Netsanet: የነጻነትና ዴሞክራሲ ራዕያችንን እውን ለማድረግ የወቅቱን የትግል እንቅስቃሴ እንደግፍ!!!

Samstag, 24. Januar 2015

የነጻነትና ዴሞክራሲ ራዕያችንን እውን ለማድረግ የወቅቱን የትግል እንቅስቃሴ እንደግፍ!!!

የነጻነትና ዴሞክራሲ ራዕያችንን እውን ለማድረግ የወቅቱን የትግል እንቅስቃሴ እንደግፍ!!!

የነጻነትና ዴሞክራሲ ራዕያችንን እውን ለማድረግ የወቅቱን የትግል እንቅስቃሴእንደግፍ!!!

Jan 19, 2015
የምንፈልገውን ነገር ጠንቅቀን ማወቃችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። መድረሻችንን ማወቅ ያለብን ለጉዞ ከመነሳታችን በፊት ነው። አዎ! ግልጽ የሆነ ራዕይ ያለን መሆኑን ማረጋገጥ ወሳኝ ነገር ነው።
ይሁን እንጂ ራዕይ ወሳኝ ነገር ቢሆንም እንኳን ብቻውን ግን የትም አያደርስም። ልንደርስ የምፈልገውን ቦታ ማወቃችን ጉዞው የሚፈልገውን ፈተና ለማሸነፍ እና ጉዞው የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያበቃ ብርታት ካልሰጠን ከንቱ ነው። መልካምን መመኘት፤ መልካምን ማለም ጥሩ ቢሆንም ምኞት በተግባራዊ እንቅስቃሴ ካልታገዘ ውጤታማ አይሆንም። በዚህ ረገድ ግንቦት 7 እና አርበኞች ግንባር የፈጸሙት ውህደት መልካምና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ፍንትው ብለው የወጡ የሰማይ ከዋክብት ያስደርጋቸዋል!!! በርቱ!!!
ginbot 7 are
በዚህ በሰለጠነ ክፍለ ዘመን እንደባሪያ አዋርዶ እየገዛን ያለው የወያኔ ጉጅሌ ተወግዶ ማየት የብዙ ኢትዮጵያዊያን ፍላጎት ነው ብለን እናምናለን። የዜጎች ነፃነት የተከበረባት፤ የህግ የበላይነት የነገሰባት፤ እኩልነት የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚጋሩት ራዕይ ነው ብለን እናምናለን። ችጋርና ድህነት ጠፍተው፤ የሌሎች አገሮች ተመፅዋችነታችን አብቅቶ፤ የህጻናትና የመሬት ሸያጭ ተወግዶ፤ በአረብ አገራት የእህቶቻችንና ወንድሞቻችን የስቃይና ውርደት ኑሮ አብቅቶ ማየት ብዙዎቻችን የምንመኘው ነገር ነው ብለን እናምናለን። ባርነትንና ድህነትን ለመሸሽ ሲሰደዱ በበረሃ ንዳድ የሚያልቁ;፤ ባህር ውስጥ የሚሰምጡ እና በጎረቤት አገራት እስር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁ ዜጎች የሌሏት ኢትዮጵያዊያን ማየት ብዙዎቻችን የምንጋራው ራዕይ ነው ብለን እናምናለን።
እነዚህን መልካም ምኞቶች፤ እነዚህን ውብና ብሩህ ራዕዮችን የሚያሳካው ማነው? እንዴት ነው የሚሳኩት? መቼ ነው የሚሳኩት? እነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ለመልሱ ጣታችንን ሽቅብ ወደ ፈጣሪያችን ወይም ወደ ጎን ወደ ሌላው ወገናችን ከመቀሰራችን በፊት ራሳችንን  እንፈትሽ።
እንግዲህ አርበኞች ግንቦት 7 ለዴሞክራሲና ለአንድነት ንቅናቄ ሰሞኑን ያደረገው ውህደት ከ97ቱ የቅንጅት ውህደት በሆላ ምናልባትም ታሪካዊና የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ከስፍራው እንደዘገበው “ማርሽ ቀያሪ” ይሆናል የሚል እምነት አለን። ደህና፡- ማርሹ ከተቀየረ የሚቀረው ሁሉም ተሳፋሪዎችና Ethiopian stakeholders መሳፈራቸውን ማረጋገጥ ነው። ለዚህ ደግሞ ተሳፋሪዎቹ ከየኪሶቻቸው ውስጥ ያሉ ዘውዶችን አራግፈው ና አውልቀው፤ በቅንነት ለሀገር አንድነት ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ፣ ስለሚወዱት ህዝባቸው፣ ስለሚያፈቅሯት፣ ዘወትር ስለሚያወሩላት ኢትዮጵያ ሲሉ ወደ ታሪካዊው ማርሽ ቀያሪ የአንድነት ጉዞ መሳፈር፣ መተባበር አለባቸው።
እዚህ ላይ በውህደቱ እጅግ ታላቅ ደስታ የተሰማው የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት በእለቱ ደስታውን በጭፈራ ሲገልጽ “አያውቁንም….ኢትዮጵያዪ” ሲል እንዲህ ሲጨፍር ታይቷል፡-
ወገን እነዚህ ወጣቶች ስለ ሀገራቸው ሲሉ ለመሰዋእትነት የተዘጋጁ የእማማ ኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ናቸው፣ ስልጣን ምቾት ድሎትን የማይሹ ንፁህና ፍጹም ቅንነት ያላቸው የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው! የአፍሪካ መሪዎች ብዙ ጊዜ እልህና ከእኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ወይም በግል ጥቅም መታወር የእደነዚህ ያሉ የታጋዮችን መሰዋእትነት ከንቱ የሚያደርጉ አጋጣሚዎችን ሊከፍቱ ይሞክራሉ። ለዚህ ደግሞ ወያኔ አንዱና ዋንኛው ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብና ተቃዋሚ ነኝ የሚል ሁሉ ይህን ነጥብ ባለመሳት ትግሉን እውነት እናድርገው። ግንቦት 7 ከአርበኞች ጋር ያደረገው ውህደት የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም። እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ከላይ እንደጠቀስነው ይህ ውህደት በሰላም ወይም አልጋ በአልጋ እንዳልነበረም መገመት ይቻላል ይሁን እንጂ የሀገር ጥቅም ከበለጠ እንዲህ ውህደት ይፈጸማል!!! ሁላችንም ደስ ብሎናል።
በአንድ ወቅት የግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ክፍል ባወጣው ርእሰ አንቀጽ በማናቸውም ምክንያት ከኛ የሚመርጡት፤ በተሻለ የእርስዎን አገራዊ ራዕይ የሚያሳካ ሌላ ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ካለ ይቀላቀሉት። ጠዋት ሲነሱ “ዛሬ ለትግሉ የማበረክተው ምንድነው?” ብለው ይጠይቁ፤ ማታ ጠዋት ያሉዋቸውን ፈጽመው እንደሆነ ራስዎን ይፈትሹ። ሲል አትሞልን ነበር። በእኛ እምነት ግንቦት 7 አንድ እርምጃ ወደፊት ብሏል፤ ከዚህ በፊት ጥምረት ለነጻነት እና ለእኩልነት በሚል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር መዋሃዱ የቅርብ ጊዜ ትውስታም ነው። እነዚህ ሁሉ ተደምረው ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም የአእዋፋትን ዝማሬ ተግባራዊ ለማድረግ በጠዋት ሲንቀሳቀሱ አይተናል አሁን ደግሞ መስክረናል።
ሌላው የኛ ነው! መደገፍ፣ ማበረታታት፣ መቀላቀል እንጂ የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ… ማለት የስንፍና አሊያም ሌላ ነው። እነሱ መንገዱን ከእነ ችግራቸው ጠርገውልናል። መሰዋእትም ሆነው አሳይተውናል!! አንዳርጋቸው በመሰዋእቱ አንድ አድርጎናል። የእሱ ራእይ እንዳይጠፋ ደግሞ እሱ ከወለዳቸው የዴሞክራሲና የነጻነት የህዝብ ሃይል ዘቦችን መቀላቀል፣ መደገፍ የግድ ነው።
የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል ስልት እና ሜዳ የሚጀምረው በኤርትራ ነው! ይህ ሀቅ እውነትነት አለው። ኤርትራያኖች ወይም የመንግስት ባለስልጣኖች ላይ እውነት ወያኔ ቅስቀሳ እንደሚያደርግባቸው እና እንደሚባለው ክፉዎች አይደሉም፣ ሃላፊነት ወስደው በርቱ አሊያም “ምንም ችግር የለም” በሚል የሚታወቁ የሚያስተሳስር ባህል ያላቸው ቅን ሰዎችም ናቸው። ይሁን እንጂ ወያኔ በሚያናፍሰው የውሸት የጥላቻ ቅስቀሳ ኢትዮጵያውያን ተታለን እነዚህን ሰዎች ወይም ህዝቦች ቀረበን ሳናያቸው አሊያም በራሳችን ስንፍና ለሀሜት እንዳርጋቸዋለን። እርግጥ ነው ስለ ኢትዮጵያ ነጻነት እነሱ ሊዋጉልን አይችልም ነገር ግን አቅርቦት እያደረጉ ነው ያውም በምእራብያውያን ማእቀብ ከተመታ ድህነታቸው ቆርሰው እየደገፉ ነው። ኤርትሪያኖች ማንነታችንንና፣ አንጡራ ሀብታችንን ለምእራብያውያን አንሸጥም የሚል አቋም አላቸው። በጥቅሉ ኢትዮጵያና ኤርትሪያ ተከባብረው እና ተዋደው በመልካም ግንኙነት ሊኖሩ የሚችሉ ሀገራት እና ቅን ህዝቦች እንጂ፤ ወያኔ የሚለፍፈው እንዳልሆነ እንረዳ! ፖለቲካንና ህዝብን ለይተን እንየው! ወያኔ ስልጣኑን ለማራዘም፣ ህዝባዊ ቁጣዎች ከዳር እንዳይነሳበት የማህበረሰቡን አመለካከት ወደ ጭራቅነት መለወጥ ይፈልጋል። እሱ በሰጠን የቤት ስራ ከመጓዝ እንቆጠብ። ከወያኔ በላይ ሀገር አጥፊ ጠላት በላይ ምንም የለም!!! ከተሳሳተ የፖለቲካ ሂሳብ እንውጣና እውነተኛ ትግሉን እንደግፍ። “ምንም ችግር የለም ሁሉም በጊዜው ይፈታል” እንደ ኤርትሪያኖች አባባል።
Ginbot 7
ይህ ሁኔታ በዚሁ እንዲቀጥል መፍቀድ የለብንም!!! በጭራሽ መፍቀድ የለብንም!!! ፈጽሞ!!!  ስንቴ እንሞኝ? እንደምን አገራችንን ለቀንለት ወያኔ በህዝባችንና በገዛ ራሳችን ህይወት ላይ እንዲሰለጥን እንፈቅዳለን? መቼ ነው አገራችንን፣ ህይወታችንን፣ ተስፋችንን ከወያኔ ነጥቀን የራሳችን የምናደርገው? ስለዚህ አርበኞች ግንቦት 7 የዴሞክራሲና የአንድነት ንቅናቄን ጅምር እንቅስቃሴን ከልባችን የነጻነትና ዴሞክራሲ ራዕያችንን እውን ለማድረግ እንደግፍ! ክፍፍል እና ጎራ ይብቃን! አንድነት ሃይል ነው!!!
አባይ ሚዲያ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen