Netsanet: የሕወሃት ታጥቂዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት በኋይል ተቆጣጥረዉታል።

Freitag, 30. Januar 2015

የሕወሃት ታጥቂዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት በኋይል ተቆጣጥረዉታል።

የሕወሃት ታጥቂዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት በኋይል ተቆጣጥረዉታል። ጥዋት ሥራ አስፈጻሚው ስብሰባ አደረጎ የነበረ ሲሆን፣ ከሰዓት በኋላ ምክር ቤት ሊሰበሰብ ታስቦ የነበረ ቢሆን፣ ደህንነቶች ጽ/ቤቱን ከበው ማስገባትና ማስወጣት ስላልተችለ፣ የምክር ቤቱ ስብሰባ ሳይደረግ ቀርቷል። ሆኖም የሥራ አስፈጻሚው ጠዋት ባደረገው ዉስኔዎችን አስተላልፏል። የመጀመሪያ ዉሳኔ በአገሪቷ ክፍል ያሉ የንድነት አባላትና ደግፊዎች በሕወሃት ለተቋቋመው ተለጣፊ ቡድን ምንም ኣይነት እውቅና እንዳይሰጡና እንዳይደገፉ ጥሪ አቀርበዋል። የሥራ አስፈጻሚው በአዲስ ስም መንቀሳቀሱ፣ ሕወሃት ተመሳሳይ እርምጃ እንዳይወሰድ የማያከላክለው በመሆኑ፣ መሰረታዊ የዲሞክራሲ ተቋማት ለዉጥ በሌለበት መልኩ አዲስ ስም አወጥቶ እንደገና መንቀሳቀስ ዋጋ እንደሌለው ገልጸዋል። ሌሎች ድርጅቶችን መቀላቀሉ በተመለከተ ያ የአባላት የግል ዉሳኔ እንደሆነ አስረድተው፣ ነገር ግን እንደ አንድነት ሥራ አስፈጻሚ ወደ ሌል ድርጅት ቢቀላቀሉም፣ አገዝዙ ተመሣሳይ እርምጃ በተቀላቀሉት ድርጅት ላይ ሊወስድ እንደሚችል አስረድተዋል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen