በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች በተደረገ የሰንደቅ አላማ መቀየር ምክንያት በርካታ ዜጎች እንደታሰሩ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣
በክልሉ ከማሽ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በክልላችን የሚደረገው የሌሎች ክልሎች ጣልቃገብነት ይቁም ህዝባችን የመረጠው እንጂ ሌሎች ክልሎች የመረጡት መሪ አያስተዳድረንም በማለት አቤቱታና ሰላማዊ ሰልፍ ያቀረቡ ቢሆንም ምንም ሰሚ አካል ባለማግኘታቸው የተነሳ ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ ነጭና ጥቁር መካከሉ ደግሞ ቀይ የV ቅርፅ ያለው ሰንደቅ አላማ ማውለብለባቸውን የገለፀው መረጃው፤ የክልሉ ተወላጂ የሆኑ የቀድሞ ባለስልጣናት የነበሩ በርካታ ዜጎች በመንግስት ፖሊሶች የታሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስረድቷል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ኢንቨስተሮች በክልሉ ባጋጠመው ግርግር ምክንያት እለታዊ ስራችንን መስራት አልቻልንም በዚህ ከቀጠለ ለደህንነታችን አስጊ ነውና ባለፈው የምርት ዘመንም ለኪሳራ ተጋልጠናል ሲሉ ከስፍራው እየለቀቁ ኣንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፣
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen