Netsanet: ​የበረከት ስምኦን “የምስክርት ቃል” ከዶ/ር ታደሰ ብሩ | የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር

Dienstag, 6. Dezember 2016

​የበረከት ስምኦን “የምስክርት ቃል” ከዶ/ር ታደሰ ብሩ | የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር

​የበረከት ስምኦን “የምስክርት ቃል”

ከዶ/ር ታደሰ ብሩ | የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር

ባለፈው ሮብ በረከት ስምዖን ከፍተኛ የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎችን አፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ሰብስቦ በአገራችን የሰፈነውን አምባገነን አገዛዝን ውስጥ ውስጡን አየተቃወሙ ያሉትን የኢሕአዴግ አባላትን ሲወርፍ …..

“እኛን ያሰቃየን ከሕዝቡ ይልቅ በውስጣችን ያለው የውስጥ አርበኛ ነው”
ዓይነት ዓረፍተ ነገር ተናገረ። እኔ ይህችን ዓረፍተነገር ብቻ ወሰድኩ እንጂ በረከት ለሰዓታት በምሬት እንደተናገረ ስብሰባው ውስጥ የነበራችሁ የምታውቁት ነው።
ከላይ ቀንጭቤ ከወሰድኳት አንዲት ዓረፍተ ነገር ሁለት አቢይ ጉዳዮችን ማንሳት አፈልጋለሁ።
1 ህወሓት/ኢሕአዴን ከሕዝብ በተፃራሪ መቆሙ፤ ሕዝብም ኢሕአዴግን “እያሰቃየ” መሆኑ በረከት ለከፍተኛ ካድሬዎቹ በሰጠው ቃል አምኗል። የማንኛውም ጦርነት የመጀመሪያ ግብ ጠላትን በስነልቦና ማሸነፍ ነው። ይህ ዓረፍተ ነገር የበረከት (ሲለጠጥ የኢሕአዴግ) ሽንፈት ጠቋሚ ነው።
2 የውስጥ አርበኘነት፣ አርበኝነት መሆኑ የበረከት ቃል ምስክር ነው። “እንዴት እናግዝ” እያላችሁ የምትጠይቁኝ የኢሕአዴግ አባላት፣ አባል የሆናችሁባቸውን የህወሓት ሎሌ ድርጅቶችን ከውሰጥ ሆናችሁ ማዳከም፤ ከውስጥ ሆናችሁ ድርጅቶቹን መግደል እጅግ ዋጋ ያለው ክቡር ሥራ መሆኑን ተደግሞ የሚነገረዉ አውነት መሆኑ አንድ ማረጋገጫ ይህ የበረከት “የምስክርነት ቃል” ነው።

በዚህ አጋጣሚ ኦህዴድ ላይ አየደረሰ ያለው ፍልሰት ብአዴንም ላይ መድረሱ አይቀርም። ብአዴን ውስጥ ያላችሁ ህሊናችው ተሟጦ ያላለቀ ወገኖች ያላችሁ ምርጫ ከሁለት እንድ ነው።
ሀ) ብአዴን ለቆ ወጥቶ የነፃነት ትግሉን መቀላቀል፣ ወይም
ለ) የተሻለ ስልጣንን ይዞ ብአዴንን ከውስጥ አዳክሞ መግደል
አለበዚያ ነገ ራሳችሁን የምታገኙት ወይ እስር ቤት አልያም ኬኒያ ነው፤ እንደ ኦህዴድ ጓዶቻችሁ ግብፅ የመድረስ አድል ያላችሁ አይመስለኝም።

http://wp.me/p5L3EG-ei

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen