Netsanet: በሳዑዲ አረቢያ የጀርምን ድምጽ ወኪል ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን ለማሰር የተቃጣው ሙከራ ከሸፈ

Montag, 1. September 2014

በሳዑዲ አረቢያ የጀርምን ድምጽ ወኪል ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን ለማሰር የተቃጣው ሙከራ ከሸፈ

ለዘ-ሐበሻ የዘገበው ኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ
(ጸሐፊው ነብዩ ሲራክ)
(ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ)
በሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በመላው አረብ አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል በማለዳ ወጉ መረጃዎችን በማቀበል የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በማያውቀው ጉዳይ ተከሶ ዛሬ ፍ/ቤት መቀረቡን ውስጥ አውቂ ምንጮች ገለጹ ። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ኦገስት በ27/8/2014 ማለዳ 4:00 በደረሰው የከስ ጥሪ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ለመቀበል ህግ እና ስረአት አክብሮ ወደ ፍ/ቤት መሄዱን የሚናገሩ ምንጮች በአካባቢው የሚገኙ የሳውዲ ህግ አሰከባሪዎች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ተመስረተበት ስለተባለው ወንጀል ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው አውስተው ጥሪውን ወዳስተላለፈለት ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ሪፖርት እንዲያደርግ መላኩን ይገልጻሉ ።
jida ethiopian
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እረፍ ሲነሳው የከረመውን የሃስተ ክስ ለማጣራት መደበኛ ስራውን አቋርጦ ዛሬ እሁድ ለ31/8/2014 ማለዳ ደግሞ ፍ/ቤት ቢቀርበም ተመሳሳይ መልስ ስለተሰጠው ጥሪውን ወዳ ስተላለፈለት በተለምዶ ሽማልያ ስለላ የሚባል ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ሪፖርት ቢያደርግም ተረኛ የሳውዲ ፖሊስ መኮንኖች ስለጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው ጋዜጠኛውን በነጻ እንዳሰናበቱት ለመረዳት ተችሏል ። ጋዜጠኛ ነበዩ ሲራክ በማለዳ ወጎቹ ያቀርባቸው በነበሩ አሳዛኝ እና አሰቃቂ የእቶቻችን የአረበ አለም ህይወት ገጽታ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አድናቆት እና ክብርን ያተረፈ ታላቅ ጋዜጠኛ መሆኑ ቢታወቅም በዚህ ስራው ባልተደሰቱ ምስለኔዎች ቀደም ብሎ በቀረበበት የሃሰት ከስ ለእስር ተዳርጎ እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ጋዜጠኛውን በእጅ አዙር ለማዋከብ የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ይህ ጋዜጠኛ በወቅቱ በተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ ህዝብ ተዕጸኖ ነጻ ቢወጣም በአረብ አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምን አይነት ዘገባ እንዳያቀርብ በተላለፈበት ከባድ ማስጠንቀቂያ ከጀርመን ድምጽ ዘጋቢነቱ በመራቅ እስካሁንም የህሊና እረኛ መሆኑን ይናገራሉ ።
በአሁኑ ግዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለሚፈጸመው ግፍ እና በደል መናገር ወንጀል ሆኗል የሚሉት ምንጮች ። በተለይ በኮንትራት ሰራተኛ እህቶቻችን ሬሳ ዶላር የሰበሰቡ አንዳንድ የአሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶች ሃላፊነት የማይሰማቸውን ደካማ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሻቸው እያሸከረከሩ በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው ግፍ እና በደል በአደባባይ በሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ተጸዕኖ ማሳደር መቻላቸውን ይገልጻሉ። እንዚህ ምንጮች አያይዘው ሲገልጹ ምን እንኳን በኮነትራት ሰራተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ግፍ እና በደል ሃገር አቀፍ ተቃውሞ በማስነሳቱ መንግስት ከግል ጥቅማቸው ባሻገር የወገኖቻቸው ህይወትን ማየት በተሳናቸው የአሰሪ እና ሰራተኛ አገኝ ኤጀንሲዎች ላይ በወስደው አንጻራዊ እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከስቃይ መታደግ ቢቻልም እነዚህን ወንጀለኞቸ ለፈርድ ለማቅረብ ረገድ የውጨ ጉዳይ ሚንስተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብተው የነበረውን ቃል ማጠፋቸው ግፉ የተፈጸመበትን ድፈን የኢትዮጵያን ህዝብ እጀግ በጣም አሳዝኗል ብለዋል ። እንደሚታወቀው በተጠቀሱት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አረብ ሃገራት በኳንተራት ቪዛ ገበተው ያሉበት ሁኔታ እሳክሁን በወል ከማይታወቀው በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ባሻገር በሰው እጅ ተገለውም ሆነ በተለያየ ምክንያት ህይወታቸው ጠፍቶ የኤንባሲ አሊያም የቆንስላ ባለስልጣናት ለወላጆቻቸው ሳያሳውቁ መርዶ ነጋሪ በሌለበት አረብ በረሃ ስረአተ ቀብራቸው የተፈፀመ እህቶቻችን ማንነት በሚስጠር መያዙ ይነገራል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen