የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጉዳይ ፍርድ ሰጠ!!!
( ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia)
(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ) የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩን በእስር ላይ ሆኖ ሲከታተል የነበረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ፡፡አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት በፌስ ቡክ አመጽ ቀስቃሽ መልክቶችን አስተላልፈሃል በሚል ነው፡፡ተከሳሹ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ያስተላለፋቸው መልክቶች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ህገ መንግስታዊ መብቴን በመጠቀም እንደሆነና መልክቶችም አመፅ ቀስቃሽ እለመሆናቸውን፣ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ በመልካም አስተዳደር ችግር እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላው በሪፖርታቸው ላይ መግለፀፃቸውን በመግለፅ ጥፋተኛ እንዳለሆነ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም አቶ ዮናታን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6ን ተላልፈው ተገኝተዋል በማለት ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፍርድ ሰጥቷል፡፡የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6 ከ10 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ያስቀጣል፡፡
https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/05/16/%e2%80%8b%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8a%a8%e1%8d%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8d%8d%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%88%8d%e1%8b%b0%e1%89%b3-%e1%88%9d%e1%8b%b5%e1%89%a5/

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen