ከፍተኛው ፍ/ቤት በ7ቱ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ !
--
[ ከፍተኛው የቅጣት ውሳኔ 4 ዓመት ከ 6 ወር እስርት ሲሆን፣ዝቅተኛው 4 ዓመት ከ 2 ወር ነው።በሌላ የክስ መዝገብ ይግባኝ የተጠየቀባቸው አቶ አብርሃ ደስታ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ጉዳያቸው በፍ/ቤት የታየ ሲሆን ፤አቶ አብርሃ ደስታ በድጋሚ ፍርድ ቤት ያልቀረበ ሲሆን ፣በእስር ላይ የሚገኘው ዳንኤል ሺበሺ የመከላከያ ምስክሮችን በዛሬው እለት አሰምቶአል]
---
በባለፈው ሣምንት በእነ መቶ ኣለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙት ከ13ቱ ተከሳሾች መካከል 6ቱን ተከሳሾችን በነፃ ያሰናበተው የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በ7ቱ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፍ የሚታወቅ ነው። በዛሬው እለት በ7ቱ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን። ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ያስተላለፈው የተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ ተመልክቶ እንደሆነ በመግለጽ ፣7ቱ ተከሳሾች መልካም ፀባይ እና የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸው ፣እንዲሁም የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን ለሁለም ተከሳሾች በማቅላያነት የተያዘላቸው ሲሆን፣በተጨማሪ ሦስት ተከሳሾች በላባቸው የጤና እክል ምክንያት አንድ አንድ ተጨማሪ የቅጣት ማቅለያ የተያዘላቸው ሲሆን። ፍርድ ቤት የቅጣት መነሻ ያደረገው ከመካከለኛ በመነሳት ሲሆን ለሁሉም ተከሳሾች መነሻ ያደረገው 6 ዓመት ከ7 ወር እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የገለጸ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ፦
--
1ኛ. አቶ በላይነህ ሲሳይ 4 ዓመት ከ 6 ወር
2ኛ. አቶ አለባቸው ማሞ 4 ዓመት ከ 2 ወር
3ኛ. አቶ ቢሆነኝ አለነ 4 ዓመት ከ6 ወር
4ኛ. አቶ ፈረጀ ሙሉ 4 ዓመት ከ 2 ወር
5ኛ.አቶ አትርሳው አስቻለው 4 ዓመት ከ 6 ወር
6ኛ. አቶ አንጋው ተገኘ 4 ዓመት ከ6 ወር
7ኛ. አቶ አባይ ዘውዱ 4 ዓመት ከ2 ወር ፣በማለት የከፊተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው እለት የቅጣት ውሳኔውን ሰጥቷል ።
--
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሰብሳቢ የነበረው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከ2 ዓመት በፊት በሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ለ2 ዓመት ያህል በእስር ቤት ከቆየ በኋል ከእስር መፈታቱ የሚታወቅ ነው።ሆኖም ግን ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው ይግባኝ መሠረት በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፣ከእሱ ጋር አንድ ላይ መቅረብ የነበረበት የዓረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ፍርድ ቤት ያልቀረበ ሲሆን፤ ያልቀረበበት ምክንያት ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ "ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ልናገኘው አልቻልንም"በማለት ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ።
--
ፍርድ ቤቱ በዳንኤል ሺበሺ ላይ የመከላከያ መስክር የሰማ ሲሆን፣ ለአቶ ዳንኤል ሺበሺ የመከላከያ ምስክር በመሆኑ የቀረቡት አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው። አቶ ዳንኤል ቀደም ብሎ ለሁለት ዓመት ያህል ታስሮ የነበረ ሲሆን፣ከእስር ከተፈታ በኋል በአስቸኳይ አዋጁ ምክንያት በድጋሚ በእስር ቤት ይገኛል።ፍርድ ቤቱ የዳንኤል ሺበሺ የመከላከያ ምስክሮችን የሰጡትን የምስክርነት ቃል ከሰማ በኋል፤ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከኢሳቲ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር አድርጎታል የተባለውን ቃለ መጠይቅ ንግግር በሲዲ ተገልቦጦ እንዲቀርብ ፣እንዲሁም አቶ አብርሃ ደስታ ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ በመስጠት ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 11ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
--
(ይድነቃቸው ከበደ)
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen