ወቅታዊው የሀገራችን ፖለቲካና የአርበኛ ታጋዩ ትዝብት – ከኤርትራ ( ክፍል አንድ)
እኔ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ የሞቀና የተመቻቸ የምዕራብ አለም ህይወትን ትተው ለሀገርና ህዝብ ሲሉ ወደ ኤርትራ በረሃ ከወረዱ ጥቂት ኢትዮጲያዊያን መካከል አንዱ ነኝ። በነበርኩበት ካናዳ አንድ ሀገር ወዳድ ዳያስፖራ ሊያደርገው የሚችለውንንና የሚገባውን አድርጌኣለሁ ባልልም ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም ነውና የምችለውን ያህል ወርውሬአለሁ።። ሆኖም ግን በኢትዮጲያ ያለው ስርአትና መንግስት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰው በደል ያሳደረብኝ ምሬትና ብሶት ከፌስቡክ ጦርነትና ገንዘብ ማሰባሰብ በላይ ጠልቆ ሄዶ ህይወትንም አሳልፌ መስጠት እንዳለብኝ ስለተዳረሁ ነበር ወደበረሃው ያቀናሁት።(ብዙ የዳያስፖራ ወንድሞቼና እህቶቼ ስጋቸው ምዕራብ ሃገር ቢሆንም ልባቸው ኤርትራ በረሃ ውስጥ እንደሆነ እረዳለሁ)።
በኤርትራ ቆይታዬ ብዙ ልምድ አግኝቼበታለሁ። የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ማን ከየትኛው ብሄር ወይንም ሃይማኖት ነው የመጣው ሳይባባል ሁሉንም በእኩል የሚያስተናግድና ሁሉም ደግሞ ለአንዲት ኢትዮጲያ ለመሞት የተዘጋጀ ሰራዊት ኣንደሆነም አየሁ። እንደማንም የፖለቲካ ድርጅት አርበኞች ግንቦት7ም የራሱ የሆኑ ችግሮች ነበሩበት። አሁንም አሉት። ግን ይህንን ድርጅት ምናልባትም ከሌሎች ብዙ ድርጅቶች የሚለየው ልዩነቶቹንና ቅራኔዎቹን የሚፈታበት የሰለጠነ አካሄድ መሆኑ ይመስለኛል። እንደልማድ የተወሰዱና ስር የሰደዱ ባህላዊ የልዩነት መፍቻ ዘዴዎቻችን በኣብዛኛው መጨረሻቸው አያምርም። ትተውት የሚያልፉት ጠበሳም በቀላሉ የሚሽር አይደለም። ወያኔን ለድርድር ከማስገደድ ወይንም ከስልጣን ለማሰወገድ ከሚደረገው የመሳሪያ ትግል በስተቀረ የሃሳብ ልዩነቶቻችንና ቅራኔዎቻችችንን በሌላ የተሻለ ሃሳብ መፍታት እንጂ መከፋፈል ወይንም ከዚያ ሲያልፍ ጠመንጃ መማዘዝ ያለፈበትና ጊዜዉን የማይመጥን አስተሳሰብ ነው ብሎ ያምናል የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር። የክርክሩና የውይይቱ ሂደት እጅግ አስቸጋሪ፣ አቀበት የበዛበትና እልህ አስጨራሽ ቢሆንም ድርጅቱ ከአቋራጭ መንገድ ይልቅ ረዥሙን ግን ዕውነተኛውን መንገድ መምረጡን አይቻለሁ። የሚያዋጣውም ይህ ነውና።
ሕወሃት በሃሳብ ስለተለዩት ብቻ ደደቢት በረሃ ውስጥ አጋድሞ ያረዳቸው የትግል ጓዶቹ ደም አሁን ድረስ እንደ አቤል ደም ይጣራል። እንዲህ ያለ የቆሸሸ ታሪክ ይዘን፣ ቂም በቀል አርግዘንና አስረግዘን ወደፊት እንጓዛለን ብለን አናስብም። አዲስ አበባ የምንገባው ሁሉንም ልዩነቶቻችን እዚሁ በረሃ ውስጥ በውይይት ፈትተን፣ ቁሻሻችንን አጥበን፣ ንጹህ ሆነን መሆን አለበት። ከፍተኛ ጊዜና ጉልበት ቢጠይቀንም።ይህ ነው የአርበኞች ግንቦት 7 መርህ።
በተለያየ ስልጠና ውስጥ አልፈው ለግዳጅ የተላኩና በጠላት ጥይት የወደቁ ወይንም የተያዙ አርበኞችን ድርጅቱም ሆነ አባላቱ በቅድሚያ የሚያውቋቸው በኢትዮጲያነታቸው እንጂ በብሄራቸው እንዳይደለም እናገራለሁ። የአርማጮሆና የአርባ ምንጭ፣ የኦሮሞና የሺናሻ አርበኛ አጥንቱና ደሙ በሰሜን ምድር ላይ አኩል ፈስሷል፣ እኩል ተከስክሷል።በወያኔ እስር ቤቶችም እኩል ይገረፋል፣ ይተለተላል። ይሰደባል፣ ይዋረዳል።( ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ጊዜ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው የድርጅታችን አባላት ለወያኔ እጃቸውን ሰጡ የሚል የወያኔ ፕሮፓጋንዳ የሚናፈስበት ወቅት ነበር። እውነቱ ግን እነኚህ ጓዶች በነጻነት ትግሉን የተቀላቀሉና መጨረሻ ላይ በተለያዩ ግላዊ ምክንያቶች ከትግሉ መልቀቅ በመምረጣቸው በነጻነት የተሸኙ ናቸው። ማንም አርበኛ ያለራሱ የግል ዕምነትና ነጻነት በግድ የሚታገልበት ምክንያት እንደሌለ መታወቅ ይኖርበታል። ዕውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ጓዶቹ ምናልባትም በጭካኔአቸውና በዘረኝነታቸው የታወቁ የማዕከላዊ እስር ቤት ገራፊዎች እጅ ላለመውደቅ ሲሉ ብዙ ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ ምቹ የሆኑ ግን ከዕውነት የራቁ ነገሮችን ሲናገሩ ተደምጠዋል። የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስቴር የአቶ መለሰ ዜናዊን አነጋገር ልዋስና “አርበኞች ግንቦት 7 የሰዎች እንጂ የመላአክት ስብስብ አይደለም”። በመሆኑም ወርቅ በእሳት ሰውም በትግል እንዲፈተን እኛም እዚህ ያለነው አርበኞች ምንም አይነት ችግር በድርጅታችን ውስጥ ቢፈጠርም እንኳን በቁርጠኝነት ለመፍታት እዚሁ በረሃ ውስጥ ሆነን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ በጽናት እንታገላለን እንጂ ቀድሞውኑም ለዚህ ሁሉ ሰቆቃና መከራ ለዳረገን ሕወሃት/ወያኔ እጃችንን ሰጥተን የድርጅታችንን ገመና አደባባይ አናወጣም። እሳቱ እያየለና እየጠነከረ ሲመጣ አፈሩና ቆርቆሮው፣ መዳብና ነሃሱ መቅለጡና መለየቱ አይቀርም። ወርቅ የሆኑ አርበኞችና ወርቅ የሆነ ድርጅትም ከዚህ የትግል እሳት ውስጥ ተፈትኖ እንደሚወጣ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለኝም)። የሆኖ ሆኖ ይህ ሰራዊት የብሄር ማንነቱን አያስቀድምም፣ የዚህ ወይንም የዚያ ነኝ ብሎም አይኮፈስም። የበላይነትም የበታችነትም ስሜት የለበትም።ኢትዮጲያዊ አርበኛ ነው።በቃ!
የዋሽንግተን የቡና ቤት ባልቴቶች በየፌስ ቡኩ እንደሚያራርቁት የእኔ ወገን ብቻ ለምን ተጎዳብኝ ብሎም ኣያጉረመርምም።ያለው የፖለቲካ ንቃትና ተሳትፎ በውጪው አለም ያለው ዳያስፖራ ከሚያስበውና ከሚገምተው በላይ ነው። በግጥሞቻቸው፡ በስነጽሁፎቻቸውም ሆነ በፖለቲካ ውይይቶቻቸው ላይ የሚያንዘባርቁትም ይሄንኑ የአንድነትና የእኩልነት መንፈስን ነው። የድርጅታችን መሪን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም ወደነበርንበት የማሰልጠኛ ጣቢያ መጥተው ከሰራዊቱ ጋር ውይይት ሲያደርጉ እነኚህ ወጣት አርበኞች የሚያቀርቡት ጥያቄና የሚነሰዝሯቸው ሃሳቦች ፍጹም ጥልቅና ፍጹም አገራዊ ናቸው።
አብዛኛዎቹ ዕድሜቸው ከሃያ አምስት አስከ ሰላሳ ባለው ክልል ውስጥ ነው። የመጡበት የኋላ ታሪካቸው እንደየግለሰቡ ይለያያል። የትምህርት ደረጃቸውም እንዲሁ። ማንበብና መጻፍ ከማይችሉት አንስቶ እስከ ማስትሬት ዲግሪ ድረስ የያዙ፣ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት ይሰሩ የነበሩ፣ በህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ውስጥ የራሳቸውን ሚና ተጫውተው መንግስት ሲያሳድዳቸው ተከዜን ተሻግረው የመጡና ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ዳግም ወያኔን ሊጋፈጡ የተዘጋጁ ወጣቶች ናቸው። የወያኔ የ26 አመት የዘርና የብሄር ቁማር ጨዋታ እንዳልሰራለትና ይልቁንም የራሱን መቃብር የቆፈረ የሚያስመስለው የእነኚህን ወጣቶች ፍጹም ጠንካራ የሆነ የኢትዮጲያዊነት ስሜት እንደኔ በአካል ላየ ብቻ ነው። የቄሮ ወጣቶች ቢሾፍቱ የኢሬቻ በአል ላይ የገጠሙት ግጥም የኛንም አርበኞች ስሜት ያንጸባርቃል።
ባንተው ዘመን ተወልደን
ባንተው ዘመን አድገን
ምንም ለውጥ ሳናይ
ባንተው ተገደልን።
እውነታው ይህ ሆነ ሳለ፣ የስልጠና ጊዜዬን ጨርሼ በሌላ ሃላፊነት ለመገናኛ ብዙሃን ቅርብ ወደሆነ አካባቢ ስመጣ በየድረ ገጹና በየፌስ ቡኩ ላይ የማነበውና የምሰማው ሁሉ ከዕውነት የራቀ፣ እጅግ ግራ የሚያጋባና አንዳንዱም ጭራሽ ቀልድና ቧልት የሞላበት ከንቱ ጩኸት ሆኖ ነበር ያገኘሁት።የጋራ ጠላት የሆነውን የሕወሃት/ወያኔ እኩይ ስርአት በጋራ ከመቃወም ይልቅ አንዱ አንዱን የማጥላላት፣ የመንቀፍና ብሎም የማደናቀፍ ጦርነቱ ከፍተኛ ደረጃ እንደደረሰም ታዘብኩ።ከወያኔ ባልተናነሰ ምናልባትም በከፋ መልኩ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ የሚሰነዘረውን ትችትና ስድብ ስመለከት ፍጹም ወለፈንዲ ሆነብኝ። ከሁሉም የባሰው ደግሞ የፈጠራ ወሬውና ቅጥፈቱ ነበር።
አብሬአቸው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በረሃ ውስጥ አብረን ያሳለፍን አርበኞችን በስውር ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ደብዛቸው ጠፍቷልና የመሳሰሉት ቅጥ ያጡ አሉባልታዎች እያናፈሱ የተወሰነዉን የዳያስፖራ ክፍል እያወናበዱት እንዳለ ታዘብኩ። በተለይም ደግሞ የዚህ አይነቱ መሰረተ ቢስ ወሬ በዘር ማንነት ላይ ብቻ ተመርኩዘው ለማሰብም ሆነ ጉዳዩን ለመርመር ጊዜውና ትዕግስቱ የሌላቸውን የብሄሩን አባላት በስሜት ፈረስ እያስጋለበ እንደሚነዳቸው አስተውያለሁ። ጎበዝ! ይህ ግልቢያ አደገኛ ነው። በፈጣሪ አምሳል ከተሰራ ክቡር የሰውነት ተራ አውርዶ ቁልቁል ወደ እንስሳነት፣ ፍጹም አውሬነት የመቀየር ልዩ ሃይል አለውና። ዮሴፍ ያሲን ‘ኣሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሀገር ልጅነት” በተሰኘው መጽሃፉ ረቻርድ ካፑቺኒስኪን ጠቅሶ ሲጽፍ “የሰው ልጅ ከእንስሳት እምብዛም ባልተለየ አደረጃጀት በመንጋ በመንጋ ተቧድኖ በሚንቀሳቀስበት ዘመን ድንገት ፊት ለፊት ሲገጣጠሙ በመጋጨት፡ አጥር በማጠር ወይንም በመነጋገር አንዱ ለሌላኛው መንጋ የተግባር መልስ ሲሰጥ ይስተዋላል” ይላል(ገጽ፡ 50)። የሚያስፈራኝም ይህ አካሄድ ነው። እንደ እንስሳ በመንጋ መቧደን፣ የብሄር አጥር አጥሮ በደመ ነፍስ እንደዞምቢ የኋሊዮሽ መንገታገቱን!
የእንግሊዙ ታዋቂ ጸሃፌ ተውኔት ዊሊያም ሺክስፒየር ” ሕይወት ለአሰላሳዮች ቀልድ ስትሆን በስሜት ለሚኖሯት ደግሞ ሃዘን ናት”ይላል። ( For those who think, life is a comedy. But for those who feel, it is a tragedy.) ያሁኑን ያገራችንን በተለይም በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ህይወታቸውን ዝም ብዬ ሳስተውል በቀልድ ይሁን በሃዘን ስሜት ማየት እንዳለብኝ አንዳንዴ ግራ ይገባኛል። እገሌ ብዬ ስም አልጠራም። የሚያውቅ ያውቃቸዋል።
እነኚህ ሰነፍ ፖለቲከኞች ከሃላፊነትና ከተጠያቂነት ዕዳ ነጻ ነን ብለው በሚያስቡ የዋሆች ልብና ጭንቅላት ውስጥ የሚያጭሩትን እሳት ለመተንበይ ብዙም ወደኋላ ሄደን የታሪክን ድርሳናትን ማገላበጥ አያስፈልገንም። የትላንቶቹ ሩዋንዳና ዩጎዝላቪያ፣ የቅርቦቹ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን በቂ ትምህርትን ይሰጡናል። እሳት ጫሪዎቹ ግን ስታር ባክስ ቡና ቤት ቁጭ ብለው የአኬልዳማውን ትርኢት በተረጋጋ ስሜት ይመለከቱታል፣ ይገመግሙታል፣ ድክመትና ጥንካሬአቸውን አጥንተው ለቀጣዩ የደም ጨዋታ እቅድ ይነድፋሉ። ግን ለምን? በህወሃት ስም ለትግሬ ሕዝብ ያላቸው የተደበቀ ንቀትና ጥላቻ ወይንስ የፖለቲካ ጡንቻው እየጎለበተና የባለድርሻነት ድምጹን ከፍ እያደረገ ስለመጣው የኦሮሞ ሕዝብ ያላቸው ፍርሃት ወይንስ ደግሞ ተነጠቅን ብለው በሚያስቡት ጥንታዊ የበላይነት ስሜትና የስልጣን እጦት ጸጸትወይንስ ደግሞ የድሮ ስርአትን ዳግመኛ ሊያመጡብህ ነው የሚለውን ፕሮፓጋንዳ ፍራቻ ወይንስ የነኚህ ሁሉ ድምር ውጤት? ዞሮ ዞሮ ከጸሃይ በታች አዲስ ነገር የለምና ውስጣዊ መግፌአቸው ቢፈተሽ ከነኚህ በገሃድ ከማይገለጡና ከማይነገሩ ግን የውስጥ አዕምሮ ጓዳ ውስጥ ተወሽቀው ከሚገፏፏቸው ስውር የስነልቦና ኋይሎች ውጪ ሊሆን አይችልም። በሌላ አነጋገር በደመ ነፍስ ይወራጫሉ። ያሻቸውን ቢፅፉና ሊያስረዱን ቢሞክሩም፣ የበደኖንና የአርባጉጉን አሰቂቂ ጭፍጨፋ ደጋግመው እያነሱ ለፈረደበት አማራ ተቆርቋሪ ቢመስሉም ወይንም የአኖሌና የጨለንቆን የሙት መንፈስ እየቀሰቀሱና እያጋነኑ ሕዝብ ቢያነሳሱበትም ዕዉነቱ ግን በኢትዮጲያና በኢትዮጲያዊነት ላይ ተስፋ ቆርጠዋል።
“የኦሮሞ ደም ደማችን ነው!” “የአማራው ደም ደማችን ነው!” የሚለው ትልቅ መፈክርና መልዕክት ከጌታቸው ረዳ በላይ ያማቸዋል። በአርሲ ጎለልቻ ውስጥ ወያኔ ባቀነባበረው የዘርና የሃይማኖት ግጭት አማሮች ሲጨፈጨፉ ጣልቃ ገብተው ይህንን እብደት በከፊል ያስቆሙት የአካባቢው ኦሮሞዎች ነበሩ ብለህ ብትነግራቸውም አይሰሙም። ኦሮሞም ሆነ አማራ እንደሕዝብ እርስበርሱ ጥላቻ የለውም፣ ጋምቤላውም፣ ሱማሌውም፣ ትግሬውም፣ ሌላውም እንዲሁ ብለህ ልታስረዳቸው ብትሞክርም አስቀድመው ጭንቅላታቸውን ዘግተውታልና ዉሃ መውቀጥ ይሆናል። ከመናናቅና ከመፈራራት የጸዳች፣ ማሕበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ሁሉም ባለቤት፣ ሁሉም እኩል ዜጋ የሚሆንባትን አዲስ ኢትዮጲያን ማሰብ ያስፈራቸዋል። በሻማ ብርሃን ውስጥ ብቻ ላደጉ እንደ አፍላጦን የዋሻ ውስጥ ነዋሪዎች ፀሃይን ማየት አይችሉም። ያጥበረብራቸዋል።
ኢትዮጲያችን ትልቅ ናት። እኛ ግን ትንንሾች ሆነን አልመጥን አልናት ብዬ አስባለሁ። ሃዘኗም ብርቱ ነው።”ቁስሌን እይልኝ እንጂ አትይብኝ ይላል” ታጋዩ ነጋ በሀሁ ወይንስ ፐፑ ተውኔት ውስጥ። ወንድሜ ቁስል ኣለኝ እናም አሞኛል ሲለኝ ስለምን አንጓጥጠዋለሁ? ስለምን የጠዘጠዘውን ቁስል ከማከም፡ ህመሙን ከማድመጥ፡እምባውን ከማበስና መንፈሳዊ ሀዘኑን ከመጋራት ይልቅ ንፍገትና ቸልተኝነትን አሳየዋለሁ? ይህን ሳደርግ ይበልጥ ቁስሉን አመረቅዝበት እንደሆን ነው እንጂ መፍትሄ እንደማልሆነውም ተረዳሁ።የሆነውም ይሄ ነውና። እኔ ለኔ ብቻ በሚል የዘመን ልክፍት ተለክፈን ሁላችንም በእልህና በቂም መንፈስ ልባችንን አደድረን፡ ከትውልድ ወደ ትዉልድ የታሪክን እዳ ስንወርስና ስናወርስ ከነበሽታችን፡ ከነድንቁርናችን፣ከነድህነታችን የኣለም ጭራ ሆነን ቀረን ስል በቁጭት ስሜት እሰቃያለሁ። ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ይህንን የዘመን ልክፍት ጥሩ አይቶታል። በተለይም የተማረው ክፍል የሚጠበቅበትን ያክል ሃላፊነቱን አለመወጣቱን እንዳውም በተቃራኒው ለበሽታችን ዋና ተጠያቂ አድርጎ የሚያቀርበውና የሚከሰው ምሁሩን/ልሂቃኑን ስለመሆኑ ስራዎቹ ምስክር ናቸው።እናም አርበኛው ዳምባል በእናት አለም ጠኑ ተዉኔታዊ አንደበቱ እንዲህ ይላል
“እኛ ፈላስሞቹ፡ ከተሜዎቹ፡አዋጅ ነጋሪዎቹ፡ የዘመናዊ ስልጣኔ ሸቃጮቹ፡ ታደምን።እኛ ያውሮፓ አደባባይ ጓሮ ቁራዎቹ፡የየዩኒቨርሲቲዎቻቸው ምሩቃኖቹ፡ ምሁራኑ የጉድ አዋጆቻቸው ተክሎቹ፡ እኛ እኛ ታደምን።…..የዘመኑ ድልድይ መሆናችን ቀርቶ የዘመኑ አዘቅት፡ ናዳ፡ ግድግዳ ሆነን በብዙሃኑ እድል ተገደገድንበት።ጭለማው ቀናችን፡ ጭጋጉ ፀሃያችን፡ ምሽቱ ንጋታችን ሆነንና ታደምንበት………”
የብሄርና የሃይማኖት ጉዳይ አንዱ የዘመናችን ምሁራኖች የቆፈሩልን አዘቅት ሆኖ አንድ ትውልድን ሙሉ አሰቃየው። ግድግዳውም ብርቱ ሆነ። አንዱ ላንዱ መተዛዘን ተረስቶ ሁሉም የራሱን ቁስል መላስ ብቻ ሆኖ አረፈው።
በደኖና አርባጉጉ፣ ጉራፍርዳና ቤኒሻንጉልስ እንደእንስሳ ስለታረዱት፣ ከተራራ ስለተወረወሩት፡ ከቤት ንብረታቸው ስለተፈናቀሉት፣ ጫካ ተጥለው ለአውሬ ሲሳይ ስለሆኑትስ አማሮችስ ኦሮሞው፣ ትግሬው፣ ጉራጌው፣ ወላይታው፣ ሶማሌውና ሌላው ካላለቀሰላቸው ማን ያልቅስላቸው ስል አሰብኩ።ብሄራቸው፣ ቋንቋቸው፣ሐይማኖታቸው ምንና ምን እንደሁኑ ሳይታወቅ በሳኡዲ አረቢያ ክብራቸው ስለተዋረደው እህቶቼ፣፡በሊቢያ ስለታረዱት ወንድሞቼ፣በየመን ተረስተው ስለቀሩት፣፣ በደቡብ አፍሪካ ስለተቃጠሉት፣፣በሜዲትራኒያን ባህር የኣሳነባሪ እራት ሁነው ስለቀሩት፣ በሲናይ በረሃ ክቡር ገላቸው እንደዶሮ እየተቀረደደ ኩላሊታቸው ለተሰረቀው ኢትዮጲያዊያን ለማልቀስ የየትኛው ብሄር ኣባል፣ የየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ መሆን አለብኝ ስል አሰብኩ።
“ያንቺ ባል በህዝብ ተሸኝቶ በክብር የተቀበረ ነውና ብዙም ሃዘን አይግባሽ። የኔ ባል ግማሽ አካሉን ጅብ ቦጫጭቆ ዘንጥሎት እንኳንስ ልቀብረው ማንነቱን እንኳን መለየት አልቻልኩም” ስትል ለወይዘሮ አዜብ መስፍን መልዕክት የላከችው የአኙዋክ ሴትም እንዲሁ በአዕምሮዬ ተመላለሰችብኝ።
የባሪያ ፈንጋዮች ዘመን ዳግም ተመልሶ የመጣ ይመስል በሰንሰለት ታግተው እንደከብት መኪና ላይ ተጭነው ያየኋቸው የኮንሶ ወድሞቼንም አሰብኩ።በኦጋዴን በረሃ ሬሳቸው የተጎተተውን የኢትዮጲያ ሱማሌዎችንም እንዲሁ።
ኢትዮጲያዊያን ስለምን ጸጸትን ይወዳሉ ስልም ራሴን ጠየቅኩ።የነገውን ትዉልድ እጣ ፈንታ በበጎ መልኩ ከመንደፍና ተግባራዊ ለማድረግ ከመነሳት ይልቅ በኋላ ታሪክ ላይ ተጣብቀን የሙጥኝ የምንልበትም ምክንያት አልገባህ አለኝ።
በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረኩ ሰውና ከዛች አገር አፈር የበቀልኩ ኢትዮጲያዊ መሆን ብቻ አይበቃኝምን? ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ሠርገኛ ጤፍ ከተደባለቀ ማን ሊለየው ይችላል ሲሉ የተናገሩት በርግጥ ለአማራውና ለኦሮሞው ብቻ ወይንስ በስፋትና በጥልቀት ካየነው ረዥም ዘመን ባስቆጠረ የታሪክ ሂደት እጅግ ስር ስለሰደደውና ድርና ማግ ሆኖ ስለተደባለው የዛች ሀገር ህዝብ ማለታቸው ይሆን?

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen