ማጥቃቱም በወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ በኦጋዴን ለተፈጸመው ጅምላ ግድያ ወታደራዊ ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።
ሕዝብን ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እያሰረ፣ እያንገላታ፣ እያሳደደና እየገደለ የሚገኘውን የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረደ በአርበኝነት ትግል እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ ጊዜያት በወያኔ ላይ በሚያካሂዳቸው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻዎች ለተጨቆነው ሕዝብ ብሶት አፀፋዊ ምላሽ በመስጠት ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።
ሰሞኑን ወያኔ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄዱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአፀፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሰረት መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ/ም በቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ ደለጎ በተባለው አካባቢ በወያኔ ፀረ-ሽምቅ ኃይሎችና በፌደራል ፖሊሶች ላይ ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ወስዷል። በዚህም የማጥቃት እርምጃ አስራ ሶስት (13) የወያኔ ታጣቂ ኃይሎች ሙት፣ ዘጠኙ (9) ደግሞ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን የእጅ ቦምቦች፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ከነመስል ጥይቶቻቸውና ትጥቆቻቸው ጋር ተማርኳል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በወገኖቻችን ላይ ወያኔ ለሚፈጸመው ጅምላ ግድያ፣ እስራትና መፈናቀል የሚሰጠውን ወታደራዊ የአፀፋ ምላሾች አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ተልዕኮ መሳካትና አምባገነናዊውን የወያኔ አገዛዝ ለመጣል ለሚደረገው ትግል ድጋፍ በመስጠት የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያደርግ ግንባሩ ጥሪውን ያስተላልፋል።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen