Netsanet: ​ጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Donnerstag, 1. Dezember 2016

​ጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

​ጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ወያኔ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ታሪኩንና አቅዋሙን ይዞ በትግሬነት ተሸፋፍኖ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቆም አይችልም፤ የትግራይ ሕዝብም ከወያኔ ጋር ቆሞና የወያኔ ምሽግ ሆኖ ወያኔ በዙሪያው ያጠረለትን የጠላትነት አጥር አልፎ ኑሮውን ለማሻሻል አይችልም፤ እንዲያውም የጦርነት ሜዳ ይሆናል፤ የወያኔ መሪዎች ዛሬም የሚያስቡት ወያኔን በሥልጣን ላይ ለማቆየት የትግራይ ሕዝብ ገና ወደፊት የሚከፍለውን መስዋእትነት ነው፤ ሥዩም መስፍን የሚከተለውን ይላል፡


ከ60 ሺ በላይ ሕይወት ከፍለን ፣ ከዚህ በላይ ሕዝብ ተጎድቶብን ነው ስልጣን ላይ የወጣነው፡፡ ዛሬትግራይ ላይ የሚነጣጠረው ነገር ለማንም አይተርፍም ሁላችን በዜሮ ነው የምንወጣው፡፡ ማንምአያተርፍም፡፡ ኢህአድግ መተኪያ የለውም፡፡

‹‹ሁላችንም በዜሮ እንወጣለን፤›› ፉከራ አይደለም፤ የእኩይ መንፈስ የመጠፋፋት ቃል ኪዳን ነው፤ የኢትዮጵያን መሬትና የተፈጥሮ ሀብቱን ለሌሎች ማስረከብ ማለት ነው፤ ይህንን ጤናማ አእምሮ ያስበዋል ለማለት አይቻልም፤ የወያኔ መሪዎች ዛሬም የሚያስቡት የትግራይ ሕዝብን መሣሪያቸው አድርገው ነው፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻ ሆኖ የራሱን ውሳኔ መወሰን እንደሚችል አያስቡም፤ የትግራይ ሕዝብ መሪዎቹ በአሜሪካና በአውሮፓ ያካበቱትን ሀብትና ያጠራቀሙትን ገንዘብ የማያውቅ ይመስላቸዋል፤ በመቀሌ ለተሠሩት የባለሥልጣኖች መኖሪያ ሰፈሮች የትግራይ ሕዝብ የሰጣቸውን ስሞች — የሙስና ሰፈር፣ የአፓርቴይድ ሰፈር — አልሰሙም ይሆናል፤ ወይም ቢሰሙም አልገባቸውም ይሆናል፤ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ለወያኔ መሪዎች ግዑዝ መሣሪያ ሆኖ የሚቀጥል አድርገው ይገምቱታል፡፡

ሥዩም መስፍን በሥልጣን ኮርቻው ላይ እንዲቀመጥ የተከፈለው ዋጋ ስድሳ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ሕይወት መሆኑንና ከዚያም የበለጠ የትግራይ ሕዝብ ተጎድቶ እንደሆነ ይነግረናል፤ በዚህ አያበቃም፤ በሚቀጥለው ዙር ትግል ‹‹ሁላችንም በዜሮ ነው የምንወጣው›› ሲል ለትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ የደገሰለትን የጥፋት ማዕበል እየነገረን ነው፤ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ በ1997 ምርጫ ላይም የሩዋንዳውን ‹‹ኢንተርሀምዌይ›› አንሥቶ ነበር፤ ብዙም ሳይቆይ አግዓዚ የሚባለውን የወያኔ ‹‹ኢንተርሀምዌይ››ን አሳየን፤ ዛሬም ለትግራይ ሕዝብ የተደገሰው የጥፋት ማዕበል የወያኔን መሪዎች በሩቁም እንደማይነካቸው ያውቃሉ፤ የትግራይን ሕዝብ በጥፋት ማዕበል ‹‹በዜሮ አስወጥቶ›› እሱ አሜሪካ ወይም አውሮፓ አንዱ ዘንድ ገብቶ የሙጢኝ ይላል፤ ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከዚህ ከተደገሰለት የጥፋት ማዕበል ለማውጣት ወያኔን እምቢ ብሎ ኢትዮጵያዊነቱን ማጠንከሩ ይጠቅመዋል፡፡ ” ይቀጥላል

http://wp.me/p5L3EG-ef

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen