Henoke Yeshetlla
«እሱም አላቸው ሂዱ ፥ እነሱም አሉ አንሄድም» ነው ያሉት እኛ የልደታ ቤ/ክርስቲያን ቄስ! እኝህ አባት ባንድ ወቅጥ « በኖህ ዘመን » አሉ « አዎ በኖህ ዘመን ልጆቼ ምድር ተጥለቀለቀች ፥ በምድር ላይ የሚኖሩ ነገሮች ሁሉ ተጥለቀለቁ ፥ በግዜው የዋና ፓንት እና መንሳፈፊያ የሰውነት ጓንት አልነበረም ፥ ቀይ መስቀል አልነበረም ፥ ጥሬ ውሃና እና ጥሬ ፍጥረት ብቻ ነበር የነበረው » አሉ ። ቀና ሲሉ አውሮፕላን ሲበር አዩ ። እና ቀጠሉ
አዎ በኖህ ዘመን አሉ « በኖህ ዘመን አውሮፕላኑም ተጥለቀለቀ » ። የእኝህን አባት ማንነት ሳጣራ ፥ ታጋይ እና ተጋዳላይ የነበሩ ፥ አንድም አይነት የቤተ ክህነት እውቀት የሌላቸው ሰው እንደሆነ ኋላ ላይ ደረስኩበት ።
እና ምን ለማለት ነው ፥ « በመስቀል ዘመን ፥ መስቀል አደባባይ በፌደራል ተጥለቀለቀች ፥ መስቀል አደባባይነቷን ረስታ ፥ ፌደራል አደባባይ ሆነች ፥ በጊዜው ምዕመን አልነበረም ፥ የነበረው ጥሬ ወታደር እና እርጥብ ችቦ ብቻ ነበር ። ህዝቡንም ውጡና በዓል አክብሩ አሏቸው ፥ ህዝቡም አንወጣም ይህ የደመራ ችቦ ሳይሆን የደም ደቦ ነው አለ» በኛ ዘመን ! እየተናቁ መግዛት ግን እንዴት ያስጠላል! በግድ ውደዱኝ ማለት ግን እንዴት ይሸክካል!? ነገሩ ያራዳ ልጅ ካልሆንክ ይህ አይገባህም ! የገገሞች ህገ መንግስት መግቢያ « አስገድደን ለምንገዛችሁ እና በግድ እንድትወዱን ላስገደድናችሁ ህዝባችን ሆይ » ነው የሚለው ? እኔ እንጃ! ጃ ያስተሰርያል!
ኄኖክ የሺጥላ
http://wp.me/p5L3EG-dl
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen