ጉድ ሳይሰማ
ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ አጀብ አሰኝቶን የተጀመረው 2007 ጉድ አሰኝቶን ተጠናቋል። በሌላ ሃያሏ ዩኤስ አሜሪካ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ኢንባሲ ኢትዮጵያዊያን የለውጥ አቀንቃኞች መስከረም 26 /2007 ዓም ለደቂቃዎች ሲቆጣጠሩ የኢምባሲው የጥበቃ ሃላፊ ተኩስ በመክፈት ለትእይንቱ ድምቀጥ ከመስጠት ባሻገር የህወሃት ሰዎች ድንቁርና ድንበር የማያግደው እርቀት የማይገድበው መሆኑን አሳይቶናል። የህወሃት ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ታጋይ የአለም የፖለቲካ መአከል በሚባለው ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ቁጭ ብሎ የ ጌትነት ካባ ደርበው ልምጭ ባልያዙ ያገሩ ልጆች ላይ አነጣጥሮ ሲተኩስና ጥይቱ ሲደነብሽበት አይተናል። በ48 ሰአታት ውስጥ አመሬካን ለቆ እንዲወጣ ተወስኖበት ጓዙን ጠቅልሎ መውጣቱንም ተከታትለናል። በዚህም ሳቢያ የህወሃት ካምፕ የነበረው ሃዘን ቁጭትና እልህ እንዲሁም ቀለብ በሚሰፈርላቸው አገልጋይ ወገኖች የነበሩ ማላዘን አንዳመት ብቻ ነውና አንረሳውም። የህወሃት ታጋዮች የነጻነት አርበኛውን አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን የጸጥታ ሃይሎች በረብጣ ዶላሮች በመግዛት የዘረኝነትና የዘረፋ ስርአታቸውን ለማደላደል ቢቋምጡም ነጻነትን የተራቡ ኢትዮጵያዊያን ሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ምላሽ ሰተዋል። እኛም አንዳርጋቸው ነን ያሉት ደግሞ አመቱን ሙሉ መረብን እየተሻገሩ ብረት ማንሳታቸውን ሰምተናል። የጠመንጃው ግብግብ እንዲያበቃና የሰለጠነ ፖለቲካ በሃገራችን እውን እንዲሆኑ የጣሩ ስልጡን ፖለቲካ ስልጡን ካልገባው ሃይል ጋር እንደማይሆን ተገንዝበው ነጻነት ፍለጋ ድንበር እያቋረጡ መሳሪያ አንስተዋል። ብረሃኑ ተክለያሬት እየሩሳሌም ተስፋሁንና ፍቅረማሪያም አስማማውን የመሳሰሉ ወጣቶች ነጻነት በሰላማዊ መንገድ እንደማይቻል በድርጊት ሲነገራቸው ነጻነት ፍለጋ ድንበር ሲያቋርጡ መያዛቸውን ለፍርድቤት በኩራት በመናገር ለወኔያቸው የብዙዎችን አትኩሮት አትርፈዋል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ጉድ ሳይሰማ https://www.facebook.com/%E1%88%B3%E1%88%9D-%E1%89%AE%E1%8B%B5-%E1%88%B6%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%88%AD%E1%8C%8B%E1%89%B8%E1%8B%8D-EH-407502636113775/timeline/#
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen