ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም አለው! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሕወሓት ሀገር ከፋፋይ ቀጣይ አጀንዳ አካል ነው
(የጉዳያችን ማስታወሻ)
ጉዳያችን / Gudayacnhn
ሰኔ 21/2009 ዓም (ጁን 28፣2017)
++++++++++++++++++++
ዛሬ ሰኔ 20፣2009 ዓም የሕወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራት ጥቅም በሚል ርዕስ ውሳኔ ማሳለፉ እና የሕወሓት ኢህአዴግ 99% አሸነፍኩ ወዳለበት ምክር ቤት እንደሚመራ ተነግሯል። ጉዳዩ ልዩ መብት የሰጠ የመሰለው ካለ እርሱ ከ26 አመታት በኃላም ገና ፖለቲካ ሀ ሁ እያለ እንደሆነ መረዳት ያለበት ይመስለኛል።
1/ ልዩ ጥቅም የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?
ልዩ ጥቅም የሚለው አባባል በእራሱ የመከፋፈል አላማ ያነገበ አባባል ነው።አንድ ሰው ልዩ ጥቅም ለማግኘት ዋናው መሰረት ሊሆን የሚገባው በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ የታሪክ የበላይነት ወይንም የዘር መሰረቱ ወይንም የተለየ አነጋገር በመናገሩን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ከሆነ መከፋፈል ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከኢትዮጵያ ምድር በመውጣቱ ነው።ከጃፓን ወይንም ብራዚል የመጣ ሰው የማይኖረው ልዩ ጥቅም ኢትዮጵያዊ ሊኖረው ይገባል።ይህ ማለት ኦሮሞው አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያዊነቱ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ አዲስ አበቤውም በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ኦሮሞው በመቀሌ ላይ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ የአክሱሙም ሰው በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የወለጋው ገበሬ በጎንደር ላይ ልዩ ጥቅም እንዳለው የራስ ዳሽን ገበሬም በነቀምት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ይህ ሁሉ ልዩ ጥቅም የሚመነጨው እንደ ህወሓት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በከፋፋይ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሙሉ መብት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ እና መሬት በሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የኦሮምያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የሚለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ በእራሱ ከፋፋይ የሆነው የስርዓቱ አጀንዳ ቀጣይ ምዕራፍ ነው።
2/ የውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ አገልግሎት አይደለም እንዴ?
“የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በአዲስ አበባ ዙርያ ላሉ የኦሮምያ ክልሎች ያካተተ ይሆናል” ይላል ከአዋጁ አካል ውስጥ አንዱ።አሁንም ውሃ የማግኘት ልዩ መብት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ነው።ይህ አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያዊነቱ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልሎች የውኃ አገልግሎት ላያገኙ ነበር? የውኃ ፍሳሽ አገልግሎት ለማግኘት የልዩ ጥቅም አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያውነታቸው የማግኘት መብት የላቸውም ነበር? ይህ በእራሱ ከፋፋይ አቀራረብ ነው።በአዲስ አበባ ዙርያ ያለ የኦሮሞ ሕዝብ ውሃ ለማግኘት ልዩ አዋጅ መጠበቅ ነው ያለበት ወይንስ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያገኘው መብት ነው መሆን ያለበት? ለአዲስ አበባ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ወጪ የሚሸፈነው ቀረጥ ከኦሮምያ የሚመጣ ገንዘብም ጭምር መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያረሳሳን ነው ? እናስ የአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ገና ለገና ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር አብሮ ይነሳብኛል ልከፋፍለው በሚል እሳቤ ውሃ በልዩ ጥቅም አዋጅ መሰረት ይዘረጋልሃል የሚል አዋጅ ረቂቅ አንድ ሐሙስ የቀረው እና የታመመ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካልሆነ ማን ያወጣዋል?
3/ የጤና አገልግሎትስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?
በአዋጁ ረቂቅ ላይ “አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ በከተማዋ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የክልሉ ተወላጆችን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል” ይላል። የጤና አገልግሎት የኢትዮጵያዊነት ልዩ ጥቅም ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍልል ቢኖር የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱ ነው።በእዚህ ረቂቅ ላይ አዲስ አበባ እና ኦሮምያ የተለያዩ ሀገሮች ይመስል በአዲስ አበባ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙርያ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ታሳቢ ያደርጋል ሲል ዛሬ ተነስቶ ልዩ ጥቅም የሰጠ አስመስሎ ሕዝብ የመከፋፈል አላማ ለማሳካት ብቻ የተገለፀ ነው።
4/ የአዲስ አበባ ሕዝብ እና የኦሮምያን ሕዝብ ከህወሓት በበለጠ ይተዋወቃል
በእዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአዲስ አበባ ስም በፊንፊኔ፣የከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች እና አደባባዮች በኦሮምያ ታሪክ ይቀየራሉ የሚል ሃሳብ የያዙ አረፍተ ነገሮች እንዲሁም ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር የስራ መጠቀምያ ይሆናል ይላል።ኦሮምኛ የስራ መጠቀምያ መሆኑ አማርኛ እስካልገባው ድረስ ኦሮምያ የተወለደ ኢትዮጵያዊ በኦሮምኛ አገልግሎት ማግኘቱ ሙሉ መብቱ ነው።ዛሬ ህወሓት እንደ ልዩ ጥቅም አድርጎ ማቅረቡ ነው የማይመቸው። ይህ እንዴት ልዩ ሆኖ ይቀርባል? ኢትዮጵያዊ መብቱ በሚለው ስር የሚገባ ነው።አንድ የጋምቤላ ተወላጅ አዲስ አበባ መጥቶ አማርኛ ካልገባው በጋምቤላ አነጋገር አገልግሎት የማግኘት መብቱ ኢትዮጵያዊነቱ ያጎናፀፈው መብት ነው እንጂ ልዩ መብት ሊባል ያችልም። ሕወሓት ለመከፋፈል ስትፈልግ ልዩ መብት ብላ ትርክት መጀመሯ አስቂኝ ነው። የአዲስ አበባ ስያሜ መቀየር እና የከተማዋን ታሪካዊ ቦታ ከመቀየር አንፃር የተነሳው አገላለጥ በእራሱ የተደናበሩ ሰዎች ያወጡት ረቂቅ አዋጅ ነው። በመጀመርያ ደረጃ በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰጡት ስሞችም ሆኑ የአዲስ አበባ የእራሷ ስያሜ እውን ታሪካዊ አመጣጥ የሌለው ባዶ ትርክት ከነበረ የታሪክ ሰዎች ይንገሩን እና እንመን።በሐሰት ታሪክ ግን የትም ሀገር ስም አይቀየርም። ይህንን ልሞክር የሚል ካለ የመስቀል አደባባይ እና የአብዮት አደባባይ ስያሜን ማስታወስ ነው።በሕልም እና በስሜት ሕዝብ ያጋጭልኛል ከሚል እሳቤ ብቻ ሕወሓት ይህንን ማሰቧን እራሱ የኦሮሞ ሕዝብ እና የአዲስ አበባ ነዋሪ ጠንቅቆ ይረዳል።
ባጠቃላይ ልዩ ጥቅም በሚል ቡልኮ የተሸፈነው የህወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን የተለያዩ ሀገር በማስመስል የአዲስ አበባ እና ዙርያዋን ያሉት የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ግንኙነት ኢትዮጵያዊ የሆነ የጋራ እሴት ሳይሆን የጥቅም ግንኙነት ብቻ ያላቸው አስመስሎ የማቅረብ ሙከራ ነው።መንግስት የተባለ አካል የመጀመርያ ስራው ዜጎቹን በእኩልነት የማስተዳደር፣ሕግ የማውጣት እና የማስፈፀም አቅሙን የማስመስከር መሆን ይገባው ነበር።ከእዚህ ውጭ አንዱን አስነስቶ በእዚህ አካባቢ ልዩ ጥቅም አለህ።አንተኛው ግን በምትኖርበት ከተማ ከእርሱ ያነሰ ጥቅም ነው የምታገኘው የሚሉ አባባሎች በእራሳቸው ህዝብን ለመከፋፈል የሚደረጉ አጀንዳዎች የማስቀጠል ሥራ አካል ካልሆኑ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። አዲስ አበባ እና ኦሮምኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል አትሞክሩ።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ሕዝብ የምታገለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ልዩ ጥቅም እንዲኖረው ነው።
ይህንን ፅሁፍ የምደመድመው አንድ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አክቲቪስት በተናገረው ንግግር ነው። አባበሉ አሁን ሕወሓት እየዳከረበት ካለው የመከፋፈል ከንቱ ሥራ ፍሬ እንደሌለው በሚገባ ያሳየ ነው። አክትቪስቱ ያለው እንዲህ ነበር
“ሕወሓት የኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ያለውን ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በመቶዎች በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ ያለፈ እና ጠንካራ የደም ትስስር መሆኑን ህወሓት በደንብ ያወቀው አይመስለኝም።እነርሱ ራቅ ካለ አካባቢ ስለመጡ የእዚህ አይነቱ ጠንካራ ግንኙነት ታሪክ በደንብ የገባቸው አልመሰለኝም።የኦሮሞ ሕብረተስብ አሁን ሕወሓት እለያይበታለሁ እያለ የሚያቀርባቸው አጀንዳዎችን የመለያያ አጀንዳዎች እንደማይሆኑ ጥንት በሰራቸው ስርዓቶች ካፈረሳቸው ቆይቷል።ሕወሓት ትልቅ የመረጃ ክፍተት ላይ እንዳለ መረዳት አለብን” ነበር ያለው።

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen