(የአርበኞች ግንቦት 7ድምፅ ሬድዬ)
ጀግናው የአርበኞች ግንቦት7 ስራዊት በህወሀት አገዛዝ የጦር ሀይል ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ።
የአርበኞች ግንቦት7ስራዊት ተደጋጋሚ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የህወሀትን መከላከያ ስራዊት ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታነቱን እየመስከረ ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት ህዳር21/2008አ.ም ጀግናው ስራዊታችን በዋልድባ በጠላት ስራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዋልድባ ወደ አዲ-አርቃይ ላይ ከወያኔ መከላከያ ስራዊት የሚሊሻ ታጣቂ ሀይል ጋር ከቀኑ10፡00 ስአት ጀምሮ እስከ 1፡00ለሶስት ተከታታይ ስአታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ በማድረግ በጠላት ላይ ሙትና ቁስለኛ በማስቆጠር ከፍተኛ ድል ተጎናፅፍዋል።
ስራዊታችን በጦር ሜዳ ውሎው ከጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት በተቀዳ ወኔ እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የወያኔን መከላከያ ስራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ሀይል በጦር ሜዳው ላይ በጥይት ቆልቶና አሳሮ አስቀርቶታል!!
ፍልሚያው በማግስቱ ረዕቡ ህዳር 29/2008 ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ስአታት በዚያው አዲ-አርቃይ ላይ የቀጠለ ሲሆን ወያኔ ከሌላ አግዞ ለጦርነት ያሰለፋቸውን ተጨማሪ የመከላከያ ስራዊት ጀግናው የአርበኞች ግንቦት7 የነፃነት ታጋይ የጠላትን ጦር ድባቅ በመምታት በመጣበት ሳይመለስ እንደ ወጣ አስቀርቶታል።
ለነፃነት የሚደረግ ጦርነት አሁንም ቀጥልዋል።
የወያኔ ባለስልጣናት የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው በተለይ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚገኘው ድንበር የበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ስራዊት ለመዝጋት ቢሩዋሩዋጥም ድንበር ላይ የተመደበው ወታደር ከወያኔ እየከዳ የነፃነት ትግል ከነትጥቁ በመቀላቀል ስልጣኑን ለሚዘውሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት የራስ ምታት ሆኖባቸው ይገኛል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ስራዊት በተቀዳጀው ድል የአካባቢው ህዝብ ጮቤ እየረገጠ እንደሚገኝ ለማውቅ ተችልዋል። ጀግናው የአርበኞች ግንቦት7 ስራዊት ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ በህዝብ ድጋፍ ታጅቦ ወደ መሀል አገር እየገሰገሰ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen