Netsanet: Oktober 2016

Dienstag, 18. Oktober 2016

​“መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ ስለመቻላቸው ( ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

​“መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ ስለመቻላቸው


በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትናትና ንግግር ውስጥ “ … ይህ የባርነት አዋጅና የአዋጁ ባለቤት ህወሓት/ኢህአዴግ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መንገዶች “መሠረተ-ልማቶች” ሳይሆኑ መሠረተ-ጥፋቶች ናቸው፤ አውራ ጎዳናዎች አስጠቂዎቻችን ናቸው” የምትል ዓረፍተ ነገር አገር አለች።
“የተከበሩ” ኮካዎች “እንዴት አንድ የኢኮሚክስ ባለሙያ መሠረተ ልማቶችን መሠረተ ጥፋቶች ናቸው” ይላል ብለው እንደሚንጨረጨሩ እገምታለሁ።

“መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያዊያን ያስተዋወቀው (እኔ እስከማውቀው ድረስ) ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ነው። የነጋድራስ ገብረሕይወትን ያህል የሕዝብ አስተዳደርና የኢኮኖሚ ግኑኝነትን የተረዳ ምሁር እንኳንስ ያኔ ዛሬም መኖሩ አጠራጣሪ ነው። ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት በ1916 ዓም በታተመው “መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር” በተሰኘው መጽሀፉ ውስጥ “መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ እንደሚችሉ ውብ በሆነ አገላለጽ ተንትኗል።

ነጋድራስ ገብረሕይወት በመጀመሪያ የአጴ ሚኒሊክ በኋላም የአጴ ኃይለሥላሴ ባለሟል ሆኖ ለፈጣን ልማት የታገለ ቢሆንም እንኳን ለሕዝቡ ደህንነት የሚጨነቅ መንግሥት በሌለበት አገር ውስጥ ዕውቀት አይሰፋፋም፤ ዕውቀት በሌለበት ደግሞ መሠረተ ልማት ቢስፋፋ ጥፋትን እንጂ ልማት አያመጣም በማለት በጣም ጠንካራ ቃላትን ተጠቅሞ ይተቻል።

በቅድሚያ የመንግሥት ሥራ ምን መሆን እንዳለበት የገለፀበትን ለ 93 ዓመታት ሰሚ ያጣ አንቀጹን ላስቀድም

“በእያንዳንዱ መንግሥት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል። ስለሆነ መንግሥት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይዶለም። አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግሥት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው። መንግሥት ሕዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ካላሰበ መንግሥት በዙፋኑ ሊቆም አይችልም። ላንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግሥት የሚገባ ሥራው አይደለም።” ገጽ 14

ቀጥሎ ስለ መሠረተ ልማቶች ወደሰጠው ትንተና ልለፍ።

ነጋድራስ ይህን መጽሀፍ በፃፈበት ወቅት (ከሞተ በኋላ ነው የታተመው) የጅቡቲ- አዲስ አበባ የምድር ባቡር ግምባታ እና የአቢሲኒያ ባንክ መቋቋም የዛሬውን ህዳሴ ግድብና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ያህል በሥርዓቱ ባለስልጣኖች የሚወደሱ እንደነበሩ መገመት ይቻላል። ነጋድራስ ግን እነዚህ ፕሮጀክቶት ሳይቀር በሚከተለው መንገድ በድፍረት ተችቷቸዋል።

“ዕውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሠራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ፤ አይጠቅመውም። ጥቅሙ ከርሱ ጋር ለሚገበያዩ ዐዋቂዎች ሕዝቦች ነው” ገጽ 75

“የሚበላውንና የሚለብሰውን ያጣ ድኻ የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና ያገሩ መንግሥት ቢበረታ ለሕዝቡ ማሠልጠኛ የሚሆነውን ነገር ሁሉ የምድር ባቡር በፍጥነት ሲያመላልስ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ርስ በርሱ ሲለዋወጥና ባንኩም በሰበሰበው ገንዘብ ሲረዳ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሕዝቡን ለማሠልጠን ቢነሳ ማለፊያ አጋዦች ይሆኑት ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ሐሳብ ከሌለው ግን የምድር ባቡርና ባንኩ ወዳገራችን አመጣጣቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ መቃብር ለመማስ እንደሆነ ጥርጥር የለውም።” ገጽ 127 -128

=====

NB: የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ለነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ የክብር ዶክሬት ሰጥቷል። እኔ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ከሰጣቸው የክብር ዶክሬቶች ተገቢ የምለው ብቸኛ የክብር ዶክሬትም ይህ ነው።

Tadesse Biru Kersmo

http://wp.me/p5L3EG-dW

Sonntag, 16. Oktober 2016

​“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” VS ሕዝባዊ አሻጥርና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ( ደ/ት ታደሰ ብሩ) 

​“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” VS ሕዝባዊ አሻጥርና ሕዝባዊ እምቢተኝነት 

“በይፋ አለመታወጁ ነው እንጂ ድሮም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ነው የነበረነው” በሚል እሳቤ ስለዚህ ጉዳይ ምንም የመፃፍ ፍላጎት አልነበረኝም። ማታ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” ስሰማ ግን መሳሳቴን አወቅሁ። በዚህ ላይ ካልተፃፈ በምን ይፃፋል???

ስለዚህ መመሪያ ያለህን አስተያየት በአንድ ዓረፍተ ነገር ግለጽ ብባል እንዲህ እላለሁ። 

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያ” ስለሕዝባዊ አሻጥር እና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ውጤታማነት የተሰጠ የምስክርነት ቃል ነው። 

ወደፊት የምመለስበት ሆኖ አሁን ትንሽ ዘና እንበልበት።

 

1. የኢትዮጵያ ከተሞች ከገጠር የሚለያቸው ዋና ባህሪ የቤቶቻቸው ጣራዎች ቆርቆሮ  መሆኑ ነው። “ከዋና ዋና መንገዶች በግራና በቀኝ 25 ኪሜ ርቀት” እያሉ ለመለካት የሚያስቸግር ነገር ከሚያስቀምጡ “የቆርቆሮ ቤቶች ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ“ ቢባል ይሻል ነበር። 

2. መመሪያውን እንደወረደ ለሚተረጉመው ሰው የሚገባው ነገር የሚከተለው ነው -  “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚፀናበት ቦታ መኖር ክልክል ነው”። በህገመንግሥታቸው  “ኢትዮጵያዊያን የመኖር መብት አላቸው” የሚል አንቀጽ እንዳለ አስታውሳለሁ። ይህ መመሪያ የከለከተለው እሱን ነው፤ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ የመኖር መብት የላቸውም እያለን ነው። 

3. መመሪያውን እንደወረደ ሳይሆን በጥንቃቄ ለሚያጠና ሰው ግን በርካታ ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛል፤ ትኩረቴ ሁለት ነጥቦች ላይ ነው። 

3.1.   መመሪያው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ምን ላይ ማትኮር እንዳለበት ፍንጭ ሰጥቷል። ለምላሴ፣ ሁከት ማስነሳት፤ ዘረፋ መፈፀም፤ ንብረት ማውደም ከልክሏል (እነዚህ የተፈቀዱበት አገር ስለመኖሩ እኔ አላውቅም)። የሕዝባዊ እምቢተኝነት ትርጉም አድርጉ የተባሉትን አለማድረግ፤ አታድርጉ የተባሉትን ማድረግ በመሆኑ ምን ምን ላይ ማትኮር እንዳለብን ጥቆማ ሰጥቶናል። መንገዶች፣ የአገዛዙ ተቋማት ንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎች የሕዝባዊ እምቢተኝነት ዒላማዎች የነበሩ መሆናቸው ትክክል መሆኑ መመሪያው አረጋግጦልናል፤ ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል ነው። 

3.2.  መመሪያው ስለሕዝባዊ አሻጥር ውጤታማነት የተሰጠ መረጃ አድርገን ልንወስደው እንችላለን። “ሥራ መበደል ክልክል ነው”  (በነገራችን ላይ ሥራ መበደል አለመበደሉን ማረጋገጥ ራሱ ትልቅ ሥራ ነው)፤ ሥራን ማስተጓጎል፤ አገልግሎት አለመስጠት፤ የስፓርት ሜዳዎችን ለተቃውሞ አለመጠቀም ....  እያለ እኛ አገር ውጤታማ የሚሆኑ የሕዝባዊ አሻጥር ዓይነቶችን ይዘረዝራል። መመሪያው የሕዝባዊ አሻጥር ዋና ዋና ማዕከላትንም ይዘረዝራል፤ ለምሳሌ የትምህርት ተቋማት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት። ባጭሩ ይህ መመሪያ ስለሕዝባዊ አሻጥር የተፃፉ ጽሁፎችን እንድናነብ፤ እኛም ለሀገራችን በሚስማማ መንገድ እንድንጽፍ እና ተግባራዊ እንድናደርጋቸው ይማፀናል።

http://wp.me/p5L3EG-dU

Freitag, 14. Oktober 2016

አቶ ጁነዲን ሳዶ ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

አቶ ጁነዲን ሳዶ  ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ
https://www.youtube.com/watch?v=uaB0O-sFWJM&feature=youtu.be

​መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ (አርበኛ በኤፍሬም ማዴቦ )

​መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ
በኤፍሬም ማዴቦ


ስድስተኛ፤  ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል አብራኝ የተማረች ሰላማዊት ነገደ የምትባል ቆንጆ ልጅ ነበረች። ሰላማዊት ስትስቅ ከሩቅ የሚታይ ስርጉድ፤ የደስ ደስና አንዴ ካዩት አመት የሚናፍቅ ፈገግታ ያላት ዉብ ልጅ ናት። ሰላማዊትን እንኳን ያያት ያገኛትም አይጠግባትም። ሰላማዊት ሁለመናዋ ቆንጆ ሆኖ ጸባይዋ ግን . . . አቤት  “ያንተ ያለህ” የሚያሰኝ ነዉ። ሰላማዊት “ቂጧ” አንድ ቦታ አርፎ የማይቀመጥ፤  ከአዋቂዉም፤  ከህጻኑም፤  ከአስተማሪዉም ከተማሪዉም ልክ እንደ እሳት እራት ካገኘችዉ ጋር ሁሉ የምትላተም በጥባጭ ልጅ ነበረች። ብቻ ምን አለፋችሁ ሰላማዊት “ከፈሷ” ጋር የተጣላች ደብረ በጥብጥ ልጅ ነበረች። ት/ቤት ዉስጥ በቀን ቢያንስ ሁለቴ ወይም ሶስቴ እየተከሰሰች ዳይረክተራችን ቢሮ መሄዷ አይቀርም። እኔም እንደ ሰላማዊት ዕብድ ባልሆንም ዳይረክተራችንን በየቀኑ ከሚጎበኙ ተማሪዎች ዉስጥ አንዱ ሰለነበርኩ ከሰላማዊት ጋር በየቀኑ እንገናኝ ነበር። የምንማርበት ካቶሊክ ሚሺን ት/ቤት ሰላማዊትንና እኔን የታገሰን ሁለታችንም በትምህርት ጎበዞች ስለነበርን ብቻ ነዉ እንጂ  . . . . እንደ ጠባያችንማ ቢሆን ሳምንትም አንቆይ።
 ሰላማዊት የሰፈሬ ልጅ ስለነበረች ቤተሰቦቼም ያዉቋታል። አባቴ የትምህርት ጉብዝናዋን ሰለሚያዉቅ ይወዳታል፤  እናቴ ግን እቺ “ሰላም የሌላት” ልጅ ወይ ስሟን አለዚያም ጸባይዋን ካልቀየረች እንኳን ቤቴ ልትገባ አጥሬን እንዳታይብኝ ባይ ነበረች። አዎ ሰላማዊት በእናቶቻችን አነጋገር “መጥኔ ይስጥሽ” የምታስብል በጥባጭ ልጅ ነበርች። የሰላማዊት ወላጆች የልጃቸዉ የወደፊት ይታያቸዉ አይታያቸዉ ለግዜዉ የሚታወቅ ነገር የለም – ለልጃቸዉ ያወጡላት ስም ግን የ”መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” ትክክለኛ ምሳሌ ነዉ።
አይዟችሁ ዛሬ የማወራችሁ ስለ ልጀነት ጓደኛዬ ስለ ሰላማዊት አይደለም። ደሞ ባወራስ! ሰላማዊት በጥባጭ እንጂ ሌባ፤  “ደብረ በጥብጥ” እንጂ “አገር በጥብጥ” አይደለችም። ለሁሉም ዛሬ የማወራችሁ በኮሚቴ አገር ስለሚመሩ፤  በኮሚቴ አገር ስለሚዘርፉ፤  በኮሚቴ ስለሚዋሹና በኮሚቴ ወገኖቻችንን ስለሚገድሉ ሰዎች ነዉ። እነዚህ የኮሚቴ ሰዎች ሁሉም መልካም ስም የተሸከሙ ነገር ግን ዉስጣቸዉም ዉጫቸዉም አስቀያሚ የሆኑ ሰዎች ናቸዉ። አንዳንዶቹን ስማቸዉን እየጠቀስኩ ብጽፍ ደስ ይለኝ ነበር ግን . . . ይቅርብኝ! ኧረ ይቅርብኝ ምነዉ እቴ!! ይልቅ እነዚህ አስቀያሚ ሰዎች በአምሳያቸዉ ስለፈጠሯቸዉ “ስማቸዉ መልካም” ስራቸዉ ግን አስቀያሚ ስለሆኑ ድርጅቶች አንድ. . . ሁለት ልበላችሁ። ለመሆኑ “አገር መከላከያ ሚኒስቴር” እየተባለ ህዝብን ስለሚያጠቃዉ፤  “ዕምባ ጠባቂ” እየተባለ ድፍን አበሻን ስለሚያስለቅሰዉ፤  “ደህንነት” መ/ቤት እየተባለ በዜጎች ላይ ሰቆቃ ስለሚፈጽመዉና “ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሺን” እየተባለ ህዝብ በየአደባባዩ በአልሞ ተኳሾች ሲገደልና በጅምላ ሲታሰር ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃና አያያዝ ተሻሽሏል እያለ ስለሚያዉጀዉ በድን መስሪያ ቤት ታዉቁ ኖሯል? 
ካላወቃችሁ እስኪ በመጀመሪያ ይህንን “ኢሰመኮ” የሚባል ድርጅት ላስተዋዉቃችሁ። ኢሰመኮ ማለት ሰዉ ሲገደል ትንኝም አልተገደለም፤  ሰዉ ሲታሰር የታሰረ የለም፤  ሰቆቃ ሲፈጸም ኧረ በፍጹም እያለ የሚሸመጥጥ ወያኔ ሰራሽ ድርጅት ነዉ። ይህ የ”ኢሰመኮ” ማንም ሰዉ የሚያዉቀዉ የመዝገበ ቃላት ትርጉሙ ነዉ። ዬኔ ችግር ትርጉሙ ላይ አይደለም። ለመሆኑ “ኢሰመኮ” የሰሜን ኮሪያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ነዉ ወይስ የኢትዮጵያ? በመብት ረገጣ አንደኛና ሁለተኛ ናቸዉና – የሁለቱም ሊሆን ይችላል  . . . የማን መሆኑም ብዙ አያሳስበኝም ። ግን ህወሓቶች ኢሰመኮ እያሉ በጥሩ ድርጅት ስም ከሚረግጡን ለምን አንዱኑ “መብት መርገጥ ህጋዊ ነዉ” እያሉ እዉነቱን እየነገሩን አይረግጡንም? እየቀለድኩ እንዳይመስላችሁ! የምሬን ነዉ። ኢሰመኮ ማለትኮ ኦሮሚያ ዉስጥ ከ500 በላይ ሰላማዊ ዜጎች በአግዓዚ ሲጨፈጨፉና ከአስር ሺዎች በላይ ሲታሰሩ – ጸጥታ አስከባሪዎች የወሰዱት እርምጃ ህጋዊ ነዉ ያለ ግዑዝ ድርጅት ነዉ። አዎ! ግዑዝ ድርጅት! እስቲ አሁን ኢትዮጵያ “ቅርጫ ቦርድ” ወይም የ “አገር ዉስጥ አጥቂ ሚኔስቴር” ነዉ እንጂ “ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሺን” የሚባል ድርጅት ምን ያደርግላታል? ይገርማል . . .  እየገደሉ ማዘን!  

በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴና በደርግ ዘመነ መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ትልቁ ስራ አገርን ከጠላት መከላከል ነበር- ለዚህም ነበር መስሪያ ቤቱ የ”አገር መከላከያ ሚኒስቴር” እየተባለ የሚጠራዉ። የዛሬዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ “ቀኃስ” ዩኒቨርሲቲ እየተባለ በሚጠራበት ወቅት ወይም የዛሬዎቹ ነብሰ ገዳዮች የዚህ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በነበሩበት ግዜ ዩኒፎርም የለበሰ ምንም አይነት ወታደር የዩኒቨርሲቲዉን መግቢያ በር አልፎ ወደ ገቢዉ አይገባም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ በየክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ ተማሪዉን፤ ወታደሩን፤  አስተማሪዉንና ነጭ ለባሹን መለየት አስቸጋሪ ነዉ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጊቢያቸዉ ዉስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ እዚያዉ ግቢያቸዉ ዉስጥ ገብቶ የሚገድላቸዉ ወታደሩ ነዉ። ኦሮሚያ ዉስጥ ዘጠኝ ወር ሙሉ ባዶ እጃቸዉን “መብታችን ይከበር” እያሉ የሚጮሁ ወጣቶችን የገደለዉ ወታደሩ ነዉ። ዛሬ ጎንደር፤ ጎጃም፤ ኮንሶና አጋዴን ዉስጥ ሰላማዊ ዜጎችን ያለ ርህራሄ የሚጨፈጭፈዉ አገርንና ህዝብን የመጠበቅ ህገ መንግስታዊ አደራ የተሸከመዉ ወታደሩ ነዉ። የሚገርመዉ ባለፈዉ ሚያዚያ ወር ከባዕድ አገር ድንበር ተሻግረዉ የመጡ መሳሪያ አንጋቾች ጋምቤላ ዉስጥ ወገኖቻችንን ጨፍጭፈዉ በሰላም ወደ መጡበት ሲመለሱ ዝም ብሎ እንዲመለከት የተደረገዉም ይሄዉ የኢትዮጵያ ተብዬዉ ወታደር ነዉ።  ለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ወታደር የማን ወታደር ነዉ? የኢትዮጵያ ወይስ የህወሓት? የአንድ ፓርቲ ጥቅምና ፍላጎት አስከባሪ ወይስ የአገር ዳር ድንበር አስከባሪ? መልሱን የራሱን ወገን ለሚጨፈጭፈዉ ወታደር እተዋለሁ። ወታደሩን ያቀፈዉን ትልቅ አገራዊ ተቋም ግን በቀድሞ ስሙ የ”አገር መከላከያ” ሚኒስቴር ብዬ መጥራት ስለሚቀፈኝ  . . . .  ”አገር ዉስጥ አጥቂ” ሚኒስቴር ብዬ ሰይሜዋለሁ። የሚስማማ ካለ አሜን ይበል። በኔ በኩል አሜን!   
መቼም ኢትዮጵያ ዉስጥ በህወሓት ዘመን ተፈጥሮ የኢትዮጵያን ህዝብ የማያጠቃ ተቋም አለ ለማለት ያዳግታል። መከላከያዉ አገርን ከጠላት መከላከል ሲገባዉ በየመኖሪያ ሰፈሩ እየገባ ህዝብን ያጠቃል። ፍርድ ቤቶች ለተበደለና ለተገፋ ፍርድ መስጠት ሲገባቸዉ ይባስ ብለዉ የተበደለዉንና የተገፋዉን ያጠቃሉ። ዘንድሮማ ምን የማንሰማዉ ጉድ አለ- እስር  ቤቱም “ማረሚያ ቤት” መሆኑ ቀርቶ ማጥቂያ ቤት ሆነኮ! ፋሺስታዊዉ የወያኔ ስርዐት ቂሊንጦ እስር ቤት ላይ የፈጸመዉ ናዚ መሰል አረመኔያዊ ድርጊት ስርዐቱ እያሰበ የሚዉለዉና የሚያድረዉ የኢትዮጵያን ህዝብ በብዛት የሚገድልበትን ዘዴ እየፈለገ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል። ወያኔ ቂሊንጦ እስር ቤት ዉስጥ የፈጸመዉ ወንጀል አንዴ ተፈጽሞ ያበቃ ወንጀል ሳይሆን ተከታታይ ወንጀል ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹ የታሰሩበት እስር ቤት በእሳት ተቃጥሎ ማን ሞተ ማን ተረፈ፤  እስር ቤቱ እንዴት ተቃጠለ ለምን ተቃጠለ ምንም ነገር ሳይነገረው ሳምንት ቆየ። ከሳምንት በኋላ አባትና እናት ልጃቸዉ በህይወት እያለ “ልጃችሁ” ሞቷልና ቅበሩ ተብለዉ ስሙን እንኳን  የማያዉቁትን የሌላ ሰዉ ልጅ “ልጃችን” ብለዉ ቀበሩ። ሳጥን ከፍተሽ የልጅሽን ሬሳ ካየሽ ድራሽሽ ይጠፋል የተባለች እናት ሌሊት ላይ አላስችል ብሏት መቃብር ቆፍራ ቀን የቀበረችዉን የልጇን አስከሬን ስትመለከት ልጇ የሞተዉ በእሳት ተቃጥሎ ሳይሆን ደረቱን በጥይት ተደብድቦ ነዉ። እነዚህን የሰዉ ልጅ አዕምሮ በፍጹም ሊቀበለዉ የማይችላቸዉን አረመኔያዊ ወንጀሎች የፈጸሙት የአገራችን ክርስትና መሰረት በሆነችዉና የ“ጽላተ ሙሴ” ማረፊያ ናት እየተባለ በሚነገርላት ትግራይ ዉስጥ የተወለዱ ሰዎች መሆናቸዉን ስናዉቅ  . . . .  እራሳችንን በሁለት እጃችን ይዘን “እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ” ከማለት ዉጭ ሌላማ ምን የሚባል ነገር አለ?
አንድ ሰሞን የአረብ አገር መሪዎች ተሰበሰቡና የ”እርሻ ቦርድ” እናቋቁም ብለዉ ዉይይት ጀመሩ። በዉይይቱ መሀል ግራ የገባቸዉ የኩዌቱ መሪ ተነሱና እኛ የሚያመርት መሬት የለንም “እርሻ ቦርድ” ምን ያደርግልናል ብለዉ ገና ንግግራቸዉን ሳይጨርሱ የሳዑዲዉ ንጉስ ቱግ ብለዉ ተነሱና  . . . አቦ ቁጭ በል! ኢትዮጵያ እንኳን የገንዘብ ሚኒስቴር አላት ብለዉ አዳራሹን በሳቅ ሞሉት። እኚህ ንጉስ አልሰሙ ይሆናል እንጂ ዛሬ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድም አላት። እግዜር ያሳያችሁ ሳሞራ የኑስንና አባ ዱላ ገመዳን የመሳሰሉ ቅልብ በሬዎች ባሉበት አገር ዉስጥ “ቅርጫ ቦርድ” እንጂ “ምርጫ ቦርድ” ምን ያደርጋል? ደግሞስ የምርጫ ቦርድ ስራ የድምጽ መስጫ ሳጥኖችን ሰብስቦ ድምጽ እየደመሩ አንድን ፓርቲ በየአምስት አመቱ አሸናፊ ማድረግ ከሆነ እንኳን “ምርጫ ቦርድ” ድምጽ መስጫ ሳጥንስ የልማት ግዜያችንን ከማባከን ዉጭ ምን ያደርግልናል? የምርጫ ቦርድ ስራ ፍትሀዊ ምርጫ ማዘጋጀትና አገራችን ዉስጥ የመድበለ ፓርቲ ስርዐት እንዲለመልም ማድረግ ነዉ። ምርጫ ቦርድ አሁን እየሰራ ያለዉ ግን ህወሓት ያጎበጣቸዉን ፓርቲዎች እየገደለ መቅበርና ህዝብ በምርጫ የሚሰጠዉን ድምጽ እየደመረ ለወያኔ/ኢሀዴግ መስጠት ነዉ። አዎ ምርጫ ቦርድ ድምር ይወዳል፤  ደግሞም ደምሮ ደምሮ መቶ ካልሞላለት ደስ አይለዉም። ወይ ጉድ “መቶ” ሲባል አንዲት ቀልድ ብጤ ትዝ አለችኝ። ሂሳብ እየወደቀ አባቱ ሁሌ የሚጮሁበት ልጅ አንዴ ሂሳብ ተፈትኖ መቶ አገኘና አባቱጋ እየሮጠ ሄዶ  . . . አባዬ . . . አባዬ ሂሳብ መቶ አገኘሁ ብሎ ይነግራቸዋል። ጆሯቸዉን ማመን ያቃታቸዉ አባቱ . . . ዘንድሮ “ምርጫ ቦርድ” ፈተናም ማረም ጀመረ እንዴ ብለዉ ሚስታቸዉን አሳቋቸዉ። 
ሌላዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስሙና ስራዉ በፍጹም የማይገናኝ መስሪያ ቤት የአገር ዉስጥ ደህንነት መ/ቤት ነዉ። የዚህ መ/ቤት ስራ የኢትዮጵያን ህዝብ ደህንነት መጠበቅና ጸረ ኢትዮጵያ ሴራዎችን ተከታትሎ ማምከን ነዉ። የወያኔዉ ደህንነት መስሪያ ቤት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ጉዳዩ አይደለም። የሱ ስራ ህዝብን መሰለልና የህዝብን ልጆች እያነቁ መግደል ነዉ። አዎ! የኢትዮጵያን ህዝብ መሰለል የወያኔ ደህንነት መ/ቤት ዋና ስራ ነዉ . . . . ደሞ አቤት የጆሮ ጠቢዉ ብዛት! ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝቡ ጆሮ ጠቢዉን እየፈራ እንኳን ከጓደኛዉ ከራሱ ጋር ማዉራት ካቆመ ሰነበተኮ! ለመሆኑ በወያኔዉ ደህንነት መ/ቤትና በኢትዮቴሌኮም መካከል ምንም ልዩነት እንደሌላ ታዉቁ ኖሯል? የደህንነት መ/ቤት ስራዬ ብሎ ይሰልላል፤  ኢትዮቴሌኮም ስራዉን ትቶ ይሰልላል  . . . ሁለቱም ሰላዮች ናቸዉ። ኬንያ ቴሌኮም የኬንያ ገበሬ የገበያ ዋጋንና የአየር ንብረትን በእጅ ስልኩ መከታል እንዲችል ባደረገበት ዘመን ኢትዮቴሌኮም ግን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያወጣ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገሮች የራሱን ዜጎች ይሰልላል። የኬንያ ቴሌኮም ዉጤታማነት የሚለካዉ ለምን ያክል ኬንያዊ ዘመናዊ የስልክ አገልግሎት ሰጠ ተበሎ ነዉ። የኢትዮቴሌኮም “ልማታዊነት” የሚለካዉ እየሰለለ ቂሊንጦ በሚልካቸዉ ዜጎች ብዛት ነዉ። ለዚህ ይመስለኛል ዶ/ር ደብረ ጽዮን ተገምግመዉም አያዉቁም ይባላልኮ! ማን አፍ አዉጥቶ ይገምግማቸዉ . . .  የእሳቸዉ የስለላ ዉጤት ነዋ ቂሊንጦን የሞላዉ። ደግሞስ ቂሊንጦ ቢሞላ ባይሞላ ምን ችግር አለበት፤  ካልሞላ ዶ/ር ደብረጽዮን አሉ፤  ሲሞላ ደግሞ  . . . ጨካኝ ልብ፤ክብሪትና ቤንዚን አለ። የዛሬዋ ኢትዮጵያ ደግሞ የሶስቱም ችግር የለባትም . . . በተለይ የጨካኝ ልብ! 
ከህወሓት ነገሮች ሁሉ የሚገርመኝ የፈለፈላቸዉ ድርጅቶች ብዛት ነዉ። እርግጠኛ ነኝ የአንዳንዶቹን ድርጅቶች ስም ድርጅቶቹን የፈጠረዉ ፓርላማም የሚያዉቅ አይመስለኝም። ዕምባ ጠባቂ፤  ይቅርታ ቦርድ፤  ሙስና ኮሚሺን ወዘተ . . .  አቤት ብዛታቸዉ! “የማያድግ ልጅ ምኑ ይበዛል” ይሉ ነበር አባቶች ሲተርቱ። እስቲ እግዜር ያሳያችሁ ካልጠፋ ስም እንስራ ሙሉ ዕምባ  የሚያስለቅስን ድርጅት “ዕምባ ጠባቂ” ብሎ መሰየም ምን የሚሉት ጉድ ነዉ?  በስመ አብ!  አንድ ሰዉ ባንክ የሚሄደዉ ገንዘብ ሊያወጣ ወይም ሊያስገባ ነዉ። ባንክ ማለት ደግሞ ወይ ገንዘብ ተቀብሎ ጠባቂ ነዉ አለዚያም አበዳሪ ነዉ። ለመሆኑ ዕምባ ጠባቂ ድርጅት ስራዉ ምንድነው?  እኔ እንደሰማሁት ዕምባ ጠባቂ ድርጅት ለጉዳይ ሄዶ ሳያለቅስ የተመለሰ ሰዉ የለም። ታዲያ ምነዉ ይህንን አለስሙ የሚጠራ ድርጅት ወይ “ዕምባ ባንክ” አለዚያም “አስለቃሽ ጪስ” ብለዉ ቢጠሩት። እዉነቱን ለመናገር ይህ ድርጅት በትክክለኛ ስሙ “ዕምባ ባንክ” ፤  የስራ አመራር ቦርዱ ደግሞ “አስለቃሽ ጪስ” ተብለዉ ቢጠሩ ለአገርም ለወገንም የሚጠቅሙ ይመስለለኛል። “አስለቃሽ ጪስ” ያስለቅሳል “ዕምባ ባንክ” ዕምባ ያጠራቅማል። አትልፋ! የስም መቀያየር ዋጋ የለዉም እንዳትሉኝ! እኔ ከ“ዕምባ ጠባቂ” ሺ ግዜ “ዕምባ ባንክ” ይሻለኛል፤  ሌላ ቢቀር ዘመድ ሲሞትበት ዕምባ ጠብ ለማይለዉ ለእንደኔ አይነቱ ሰዉ ዕምባ ያበድራል።  
አምላኬን የምወድ ክርስቲያን ነኝ። አዎ የአባቴን ገዳይም ቢሆን ይቅር ማለት የሚችል ልብ ያለኝ ክርስቲያን ነኝ። ይቅር ካልተባባልን የወደፊቷን ኢትዮጵያ ማየት እንደማንችልም በሚገባ የምረዳ ሰዉ ነኝ። ግን በይቅርታ ስም አገርና ህዝብ ሲበደል ማየትም መስማትም አልፈልግም። “በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል” መለኮታዊ ትዕዛዝ ናት። እቺን መለኮታዊ ትዕዛዝ ነብሰ ገዳዮች የራሳቸዉ መጠቀሚያ ሲያደርጉ አንገቴን ደፍቼ አልመለከትም። የአገር ሽማግሌዎች፤  ቄሶችና ፓስተሮች በይቅርታ ስም  የነብሰገዳዮች ተላላኪ ሲሆኑ ማቅለሽለሽ ብቻ ሳይሆን ዉስጥ አጥንቴ ድረስ እየገባ ያመኛል።  በኔ እምነት ይቅርታ የሚጀምረዉ ከራስ ነዉና የህወሓት መሪዎች ስለ “ይቅርታ ቦርድ” ከማዉራታቸዉ በፊት እያንዳንዳቸዉ ቢያንስ መንፈቅ ሱባኤ ገብተዉ በየወንዙ፤  በየተራራዉና በየአደባባዩ ገድለዉ ለቀበሯቸዉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ፈጣሪያቸዉንና የሟች ቤተሰቦችን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸዉ። ይህንን ካደረጉ ብቻ ነዉ “ይቅርታ ቦርድ” የሚባለዉ እነሱ የፈጠሩት ተቋም ተቀባይነት የሚኖረዉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ “ይቅርታ ቦርድ” የሚባለዉ ተቋምና ተቋሙ ዉስጥ ያሉት ፍጹም የወያኔ አሻንጉሊት የሆኑ ተላላኪ ግለሰቦች ግን ከይቅርታ ጋር የሚያገናኛቸዉ ምንም ነገር የለም። በተለይ ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴን የመሳሰሉ ትዕዛዝ የምቀበለዉ ከፈጠሪዬ ብቻ ነዉ የሚሉ ነገር ግን የነብሰ ገዳዮችን ትዕዛዝ እየተቀበሉ ያለ ምንም ጥፋት የታሰሩ ሰላማዊ ዜጎችን አሳሪዎቻችሁን ይቅርታ ካልጠየቃችሁ እያሉ ሲጨቀጭቋቸዉ ስመለከት ኢትዮጵያ እዉነትም የነአቡነ ጴጥሮስና የነቄስ ጉዲና ቶምሳ አገር ናት እንዴ እያልኩ እራሴን እንድጠራጠር ያደርገኛል። ፓስተር ዳኔልን የመሳሰሉ እንኳን ለፈጠሪ ለገዛ ሂሊናቸዉም የማይገዙና ወያኔ ሂዱ ሲላቸዉ ወዴት ብለዉ የማይጠይቁ ሆዳም ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያን “Pastor” ተብለዉ ከሚጠሩ የህወሓት “Patter” ተብለዉ ቢጠሩ የሚያምርባቸዉ ይመስለኛል። ፓስተር እስኪ ያስቡበት . . .  ፈጣሪም የሚወደዉኮ ሰዉ እራሱን ሲመስልና እራሱን ሲሆን ነዉ! አሜን ነዉ ፓስተር? . . . አሜን!
ሌላዉ ህወሓት ያንን አስቀያሚ ፊቱን በዲሞክራሲ ለመሸፈን ሲል ብቻ የፈጠረዉ ተቋም ፓርላማዉ ነዉ። በአለም ዉስጥ የማያስብ፤  የማይወያይ፤  ህግ የማያወጣና ምንም አይነት ዉሳኔ የማይወስን ግዑዝ ፓርላማ ቢኖር አዲስ አበባ ዉስጥ ያለዉ የወያኔ ፓርላማ ብቻ ነዉ። ስለ ወያኔ ፓርላማማ ባላወራ ደስ ይለኛል  . .  . . .   ደግሞስ ይህ ሲሰበሰብም ሳይሰበሰብም የሚተኛ እንቅልፋም ፓርላማ ምን የሚወራ ነገር አለዉ? እኔማ ፓርላማዉን ባሰብኩ ቁጥር ትዝ የሚለኝ አባዱላ ገመዳ ብቻ ነዉ። መቼም አባዱላ ሲወለድ ስም ያወጣሁለት እኔ ብሆን ኖሮ ከ”አባ ዱላ” “ዱላዉ” ስለሚሻለኝ “አባ”ን አስቀራት ነበር። የወያኔ ፓርላማ ተረት የሚተረትበት ቤት ነዉ ሲባል በተደጋጋሚ እሰማለሁ። በፍጹም የማልስማማበት አባባል ነዉ። ተረት የሚተርተዉኮ የሚያስብ ሰዉ ነዉ፤  የሚተረተዉም ለሚሰማ ሰዉ ነዉ። የወያኔ ፓርላማ የሚያስብም የሚሰማም ሰዉ የለበትም- ይልቅ ለእናንተ መስማት ለምትችሉት ወገኖቼ ተረት ብጤ ልንገራችሁ – ተረት አበዛሁባችሁ አይደል? አይዟችሁ! እኔ ሰለማስብ እናንተም ስለምትሰሙ ነዉ። አንዴ ኢትዮጵያ ዉስጥ ማየትና መስማት የተሳናቸዉ ሰዎች ጉዳያችን በፓርላማ ካልታየልን አሉና ጉዳያቸዉን ይዘዉ ፓርላማ ሄዱ። አራት ኪሎ ደርሰዉ መንገድ ሲያቋርጡ ያየ አንድ ባለታክሲ አንዱን ማየት የተሳነዉ አቤቱታ አቅራቢ ዬት ነዉ የምትሄዱት ብሎ ጠየቀዉ። ፓርላማ ብሎ መለለት። ለምን አለዉ? ጉዳያችንን ለፓርላማ ልናሰማ . . .  እነማናችሁ እናንተ? እኛ ማየትና መስማት የተሳነን ኢትዮጵያዊያን ነን። እንዴ! የኢትዮጵያ ፓርላማ ከመቼ ጀምሮ ነዉ ማየትና መስማት የተሳናቸዉን ሰዎች ጉዳይ ማየት የጀመረዉ . . . . ፓርላማዉ እራሱ እኮ “ማየትና መስማት የተሳነዉ” ፓርላማ ነዉ ብሎ ባለ አቤቱታዉን አሳቀዉ።  
ወያኔ ደርግን አሸንፎ አዲስ አበባ ሲገባ የረባ ቅያሪ ልብስ ያልነበራቸዉ እነ ስብሐት ነጋ፤  አባይ ጸሀዬ፤  መስፍን ስዩም፤  አባይ ወልዱና ጓደኞቻቸዉ ዛሬ የሚነዱት መኪና  “ቤንትሊ” እና “ሮይስሮልስ” ነዉ። የሚኖሩባቸዉ የተንጣለሉ ቪላዎች ዉበትማ እንኳን በየቀኑ እላዩ ላይ ቤቱ የሚፈርስበት ደሃዉ ኢትዮጵያዊ እነሱንም ይገርማቸዋል። እነዚህ ሰዎች በገቢያቸዉ ልክ ቢኖሩ ኖሮ የሚኖሩባቸዉን ቪላዎች እንኳን ሊኖሩባቸዉ በአይናቸዉም ማየት የማይችሉ ሰዎች ናቸዉ። እነዚህ የለየላቸዉ ዘራፊዎች ከስራ መልስ . . .  ስራ እንኳን የላቸዉም . . . ከወሬ መልስ ለሁለተኛ ዙር ወሬ ሲሰበሰቡ የሚጠጡትን መጠጥ ስም እንኳን እኔ እነሱም አያዉቁም። የህወሓት ስራ አመራር ኮሚቴ አባል ሆኖ አዉሮፓና አሜሪካ ቪላና የባህር ማዶ ባንክ ሂሳብ የሌለዉ ሰዉ የለም። አዲስ አበባ ዉስጥ ትላልቆቹ ህንጻዎች የሚጠሩት በወያኔ ጄኔራሎች ስም ነዉ። መሬት የሚሰጠዉ ለእነሱ ብቻ፤  አለችሎታቸዉ ብድር የሚያገኙት እነሱ ብቻ፤  ህንጻ መስራት የሚችሉትም እነሱ ብቻ ናቸዋ። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ የህወሐት ባለስልጣኖች ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባለፉት ሀያ አምስት አመታት የዘረፉት ገንዘብ 100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ስራ ሳይሰራ እየተኛ ቢዉል ሰላሳ አመት ይኖርበታል። እንግዲህ ይታያችሁ እነዚህ ወስላቶች አገራችንን እንደዚህ ሙልጭ አድርገዉ ከዘረፏት በኋላ ነዉ ትናንሹን ሌባ ለመቅጣት “ሙስና ኮሚሺን” የሚባል ከሌባ ሌባ እየመረጠ የሚቀጣ ድርጅት የፈጠሩት። አቶ ሃይልዬን በስኳር መላስ አልጠረጥራቸዉም ነበር፤ ግን ከ”አህያ” ጋር ዉለዉ እቺን ስኳር መላስ ተማሩ መሰለኝ እየመረጡ የሚያስሩት “ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል” አይነቱን ትናንሹን ሌባ ነዉ። እዉነቱን ለመናገር ኢትዮጵያ ዉስጥ “ሙስና ኮሚሺን” መቋቋም አልነበረበትም – ከተቋቋመም ስሙ “ሙስና ከማና” ነዉ መሆን የነበረበት፤  አማርኛ ለማይገባቸዉ ለነፕሮፌሰር ሳሞራ ደግሞ “ስርቂ እንተኮይኑ ከማና” መባል ነዉ ያለበት . . . .  ኡወ ፕሮፌሰሬ ስርቂ ከማሁም!

ኢትዮጵያ ፍትህን ሳያዛባ ህዝብን በእኩልነት ያሰተዳደረ መንግስት ኖሯት አያዉቅም። ሁሉም መንግስታት ዜጎችን አላግባብ አስረዋል፤  ገርፈዋል፤  ገድለዋል። የኃይለ ስላሴ ስርዐት የኢትዮጵያን ገበሬ እንደ ዕቃ የባላባቶች ንብረት ያደረገ ፊዉዳል መንግስት ነበር። ደርግም . . . እንደ ስሙ ደብድብ፤ ርገጥ ግደል ስርዐት ነበር። ሆኖም ቅድመ ህወሓት የነበሩት መንግስታት ሌላ ቢቀር በኢትዮጵያ አንድነትና ዳር ድንበር ከባዕዳን ጋር አይዋዋሉም። ቅድመ ህወሓት መሪዎቻችን ኢትዮጵያን “አገሬ ኢትዮጵያ” ወይም “አገራችን ኢትዮጵያ” እያሉ ነበር የሚጠሯት እንጂ “እቺ አገር” እያሉ አይጸየፏትም። ዛሬ ኢትዮጵያን “እናት አገሬ ኢትዮጵያ” እያለ በአለም ዙሪያ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ጠበቃ የቆመዉ ዕድሜዉ አርባና ከአርባ በላይ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ የአገር ፍቅርን እንደ ምግብ እየበላ ያደገዉ በቀሀስና በደርግ ዘመነ መንግስት ነዉ። በእነዚህ ሁለት ስርዐቶች ወቅት በተለይ በሀይለ ስላሴ ዘመን ኢትዮጵያዊ በየሄደበት ይከበር ነበር።  

በደርግና በኃይለ ስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያና የዜጎቿ ጥቅም ማስጠበቂያ ቦታዎች እንጂ የህወሓት አባላት መሰብሰቢያና የጥላቻ ዘፈን መዝፈኛ መድረኮች አልነበሩም። ኢትዮጵያዊያን በአምስትና ስድስት መቶዎች ሲገደሉና የኢትዮጵያ ህዝብ በቅዱስ ዮሐንስ ጥቁር ለብሶ ሀዘን ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ይህንን ሀዘን ይጋራሉ እንጂ ጭራሽ ሞታችንና መከራችን ያስደሰታቸዉ ይመስል የአንድን ዘር የበላይነት እያወጁ ጮቤ አይረግጡም! በዋሺንግተን ዲሲዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዉስጥ “ትግራዋይነት ክቡር መንነት” እየተባለ ሲጨፈር ያ በወጣትነቱ አድር ባይ ዛሬም አድር ባይ የሆነዉ ግርማ ብሩ ቁጭ ብሎ ይመለከት ነበር። ይህ ህይወቱን ሙሉ ለሆዱ ብቻ የኖረ አድር ባይ አልገባዉም እንጂ ኦሮሚያ ዉስጥ ዘጠኝ ወር ሙሉ የሱን ወገኖች የጨፈጨፉት እነዚያ “ትግራዋይነት ክቡር መንነት” እያሉ ሲጨፍሩ የነበሩትና የትግራይን ህዝብ ከተቀረዉ ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ለማጋጨት ሆን ብለዉ የተነሱ የህወሓት አባላት ናቸዉ ። 
ኢትዮጵያ ሁለቱ የአለማችን ትልልቅ ሀይማኖቶች ክርስትናና እስልምና ከሺ አመታት በላይ ጎን ለጎን የኖሩባት አገር ናት።  እነዚህ በስነ ምግባር የታነጹ መልካም ዜጎችን የሚያፈልቁ ተቋሞች ዛሬ የህወሓት ስልጣን ማስጠበቂያ ተቋሞች ሆነዋል። የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” የማይዋጥላቸዉን ዜጎች ቃሊቲና ቂሊንጦ የሚልኩ የህወሓት ማጥቂያ መሳሪያዎች ናቸዉ። ዩኒቨርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ገዢዎቹ ያሰቡለትን ብቻ የሚያስብ ደካማ ትወልድ የሚፈጥሩ የፕሮፓጋንዳ ተቋሞች ናቸዉ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን አዉቀዋለሁ፤  ማወቅ ብቻ ሳይሆን የዚህ ዩኒቭርሲቲ ኩሩ ተመራቂ ነኝ፤ ይህ ዩኒቨርሲቲ እኔን “እኔ” ያደረገ ምርጥ የአገራችን ተቋም ነበር፤  እንደዛሬዉ ከጫካ የመጡ ተፈራ ዋልዋና በረከት ስምኦንን የመሳሰሉ በወጉ 12ኛ ክፍል ያልጨረሱ ደናቁርት እነ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትንና እነ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘዉዴን ቁጭ አድርገዉ ታሪክ ለማስተማር ከመሞከራቸዉ በፊት! 
ዛሬ ኦሮሚያ፤  ጎንደር፤  ጎጃም ፤  ኮንሶ፤ ኦጋዴን፤  ቢኒሻንጉል፤ አፋርና ጋምቤላ ዉስጥ “እንዳሰኛችሁ ትገድሉናላችሁ” እንጂ ካሁን በኋላስ ለ”ህወሓት አንገዛም” እያሉ ለፍትህና ለእኩልነት ውድ ህይወታቸዉን የሚሰጡት የኢትዮጵያ ወጣቶች ከሰሞኑ በረከት ስሞኦን፤  አባይ ጸሐዬና እነዚያ ሁለት አሻንጉሊቶች “EBC”  ላይ ቀርበዉ የነገሩን አይነት “መልካም አስተዳደር” ስለጎደላቸዉ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ ወጣት የአንድ ዘር የበላይነት እንዲጠፋ ይፈልጋል፤ የኢትዮጵያ ወጣት ነጻነት፤ ፍትህ፤  እኩልነትና ዲሞክራሲ በተረጋገጡበት አገር ዉስጥ መኖር ይፈልጋል፤ የኢትዮጵያ ወጣት ዬትም ቦታ ይወለድ ወይም ከየትኛዉም ዘር ይወለድ የወደፊት ዕድሉ በችሎታዉና በባህሪይዉ እንጂ በዘሩ እንዲመዘን አይፈልግም። ለዚህ ነዉ ይህ ወጣት ዛሬ በአራቱም ማዕዘን ባዶ እጁን እስካፍንጫቸዉ ከታጠቁ የአግዓዚ ነብሰ ገዳዮች ጋር ፊት ለፊት የሚጋፈጠው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነትና ለእኩልነት የሚያደርገዉ ትግል ክፉኛ ያስደነገጠዉ ዕብሪተኛዉ ስዩም መስፍን የመንና ሊቢያ ዉስጥ የደረሰዉ ቀዉስ ኢትዮጵያም ዉስጥ መድረሱ አይቀርም ብሎ የአዞ ዕምባ እያነባ የሱንና የጓደኞቹን ምኞት ነግሮናል። ወይ አቶ ስዩም ! . . . ይህ ያነበበዉን እንኳን የማይረዳ ጅላጅል የባድሜ ጉዱን የረሳን መስሎታል። ኢትዮጵያን የመን፥ ሶሪያና ሊቢያ ወደ ተጓዙበት መንገድ የሚወስዳት ስዩም መስፍን የገነባዉን ዘረኛ ስርዐት ዘለአለማዊ ለማድረግ የሚደረገዉ የጅምላ ግድያና ጭፍጨፋ ነዉ እንጂ ይህ ዕብሪተኛ ሊነግረን እንደሞከረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነጻነቱ የሚያደረግዉ ትግል አይደለም። የኢትዮጵያ ወጣት በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የመብት፥ የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል እነ መስፍን ስዩም “EBC” ላይ ቀርበዉ ስለደነፉ የሚቆም ትግል አይደለም። አባይ ጸሐዬ፤  ስዩም መስፍን፤ ሳሞራ የኑስና አባይ ወልዱ የሚገነፍሉ ድስቶች ናቸዉ  . . . . እነዚህ ጡንቻ እራሶች አልገባቸዉም እንጂ “የሚገነፍል ድስት” የሚያበላሻዉ እራሱን ነዉ! ቸር ይግጠመን!!!
አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር  
ebini23@yahoo.com

http://wp.me/p5L3EG-dG

መንፈሳዊ ወኔና ሥልጣን ( ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

መንፈሳዊ ወኔና ሥልጣን

መስፍን ወልደ ማርያም

ጥቅምት 2009

ባለሥልጣኖቻችን ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን በጣም የናቋቸው ይመስላል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀውን ሁሉ ያውቃሉ፤ የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን ያያሉ፤ የኢትዮጵያን ራድዮ ይሰማሉ፤ ባሎቻቸውና አባቶቻቸው የዛሬ ሳምንት የተናገሩትን ረስተው፣ ወይም ክደው፣ ወይም ዋሽተው ተቃራኒውን ሲናገሩ መሸማቀቃቸው አይቀርም፤ እንዲህ ያለው የንግግር መገለባበጥ የእምነት መገለባበጥን፣ የማሰብ ችግርን፣ የመንፈስ ልልነትን ያሳያል፤ ታዲያ ሚስቶችና ልጆች እየተሸማቀቁ አካላቸውም ነፍሳቸውም ሲያልቅ ለባለሥልጣኖቹ አይታወቃቸውም? ወይስ የቤተሰብ አባሎች ጠባይ እየሆነ ሽታዬ ሽታዬ እየተባባሉ ነው?

አንዳንዶች ባለሥልጣኖች ወንበሩ ላይ የወጡት እግዚአብሔርን ሳይይዙ ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እግዚአብሔርን ይዘው ወንበሩ ላይ ይወጡና እግዚአብሔርን ከተቆናጠጡ በኋላ እግዚአብሔርን ከውስጣቸው የሚያስወጡት ይመስላል፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ብዙ አናውቅምና ለሱ እንተውለት፡

ግን እኛም ሰዎቹ ባለሥልጣኖቻችን እውነተኞች ቢሆኑ፣ በትክክል ቢያስቡና የመንፈስ ልዕልና ቢኖራቸው እንኮራባቸው ነበር፤ አርአያም ይሆኑን ነበር፤ ልጆቻቸውም ከልጆቻችን ጋር ተግባብተው ያድጉ ነበር፤ ባለሥልጣኖቻችን ለቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የመንፈስ ልዕልና አርአያ እንዲሆኑልን ኃላፊነት አለባቸው፤ ተደጋግሞ እንዳየነው በየዘመኑ የተሰየሙልን ባለሥልጣኖቻችን የኃላፊነት ግዴታ የሚጎድላቸው ናቸው፤ ለአምላካቸው የኃላፊነት ግዴታ አይታይባቸውም፤ ለቤተሰቦቻቸው የመንፈሳዊ ኃላፊነት ግዴታ አላደረባቸውም፤ ለአገራቸውና ለወገናቸው ደኅንነትና ብልጽግና ኃላፊነት አይሰማቸውም፤ የሥልጣን ወንበሩ የሚፈለገው ለሁለት ዓላማዎች ብቻ ነው፤ ለጉልበትና ለሀብት ብቻ!

በእኔ ዕድሜ ሥልጣንና የኃላፊነት ስሜት ሲጋጩና ነፍስን ሲገነጥሉ ‹‹በቃኝ!›› ብለው የመንፈስ ልዕልናቸውን መርጠው ሥልጣናቸውን ያስረከቡት ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ኃብተ ወልድ ናቸው፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ፊት ቀርበው፣ የማይደፈረውን ደፍረው፣ አሻፈረኝ! የማይባለውን አሻፈረኝ! ብለው ሥልጣን የሌለበትን የአገር ኃላፊነት በአጼ ኃይለ ሥላሴ እግር ስር አስቀምጠው ራሳቸውን ነጻ አወጡ! ትልቅ ድፍረት ነው፤ እንኳን በአገር ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትርን የሚያህል ሹመትና በትንሹ በአውራጃ አስተዳደሪ ደረጃም ቢሆን የጃንሆይን ትእዛዝ አልቀበልም ማለት ዋጋ ያስከፍላል፤ (እኔ በትንሹ ከፍያለሁ!)

ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ለአገራቸው ብዙ የደከሙ ሰው ናቸው፤ በታወቀው በፈረንሳዩ ሶርቦን ዩኒቨርሲቲ ተኮትኩተው ያደጉና በኢጣልያ ወረራ ጊዜ በአውሮፓ እየተዘዋወሩ ለኢትዮጵያ ነጻነት የታገሉ ሰው ናቸው፤ ከጦርነቱም በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተባበሩት መንግሥታት የአውሮፓውያን (የነጮች)ኃይል አክሊሉ በልበ-ሙሉነት ከምዕራባውያን ኃይሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በክርክር ሲተናነቁ ነበር፤ የምዕራባውያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጸሐፌ ትእዛዝን በጥቁርነታቸው ሊንቁ ሲቃጡ በአእምሮና በመንፈስ ልዕልናቸው እያሳፈሩ ልካቸውን አሳይተዋቸዋል፤ ነጮቹ በግዳቸው እንዲያከብሯቸው አደረጉ፤ እኝህ ሰው ናቸው በባህል ተጽእኖና በይሉኝታ ሥልጣን የሌለበትን ኃላፊነት ተቀብለውና ተሸክመው ለብዙ ዓመታት በጨዋ ደንብ የታገሉት፤ በመጨረሻም በቃኝ! አብዮታዊ እርምጃ ወሰዱና ለአጼ ኃይለ ሥላሴ ገበጣ መጫወቻ አልሆንም ሲሉ የኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ አቅጣጫን ያዘ፡፡

የዛሬው ጠቅላይ ሚኒስትር ከመጽሐፍ ቅዱስ ካልተማረ ከጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ ሊማር ይችላል፤ በመማርም ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ከአደጋ ሊያድን ይችል ይሆናል፤ አንድ ሰው ታሪክን ለመሥራት ይችላል፤ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ወኔውን ይስጠው!

http://wp.me/p5L3EG-dL

​ከሰሞኑ አስደናቂ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻዎች ሁለቱ ! Dr Tadesse Biru Kersmo

​ከሰሞኑ አስደናቂ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻዎች ሁለቱ !
Dr Tadesse Biru Kersmo
1. በ1997 ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የአመጽ አማራጮችን ሁሉ ይቃወም የነበረው ሰላማዊ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሁን የአመጽ ጥሪ ማቅረቡ በንጽጽር እየቀረበ ትናንት “ሰላምን በመስበክ ሲያሞኘን የነበረ ሰው ዛሬ ይኸው በይፋ ጦርነት አወጀብን” እያሉን ነው። በህወሓት ፕሮፖጋንዲስቶች ትንተና መሠረት፣ ይህ የአቋም ለውጥ የመጣው ስልጣን ፈላጊ ስለሆነ ነው።
ፕ/ር ብርሃኑ ከመነሻው የትጥቅ ትግል አማራጭን አለመስወዱ፤ ለሰላማዊ ትግል እድል መስጠቱ፤ በሰላማዊ መንገድ ታግሎ ለውጥ ለማምጣት በሙሉ እምነትና ጉልበት መንቀሳቀሱ ያስመሰግነዋል እንጂ እንዴት ሊያስወስቅሰው ይችላል? ትንሽ የማሰላሰል ችሎታ ያለው ሰው  “ለመሆኑ በ 1997 ምን ሆነ? ከ 1997 በኋላ የዚህን ሰው አቋም የሚያስቀይር ነገር ምን ተፈፀመ?” ብሎ አይጠይቅም ብለው ለማመን እንዴት ቻሉ?
ምርጫ 97 ለፕ/ር ብርሃኑ ያረጋገጠለት ህወሓት በሰላማዊ ምርጫ ስልጣን እንደማይለቅ ነው። ባይሆን “በ97ስ እንዴት በምርጫ ይለቃል ብሎ አመነ?” ቢባል እንኳን ትንሽ ወግ ያለው ጥያቄ በሆነ። ይኸ ጥያቄም ብዙ ጊዜ ተጠይቆ መልስ ሰጥቶበታል “ወያኔ በሰላም ለመልቀቅ ተፈጥሮው አይፈቅድለትም ከሚል ነቢባዊ ውሳኔ በተግባር ተፈትኖ የሚሰጥ ውሳኔ ይሻላል” ዓይነት ምላሽ ሲሰጥ ብዙ ጊዜ ሰምቸዋለሁ።
ይኸ ጉዳይ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ታህሳስ 4 ቀን 2002 ዓ. ም. (December 10, 2009) የኖቤል የሰላም ሽልማት ሲቀበሉ ያደረጉት ንግግር ያስታውሰኛል።  እንዲህ ብለው ነበር።
“እውነቱን በመቀበል እንጀምር − ብጥብጥ ያለበት ቅራኔን በእኛ እድሜ ማስቀረት አንችልም። ለወደፊቱም  ሕዝቦች − በግልም ሆነ በጋራ − ኃይልን መጠቀም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ከሞራል አንፃርም ተገቢ የሚሆንበት ሁኔታ ይኖራል።  ...  አንሳሳት! ክፋት በዓለም ላይ አለ። በሰላማዊ ትግል ሂትለርን መግታት አይቻልም ነበር።  ...  አንዳንዴ ጉልበት መጠቀም ያስፈልጋል ማለት ከሃቅ የራቀ ምፀት አይደለም፤ ይልቁንስ ታሪክን በቅጡ መረዳት፤ የሰውን ልጅ ድክመቶችን ማወቅ እና የምክንያታዊነት ውስንነትን መገንዘብ ነው።  ...  ሰላም ተመራጭ መሆኑ መታመኑ ብቻውን ሰላምን ለማስገኘት አይበቃም።”
2. ፕ/ር ብርሃኑ ከግብጽ መንግሥት 500,000 የአሜሪካ ዶላር “ተቀብሎ ሲደለደልድ” በብሔራዊ የደህንነት  መረብ “የረቀቀ” ስለላ የተገኘ የተባለው ድምፅ ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ነው።
ይህ ጉዳይ በቀጥታ እኔን የሚመለከት በመሆኑ ትንሽ ዘርዘር አድርጎ መግለጽ ያስፈልጋል።  ማንም ሰው የኔን ስምና የአያት ስም (Tadesse Kersmo) google search ውስጥ ቢያስገባ በብዛት የሚያገኘው አንድ የከሸፈ የኢንሳ የስለላ ታሪክ ነው። ከብዙዎቹ ጽሁፎች ኒውዮርከር ያወጣውን “Hacked by One’s Own Government” የሚለውን በዚህኛው ሊንክ ያገኙታል።
http://www.newyorker.com/online/blogs/elements/2014/03/hacked-by-ones-own-government.html
ነገሩ በአጭሩ የሚከተለው ነው። ደብረጽዮን በበላይነት የሚቆጣጠረው በስልኮች፣ በራድዮና የቴሌቪዥን ሞገዶች ላይ አፈና የሚያደርግ፤ በኢንተርኔትና ማኅበራዊ ሚያዎች (በተለይም ፌስ ቡክ) ስለላ ላይ የተሰማራ INSA የሚሉት አሳፋሪ ድርጅት አለ። ይህ ድርጅት እንደብዙዎቹ የህወሓት ተቋማት አጠቃቀሙን ባያውቅበት ውድ እቃዎችን መግዛት ይወዳል። ከሁሉ በላይ ውድ ወጪ ያስወጣው FinFisher የተባለው Gamma International የብርታኒያ ካምፓኒ የሚያመርተው የስለላ ሶፍት ዌር ነው። ባለሙያዎች እንደነገሩኝ ሶፍት ዌሩ 500 000 የእንግሊዝ ፓውንድ ያወጣል፤ እሱ በተጫነበት እያንዳንዱ ኮምፒተርም 100 000 የእንግሊዝ ፓውንድ ሰርቪስ ያስከፍላል። ኢንሳ ይህንን “አውዳሚ” መሳሪያ 2012 እአአ ታጥቆ በዚያኔው ግንቦት 7 ላይ ዘመተ።
የዚህ ሶፍት ዌር አንዱ ታርጌት የእኔ ላፕቶፕ ሆነ። ባለሙያዎች ለእንግሊዝ ፓሊስና ፍርድ ቤት ባቀረቡት መረጃ መሠረት FinFisher በኔ ላፕቶት “been active on or around 9 June 2012”. ከዚህ “ኢንቨስትመንት” ያገኙት የአንድ ቀን የስካይፕ ውይይት ነው - ዶ/ር ብርሃኑ የመራው እኔም የነበርኩበት። የተነጋገርነው እዚህ ከቀረበው ጋር ፈጽሞ ተያያዥነት የሌለው ነገር ነበር፤ ስለግብጽ አልተነሳም፤ ግኑኝነት ኑሮን ስለማያውቅም ሊነሳ አይችልም ነበር። ቆራርጠውና ቀጣለው አሁን ከካፕሽን የታጀበውን ቪድዮ በዩቱብ ለቀቁት። ይህ የተፈፀመው በ2012 መሆኑን ልብ በሉ።
በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች በሚሠራው Privacy International ድጋፍ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ስናቀርበው አንዱ የጉዳት ማስረጃዬ በዩቱብ የተለቀቀው ቪዲዮ ነበር። በመጀመሪያው የፍርድ ሂደት ተከሳሽ ሆኖ  የቀረበው የብሪታኒ የጉምሩክና የአገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤት ነበር - ለ Gamma International ይህን ሶፍት ዌር ለኢትዮጵያ ደንበኞቹ እንዲሸጥ ፈቃድ መስጠት አለመስጠቱ የሚገልጹ መረጃዎችን ይፋ አንዲያደርግ ነበር። ተፈረደልን፤ ይህም በወቅቱ ትልቅ ዜና ነበር። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ማየት ለሚፈልጉ https://www.privacyinternational.org/node/57
አሁን ክሱ ወደ Gamma International ዞሮ በሂደት ላይ ነው። እኔ እንዲከሰስ የፈለግሁት “የኢትዮጵያ መንግሥት” በሚል ኦፊሲያላዊ መጠሪያ የሚታወቀው የህወሓት አገዛዝ ነበር፤ ጠበቆች ማሳመን ባለማቻሌ ግን Gamma International  ላይ ተወሰንን። ይህ ጉዳይ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች የሚከታተሉት በቢቢሲ ሬድዮም መግለጫ የሰጠኹበት፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲም በተደጋጋሚ ተጠይቆ “ልማት ላይ ተጠምደናልና ዜጎቻችንን በመሰለል ጊዜና ገንዘብ አናጠፋም” ዓይነት ፈጣጣ ምላሾች እየሰጠቡት የነበረ ጉዳይ ነው። የዩቱብ ማስረጃን ከመንግሥት ወይም INSA የማዛመድ ችግር ነበር ጠበቆቹ የታየቸው።  እነሆ አሁን ይኸንኑ ቪዲዮ በብሄራዊ ቴሌቪዥናቸው አወጡት !!! Bingo !!!!
[በነገራችን ላይ ከ FinFisher ትንሽ አነስ ያለ Hacking Team የሚሉት ሶፍትዌርና በዚሁ ስም የሚጠራ የጣልያን ድርጅት አለ። እሱን ገዝተው ደግሞ ኢሳት ጋዜጠኞች ሞከሩት፤ እሱም ወዲያው “በቁጥጥር” ስር ዋለ። የሚገርመው ኢሳት ላይ ጥቃት ከተቃጣ ጥቂት ጊዜ በኋላ Hacking Team ራሱ Hack ተደረገና መረጃዎቹ በኢንተርኔት ተዘረገፉለት። INSA ለ Hacking Team የከፈለበት የ 1.2 ሚሊዮን ዮሮ አካባቢ ደረሰኝ ተገኘ። ከዚህ በላይ ደግም “እረ ባካችሁ ይኼ ነገር አልሠራ አለን” አቤታዎች ይፋ ሆኑ። ይህንን Wickileaks ላይ ማግኘት ይቻላል]
http://wp.me/p5L3EG-dN