ሕዝባዊ አሻጥር በየፈርጁ፤ ኦህዴድ እየታመሰ ነው
“በጥልቅ በመታደስ” አመራሩን ከህወሓት በላይ ህወሓት እያደረገ ያለው ኦህዴድ በግምገማና ዳግም ግምገማ እየታመሰ ነው። የአሁኑ ከቀድሞው ለየት የሚያደርገው “አርበኞች ግንቦት 7 ኦህዴድ ውስጥ ገብቶብናል፤ ሴሎቹንም ዘርግቶብናል” የሚለው ስሞታ አይሉት መርዶ መብዛቱ ነው። በዚህም ሰበብ በርካታ የዞንና የወረዳ አመራሮች እየለቀቁ ነው፤ ጥቂት የማይባሉ ከአገር ለቀው ወጥተዋል፤ የታሰሩም አሉ።
ባለፈው ሳምንት በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን አፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ሰስብስቦ “እኛን እያሰቃየን ያለው ከሕዝቡ ይልቅ በውስጣችን ያለው የውስጥ አርበኛ ነው” ማለቱ ይታወሳል።
በረከትም ሆነ አዳዲሶቹ የኦህዴድ ሹማምንት ይህንኑ የሚናገሩት “የውስጥ አርበኞች” ለሚሏቸው ካድሬዎቻቸው መሆኑ የተረዱት አይመስልም። የበረከትን መልዕክት ለካድሬዎቹ የሚያደርሱ ገምጋሚዎች ውስጥም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ መጠርጠር እንኳን የቻሉ አይመስልም። ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ በሙሉ የህወሓትን መሰሪ ሥራዎችን በሚችለው ሁሉ እየተዋጋ መሆኑን እያወቁም አያውቁም፤ እያዩም አያዩም።
በኦህዴድ ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ኦህዴድ እንደ ድርጅት እየፈራረሰ መሆኑን የምታውቁት ነው። በግምገማዎችና ዳግም ግምገማዎች ተማራችሁ ጠቅልላችሁ ብትወጡላቸው አዲሶቹ አመራሮች ደስታቸውን አይችሉትም፤ ድርጅቱን በለየላቸው አድርባዮች ይሞሉታል።
የተሻለው አማራጭ ኦህዴድን ከውስጥ መግደል ነው፤ ይህን ለማድረግ አሁን አመች ጊዜ ነውና ተጠቀሙበት።
http://wp.me/p5L3EG-ep
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen