Netsanet: Mai 2017

Dienstag, 16. Mai 2017

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጉዳይ ፍርድ ሰጠ!!! ( ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia)

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጉዳይ ፍርድ ሰጠ!!!
( ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia)
(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ) የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩን በእስር ላይ ሆኖ ሲከታተል የነበረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ፡፡አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት በፌስ ቡክ አመጽ ቀስቃሽ መልክቶችን አስተላልፈሃል በሚል ነው፡፡ተከሳሹ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ያስተላለፋቸው መልክቶች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ህገ መንግስታዊ መብቴን በመጠቀም እንደሆነና መልክቶችም አመፅ ቀስቃሽ እለመሆናቸውን፣ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ በመልካም አስተዳደር ችግር እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላው በሪፖርታቸው ላይ መግለፀፃቸውን በመግለፅ ጥፋተኛ እንዳለሆነ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም አቶ ዮናታን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6ን ተላልፈው ተገኝተዋል በማለት ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፍርድ ሰጥቷል፡፡የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6 ከ10 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ያስቀጣል፡፡

https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/16/%e2%80%8b%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8a%a8%e1%8d%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8d%8d%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%88%8d%e1%8b%b0%e1%89%b3-%e1%88%9d%e1%8b%b5%e1%89%a5/
https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/16/%e2%80%8b%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8a%a8%e1%8d%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8d%8d%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%88%8d%e1%8b%b0%e1%89%b3-%e1%88%9d%e1%8b%b5%e1%89%a5/

Samstag, 13. Mai 2017

"እጆቻችን ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ማታ በካቴና የታሰርን የተፈታነው ታኅሳስ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡" ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

"እጆቻችን ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ማታ በካቴና የታሰርን የተፈታነው ታኅሳስ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡"

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

"ከጠዋቱ 3 ሰዓት አካባቢ ከሶስቱም ዞን በተመሳሳይ ሰዓት ከውጭ ወደ ታራሚው መጥሪያ በመትረየስ እና በክላሽ ከፍተኛ የሆነ ተኩስ ወደ ታራሚው ተተኮሰ፡፡" "እጆቻችን ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ማታ በካቴና የታሰርን የተፈታነው ታኅሳስ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡" "እኛ የደሀ ልጆች ፍትህ ፊቷን አዙራብን መንግስት ሁሉን አጠንክሮብን ስለኛ የሚሟገትልን አካል አጥተን አሁን ለብቻ በተሰራልን ቂ/ማ/ቤት ጠባብ ጊቢ ውስጥ ተስፋ በቆረጠ ኑሮ ውስጥ እንገኛለን፡፡" "የሐይማኖ አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጋዜጠኞች እና የሟች ቤተሰቦች ዝም ማለታቸው እጅግ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እና አለማቀፍ ማህበረሰቡን የሚመለከት የህሊናና የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው፡፡" ግንቦት 01 ቀን 2009 ዓ.ም ግልፅ ደብዳቤ ለሚመለከታቸው ሁሉ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቂሊንጦ በቂሊንጦ ማ/ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ምክንያት የ23 ሰዎች ህይወት መጥፋት እና የመንግስት እና የህዝብ ንብረት መውደሙ ይታወቃል፡፡ ይህንንም መነሻ በማድረግ በሸዋ ሮቢት ማ/ቤት በፖሊስ እና ደህንነቶች ታራሚዎች ላይ የተደረገው ምርመራ እውነቱን ወደ ጎን በመተው በማ/ቤት ውስጥ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተንቀሳቀሰ እና ማ/ቤቱ ከመቃጠሉ በፊት ለረዥም ጊዜ የታቀደና ሲሰራበት የቆየ በማስመሰል ማ/ቤት በረዥም ጊዜ ዕቅድ እንደተቃጠለ አጣርቻለሁ ብሎ አቅርቧል፡፡ እውነቱ ግን የማ/ቤቱ አተት ገብቷል በሚል ምክንያት የቤተሰብ ምግብ አይገባም ብለው የለጠፉት ማስታወቂያ ምክንያት ታራሚዎች ኃላፊነት እንዲያነጋግሯቸው ሊጠይቁም የማ/ቤት አስተዳደር በወሰደው የኃይል እርምጃ ምክንያት የተፈጠረ በዕለት ግጭት የደረሰ አደጋ እንጂ ቀደም የታቀደ አይደለም እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ግን የአደጋው ምክንያት የሆኑትን የማ/ቤቱ ኃላፊዎችን ከተጠያቂነት ለማዳን ሲባል እኛ ጠያቂ እና ተቆርቋሪ የሌለን የደሀ ልጆች መልስ ሆነናል፡፡ ይህም በቅርቡ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለቀ/ማ/ቤት በደረሰው አጣርቻለሁ ብሎ ለህ/ተ/ም/ቤት ያቀረበው ሪፖርት እኛ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ተከሳሾች ያለ ነገር እና የእኛ እምነት ያላካተተ ቢሆንም የሪፖርቱ ውጤት የሚያሳየው የተከሰስንበት የክስ ጭብጥ ጋር በጭራሽ የማይገናኝ እና የሚጣረስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ፖሊስ በምርመራ ደረስኩበት ብሎ እኛን የከሰስንበት ሐሰት እና ያለውን የፖለቲካ ጫና ለመቀነስ የቀረበ የፖለቲካ መልስ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ማረሚያ ቤት ከፌ/መ/ቤቶች አንዱ የሆነና ጠንካራ ጥበቃ እና ከፍተኛ የሆነ ፍተሻ የሚደረግበት ሲሆን ቤተሰቦቻችን ለጥየቃ በሚመጡበት ጊዜ በኤሌትሪክ ማሽን እና በእጅ ከፍተኛ ፍተሻ ይደረግባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንኳ የማያደርገው እናቶቻችን እና ሴት እህቶቻችን ሞዴሳቸው ሳይቀር ከፍተኛ የሆነ አስነዋሪ ፍተሻ ይደረግባቸዋል፡፡ ፍ/ቤት ስንሄድ፣ ከጠበቃ ጋር ስንገናኝ እና ህክምና በምንወጣበት እና በምንገባበት ወቅት ከሁለት ጊዜ በላይ ጥብቅ ፍተሻ በሚደረግበት ታራሚው 1-10 በሚባል አደረጃጀት ተደራጅቶ ስለ ሀገሩ ስለፖለቲካ እና ሌሎችም ጉዳዮች እንዳያወራ እርስ በእርሱ በሚጠባበቁበት፣ ከ1-10 ውጭ በቡድን ሰው በማይቀመጥበት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ተላልፎ የተገኘ ታራሚ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የሚፈፀምበት እና ጨለማ ቤት በሚወረወርበት፣ መኝታ ክፍላችን ቢያንስ በሳምንት 1 ጊዜ በሚፈተሽበት፣ ጠያቂ ቤተሰብ ለአንድ ታራሚ ከ200 ብር በላይ መስጠት በማይቻልበት፣ የማ/ቤት ኃላፊዎች በማ/ቤት ግቢ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ንግድ በሚያካሔዱበት፣ ኦዲት ተደርጎ የማያውቀው መ/ቤት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ያለበት ሲሆን ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊ እረገጣ የሚካሄድበት ፌ/ማ/ቤት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ማ/ቤቱ በመቃጠሉ ለ23 ሰው ሞት ለ15 ሰው በጥይት መቁሰል እና የንብረት ውድመት የተከሰተ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ ደግሞ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው፡፡ ይኸውም ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም የማ/ቤቱ ኃላፊዎች የታራሚውን የየቤቱ አስተዳዳሪዎች በማስጠራት "በአተት በሽታ ምክንያት ከነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የቤተሰብ ምግብ የማይገባ መሆኑን ለታራሚው አሳውቁ" በማለት እነሱም/የታራሚ ተወካዮች/ "ለታራሚው እራሳችሁ ተናገሩ ታራሚውን አነጋግሩ" ቢሉም ኃላፊዎች "ለታራሚው ሔደን ከመንነግር አጥራችንን ብንጠብቅ ይሻለናል" በማለት ትዕዛዙን በዚህ መልኩ ካስተላለፈ በኋላ ነሀሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም ከነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ከቤተሰብ የሚመጣ ምግብ የማይገባ መሆኑን የሚገልፅ ማስታወቂያ በግቢው በር/ኮሪደር/ በመለጠፉ ታራሚው ለየዞን ተጠሪ ፖሊሶች "የቤተሰብ ምግብ ልንከለከል አይገባንም ኃላፊዎች መጥተው ያነጋግሩን" በማለት የጠየቀ ሲሆን በነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ጧት 12 ሰዓት ለቆጠራ ለመጡት ፖሊሶችም ታራሚው ይህንኑ ጥያቄ ሲያቀርብ ፖሊሶች ባልተለመደ ሁኔታ የግቢውን በር (ኮሪደር) ቆልፈው በመሄዳቸው ታራሚው እስከ 3 ሰዓት ድረስ በተስፋ ሲጠብቅ ቢቆይም ከጠዋቱ 3 ሰዓት አካባቢ ከሶስቱም ዞን በተመሳሳይ ሰዓት ከውጭ ወደ ታራሚው መጥሪያ በመትረየስ እና በክላሽ ከፍተኛ የሆነ ተኩስ ወደ ታራሚው ተተኮሰ፡፡ ታራሚውም እየተመታ ሲወድቅ ቀሪው ነብስ አውጭኝ በማለት ወደ መኝታ ክፍል በመግባት በሚሯሯጥበት ሰዓት የጭስ ቦንብ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ግቢው በመወርወሩ እና ግቢው በመቃጠሉ (ዞን 2 እና ዞን 3) ታራሚው በከፍተኛ ስቃይ ወደ ቅጥር ጊቢው ለመውጣት በምንታገልበት ጊዜ ወንድሞቻችን በጥይት ተመትተው ወደቁ፡፡ ወደ ቅጥር ጊቢው ከወጣን በኋላ እስከ ማታ እንድንውል ተደርጎ በማንነታችን በዘራችን ተጠርጥረን በገባንበት ክሳችን እናም በሐይማኖታችን በማ/ቤት ተለይተን 175 ሰዎች ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞብን ወደ ሸዋሮቢት ማ/ቤት የተወሰድን ሲሆን በጠቅላላው ታራሚው ልብሱን የአንገት ሐብሉን (የወርቅ የብር) የጣት ቀለበት (የጋብቻ የጌጥ) መፅሐፍት ለመፅሐፍ ቅዱሱ ቁራን እና ሌሎችን ጨምሮ) በኪሱ የያዘውን ገንዘብ እና ጫማውን ከተዘረፉ በኋላ ወደ ሸዋሮቢት እና ዝዋይ ማ/ቤት ተጭነን እስከ መስከረም 19 ቀን 2009 ዓ.ም በማ/ቤት ፖሊሶች በየቀኑ ሽንት ቤት ስንጠቀም ምግብ ስንመገብ ለሁለት ለሁለት እንደታሰርን እንድንጠቀም ተደርጎ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ይፈፀምብን ነበር፡፡ ሽንት ቤት ለሁለት እንደታሰርን በተቀመጥንበትም ጭምር እየተደበደብን እጃችን ወደ ኋላ እየታሰርን ጭቃ ላይ እየተንከባለልን ውሃ እየተርከፈከፈብን ዘግናኝ ድብደባ የተፈፀመብን ቆይተናል፡፡ ያለ ጫማ ሽንት ቤት እንጠቀም ነበር፡፡ ከመስከረም 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ከዝዋይ እና ከሸዋ ሮቢት የመረጡንን ታራሚዎች እና በወቅቱ ቃጠሎ ሲፈፀም በጨለማ ቤት የነበሩትን (ከግንቦት 2 ቀን 2008 ዓ.ም) ጀምሮ መ/አ/ ማስረሻ ሰጤ፣ አበበ ኡርጌሳ እና እስሜኤል በቀለን እንዲሁም ከእነሱ ጋር በጨለማ ቤት የነበረው ተፈርዶበት ወደ ዝዋይ ማ/ቤት ሄዶ የነበረው ፍቅረማርያም አስማማውን ቃጠሎውን የረዥም ጊዜ ዝግጅት በማስመሰል እነሱንም ወደ ሸዋ ሮቢት በማምጣት ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀቻቸው አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን እና ህገ መንግስታዊ መብታችን እንዲሁም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መሪዎች ደርግን አስወግደው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት ሲቃይ(ቶርቸር) አይደገምም ብለው ሐውልት ያቆሙለትን ነገር እጅግ አሰቃቂ፣ አስነዋሪ እና ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ "በተሰፋልህ ልክ ትለብሳለህ ወደድክም ጠላህም የፖለቲካ መልስ ትሆናለህ" እየተባልን፡- 1ኛ. ሁለት እጃችን በካቴና ታስሮ ወደ ጣራ በማንጠልጠል እግሮቻችን በአየር ላይ በየአቅጣጫው ከማገር ጋር እየወጠሩ፤ 2ኛ. የእጃችን አውራ ጣቶች በሲባጎ በአንድ ላይ ከታሰሩ በኋላ በእጃችን መሀል ጉልበታችን ታጥፎ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ በጉልበታችን መሀል እንጨት ተደርጎ ተዘቅዝቀን ተሰቀለን ውስጥ እግራችን በከፍተኛ ሁኔታ ተደብድበናል፤ 3ኛ. በኤሌክትሪክ ሾክ ተደርገናል፤ 4ኛ. ብልታችን ላይ ሀይላንድ ውሃ ተንጠልጥሏል አሁን ማህን እንሁን አንሁን አናውቅም፤ 5ኛ. ጥፍራችን በፒንሳ ተነቅሏል፡፡ እጆቻችን ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ማታ በካቴና የታሰርን የተፈታነው ታኅሳስ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡ በአጠቃላይ መሬት እና ሰማይ ድብልቅልቅ እስከሚልብን ድረስ እየተደበደብንና እየተሰቃየን ዘግናኝ የሆነ ኢ-ሰብዓዊ ረገጣ ተፈፅሞብናል፡፡ አንዱን ተሰቃይ አደራጅ ሌላውን ተደራጅ በማስመሰል አማራ፣ ጉራጌ እና ደቡቡን የግንቦት 7 አደራጅ፤ ኦሮሞውን የኦነግ አደራጅ፤ በሐይማኖት ነፃነት ጥያቄ የገቡ ሙስሊሞችን የአልሸባብ አደራጆች፤ ድሃውን የአዲስ አበባ ወጣት ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት ተደራጅ እና ሀገራቸውን በህክምና ሊያገለግሉ ከስዊድን አገር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የአዲስ የልብ ህክምና ባለቤት የሆኑትን ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ እና በሙስና ተጠርጥሮ የታሰረው ሚስባህ ከድርን የገንዘብ ምንጭ (ደጋፊ) በማስመሰል በነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በቃጠሎው ዕለት ዶ/ር ፍቅሩ ባዘጋጁት 60 መኪኖች በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ እንዲቆም ተደርጎ ከእስር ቤት አምልጠን በአምስት አቅጣጫ (በጎንደር በአሶሳ በሞያሌ በኢትዮጵያ ሶማሌ) አድርጋችሁ ወደ ኤርትራ በመሄድ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ልትገናኙ አስባችኋል፣ ቂ/ማ/ቤት አቃጥላችኋል (በዕለቱ ግን አንድም ታራሚ የተለየ እንቅስቃሴ አላደረገም/የሚል ሰነድ በማዘጋጀት የእኛ ያልሆነ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 27/2 ቃል እንድንፈርም ተደርጎ ፅሁፉንም እያጠናን እንድንለማመድ ከተደረገ በኋላ ቪዲዮ የተቀረፅን ሲሆን እርስ በርስ ከስቃይ ብዛት እንድንገናኝ እያደረጉ "አደራጅቻለሁ፣ ገንዘብ ሰጥቻለሁ፣ ኤርትራ ልንሄድ ነበር፣ ከእስር ቤት ልናመልጥ ነበር" እንድንባባል አደረጉ፡፡ የቃጠሎውን መንስኤ እና እውነት ወደ ጎን በመተው የማናውቀውን እና የእኛ ያልሆነውን በተባለው መልኩም ያልተፈፀመውን ወንጀል የእኛ ለማስመሰል በእንዲህ አይነት ሁኔታ ከ1 ወር ከ15 ቀን በላይ (ለሁሉም ሰው የፈጀው ጊዜ ነው) የፈጣሪ ያለህ፣ የመንግስት ያለህ፣ በህግ አምላክ ግደሉን እናቴ አባቴ ወየው ስንል ሰሚ አጥተን አካላችን ጎሎ ሞራላችን ተነክቶ 38 ሰዎች 19ኛ ወ/ችሎት በሽብር አንቀፅ 3/11214/ እና 6 ተከፍቶብን በግፍ እስር ላይ እንገኛለን፡፡ ፍ/ቤት ቀርበን ህገ መንግስታዊ መብቶቻችን ተጥሰዋል፤ 1ኛ በግዳጅ የተገኘ ቃል በህገ መንግስቱ የተከለከለ መሆኑን አስረድተን በ27/2 መሰረት በሲቃይ ብዛት የሰጠነው ቃል ውድቅ ይደረግልን፤2ኛ ያሰቃዩንን እና ኢሰብዓዊ ድርጊት የፈፀሙብንን የመርማሪ ፖሊሶች የማ/ቤት አመራር እና ፖሊሶች መክሰስ እንድንችል ፖሊስ ቃላችን እንዲቀበለን፤ 3ኛ አካላችን ላይ የነበረው ጠባሳ (በአሁኑ ወቅት የአብዛኞቻችን ድኗል/ሽሯል) ፎቶ ግራፍ እንድንነሳ፤ 4ኛ የቂሊንጦ ቃጠሎ መንስኤውን ገለልተኛ ወገን እንዲያጣራው ፍ/ቤቱ እንዲያዝ እና ፍርደኞች ወደ ፍርድ ክልል (ቃሊቲ) እንዲሄዱ ተደርጎ ክሳችንን ከዚያ ሆነን እንድንከታተል ያቀረብነው አቤቱታ እና የህይወት ዋስትና እንዲሰጠን አቤቱታ ያቀረብን ቢሆንም ፍ/ቤቱ አንድም ነገር ሳይበይን ለግንቦት 14 ዓቃቢ ህግ በሃሰት ያደራጃቸውን ምሰክሮች ለመስማት ቀጥሮናል፡፡ ማ/ቤቱም ለምን አቤቱታ አቀረባችሁ በማለት 37 ሰዎችን 4 በ5 በሆነች ጠባብ ቤት ውስጥ ጨለማ ክፍል ከ2 ወር በላይ በመቆየት አሰቃይተውናል፡፡ ከዚሁ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ 121 ሰዎች ልደታ 3ኛ ወ/ችሎት በአንድ መዝገብ የከሰሱ ሲሆን 8 ሰዎችን እያንዳንዳቸው እና የ539/1ሐ የወ/ህግን በመተላለፍ የከሰሳቸው ሲሆን ቀሪዎችን ደግሞ በከባድ ንብረት ማውደም እና ሁከት ሁለት ክስ ከፍቶባቸው አቤቱታ አንሰማም ተብለን እኛም ፍ/ቤቱን ሳይስማ ክሱ አይነበብም ብለን አሁን ለግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ.ም ዐ/ህግ ክሱን 20/20 እያደረገ እንዲያደራጅ የቀጠረን ሲሆን ልደታ 3ኛ ወ/ችሎት እናቀርባለን፡፡አንደኛ በእስር ላይ የነበሩ ሰዎችን በቃሊቲ ማ/ቤት ዞን 8 አስቀምጠው በሐሰት እኛ ላይ ከመሰከሩ ከዚህ ቀደም ተከሰውበት የገቡበት ክስ እንደሚቋረጥላቸው (እንደሚፈቱ) ቃል ተገብቶላቸው በሀሰት ሊመሰክሩብን ተዘጋጅተዋል፡፡ እኛ የደሀ ልጆች ፍትህ ፊቷን አዙራብን መንግስት ሁሉን አጠንክሮብን ስለኛ የሚሟገትልን አካል አጥተን አሁን ለብቻ በተሰራልን ቂ/ማ/ቤት ጠባብ ጊቢ ውስጥ ተስፋ በቆረጠ ኑሮ ውስጥ እንገኛለን፡፡ ክሱን እንቆቅልሽ የሚያደርገው ደግሞ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ አስገብተውላቸዋል በማለት የማ/ቤት 8 ፖሊሶች ነገሩን እውነት ለማስመሰል ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወስደው ከመረመሯቸው በኋላ በዋስትና ለቀዋቸዋል፡፡ ይህም ከሽብር አዋጁ ጋር በተፃረረ መልኩ ሲሆን እኛ ግን ቀደም በገባንበት ክሳችን ነፃ ብንባልም (ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ እና ሚስባህ ከድርን ጨምሮ ብዙ ሰው ነፃ የተባለ አለ) እንዲሁም በቀደም ክሳችን ተፈርዶብን የተፈረደብንን ፍርድ ብንጨርስም በአሁኑ የሀሰት ክስ በግፍ እስር ላይ እንገኛለን፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ስደተኞችን ለመቀበል በአለም 2ኛ ሆና እያለ በእኛ በዜጎች ላይ እንዲህ አይነት አረመናዊ ኢሰብዓዊ ድርጊት ሲፈፀም እውን በስልጣን ላይ ያሉ መሪዎች አያውቁምን? የሐይማኖ አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጋዜጠኞች እና የሟች ቤተሰቦች ዝም ማለታቸው እጅግ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እና አለማቀፍ ማህበረሰቡን የሚመለከት የህሊናና የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም በፖሊስ የተሰጠን የሐሰት ክስ ተቋርጦ በሰብዓዊ መብት ሪፖርት መሰረት እንደገና ምርመራ ተደርጎ እኛን ስለማይመለከተን ክሱ ለባለቤቱ እንዲሰጥ እያልን ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ አደረግን በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት የተነሱ እና ያልተነሱ በተጨማሪ በምርመራ የደረሰብንን አጠቃላይና ያለውን እውነት አያይዘን የላክን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/13/%e1%8a%a5%e1%8c%86%e1%89%bb%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8a%90%e1%88%90%e1%88%b4-28-%e1%89%80%e1%8a%95-2008-%e1%8b%93-%e1%88%9d-%e1%88%9b%e1%89%b3-%e1%89%a0%e1%8a%ab%e1%89%b4%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%89%b3/
https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/13/%e1%8a%a5%e1%8c%86%e1%89%bb%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8a%90%e1%88%90%e1%88%b4-28-%e1%89%80%e1%8a%95-2008-%e1%8b%93-%e1%88%9d-%e1%88%9b%e1%89%b3-%e1%89%a0%e1%8a%ab%e1%89%b4%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%89%b3/

Donnerstag, 4. Mai 2017

“አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” (ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

“አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ”

ሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት፣ በኔ ግምት አገራችን የገባችበትን ማጥ በጥሩ ሁኔታ የተነተነ ጽሁፍ አቅርበዋል። የጽሁፉ አጠቃላይ ይዘት መደምደሚያ ላይ በቀረቡት የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ማጠቃለል ይቻላል።

“አገራችን የገጠማት ችግር ተራ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳይሆን፣ እንደ አገር ቆሞ የመቀጠልን ሥጋት የጋረጠ ከፍተኛ የደኅንነት አደጋ [ነው] ....  መወያያትና መነጋገር ያለብን ከሕገ መንግሥቱ በታች የፖሊሲዎች ቁንጮ በሆነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ዙርያ ነው። ... የደኅንነታችን ዋና የሥጋትም የኩራትም ምንጭ ውስጣዊ የዴሞክራሲና የልማት ሁኔታ መሆኑ በመገንዘብ፣ የችግሩን ሥረ መሠረት ትቶ አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተንጠላጥሎ የሚመጣ ለውጥ ሊኖር እንደማይችል መረዳት [አለብን]።”

ሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት አገዛዙ አገራችንን ወዴት እየመራት እንደሆነ በትክክል ያብራሩ በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል። ይሁን እንጂ ችግሩን በተገነዘቡበት ጥልቀት ልክ ለመፍትሄ ሲተጉ አልታየኝም። ለመዋቅራዊ ችግር መዋቅራዊ መፍትሄ የሚያስፈልገው መሆኑ ተቀብለው እያለ “ይህን መዋቅራዊ መፍትሄ የሚያመጣው ማነው? እንዴት ነው?” የሚሉትን ቁልፍ ጥያቄዎች አድበስብሰው አልፈዋቸዋል። እሳቸው መፍትሄ ብለው ያቀረቡት ሃሳብ ሲጨመቅ የሚከተለው ነው “እያጠናሁት ነው የሚለው የፖሊሲ ክለሳም ሆነ ጥልቅ ተሃድሶ ... የፖለቲካዊ ፓርቲዎች፣ የሲቪልና የሙያ ማኅበራት፣ የክልል ምክር ቤቶች፣ ወዘተ. ተሳትፎና የተለያዩ አስተያየቶች ተጨምሮበት መሆን ይገባዋል።”

ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት የሚከተሉት ጥያቄዎችን እንዲያጤኑልኝ እጠይቃለሁ።

1. እምነትዎ ”እያጠናሁት ነው” በሚለው አካል ነው። የችግሩ ፈጣሪ የመትሄው አምጭ ይሆናል ብለው እንዴት ሊያምኑ ቻሉ?
2. “የፓለቲካ ፓርቲዎች” ሲሉ እነማንን ነው? በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች አሉ ወይ?
3. “የሲቢክና የሙያ ማኅበራት” ሲሉስ እነማንን ነው? በኢትዮጵያ ውስጥ የሲቢክ ማኅበራት አሉ ወይ? በኢትዮጵያ ነፃ የሙያ ማኅበራት አሉ?
4. የክልል ምክር ቤቶችስ ያው “እያጠናሁት ነው” የሚሉ ሸንጎዎች አይደሉምን?
5. የችግሩ ጥልቀት ስር ነቀል የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ የሚሻ መሆኑ ትንተናዎ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። እርሶ መፍትሄ ይሆናል ብለው ተስፋ ያደረጉት ”የብሔራዊ ደህንነት ፓሊሲና የአመራሩ መግባባት” ውጤት የሆነ “የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ“ ነው። ለእርስዎ ቁልፍ መፍትሄ የሆነው ይህ ፓሊሲ እንዴት በክለሳና በተሃድሶ ይመጣል?  ይህንን ትልቅ ተቃርኖ እንዴት ዘለሉት?
6. እርስዎ በመፍትሄነት ያቀረቡት ፓሊሲ የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ይሻል። የራስዎ ትንተና ወደሚመራን መፍትሄ ከመሄድ ማፍግፈግን ለምን መረጡ? “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” አይሆንም ወይ?

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=75797

Dienstag, 2. Mai 2017

ኢትዮጽያ እውን የሁላችንም ናት ካልሆነችስ የማን ናት?

ኢትዮጽያ እውን የሁላችንም ናት ካልሆነችስ የማን ናት?
========================
በፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊወርጊስ እጅ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት የተሰጣቸዉ የኢፌደሪ መከላከያ አባላት =================================== 1. ብ/ጀ ያይኔ ስዩም ገ/ማሪያም (ትግሬ) 2. " ኣታክልቲ በርሄ ገ/ማሪያም(ትግሬ) 3. " ፍስሀ በየነ ስዩም(ትግሬ) 4. " ጉኡሽ ጽጌ ወ/ገብኤል(ትግሬ) 5. " ገ/ኪዳን ገ/ማሪያም ያአቢዩ(ትግሬ) 6. " ማሀሾ ሃጎስ ስዩም(ትግሬ) 7. " ገብሩ ገ/ማሪያም ወልድ(ትግሬ) 8. " በሻህ ገ/ሚካኤል ኪ/ማሪያም(ትግሬ) 9. " አብርሃ አረጋይ ለገሰ(ትግሬ) 10. " አስካለ ብርሃነ ተራ(ትግሬ) 11. " ሀፍሎም እጅጉ መጎሰ(ትግሬ) 12. " አብርሃ ተስፋይ በርሄ(ትግሬ) 13. " ሙሉ ግርማይ ገ/ህይወት(ትግሬ) 14. " ወ/ገብርኤል ባቢ ገ/መድህን(ትግሬ) 15. " ፍስሃ ኪ/ማሪያም ወ/ህይወት (ትግሬ) 16. " አሰፋ ገብሩ ወርቅነህ(ትግሬ) 17. " የማነ ሙሉ ሀብተ (ትግሬ) 18. " ገ/መድህን ፍቃዱ ሃይሉ (ትግሬ) 19. " ታረቀኝ ካሳሁን ብሩ (ትግሬ) =========================== በፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እጅ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት የተሰጣቸዉ የኢፌደሪ መከላከያ አባላት ======================== ሜ/ጀኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ተስፋማሪያም ወደ ሌትናል ጀነራልነት(ትገሬ) ========================== ከብ/ጀኔራል ወደ ሜ/ጀኔራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው =========================== 1. ሜ/ጀ ፍስሃ ኪዳኑ ፋንታ (ትግሬ) 2. " ተስፋይ ግደይ ሀ/ሚካኤል (ትግሬ) 3. " ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊስ ተስፋይ (ትግሬ) 4. " ኢብራሂም አብደልጀዲል መሃመድዚን(ትግሬ) 5. " ገ/አድሃነ ወለዝሁ (ትግሬ) 6. " ማሞ ግርማይ ወንዳጥር(ትግሬ) ============================ ከኮ/ል ወደ ብ/ጀኔራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው ============================= 1. ብ/ጀ አብዱራሃማን እስማኤል አሎ (ትግሬ) 2. " ዘነበ አማረ ወ/ኢየሱስ(ትግሬ) 3. " ዜናዊ ገ/እግዚአብሄር ደስታ(ትግሬ) 4. " ዘዉዱ ኪሮስ ገ/ኪዳን (ትግሬ) 5. " ሙዘይ መኮንን ተወልደ(ትግሬ) 6. " ገ/እግዜር በየነ ሃይሉ(ትግሬ) 7. " ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሄር ሃጎስ(ትግሬ) 8. " አማረ ገብሩ ሃይሉ(ትግሬ)(ትግሬ) 9. " ተስፋይ ወ/ማሪያም ሃብቱ(ትግሬ) ========================= አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት መዋቅር ========================= 1. የመከላከያ ኢታማጆር ሹም ፕ/ር ሜ/ጀ ሳሞራ የኑስ (ትግሬ) 2. የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀ ገ/ኪዳን ገ/ማሪያም(ትግሬ) 3. የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ፍፁም ገ/እግዚአብሄር(ትግሬ) 4. የመከላከያ በጀትና ፕሮገራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ምቡዝ አብርሃ(ትግሬ) 5. የመከላከያ የኪነ-ጥበባት ስራወች ሀላፊ ኮ/ል ክብሮም ገ/ እግዚአብሄር(ትግሬ) 6. የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን የግንኙነት መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል ነጋሲ ትኩ(ትግሬ) 7. የመከላከያ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ገ/ትንሳይ ሃጎስ(ትግሬ) 8. የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ ሌ/ጀ ሳህረ መኮንን(ትግሬ) 9. የመከላከያ ሎጅስቲክ መምሪያ ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ኢብራሂም አብደል ጀሊድ(ትግሬ) 10. የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሃላፊ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኛዉ(ትግሬ) 11. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንደንት ብ/ጀ ሃለፎም እጅጉ (ትግሬ) 12. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ሃላፊ ኮ/ል ሃጎስ ብርሃነ (ትግሬ) 13. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ብ/ጀ ገ/እግዚአብሄር በየነ (ትግሬ) 14. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊ ኮ/ል ግርማይ ገ/ጨርቆስ(ትግሬ) 15. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዱክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ኮ/ል ጌታሁን ካህሳይ (ትግሬ) 16. የብላቴ ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል ዮሃንስ ካህሳይ (ትግሬ) 17. በልዩ ሀይል ማሰልጠኛ ማእከል የልዩ ኃይልና ጸረ ሽብር ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ ሻለቃ ተክላይ ወ/ገብርኤል(ትግሬ) 18. የሜ/ጀ ሀየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ ኮ/ ል ጎይቶም ፋሮስ(ትግሬ) 19. የጦር ላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል አደም ምትኩ(ትግሬ) 20. የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አሰፋ ዮሃንስ(ትግሬ) 21. የሆሚት አሙኒሽን ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ዋና ሀላፊ ኮ/ል ሃድጉ ገ/ጊዮርጊስ(ትግሬ) 22. የሜ/ጀ ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ኮ/ል ብርሃነ ተክሌ(ትግሬ) 23. የመከላከያ ኮንስትራክሽንና ኢንጅነሪንግ ማሽነሪ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ካህሳይ ክህሸን(ትግሬ) 24. የመከላከያ መሰረታዊ ልማትና ግንባታ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄ(ትግሬ) 25. የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ኢንዱስትሪ ም/ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አማኑኤል አብርሃ(ትግሬ) 26. የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ ሓላፊ ሌ/ኮ ለተብርሃን ደመወዝ(ትግሬ) 27. የመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ሃጎስ አስመላሽ(ትግሬ) 28. የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ጸጋዬ ግርማይ(ትግሬ) 29. የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግኑኝነትና ስርአት ደህንነት መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል በርሄ አረጋይ (ትግሬ) 30. የመከላከያ ፋዉንዴሽን ሃላፊ ብ/ጀ ያይኔ ስዩም (ትግሬ) 31. የሽሬ ከተማ ኮሪደር ሜንተናንስ ሀላፊ ኮ/ል አብርሀ ገ/ መድህን(ትግሬ) 32. የብሄራዊ ተጠባባቂ የሃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ማሞ ግርማይ(ትግሬ) 33. የኢንሳ ዳይሬክተር ሜ/ጀ ተክለብርሃን/ካህሳይ(ትግሬ) 34. የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተርና የጅኦስፓሻል ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ታዚር ገ/እግዚአብሄር(ትግሬ) 35. የሰሜን እዝ አዛዥ ጄ/ል መብራት አየለ(ትግሬ) 36. የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ሀላፊ ብ/ጀ ማዕሾ በየነ(ትግሬ) 37. የሰሜን እዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ሀላፊ ሌ/ኮ ሙሉ አብርሃ 38. የሰሜን እዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ሀላፊ ኮ/ል ገ/ስላሴ በላይ(ትግሬ) 39. የሰሜን እዝ የሰሜን ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ ል ላዕከ አረጋዊ(ትግሬ) 40. የሰሜን እዝ መሃንዲስ አዛዥ ኮ/ል ተሰስፋየ ብርሃኔ(ትግሬ) 41. የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ፅ/ቤት ሀላፊ ኮ/ል ገ/ዮሃንስ ተክሌ(ትግሬ) 42. የሰሜን እዝ አጠቃላይ የትምህርት አገልግሎት ኃላፊ ኮ/ል ግደይ ሃይሌ(ትግሬ) 43. የሰሜን እዝ የመድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ሀላፊ ኮ/ል ሰገደ/ ገ/መስቀል(ትግሬ) 44. የሰሜን እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ሀላፊ ኪሮስ ወ/ስላሴ(ትግሬ) 45. የሰሜን እዝ ዘመቻ ሀላፊ ኮ/ል ታደለ ገ/ህይወት(ትግሬ) 46. የሰሜን እዝ የሰዉ ሃይል አመራር መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል መሃሪ አሰፋ(ትግሬ) 47. የሰሜን እዝ የብ/ጀ በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ኮ/ል ጀማል መሃመድ(ትግሬ) 48. የሰሜን እዝ የብ/ጀ በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ሆስፒታል ጤና ሀላፊ ሌ/ኮ ተክላይ ገ/ መድህን(ትግሬ) 49. የሰሜን እዝ የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ዳይሬክተር ሻለቃ ነጋሲ ሃጎስ(ትግሬ) 50. የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ዮሃንስ ወ/ዮሃንስ (ትግሬ) 51. የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ሀላፊ ብ/ጀ አብርሀ ተስፋይ(ትግሬ) 52. የማዕከላዊ ዕዝ የትምህርት ክትትል ሀላፊ ሌ/ኮ ሀጎስ ሀይሌ(ትግሬ) 53. የማዕከላዊ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ አዛዥ ኮ/ል ገ/ሚካኤል ኪ/ማርያም(ትግሬ) 54. በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ ምክትል አዛዝና የኦፕሬሽን ሀላፊ ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ገ/ሰላማ(ትግሬ) 55. በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪና ማመላለሻ ዲፓርትምንት ሀላፊ ሻለቃ ተክላይ ካህሳይ (ትግሬ) 56. የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ፍስሀ ኪዳኑ(ትግሬ) 57. የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የሎጅስቲክ ሀላፊ ብ/ጀ አብድራሃማን ኢስማኤል(ትግሬ) 58. የምዕራብ ዕዝ ኢንሰፔክሽን ሀላፊ ኮ/ል ዮሃንስ ገ/ሊባኖስ (ትግሬ) 59. የምዕራብ ዕዝ ሲግናል ሬጅመንት አዛዥ ኮ/ል ተክላይ ገ/ ጻድቃን (ትግሬ) 60. የምዕ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ገ/ ኪዳን ቸኮል(ትግሬ) 61. የምዕራብ ዕዝ የስልጠና ሀላፊ ኮ/ል በርሄ ኪዳነ(ትግሬ) 62. የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ሀላፊ ኮ/ል ንጉሴ ሐ

https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/02/%e2%80%8b%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%bd%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%81%e1%88%8b%e1%89%bd%e1%8a%95%e1%88%9d-%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%8d%e1%88%86%e1%8a%90
https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/02/%e2%80%8b%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%bd%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%81%e1%88%8b%e1%89%bd%e1%8a%95%e1%88%9d-%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%8d%e1%88%86%e1%8a%90/

ቀላል የስነልቦና ጦርነት ስልቶች:  ማግለል፣ ማድነቅ እና ማብራራት ( ዶ /ር ታደሰ ብሩ) 

ቀላል የስነልቦና ጦርነት ስልቶች:  ማግለል፣ ማድነቅ እና ማብራራት

ማግለል – የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድና የደኢህዴን እንዲሁ የአጋር ድርጅቶች ቀንደኛ አባላትን፤ ግፈኛ የፌደራል ፓሊስ አባላትን፣ በየመንደሩ እያነፈነፉ ያሉት ጆሮ ጠቢዎችን፣ ጭንቅላት የለሽ ፓሊሶችን፣ ፍርደ ገምድል ዳኞችን፣ ሀሰተኛ አቃቢያነ ህግ፣ ካድሬ መምህራንን፣ የመንደር ለፍላፊ ውሸታም ካድሬዎችን፣ አድርባይ “አርቲስቶችን”፣ “ልማታዊ ጋዜጠኞችን” ማግለል፣ መጠየፍ፣ ማራቅ፣ መናቅ፣ ማዋረድ፤ በእነሱ ላይ ማፌዝ፤ ድንቁርናቸውን፣ ሆዳምነታቸውንና አድርባይነታቸውን  የሚገልፁ የቅሌት ስሞችን ማውጣት እና ማሰራጨት። 
ማድነቅን – ለነፃነት ሲሉ ዋጋ የከፈሉ እና እየከፈሉ ያሉ ዜጎችን ማድነቅ፤ አርዓያነታቸውን ማጉላት፤ ማበረታታት፤ ሁለተናዊ ድጋፍ መስጠት። 
ማብራራት – የሥርዓቱ አገልጋዮች አድርባይነት ከዚያም አልፎ ወንጀለኝነት በማስረጃዎች አስደግፎ ይፋ ማድረግ።   ስለ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፤ ሰለ ሀብት ዘረፋ፣ ስለ ሙስናን፣ ስለ መሬት ቅርምት፣ የባለስልጣኖች ሀብት ማሸሽን በሀሪቱ ከተንሰራፋው እና እያደገ ከመጣው ድህነት ጋር እያነፃፀሩ ማቅረብ። አስከፊ ስለሆነው የእስረኞች አያያዝ በሀቅ ላይ የተመሠረቱ ጽሁፎችን በጋዜጦች፣ ሬድዮና ቴሌቪዥኖች መሰል መገናኛ ብዙሀን እንዲሰራጭ ማድረግ።

https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/02/%e1%89%80%e1%88%8b%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%b5%e1%8a%90%e1%88%8d%e1%89%a6%e1%8a%93-%e1%8c%a6%e1%88%ad%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%88%b5%e1%88%8d%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%88%9b%e1%8c%8d%e1%88%88%e1%88%8d/