Netsanet: በሻርለት አንድ ለአምስት ጠርናፊው ዶክተር ከግሎባል አልያንስ ተወገደ

Montag, 19. Januar 2015

በሻርለት አንድ ለአምስት ጠርናፊው ዶክተር ከግሎባል አልያንስ ተወገደ

ተክለ ጊዮርጊስ ከአትላንታ

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ ከዳር እስከ ዳር በአንድ ለአምስት የስለላ መረብ ጠርንፎ እንደያዘ ይታወቃል።በመሆኑም በመስሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በእምነት ቦታዎችና በተለያዩ የማህበራዊ ህይወት ስብስቦች ውስጥ ሰላዮቻቸውን ሰርገው አስገብተዋል :: በዚህ ምክንያት በሀገር ቤት ህዝቡ እርስ በርስ ተማምኖ በአገሩ ጉዳይ ላይ እንዳይነጋገርና እንዳይወያይ አንደበቱ እንዲሸብብ ተደርጎአል። በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ነጻ አውጪ መንግሥት ከፍተኛ አፈናን ፤የጅምላ እስራትን፤ መፈናቀልን፤ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነትንና በጠቅላላው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በከፍተኛ ደረጃ እየፈጸመ ይገኛል::

በስደት የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ይህንን ወንጀል በመቃወም ድምጹን ከፍ አድርጎ በዓለም አቀፍ መድረክ በመጮህ ድምፅ አልባ ለሆነው ወገናችን አንደበቱ ሆኖ እየተፋለመ ነው:: ይህንን የተባበረና የጠነከረ ድምጽ ለመከፋፈልና አቅምለማሳጣት ይችል ዘንድ ወያኔ የስለላ መረቡን በዲያስፖራ ከዘረጋ ውሎ አድሮአል::
ወያኔ በውጭ አገር በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ሆድ አደሮችን ሰርጎ በማስገባት የመከፋፈል ስራውን በሰፊው ለማካሄድ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ የአወቃቀር ስልቱን ባህር አሻግሮ እዚህ ዲያስፖራ ውስጥ እየተጠቀመበት ይገኛል:: ውጤቱንም እያየነው ነው:: [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen