Netsanet: አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ።

Dienstag, 13. Juni 2017

አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ።

አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ።

 የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ። ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓ.ም አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ከቀድሞ ናዝሬት አውቶቡስ ተራ አጠገብ የሚገኘውን የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ። ቦታው ቀደም ባሉ ዓመታት የጉምሩክ መጋዘን ሆኖ ያገለግል ነበር። በቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ቦታው የሚያገለግለው በፌደራል ፓሊስ የመሣሪያ ግምጃ ቤትነትና በስውር ማሰቃያነት ነው። በርካታ ወገኖቻችን ዓይኖቻቸው እየታሰሩ ወደዚህ ቦታ እየተወሰዱ ስቃይ (ቶርቸር) እንዲደርስባቸው በመደረጉ ለዘላቂ የአካልና የስነልቦና ጉዳት ተዳርገዋል። በዚህ ግቢ ውስጥ በደረሰባቸው ስቃይ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችም አሉ። በዚህ ግቢ ውስጥ በርካታ ወንድና ሴት እስረኞች እጅግ አሰቃቂና ኢሰብዓዊ በደል ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ ግቢ ውስጥ በደሰረባቸው ስቃይ ምክንያት ዘር ማፍራት እንዳይችሉ የተደረጉ ወገኖቻችን በርካቶች ናቸው። በዚህ ፀረ ትውልድ እና ፀረ ኢትዮጵያ ተቋም ላይ ነው የአርበኞች ግንቦት 7 ህዋስ እርምጃ የወሰደው። በተወሰደው ጥንቃቄ የተሞላበትና የተጠና እርምጃ ሳቢያ በግቢው ውስጥ የነበሩ መጋዘኞች ከነመሣርያዎቻቸው በእሳት እንዲጋዩ ተደርጓል፤ በተወሰደው እርምጃ ሳቢያ የተቀሰው እሳት በሁለት ሰዓታት ያህል ማጥፋት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ የተወሰደውን እርምጃ በዓይኖቹ እንዲያይና በህወሓት አምባገነን አገዛዝ የሚደርስበት ስቃይ ቁጭት እንዲወጣ እድል ፈጥሯል። በተወሰደው እርምጃም አገር ወዳድ የፌደራል ፓሊስ አባላት የህቡዕ እርዳታ አድርገዋል። ለወደፊቱም ተመሳሳይ እርጃዎች ሊወሰዱ እንደሚችሉ የአርበኞች ግንቦት 7 የአገር ውስጥ ህቡዕ አመራር ገልጿል። በተጨማሪም እያንዳንዱ አገሩንና ነፃነቱን የሚወድ ዜጋ በየተሰማረበት መስክ ሥርዓቱን የሚያዳክሙ የሕዝባዊ እምቢተኝነትና የሕዝባዊ አሻጥር እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል።

https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/06/13/%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%a0%e1%8a%9e%e1%89%bd-%e1%8c%8d%e1%8a%95%e1%89%a6%e1%89%b5-7-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%88%85/

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen