Netsanet: እና አሁን ምንድን ነው መደረግ ያለበት?። ዳዊት ዳባ

Samstag, 31. Januar 2015

እና አሁን ምንድን ነው መደረግ ያለበት?። ዳዊት ዳባ

የተለመደውን ኮሮጆ ገልብጦ አሸንፌያለው ማለት ሁሌ የሚሰራም አስተማማኝም በጭራሽ አልሆነም። በይበልጥ ደግሞ አሁን ባለው ጠቅላላ ያገራችን ሁኔታ መስረቅ እሰከጭራሹ እንዳይቻል ለማድረግ በቀላሉ ይቻል ነበራ። ካነሰም ሌብነቱ መውጫ የሌለው ጦስ ይዞ እንዲመጣ ለማድረግ የሚቻልባቸው መንገዶች እንዳሉ በጥልቀት ያሰቡበት አይተውታል። በይበልጥ ደግሞ አንድነቶች። አገዛዙ የምርጫ ጫወታ ይኖራል እስካለ መጫወቱ የምናተርፍበት ነው ተብሎ ሱገፋ የነበረው ለዚህ ነው። እኛ ጠንካራ ሆነን የመቅረባችን ጉዳይ ነው እንጂ አንድ ቀን ተነስቶ ምርጫ የሚባል ጫወታ ከዛሬ ጀምሮ የለም ሊል እንደሚችልም ግልፅ ነበር። በእርግጥ ያአንባገነን ለከት ያጣ የፍራቻ ባህሪ ሆኖ ነው እንጂ አሁን ላይ ወደዚህ ውሳኔ እንዲደርስ የሚያስገድደው ዝግጅትና ጥንካሬው ተቃዋሚው ነበረው ለማለት ይከብዳል።

ስለዚህ ምርጫ በፃፍኩ ቁጥር ከፈለገ “እራሱ የምርጫ ጫወታ ቀርቷል” ይበል የምትለዋን ነገር በአፅኖት በተደጋጋሚ አንስቻታለው። ለምን ቢባል እዚህ ውሳኔ ላይ በቀላሉ ማድረስ እንደሚቻል ስላወኩ ነው። ገና ከመነሻው ከምርጫው እንታቀብ የሚለው ሀሳብ ትርፉ አላጠገበኝም። ያን በማድረግ ሊገኝ የሚታሰበውን ትርፍ በተሻለ መንገድ ጨማምሮ በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበትም መንገድ ስላለም ነዋ።

አሁን በገሀድ ወናዎቹን ተቀዋሚዎች አግዷዋችዋል። አንድነትና መኢአድን ከምርጫው ማገድ ማለት ምርጫ ጫወታ የለም ማለት ነው በራሱ። በአዋጅ መልክ ባያስነግረውም በቀላሉ የምርጫ ጫወታ ቀርቷል እንዲል ተገዷል ማለት ይቻላል። በአዋጅ መከልከሉም በቀጣይ በምንወስደው ፖለቲካዊ ውሳኔ ድግሞ የሚወሰን ነው የሚሆነው። ይህን ወይ ያንን እውነተኛ ተቃዋሚ ከምርጫው በማገድ ተሳስቶ ነው እንጂ ወያኔ የሚያገኘው ትርፍ የለም። ባቂላ ጠፋ ቢሉ አይነት ነው ለለውጥ ፈላጊው የመጨረሻ ወጤቱ። በግድ በአንድ ይሰባስበናል አለቀ። ይህ ደግሞ ያቃተን ልንሰራው ግድ ይል የነበረ የቤት ስረችን ተሰራ ማለት ነው። በእርግጥ በዚህ ታስቧቸውና ፍራቻቸው ሰማያዊ ፓርቲንም ከምርጫው ማገዳቸው እንደማይቀር እሙን ነው። ላሁኑ ግን ሰማያዊም መድረክም የምርጫው ጫወታውስጥ አሉ። እና አሁን ምንድን ነው ማድረግ ያለብን?።

በመጀመርያ በተፈጠረው ሁኔታ የተናደድን ያዘንን የተናደድንበትና ያዘንበት አካል። እንዲሁ ለዚህ ፍፁም ኢፍትሀዊና አንባገነናዊ እርምጃ ተጠያቂ የምናደርገው ክፍል አምታች መሆን አልነበረበትም። በዚህ ተጨባጭ ሁኔታ ጅብ በቀደደውም አይሰራም። ያለው ጅብ ብቻ ነዋ። የቀደደውም የገባውም ጅብ ነው። ድርጅቶቹ በትንሹ ቢሰላ እንኳ ብዙሺ አባላት አላቸው አስርጎም ለማስገባት ሆነ ያኮረፈ፤ ገንዘብና ስልጣን ፈላጊ፤ ሰርቆ ወይ ቦርቧሪ ሆኖ የተባረረ አንድና ሁለት ሰው ከየደርጅቶቹ ማግኘት ከባድ ተደርጎ የታየው ለታየው እንዴት ነው?። ቆይ በረከት ስሞንን የአንድነት። ተክላይ ተክሉ የመኢአድ አባል ነበሩ ብሎ ፎርጅድ መታወቂያ ሰርቶ አሳይቶን ለበረከትና ለተክላይ ቢያድላቸውስ ኖሮስ። ይህን አበባውና አወልን ባይገኙ ኖሮ የማያደርጉት ነበር ወይ?። ይቁረጥ አለዛ እኔ እቆርጥልሀለው። እዚህ ደረጃ የሚወርድ ፍፁም የሆነ አሪዬስ ስልጣን ላይ እስካለ ለወደፊቱም የትኛውም ድርጅት ሊያስቀረው የሚቻለው ችግር በጭራሽ አይደለም። የፈለገ ጊዜ በቀላሉ የትኛውም ድርጅት ላይ ሊያደርገው የሚችለው ቀላል ነገር ነው።ለነገሩ ደደብነታቸው ነው እንጂ ፍርድ ቤቱም የነሱ በምርጫ ቦርድ ተብዬው ከሚያደርጉት በፍርድ ቤት ቢያደርጉት ይሻላቸው ነበር።

ለማንኛውም የምናለቅስበትን አካል እንለይ። ተቃዋሚዎች ታቃዋሚዎች ሲሉ ማስለቀሱ ላይ ወያኔዎች ማልያ ቀይረው በመጀመርያ ረድፍ አሉበት ይግባችሁ። ጅብ በቀደደው የሚሰራው እዚህ ላይ ነው። ፋይዳ የሌለው አመል ብቻ የሆነ ፖለቲካል ትርፍ ለማግኘት ወይ እኛ ትክክል ነበርን ለማለት ሲባል በዚህ መንገድ ልናጮህው የምንፈልግ አደብ እንግዛ ። ምርጫ 97 ላይ ወያኔ ከወሰደው እርምጃ በላይ ትግል ላይ ነን የሚሉ ክፍሎች የሰሩት ስህተት ነው። ብዙ የዋህ ዜጎችን ዛሬም ድረስ ተቃዋሚ፤ ፖለቲካና ትግል የሚባል ነገር ሲሰሙ እንዲንዘፈዘፉ ያደረገው። በሗላ ማቃናቱ እንደማጥፋቱ ቀላል አይሆንም። አንዳንዴ ዝም ብዬ ሳየው ላፉ ተተኩሶ ነው መባረር ያለባቸው ከሚለው ክፍል በላይ በሰላም እንታገላላን የሚሉት በሰላም ሲሉ የነሱን ሰላማዊነት ለመግለፅ ነው እንጂ ከሰላማዊ ሀይል ጋር እንደማይታገሉ በደንብ ያውቃሉ። እንደሚገለን እናውቃለን፤ እንደሚያስረን እናውቃለን፤ እንደሚጨፈጭፈን አውቀን ነው ሌባ ነው ኮሮጆ ይገለብጣል። ይኮ የሁሉም በጋራም የተደረሰበት ከልብ የሆነ አቋም ነው። የዘመኑን ትግል ክፉም ልዩም ያደረገውም ይህ ነው።

ሰማያዊና መድረክ ከምርጫው አንዱ የሚታገድ ከሆነ አብሮ ከምርጫው ለመወጣትና፤ ለምርጫው እጩዎችን መደላደል ላይ ብቻ ስምምነት በቀናት ሰርቶ ቅንጅት መፍጠራችሁን ይፋ ማድረግ ሁለት።

አንድነትና መኢአዶች በህግ ቤት የተቀማችሁትን መብት ለማስመለስ መሞከሩ። በሂደት አዲስ ድርጅት ሆኖ መውጣቱም ሆነ ያሉት ድርጅቶች ውስጥ ተደባልቆ የመታገሉ አማራጭ እንዳለ ሆኖ አሁን ሙሉ እውቅና ምርጫው ውስጥ ለቀሩት ድርጅቶች መስጠት። በአዋጅ ላአባሎቻችሁም ለደጋፊዎቻችሁም ለህዘብም ሙሉ ድጋፍና ርብርቦሽ ይሆን ዘንድ መናገር። ሶስት
ከአገር ውጪ ያሉ ድርጅቶች አመራሮች በሙሉ አንድ ቦታ ላይ በአካል ተገናኝታችሁ በሚታይ፤ በሚሰማ መንገድና ፕሮቶኮል በጠበቀ ሁኔታ እጥር ያለና ቀጥተኛ ጠንካራ የሆነ እውቅናን ምርጫው ላይ ለቀሩት ድርጅቶች መስጠት። ድጋፍ ሰጪ አካል ማቆም። ሶስት ወር የሚቆይ የምርጫ ዘመቻ መጀመር። አራት።

ለየትኛውም አይነት ምት የፃፈ ምት ያስፈልገዋል። አናደርገውም እንጂ ሁሌም ደግሞ ድላው ነበረን። ተመጣጣኝ ነው አይደለም ሌላ ጉዳይ ነው። ለቅሶ እንጂ አፀፋ ስለማንመልስ ግን ዜጋውንም አፈዘዝነው። አለማምደነው ቢሆን ይህ ህዝብ ጉለበተኛነቱን የሚያሳይበት መልካም አጋጣሚ ነበር። ባለመሆኑ ማንን ፍርቼ ገደባ አጣ። ለነገ እየተሰራበት ያለው ዱላ በጊዜው ይደርሳል። አሁን ላይ የሚቻለውንና ያለንን ዱላ ስናሳርፍ ነው ለትልቅ ጉዳይ ህዝባችንን ማሰለፍ መቻላችንን እርግጠኛ መሆን የሚቻለው።

ሰማያዊና መድረኮች መጠንቀቅ የሚገባችሁ ሶስት ወር አምስት አመት አይደለም። በቀጥታ ምርጫው ላይ ልትሰሩበት ይገባ የነበረ ጊዜ እያማሸከ ነው። በዛ ላይ ለመምረጥ መመዝገቡ የጊዜ ገደብ አለው። በሌሎች ነገሮች ተወጣጥራችሁ ስላላችሁ ለመምረጥ ምርጫው ላይ እናንተ መኖራችሁን ብቻ ሳይሆን ቀጥሉን የሚጠብቁ ሚሊዬን ለውጥ ፈላጊዎች መመዝገቢያው ጊዜ እንዳያልፍባቸው ጠንከር ተደርጎ አሁኑኑ መምረጫ ካርዳችሁን ያዙ ሊባሉ ይገባል። ካርድ ይዞ አለመምረጥ ይቻላል። ካርድ ሳይዙ መምረጥ ግን አይቻልም። ምርጫውን በሚመለከት ሌሎችም የጊዜ ገደብ ያላቸው ጉዳዬች ይኖራሉና ድርጅቶች ጠንቀቅ ነው። ምረጡንም ስራ አሁን እንደውም ዛሬ ነው መጀመር ያለበት። አደባባይ ሰልፉን ለጊዜው ተውትና ምረጡን ምረጡን ብቻ በቀረው ጊዜ።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen