ብሔር በተለየ መልኩ በደል አድርሷል፣ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈፅሟል… መሰል ትርክቶች ጭራና ቀንድ ተሰክቶባቸው ግብረ-ሂትለርና ፋሽስታዊ ድርጊቶች ተመስለው የሚቀርቡበት አውድ ከተራ ጊዜያዊ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳነት ያለፈ፣ በዕውን ለመፈፀማቸው ምንም አይነት የታሪክ ሰነድ አልተገኘም፡፡ ከጥቂት ሳምንት ቀደም ብሎ በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ ከታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ስንወያይ ‹‹ወደ አኖሌ (አርሲ) ከዘመተው የአፄ ምኒሊክ ሠራዊት መካከል አብላጫው ኦሮሞ ነው›› ሲሉ መግለፃቸውም፣ ከዶ/ሩ የትምህርት ደረጃ፣ ከረዥም ዓመት የሥራ ልምዳቸው እና ከቋንቋው ተናጋሪ አብራክ የተገኙ ከመሆናቸው አኳያ ችግሩን ወደ አንድ ብሔር ማላከኩ ስህተትለመሆኑ ሁሉንም የሚያስማማ ይመስለኛል፡፡ ታቦር ዋሚም ከላይ በጠቀስኩት መጽሐፍ (ከገፅ 275-278) ከአማራው ነገስታቶች ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ኦሮሞ ንጉስና ንግስት በማለት በስዕላዊ መግለጫ አስደግፈው ያቀረቡት የቋንቋው ተናጋሪ ንጉሦችና ነገስታት ስም ዝርዝር እንደተጨማሪ ማስረጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ጸሐፊው ለማሳያነት ከጠቀሷቸው ውስጥ የአፄ ቴዎድሮስ-እቴጌ ተዋበች፣ የአፄ ምኒሊክ-ጣይቱ ብጡል፣ የንግስት ዘውዲቱ-ወሌ ብጡል፣ የአፄ ኃይለስላሴ-እቴጌ መነን፣ የምኒልክን እህት ያገቡት-ንጉስ ሚካኤል… የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት እንደነበሩ አትተዋል፡፡ ከዚሁ ጋርም አያይዘው በተለያየ ጊዜ በሀገሪቷ የተከሰቱት የኃይል ግጭቶች አሰላለፍ በብሔር ከመቧደን ይልቅ፣ በሥልጣንና በጥቅመኝነት ላይ የተመሰረቱ እንደነበረ ፈራ-ተባ እያሉም ቢሆን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡- ‹‹በጣም የሚገርመው ከሣህለ ሥላሴ ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ በኦሮሞው ላይ ሲካሄዱ ለነበሩት ዘመቻዎች ሁሉ ግንባር ቀደም ተዋናዮቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከነገሥታቶቹ ጋር ጊዜያዊና ዘላቂ ዝምድና የፈጠሩ እራሳቸው ኦሮሞዎች መሆናቸው ነው፡፡ …(ራስ ጎበና) እኚህ የኦሮሞ መስፍን የታወቁ ፈረሰኛ፣ ጀግና፣ ተዋጊና ወታደራዊ ስትራቴጂስት ከመሆናቸው በላይ በኦሮሞ የውጊያ ስልትና በኦሮሞ ሥነ-ልቡና ላይ የጠለቀ እውቀት ነበራቸው፡፡

ይህንን ብቃት ሙሉ በሙሉ ለምኒሊክ አገልግሎት አውለውታል፡፡ ከሁሉም በፊት ምኒልክ ሳይሆኑ የኦሮሞን ግዛት ያሸነፉት ራስ ጎበና ነበሩ፡፡›› (ገፅ 499-500 እና 503)፡፡ ይህን መሰሉ የኃይል ትንቅንቅ ከአርሲና ባሌ በፊት ቤጌምድርና ትግራይ ውስጥ በተከሰተበት ወቅት ኦሮምኛ ተናጋሪው በአሸናፊነት በመውጣቱ ለ86 ዓመት ያህል ሥልጣን ይዞ መቆየቱን ከላይ አይተናል፡፡ መቼም የጁዎች፣ ጎንደሮችን ድል አድርገው ሥርወ-መንግስታቸውን ደብረ ታቦር ላይ የመሰረቱት በምርጫ ካርድ (ያለነፍጥ) ነበር ካልተባለ በቀር፣ አንዱን ወገን ለይቶ በሂትለርነት መኮነኑ ፍትሃዊ ካለመሆኑም ባለፈ፤ የሚጠቅመው ከመከራ ነፃ እንዲወጣ የምንዋትትለትን ሕዝብ ሳይሆን፣ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ነው፡፡

በተጨማሪም በራሱ በቋንቋው ተናጋሪዎች ብቻ ከተዘጋጁ ድርሳናት የጠቀስኳቸው እነዚህ ሁነቶች፣ በማስረጃ ያልተደገፈውን (አፈ-ታሪኩን) የአኖሌ ጡት ቆረጣ ትርክት ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ከዚህ ባለፈ የተሸነፈ ሠራዊትን እጅ-እግር መቁረጥ ምኒሊክም ሆኑ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ገዥዎች ይፈፅሙት የነበረ ጭካኔ መሆኑ አይስተባበልም፤ እንዲያውም በአንድ ወቅት አፄ ቴዎድሮስ፣ በሸዋ ላይ ሾመውት የነበረው የምኒሊክ አጎት አቤቶ ሠይፈ ‹‹ሸፍቶብኛል›› በሚል አንኮበር ድረስ መጥተው ወግተው ድል ካደረጉት በኋላ ሠራዊቱ በሙሉ አንድ እጅና አንድ እግሩ እንዲቆረጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ፡- “አፄ ቴዎድሮስ እጅግ ተዋረዱ የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነስተው ሄዱ”ተብሎ መገጠሙ የጉዳዩን እውነታነት ለማሳየት በቂ ነው፡፡ (የእስልምና እምነት እና የኦሮምኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ጥያቄዎች፣ በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› የሚኖራቸውን የመፍትሔ ሃሳብ በተመለከተ ሳምንት እመለስበታለሁ)

በፖለቲካ ጭነት የተማረሩ የነጻነት አየር መተንፈስ የሚፈልጉ አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከኦሪገን ካምፓቸው መጥፋታቸው ታወቀ ።

በፖለቲካ ጭነት የተማረሩ የነጻነት አየር መተንፈስ የሚፈልጉ አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከኦሪገን ካምፓቸው መጥፋታቸው ታወቀ ። Four #Ethiopia n #Athletes missing from international meet in Eugene http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=83966

Sonntag, 27. Juli 2014

ህውሃቶች ታዲያ ለምንድነው ጦሩን ወደትግራይና ሰሜን ጎንደር የሚያንቀሳቅሱት?መቸም ህውሃት ለምንድነው

I’m not happy with this shit drama; we don’t believe this. tplf is the worst enemy for Ethiopia&Ethiopians.Andargachew Tsege Speaks with the tplf mafia detectives about Ginbot 7አሄሄሄ....ሆድ ሲያውቅ ዶሮማታ አለ ያገሬ ሰው።ህውሃቶች ግንቦት7 በቂ ዝግጂትና ጦር እንደሌለው ካወቁ እነሱ እንዳሉት የንቡን አውራ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከያዙ ምን አስፈራቸው?ህውሃቶች ታዲያ ለምንድነው ጦሩን ወደትግራይና ሰሜን ጎንደር የሚያንቀሳቅሱት?መቸም ህውሃት ለምንድነው አፋቸውና ተግባራቸው አንድለይ አብሮ የማሄድ ብየ አልጠይቅም። ድሮስ ህውሃት ሲፈጠር መቸ እውነት ተናግሮ ያውቅና ነው።
https://www.facebook.com/photo.php?v=654891787925467

Samstag, 26. Juli 2014

ኢትዮጵያ በፍርሀት የሞት እና ሽረት ትግል መካከል የምትንጠራወዝ ምስኪን አገር፣

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
(የጸሐፊው ማስታወሻ) በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ አካል  በቅርቡ ገንቢ ያልሆነእና በእራስ አሸናፊነት ጎልቶ ለመውጣት በሚል ዕኩይ ምግባር በተቃዋሚዎቹ እናትችት በሚያቀርቡበት ወገኖች ላይ እየወሰደ ያለውን የቅጣት እርምጃ አሳፋሪ ነው::ገዥው አካል በተደጋጋሚ በሚሰራቸው አስቂኝ የስህተት ቀልዶች (በሚከተላቸውብልሽቶች እና ድሁር አቅመቢስነትእና በሚፈጽማቸው የመድረክ ትወናዎች(ለአጭር ጊዜ እኩይ ፍላጎቱ እርካታ ሲል በሚያራምዳቸው ውዥንብሮቹበሁለቱምድርጊቶቹ የሚያስደንቅ እና ግራ የሚያጋባ ሆኗል ፡፡ ገዥው አካል ለምንድን ነው 20እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ጦማሪያንን እና በጣት የሚቆጠሩ ሃያሲ ጋዜጠኞችን ሸፍጥበተመላበት ሁኔታ በሀሰት በተፈበረከ እራሱ “አሸባሪነት” እያለ በሚጠራው ክስ ከሶበእስር ቤት አጉሮ ንጹሀን ዜጎችን እያማቀቀ ያለውለምንስ ነው ክቡር የሆነውንየጋዜጠኝነትን ሙያ እየወነጀሉት ያለውለምንድን ነው ገዥው አካል የአገሪቱንኢኮኖሚ በመዳፉ ስር ጨምድዶ ይዞ  በተጠንቀቅ በአንድ ቦታ ቆሞ የሚጠባበቅወታደራዊ ኃይል እያለው እና ብዛት ያላቸው ጠብመንጃዎች፣ ታንኮች እና የጦርአውሮፕላኖች በእራሱ ቁጥጥር ስር እያሉት በጥቂት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ልቡበፍርኃት እየራደ በጭንቀት ማዕበል ውስጥ እየዋኘ የሚገኘውጉልበትን እንጅ ህግንእና ስርዓትን የሚጠየፈው ገዥ አካል በነጋ በጠባ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ በመፎከር የራሱ ጥላ አያስበረገገው ተሸበሮ የሚሸበረው? 
በገዥው አካል በኢትዮጵያ የፕሬስ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እየተሸረሸረበማለቁ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት እያጎረያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ ምክንያት ኢትዮጵያ “13 የብርሀን ወራት ያላት አገር “መባሏ ቀርቶ ይልቁንም  በጨለማው አህጉር “13 ወራት የጨለማ አገር” ተብላለች ፡፡ በጣም ያስገርመኛል ገዥ አካል በእራሱ የፖለቲካ ምህዋር የሚዞር እና እንደገደል ማሚቶ እያስተጋባ የሚኖር የእራሱ ነጻነት የሌለው ግኡዝ አካል ነውንከዚህአንጻር በኢትዮጵያ ስርዓቱን የሚያሽከረክረው ገዥው አካል በፍርሀት ቆፈን ውስጥተወሽቆ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ያለ ሆኖም ግን በዞን 9 ጦማርያን እና ሰላማዊህዝብ እንቅስቃሴ  እያወደመ  የሚኖር የሽብር መንግስት ሆኗል፡፡ )
በሞት  ሽረት  ትግል  ውስጥ  የሚገኙት  የዞን 9  ትንታግ  ወጣት  ጦማርያን
የኔ ጥያቄ እውን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሬፐብሊክ መንግስት” ነው ወይስ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቆ የሚገኝ “የፖሊስ መንግስት”? ኢትዮጵያ በሌላ ጠፈር (ህዋ) የምትገኝ አገር ናትን? እነዚህን ጥያቄዎች በጥሞና የማነሳቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ “የፖሊስ ሬፐብሊክ መንግስት” ተብላ ልትጠራ ትችላለች፡፡ በ20ዎቹ አካባቢ የዕድሜ ጣሪያ ላይ የሚገኙ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች በፌስቡክ እና በሌሎች የማህበረሰብ ድረገጾች ያለምንም ፍርሀት በመጻፋቸው እና ሀሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸው ምክንያት ብቻ በገዥው አካል ሽብርተኛ በሚል የሸፍጥ ፍረጃ እና ክስ በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ቤት በመማቀቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል 6 ጦማሪያንን እና 3 ጋዜጠኞችን (የዞን 9 ጦማርያን እየተባሉ የሚጠሩትን) በተለምዶ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው በአስፈሪው የመለስ ዜናዊ የማሰቃያ እስር ቤት ከሚማቅቁት የፖለቲካ እስረኞች የእስር ቤት ቁጥር 8 ቀጥሎ በተሰየመው የማጎሪያ እስር ቤት ለ80 ቀናት ያህል ሲያማቅቅ ከቆየ በኋላ ህገወጥ በሆነ መልኩ ሽብርተኛ የሚል ታፔላ በመለጠፍ መሰረተቢስ የሆነ የሸፍጥ ውንጀላ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ሀሳባቸውን ያለምንም ፍርሀት በፌስቡክ እና በማህበረሰብ ድረገጽ ነጻ በሆነ መልኩ ከገለጹት ውሰጥ የሚከተሉት ትንታግ ወጣት ጦማሪያን ይገኙበታል፤ አቤል ዋቤላ(በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመሀንዲስነት ተቀጥሮ የሚሰራ)፣ አጥናፍ ብርሀኔ(በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሙያ በክፍለ ከተማ ተቀጥሮ የሚሰራ)፣ ማህሌትፋንታሁን (በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በስታቲስቲክስ ባለሙያነት ተቀጥራ የምትሰራ)፣ናትናኤል ፈለቀ (በኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንክ በማኔጀርነት ተቀጥሮ የሚሰራ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ)፣ ሲሆን ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑት ጆን ኬሪ ጋር ከዚህ በታች የተነሳውን ፍቶግራፍ ማየት ይቻላል፣ ዘላለምክብረት (በአምቦ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት መምህር)፣ እና በፈቃዱ ኃይሉ(በቅድስት ማሪያም ዩኒቨርስቲ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ እና በቅርብ ጊዜ ደግሞ የዕንቁ መፅሔት አርታኢ በመሆን ሲያገለግል የነበረ)፡፡ ሌሎቹ በገዥው አካል ህገወጥ ውሳኔ እስረኛ ጦማሪያን የሚከተሉትን ያካትታል፤ ጋዜጠኛ አስማማው /ጊዮርጊስ (ከአዲስ ጉዳይ ጋዜጣ)፣ እና ፍሪላንሰሮች ተስፋሁን ወልደየስ (ከአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት) እና ኤዶም ካሳዬ (የቀድሞ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሰራተኛ የነበረች) ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት ጋዜጠኞች እና ጦማርያንን (ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ጥቂቶችን ጨምሮ) በተጨባጭ እውነታ ላይ በመመስረት የሰጡትን ቃለ መጠይቅ በሚመለከት መሰረቱን በእንግሊዝ አገር ያደረገ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ቡድን አንቀጽ 19 በሚል ርዕስ በድረገጽ ላይ ያደረገውን ቃለመጠይቅ ከእዚህ ጋ በመጫን ማዳመጥ ይቻላል)፡፡
የሽብርተኝነት ክሱ ዋና ጭብጥ ጦማሪያኑ “በውጭ ከሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ነን ከሚሉ ድርጅቶች ጋር ህብረት በመፍጠር በአገር ውስጥ ሁከት እና እረብሻ ለመፍጠር“ እና “ከውጭ የእርዳታ ገንዘብ በመቀበል ህዝባዊ አመጽ ለመቀስቀስ የማህበረሰብ ድረገጾችን ይጠቀማሉ“ የሚል ነው፡፡
በአማርኛ ተዘጋጅቶ ይፋ የሆነውን የክስ ሰነድ ለማየት ከእዚህ ጋ ይጫኑ፡፡ (በባለአርማ የተጻፈው የመጻጻፊያ ቋሚ ወረቀት ላይ “ኢትዮጵያ” የሚለው የንግሊዘኛ ቃል  ቃል በስህተት “ኢትዮያ” ተብሎ መጻፉን ልብ ይሏል)፡፡ አገሪቱ በይፋ በምትጠቀምበት በባለአርማ ወረቀት በታተመው የመጻጻፊያ ደብዳቤ ላይ የአገሪቱን ስም በትክክል መጻፍ ያቃተው ገዥ አካል በጦማሪያኑ ላይ የመሰረተው ክስ ትክክል ይሆናል ብሎ መውሰድ እንደምን ይቻላል? ምን ዓይነት አሳፋሪ ሁኔታ ነው!!!
በሽብርተኝነት ስም የተመሰረተው የውንጀላ ክስ በርካታ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚያካትት ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሽብርተኝነትን ለመፈጸም ከሌሎች ጋር አብሮ መዶለት፣ የማህበረሰብ መገናኛ ድረገጾችን በመጠቀም የአመጽ ቅስቀሳ ማካሄድ፣ ለኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን/ኢሳት እና ሬዲዮ ዘገባዎችን ማቅረብ፣ ለግንቦት ሰባት የሚሆኑ አባላትን በመመልመል የትብብር አገልግሎት መስጠት፣ በሰው እና በንብረት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፍንዳታዎችን ለማካሄድ የአሸባሪነት ስልጠናዎችን መውሰድ፣ ለአሸባሪ ኃይሎች ስልት መንደፍ እና የአሮሞ ነጻነት ግንባርን ፕሮፓጋንዳ መንዛት የሚሉት ናቸው፡፡ ለውንጀላው አስረጅ ይሆናሉ የተባሉ ዝርዝር ሰነዶች በዋናነት በተከላካዮች እጅ የሚገኙትን ብዙ ዲጂታል የኤሌክትሮኒክ መገናኛ ዘዴዎችን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት መምሪያ በዞን 9 ጦማሪያን ላይ የቀረበውን የክስ ውንጀላ ያለውን ስጋት በመግለጽ ለገዥው አንዲህ ስል አስገንዝቧል፣ “ኢትዮጵያ ነጻ ሀሳብን ከመግለጽ የሚገድበውን የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ከመተግበር እንድትቆጠብ“ በማለት መግለጫው የሚከተለውን አውጇል፣ “ሀሳብን በነጻ መግለጽ እና የነጻው ፕሬስ ነጻነት የዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መሰረታዊ ምርጫዎች ናቸው፡፡ ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን በቁጥጥር ስር በማዋል በጸረ ሽብርተኝነት ህግ ወንጀል ክስ መስርቶ ዜጎችን በፍርድ ቤት ቀጠሮ ማንገላታት በመላ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሰብአዊ መብት ጥበቃ እና በመገናኛ ብዙሀን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡“ ከዚህም በተጨማሪ ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የዞን 9 ጦማሪያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ መግለጫ በማውጣት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በእስር ቤት ታጉረው ይጠበቃሉ፣ እናም የሙያ ስነምግባራቸውን በመተግበራቸው ብቻ በእስር ቤት እንዲማቅቁ ይደረጋሉ፡፡ እ.ኤ.አ የ2014 ትልቅ ክብር ያለውን እና ዓመታዊ ለፕሬስ ነጻነት አሸናፊዎች የሚሰጠውን ወርቃማውን የብዕር ሽልማት ከዓለም ጋዜጦች እና ዜና አታሚዎች ማህበር (ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶች አሸናፊ የሆነው) በቅርቡ የተሸለመው እስክንድር ነጋ በነጻ በመጻፉ ብቻ የ18 ዓመታት እስራት ተበይኖበታል፡፡ የ34 ዓመቷ ሴት ጀግና ወጣት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ነጻነት ቀንዲል የሆነችው እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን የተጎናጸፈችው “እውነት ተናጋሪዋ እስረኛ“ እየተባለች የምትጠራው እና የበርካታ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አሸናፊ የሆነችው ርዕዮት ዓለሙ የገዥውን የፖለቲካ ፓርቲ በአገር አቀፍ የግድብ ፕሮጀክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴ ላይ የሰላ የጽሁፍ ትችት በማቅረቧ እና በሞት በተለዩት በመለስ ዜናዊ እና አሁን በህይወት በሌለው በሊቢያው አምባገነን መሪ በሞአማር ጋዳፊ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የሌላቸው አምባገነኖች ናቸው በማለቷ ብቻ የ14 ዓመታት እስራት ተበይኖባታል፡፡ ሌላው የዓለም ዓቀፍ የፕሬስ ሽልማት አሸናፊ የሆነው ትንታግ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሲያዘጋጀው በነበረው ጋዜጣ ላይ የገዥው አካል በሙስና የበከተ መሆኑን እና የያዘውን ስልጣንም ከህግ አግባብ ውጭ እየተጠቀመ መሆኑን በመግለጹ ብቻ የ14 ዓመታት እስራት ተፈርዶበታል፡፡ በዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ የሚጽፉ እና የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ሲሉ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚፋለሙ ሌሎች በርካታ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች አሉ፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ  ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን እና ሰላማዊ አማጺያንን በመወንጀል፣ ስማቸውን ጥላሸት በመቀባት እና ኢሰብአዊ ድርጊትን በመፈጸም አሸባሪዎች፣ አመጸኞች እና ሌላ ሌላም በመሰየም ይፈርጇቸዋል፡፡ አሁን በህይወት የሌለው የገዥው አካል ቁንጮ መሪ እና ዘዋሪ፣ አድራጊ እና ፈጣሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ የ2005 አገር አቀፍ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ የበርካታ ጋዜጦች አታሚዎችን በእስር ቤት ካጎረ በኋላ በነጻው ፕሬስ ላይ ጦርነት በማወጅ እንዲህ የሚል መግለጫ ሰጥቶ ነበር፣ “ለእኛ እነዚህ ጋዜጠኞች አይደሉም፣ የፕሬስ ህጉን ጥሰዋል ተብለው ክስ አይመሰረትባቸውም፡፡ እንደ ለቅንጅት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ አመራሮች በአገር ክህደት ወንጀል ይከሰሳሉ“ በማለት ሲሳለቅ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ ጆን ፔርሰን እና ማርቲን ሽብዬ የተባሉትን ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ ዘብጥያ ከወረወረ በኋላ እንዲህ በማለት ፈርጇቸው ነበር፣ “የሽብርተኛ ድርጅት ተላላኪዎች“  እንዲህ ሲል ተሳልቋል፣“እነዚህ ወንጀለኞች አሁን እየሰሩት ያለው ጋዜጠኝነት የሚያሰኝ ከሆነ እኔ እራሴ ሽብርተኝነት ምን እንደሆነ አላውቅም ማለት ነው“ በማለት የተለመደውን የቅጥፍና ፍልስፍና አሰምቶ ነበር፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ  ጋዜጠኝነት ማለት አሸባሪነት ማለት ነው፡፡ ጋዜጠኞች ለመንግስት ጠላቶች ናቸው፡፡ መጦመር ወይም መጻፍ የሀገር ክህደት ወንጀል ነው፡፡ ጦማሪያን የመንግስት ደመኛ ጠላቶች ናቸው፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር በየመን በአውሮፕላን በትራንዚት ላይ እያለ አስነዋሪ እና አሳፋሪ የሆነ የጠለፋ ወንጀል ተፈጽሞበታል፣ እናም ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ዓለም አቀፍ ህግን በመደፍጠጥ ወደ ዘብጥያ እንዲወረወር ተደርጓል፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ሰዎች ኢሰብአዊነት ድርጊት ይፈጸምባቸዋል፣ ስልጣኔ ወደ ኋላቀርነት ይቀየራል፣ ፍትህ በሙስና ይጣመማል፣ የጎሳ ማጥራት ዘመቻ ይካሄዳል፣ ህዝቦች በድህነት እንዲማቅቁ እና የረሀብ ሰለባ እንዲሆኑ ይደረጋል፣ ወጣቶች በችግር እንዲጠረነፉ ይደረጋል፣ የግዳጅ ስራ እንዲሰሩ ይደረጋል፣ ሰካራም እንዲሆኑ እንዲሁም የጫት እና የሌሎች ሱሶች ተገዥዎች እንዲሆኑ ስልታዊ ስራ ይሰራል፣ ተፈጥሯዊ ከባቢያችን እንዲወድም ይደረጋል፣ ግድቦች በዘላቂነት በአንድ ቦታ አካባቢ የሚኖሩትን የወገኖቻችንን ህይወት በሚጎዳ መልኩ በመገደብ በህብረተሱ ዘንድ መቅሰፍታዊ አደጋ እንዲመጣ ይደረጋል፣
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ድህነት ሀብታምነት ማለት ነው፣ ረሀብ ማለት በጥጋብ መወጠር ማለት ነው፣ የመንግስት በስህተት መዘፈቅ የሰብአዊ መብት ማክበር ማለት ነው፡፡ ጭቆና ፍትሀዊነት ነው፣ እናም ወሮበልነት ዴሞክራሲያዊነት ማለት ነው፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ድንቁርና ምሁርነት ነው፡፡ የመንግስት ዋና ዓላማ ህዝቡን አደንቁሮ ለማቆየት እና በህገወጥነት መንገድ ለመግዛት እውነታውን ማጣመም፣ መወጠር እና እውነታውን ማፍተልተል፣ ጸጥ ማድረግ እና ምንም ሳያስቡ ባላወቁት እና ባላመኑበት ነገር ላይ ስምምነት እንዲያደርጉ ማስቻል ነው፡፡
በሀሰተኛዋ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ወሮበሎች ይገዛሉ! ወሮበሎችን መፍራት የህግ የበላይነት ማለት ነው!
በዞን 9 ሰላማዊ እንቅስቃሴ ምክንያት የሚደረግ የፍርሀት የሞት ሽረት ትግል፣
በ196ዎቹ  አመታት ሮድ ሴርሊንግ በተባለ በአንድ ታዋቂ እና ተወዳዳሪ በሌለው “የሞት ሽረት ትግል” በተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን የተውኔት ደራሲ አስፈሪ ተውኔቶችን፣ ጭንቀት የተሞላበት እና በጣም አስቸጋሪ የሆነ የአውዳሚነት ባህሪን የተላበሰ የሳይንስ ልብወለድ ድርሰት ተዘጋጅቶ ቀርቦ ነበር፡፡ በአንድ ትርኢት ያቀርበው ታሪክ የቤተመጽሐፍት ባለሙያ ሰው ላይ የተመሰረተ ነበር:: ይህ የቤተመጽሐፍት ባለሙያ “አታስፈለግም” የሚል ክስ ቀርቦበት ነበር:: በዚህ በቀረበበት ክስ ምክንያት የሞት ፍርድ ሊበየንበት እንደሚገባ የግዛቱ አስተዳዳሪ የሆነው ባለስልጣን በችሎት በተሰየመው የዳኞች ስብሰባ ፊት በመገኘት ችሎቱን ለማሳመን ሞከረ፡፡ በፍርድ አሰጣጥ ሂደቱ ወቅት ባለስልጣኑ ( ቻንስለሩ) እና የቤተመጽሐፍት ባለሙያው በሰው ልጅ ክብር ላይ በሚከተለው መልኩ ጠንካራ የሆነ ክርክር በማድረግ ስራ ላይ ተጠመዱ፣
ባለስልጣኑ  (ቻንስለሩ) (ለቤተመጽሐፍት ባለሙያው)፡ “አንተ የማታስፈለግ ባለሙያ ነህ!
የቤተመጽሐፍት ባለሙያው፡ የመጽሐፍ ገጾችን በማቃጠል እውነታውን ልታወድም እንደማትችል ከማሳሰብ የዘለለ ሚና የለኝም!
ባለስልጣኑ፡ አንተ ትኋን ነህ፡፡ በመሬት ላይ የምትሳብ ነብሳት፡፡ አስቀያሚ እና ምንም ዓይነት ቅርጽ የሌለህ ዓላማ ቢስ አናሳ ፍጡር ነህ! ምንም ዓይነት ስራ የለህም…“
የቤተመጽሐፍት ባለሙያ፡ “እኔ ሰብአዊ ፍጡር ነኝ…”
ባለስልጣኑ፡ “አንተ የመጽሐፍት አከፋፋይ ነህ፣ በመጽሐፍት ማውጫ መደርደሪያው መስመር ላይ ትርጉም የለሽ የሆኑ ቃላትን በኃይል በማውጣት በተዘጋጀው የመጽሐፍት መደርደሪያ ላይ ሁለት ሳንቲም የሚያወጡ ጥራዞችን እያወጣህ የምትደርድር ከንቱ ፍጡር ነህ፡፡ ምንም ዓይነት ዋጋ የሌላቸው ቃላት፣ እንደ ነፋስ፣ ምንም ዓይነት አቅጣጫ የሌላቸው ናቸው፡፡ እንደ ባዶ ህዋ በትንሽ ካርድ ላይ አመልካች ቁጥሮችን በመደርደር ትርጉም የለሽ ምልክት በማድረግ ህልውና እንዳለህ በመቁጠር እምነት እንዲያድርብህ ታደርጋለህ፡፡“
የቤተመጽሐፍት ባለሙያው፡ “እኔ ደንታዬ አይደለም፡፡ ነግሬሀለሁ፣ ደንታዬ አይደለም፡፡ ሰብአዊ ፍጡር ነኝ፣ እኖራለሁ… እናም አንድን ሀሳብ ከፍ በማድረግ በተናገርሁ ጊዜ ያ ሀሳብ በዘላቂነት ይኖራል ወደ መቃብር ከተወረወርኩ በኋላም ቢሆን እንኳ፡፡“
ባለስልጣኑ፡ እነዚህ ሁሉ ከንቱ የውሸት እምነቶች ናቸው!! የማተሚያ ቀለሙን በደምህ ውስጥ በማዋሀድ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ግጥም፣ ድርሰት እና ሌላም ነገር ሁሉ ስነጽሁፍ እያልክ የምትጠራውን አደንዛዥ ዕጽ በመውሰድ ምንም ዓይነት ኃይል ሳይኖርህ ኃይል እንዳለህ አድርገህ እራስህን ትቆጥራለህ!!! አንተ ምንም ማለት አይደለህም፣ ሆኖም ግን አንተ ማለት የሚንቀሳቀሱ የእጆች እና እግሮች ቅርጽ አንዲሁም ህልም ብቻ ያሉህ ፍጡር ነህ፡፡ እናም መንግስት አንተ የዋህ በመሆንህ የሚያገኘው አንዳችም ጥቅም የለም!!! ጊዚያችንን አቃጥለሀል፣ እናም ያቃጠልከውን ጊዜ ያህል ጠቀሜታ የሌለህ ከንቱ ፍጡር ነህ፡፡
ፍርድ ቤቱ  የሞት ቅጣቱን ውሳኔ የቤተመጽሐፍት ባለሙያ ላይ ተግባራዊ አደረገ፡፡
የቤተመጽሐፍት ባለሙያው ድፍረት በተመላበት መልኩ የሞት ቅጣቱን ዕጣ ፈንታ በጸጋ ተቀበለ፡፡ ጨካኝ አረመኔዎቹ ምህረትን እንዲያደርጉለት ከመጠየቅ ይልቅ የእራሱን ሰብአዊ ክብር እና ነጻነት ለማስጠበቅ ሲል ከኃይለኞቹ ጉልበተኞች ፊት በጽናት ቆመ፡፡ ሁለት ልዩ የሆኑ ጥያቄዎችን አቀረበ፣ 1ኛ) በምን ዓይነት መንገድ የሞት ቅጣቱ ሊፈጸምበት እንደሚገባ እንዲመርጥ የሞት ቅጣቱን የወሰኑበት  እብሪተኞች ዕድል እንዲሰጡት ጠየቀ፣ 2ኛ) የሚፈጸምበት የሞት ቅጣት እና በመሬት ላይ በህይወት የሚቆይባቸው የመጨረሻዎቹ ጥቂት ሰዓታት በቴሌቪዥን ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ ጠየቀ፡፡ ሁሉም ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ የቤተመጽሐፍት ባለሙያው የሞት ቅጣቱን የሚያስፈጽመውን ባለስልጣን ወደ ማቆያ ክፍሉ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲመጣ ጋበዘው፡፡  ባለስልጣኑ/ቻንስለሩ የሞት ቅጣቱ ከሚፈጸምበት ጊዜ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም በማለት ደረሰ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ተወያዩ፡፡ የውይይታቸው ዳህራ እንደሚከተለው ቀርቧል፣
የቤተመጽሐፍት ባለሙያ፡ እዚህ ድረስ ጥያቄዬን አክብረው በመምጣትዎ አመሰግናለሁ፡፡
ባለስልጣን፡ ለመሆኑ ለምን እንደመጣሁ ታውቃለህ?
የቤተመጽሐፍት ባለሙያ፡ አዎ እንዲመጡ ስለጋበዝኩዎ ነው፡፡
ባለስልጣን፡ እዚህ አንተ ጋ ለምን እምደመጣሁ ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡ ምናልባት ስለአንተ ጉዳይ አንድ ነገር ለማረጋገጥ ነው፡፡
የቤተመጽሐፍት ባለሙያ፡ እና ያ….?
ባለስልጣን፡ መንግስቱ ምንም ዓይነት ፍርሀት የለውም፣ ይህንን ላረጋግጥልህ ነው የመጣሁት፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን ምንም ፍርሀት የሚባል ነገር የለም፣ ምንም…
የቤተመጽሐፍት ባለሙያ፡ ክቡር ባለስልጣን እንደዚህ ላለ የተለቀቀ ፌዝ ይቅርታ እንዲያደርጉልኝ እጠይቃለሁ…ማለቴ ወደ እኔ ማቆያ ክፍል የመጡት መንግስት… እኔን የማይፈራኝ መሆኑን ለመግለጽ ነውን!? እኔ ለምንድን  እንደዚህ ያለ የማይታመን ሸክም ለመሆን እንደቻልኩ የሚገርም ጉዳይ ነው! መንግስት አንድ እንደ እኔ ያለውን ያረጀ የቤተመጽሐፍት ባለሙያ የማይፈራ መሆኑን ለማረጋገጥ እዚህ ድረስ መምጣቱ የሚያስደንቅ ነው፡፡ ኦ! አይደለም፡፡ እዚህ ድረስ የመጡበትን ምክንያ በግልጽ ልነግርዎት እፈልጋለሁ… እርስዎ ለእራስዎ ለመቀበል ፈቃደኛ ባይሆኑም እንኳ ምክንያቱን እንግረወታለሁ፡፡
ባለስልጣን፡ ያ ለምን መሆን እንዳለበት አሁን ጥያቄ የማቅረብ ተራው የእኔ መሆን የለበትምን?
የቤተመጽሐፍት ባለሙያ፡ የእርስዎን መስፈርት አላሟላም፡፡ የእርስዎ መንግስት ሁሉንም ነገር ፈርጆ አስቀምጧል…መለያ ቁጥር እና ኮድ ሰጥቷል፣ እንደዚሁም የመለያ ተለጣፊ ጸሑፍ/ታግ ሰጥቷል፡፡ እንደ እርስዎ ያሉ ሰዎች ኃያል ናቸው፡፡ እንደ እኔ ያሉ ሰዎች ደግሞ ደካሞች ናቸው፡፡ እርስዎ ስርዓትን ይቆጣጠራሉ፤ እናም ያስገድዳሉ… እኔ እና መሰል ደካሞች ፍጡራን ደግሞ እርስዎን መከተል እና መታዘዝ ነው፡፡ ሆኖም ግን አንድ ነገር ስህተት ተሰርቷል፣ አይደለምን? ለዚህ ጉዳይ ተስማሚ አይደለሁም፣ ነኝ እንዴ?
የቤተመጽሐፍት ባለሙያው ለባለስልጣኑ ማሳየት የፈለገው ህዝቦች በምን ዓይነት መንገድ ክብራቸው እና ሰብዕናቸው መጠበቅ እንዳለበት መከራከር እና መብትን መጠየቅ ለሞት ቅጣት እንደሚያደርስ አየተከራከረ  ከዳዊት መዝሙር ምዕራፍ 23 እና 53ን ማንበብ ጀመረ ፡፡ በቴሌቪዥን ህዝቡ የቤተመጽሐፍት ባለሙያው እና ባለስልጣኑ ክርክር ሲያደርጉ ይመለከታል፡፡ የሞት ቅጣት የሚፈጸምበት ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ ባለስልጣኑ የቤተመጽሐፍት ባለሙያውን ክፍል ለቅቆ ለመውጣት ሞከረ፡፡ ሆኖም ግን የክፍሉ በር ተዘግቶ አገኘው፡፡ የሞት ቅጣቱ ሰዓት እኩለ ሌሊት መሆኑን ከማመልከቱ በፊት ባለስልጣኑ በጭንቀት ማዕበል ውስጥ ሰምጦ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ፡፡ የቤተመጽሐፍት ባለሙያው ግን በተረጋጋ መንፈስ እና ከፍርሀት በጸዳ መልኩ ይመለከት ነበር፡፡ ባለስልጣኑ የቤተመጽሐፍት ባለሙያው የተቆለፈውን በር እንዲከፍትለት እና መውጣት እንዲችል እንዲህ በማለት ለመነው፣ “በእግዚአብሔር ስም ይዠሀለሁ ከዚህ ክፍል ውስጥ ልውጣ!“ የቤተመጽሐፍት ባለሙያው ደስታ በተቀላቀለበት ሁኔታ ሆኖም ግን መንግስት “እግዚአብሔር እንደማይኖር ያረጋገጠውን” ቃል ሳይደግም ባለስልጣኑ እንዲወጣ በሩን ከፈተለት፡፡ ከዚያ በኋላ ባለስልጣኑ በደረጃው ላይ አድርጎ ከክፍሏ በመውጣት ቁልቁል እየወረደ ከውስጥ ባለው የቤተመጽሐፍት ባለሙያ ክፍል ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነሳ፡፡ በመጨረሻው ሁኔታ ባለስልጣኑ እንደ ወንጀለኛ የተፈረጀ እና አስፈላጊ አንዳልሆነ  ወደ ፍርድ ሰጭ ጉባኤው ተመለሰ፡፡ የምክንያቱም ፍርሃት በማሳየት ያለዉን መንግስት መሳቂያ ስላደረገ:: ፈራጆቹ ባለስልጣኑን በጠረጴዛ ላይ በመጎተት እስከሚሞት ድረስ ጨፈጨፉት፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን አሸባሪ ብሎ በመፈረጅ ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ እያሰቃዬ በተጨባጭ እነርሱ “የማያስፈለጉ” ናቸው በማለት በመዘባበት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም “ትኋኖች እና የሚሳቡ ነብሳት ናቸው” ይላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ “እነርሱ መጥፎዎች፣ የተበላሸ ቅርጽ ያላቸው፣ ምንም ዓይነት ዓላማ የሌላቸው እና ትርጉምየለሽ ፍጡሮች ናቸው!” ይላል፡፡ ገዥው አካል እንዲህ በማለት ይነግራቸዋል፣ “በሳንቲም የሚሸጡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች እና በድረገጽ የሚለቀቁ ኃይል ያዘሉ ትርጉም የለሽ ጽሑፎች አከፋፋዮች ናቸው፡፡“ “ምንም ዓይነት ጥራት የሌላቸው እንደ ነፋስ እና እንደ አየር ምንም ዓይነት ቅርጽ የሌላቸው፣ እንደ ህዋ ባዶ የሆኑ፣ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ቃላትን በጋዜጦች፣ በድረገጾች እና በብሎጎች ላይ በመሞነጫጨር የሚኖሩ ትርጉመ ቢስ ፍጡሮች ናቸው” በማለት በህዝቡ ዘንድ እምነት እንዳይጣልባቸው ይዘባበታሉ፡፡
በሴርሊንግ ታሪክ እንደ የቤተመጽሐፍት ባለሙያው ሁሉ በእስር ላይ የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያን እና የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ጸጥታ በተላበሰ መልኩ እንዲህ በማለት ሀሳባቸውን ይገልጻሉ፣ “እኛ ሰብአዊ ፍጡሮች ነን… ገዥው አካል ስለሚናገራቸውም ሆነ ስለማይናገራቸው ነገሮች ደንታ የለንም፡፡ አለን፣ እንኖራለን… እናም አንድ ነገር ድምጻችንን ከፍ አድርገን በተናገርን ቁጥር ያ ሀሳብ ለዘለቄታው ይኖራል፣ እኛ ወደ መቃብር ከተወረወርን በኋላ እንኳ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡“ ገዥው አካል “ስርዓትን መቆጣጠር እና ማስገደድ” ይችላል፣ ሆኖም ግን የዞን 9 ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች “እንደ ቀላል ነገር በዘፈቀደ የሚከተሉ እና የሚታዘዙ አይደሉም” በውሸታሟ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ላይ አንድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት ተከስቷል! በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መስፈርቱን አያሟሉም፡፡
“የማያስፈለጉት” የውሸታሟ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ወይስ የማያስፈለጉት  የውሸታሟ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ መሪዎች?
ሮድ ሴርሊንግ አሁን ቢኖር ኖሮ የውሸታሟ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ የጽሑፉ ትረካ መግቢያ በሚከተለው መልክ ይናገር ነበር:
(የተራኪው ድምጽ፡፡) በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ የፖሊስ መንግስት ገዥ የወሮበላ ስብስብ በብረት ጡንቻቸው ህዝብን ቀጥቅጠው በመግዛት ላይ ይገኛሉ፡፡ በግልጽ ለመናገር “የአፍሪካ የወሮበላ አገዛዝ” ነው በአህጉሪቱ ተንሰራፍቶ ያለው፡፡ ዋናው ዓላማቸው፣ “የተቃዋሚ ቡድኖች ምርጫችንን ዋጋ የሚያሳጣ የኃይል እርምጃ የሚወስዱ ከሆነ በሙሉ ኃይላችን እንደመስሳቸዋለን፡፡ ለዘላለም በእስር ቤት ውስጥ ሆነው ይበሰብሳሉ፡፡“ በዚህ የወሮበላ አገዛዝ ስርዓት ውስጥ በህሊና መኖር እና ማሰብ ወንጀል ነው፡፡ በስልጣን ላይ ላሉት ሸፍጠኞች እውነቱን መናገር ወንጀል ነው፡፡ ሰላማዊ ተቃውሞ ወንጀል ነው፡፡ የአንድን ሰው ህይወት ለመሸጥ ተቃውሞ ማሰማት ወንጀል ነው፡፡ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ መከበር መቆም ወንጀል ነው፡፡ የህግ የበላይነት እንዲጠበቅ መሟገት እና መከራከር ወንጀል ነው፡፡ ሰላማዊ በሆነ መልክ መንግስታዊ ሽብርተኝነትን ለማስቆም መታገል ወንጀል ነው፡፡
በዚህ የአፍሪካ የወሮበላ አገዛዝ ጋዜጠኝነት በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ጦማሪነት ወይም ጸሐፊ መሆን በሞት የሚያስቀጥ ወንጀል ነው፡፡ ማንም ቢሆን በዥው አካል ላይ ትችት ካቀረበ በጆሮ ጠቢ ደህንነት ወይም በጦር ኃይል ይታፈናል፣ ይታሰራል፣ ይሰቃያል፣ እንዲሁም ይሰወራል፣ ይገደላል፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባመጹ ጊዜ በአነጠጥሮ ተኳሾች በጥይት ይደበደባሉ፡፡ ሰላማዊ አመጸኞች በተጭበረበረ የምርጫ ውጤት ምክንያት ተቃዎሟቸውን ለማሰማት ወደ አደባባይ በወጡ ጊዜ በይፋ በጥይት በመንገዶች ላይ ይደበደባሉ፡፡ የወሮበላ አገዛዝ ስርዓት እድሜውን ለማራዘም እና በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመቆየት ሲል ከውጭ የሚገኝ የገንዘብ እና የማቴሪያል እርዳታ ይጠቀማል፡፡
(ተራኪው የካሜራ እይታ፡፡) በእራስህ ኃላፊነት አዝሂች የውሸታሟ ሬፐብሊካዊት አገር ትገባለህ ፡፡ ይህ አዲስ አገዛዝ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከዚህ በፊት  የነበረው የቀድሞው ያፍዝ ያደንግዝ አገዛዝ ስርዓት ቅጥያ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ አምባገነን መሪ በኋላ በታሪክ ሂደት ውስጥ የእራሱን አምባገነናዊ ስርዓት እና ባህል ጥሎ ካለፈው አምባገንን የሚመነጭ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሰብአዊ መብትን እና ነጻነትን ለማፈን የቴክኖሎጂ መስፋፋትን እና ምጥቀትን በመሳሪያነት ይጠቀማሉ፡፡ ሆኖም ግን ከእነርሱ በፊት እንደነበሩት አገዛዞች ሁሉ እነዚህም አንድ ዓይነት የመቀጥቀጫ የብረት ጡንቻ አላቸው፡፡ ምክንያታዊነት ጠላት ነው እናም እውነት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ (ካሜራ ወደ ተከሰሱት ተከላካዮች ፊቱን ያዞራል፡፡) እነዚህም የዞን 9 ጦማሪያን፣ ጋዜጠኞች፣ ዜና ዘጋቢዎች፣ አታሚዎች እና አርታዒኦች በወሮበላው አገዛዝ በአሸባሪነት ተከስሰው በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊወገዱ የሚችሉ የአንድ መንግስት ዜጎች ናቸው ምክንያቱም ከስጋ የተሰሩ ፍጡሮች እና የሚያስቡበት አእምሮ እና ስቃይን የሚመለከቱበት ልብ አላቸው፡፡
“ባላስፈላጊ ሰው” ተራኪው እንዲህ በማለት ማጠቃለያ ሰጠ፣ “ባለስልጣኑ/ቻንስለሩ አሁን በህይወት የሌለው ባለስልጣን ብቻ ነበር ትክክለኛው ሰው፡፡ እርሱ አስፈላጊ ሰው አይደለም፣ እንዲሁም ያመልክበት የነበረው አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስትም አስፈላጊ አይደለም፡፡“ በስልጣን ላይ ያለ ማንም መንግስት፣ የትኛውም አካል ቢሆን እና የትኛውም የአመለካከት ፍልስፍና ጠቃሚነትን፣ ክብርን፣ የሰውን ልጅ መብት መጠበቅ ከግምት የማሰያስገባ ወዳቂ ከሆነ ያ መንግስት አስፈላጊ አይደለም፡፡
በህይወት የተለየው የውሸታሟ ሬፐብሊካዊት ኢትዮጵያ ባለስልጣን/ቻንስለር እና የመሰረተው መንግስት እና አምልኮ አስፈላጊ አይደለም!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሀምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም