Netsanet: August 2014

Sonntag, 31. August 2014

ካርቱም ለምትገኙ ስደተኞች በሙሉ – በሱዳን የሚገኙትን 5ቱን የወያኔ ሰላዮች/ ተላላኪዎች ይወቁ

በሱዳን ከሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ፦
በሱዳን ሀገር ለምትገኙ ኢትዮጽያውያን በሙሉ መብታችን ሰብአዊ ክብራችን ለዘመናት በስደት በምንኖርበት ሀገረ ሱዳን በ ዩን ኤች ሲ አር በኩል ከፍተኛ አድሎ በደል እንደሚደረግብን ለማንም ግልፅ ነው። ይሂም የኛ ዝምታና አንድነት አለመኖር እረሳችንን እንደጎዳን በማንም ይታወቃል በሕብረት በአንድነት ቆመን መብታችን ለማስከበር እንዳንታገል ያደረግን የወያኔ ረቂቅ ተንኮል መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው። ይህንን አሳዛኝ ሕይወት ማንም በየቤቱ ይናገራወል በቅርብ በሚያውቀው ጓደኛ ጎረቤት ይወያይበታል የስደተኛ መብታችንም እንዳናስከብር እንደኛው የስደተኛ መታወቂያ የያዙ ለረዥም ዓመት በጉርብትና በመሀበር በእድር የምናውቃቸው ሁለት አይነት መታወቂያ ያላቸው እስስት ሰላዮችን ስደተኛው ማህበረሰብ በይሉኝታ እስከ ዛሬ በዝምታ ሲያልፋቸው ኖረዋል። እነሆ እሰከ ዛሬ የስደተኛ መብታችን ከመጋራት አልፎ እኛን መስለው ሲሰልሉን እያየን እየሰማን አንድ ለአምስት በሚባል በስለላ ስራ ተሰማርተው በቤተክርስትያን በእድር በጉርብትና በየፀበል ፀዲቁ በዩ ኤን ኤች ሲ አር በኮር ስደተኛው በሚገኝበት በስውር ተመድበው ሰርገው በመግባት በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። እነዚህ ከሀዲ ባንዳዎች ሰርቶ የሚኖረውን ስደተኛ እለት በእለት እየተከታተሉ ለወያኔ ኢንባሲ ዘርፈው ለማይጠግቡ ኢትዮጽያን ሸጠው ለማይረኩ ቅጥረኞች ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሪፖርት ያደርጋሉ። ከዚህ በኋላ ዝምታችን ሰብረን ዝምታ ለበጓም አልባጃት እንዲሉ ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን ወራዳ እንደ ሚሸጥ ስጋ ምንግዜም እራሳቸውን በፍርፋሪ የሚሸጡ በፍፁም ኢትዮጽያዊ ክብር
የለላቸውን በስደተኛ ስም ስደተኛ ነን የሚሉትን ከሀዲ ባንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ በካርቱም በተለያዩ ቦታዎች በበሀሪ በእምድሩማን በጅሬፍ በሰሀፋ ሸሪክ በሰሀፋ ዘለጥ በጀብራ በጎዝ በዴም ውስጥ የሚገኙትን ተራ በተራ እናጋልጣለን ለግዜው።……..
የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)
የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)

1ኛ. አየልኝ ተድላ መኮነን (ኰከቤ)፡− ይህ ግለሰብ በ2005 የተቋቋመው የስደተኞች ኮሚቴ ውስጥ አባል ሆኖ እየሰራ እያለ በኮሚቴ አባላት መካከል ጠንካራ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩትን ወያኔ ሆነዋል ብሎ በማስወራትና ክፍፍል በመፍጠር ኰሚቲው እንዲፈራርስ ትልቅ ሚና ተጫውቶዋል። በዚህ ሳይቆም ከኢትዮጵያ ሸሽቶ የመጣ አንድ የግንቦት 7 ዓባል አቶ አንዱአለም የተባለ ሰውየ እዚህ ካርቱም እንዲታፈንም ከፍተኛ አስተዋጾ ካደረጉት ሰዎች አንዱ ነው። COR እና UNHCR ሲሄድ ተቃዋሚ መስሎ የሚቀርብ በተግባር ግን የወያኔ ቅጥረኛ የሆነ ግለሠብ ነው።
2ኛ. ወርቁ አለባቸው (ባሪያው) ፡− ግለሰቡ የወያኔው የማፍያ ቡድን መሪ የነበረው የመለሰ ዜናዊ የሃዘን ቀን በሚከበርበት ቀን የሟቹን ፎቶ ይዞ ምሾ ሲወርድ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ባጋጣሚ ፎቶው ይቀደዳል ወያኔ ለመሆን ይረዳኛል ብሎ ያሰበው እለቅሶ ወያኔ በሆኑት ሆን ብለህ ነው የቀደድከው አንተ ሆዳም ዓማራ ተብሎ ተዋረደ እና ተደበደበበት። ከዛን ቀን በሆላ ጠቅልሎ እንደገባ በአደባባይ አስመሰከረ።
3ኛ. ተስፉ የሽወንድም ፡− በዘመነ ደርግ በጎንደር ውስጥ በኢሰፓ ውስጥ ሲሰራ የነበረ ሲሆን ስደት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በየሄደበት ወሬ በመለቃቀም ለኢንባሲው የሚያቀብል አደገኛ ወሬ አነፍናፊ የሆነ ግለሰብ ነው።
4ኛ. ሽዋየ ሲሳይ ፡− በባሏ መሞት አማራነቷን ያወቀችው ቀዳማዊ ዕመቤት እየተባለች ስትሞካሽ የነበረችው አዚብ መስፍን ሱዳን ስትመጣ በቤቷ ተቀብላ በማስተናገድ ብቻ ሳትወሰን የስለላም ስራ በመስራት ሪፖርት የምታቀርብ ናት።
5ኛ. መኪ ጉራጌው ፡− በመባል የሚታወቀ ኦምዱሩማን የሚኖር ይሂው ግለሰብ ኦምዱሩማን የሚኖሩ ስደተኞችን በማማበል ስደተኞች በኢንባሲው ውስጥ በተዋቀረው እድር እንዲሳተፉ እና የተለያየ ጥቅማጥቅም እንደሚያገኙ በማሳመን የአባላት ምልመላ ያካደርጋል። እግረመንገዱንም ለኢምባሲው በመሰለል መረጃ ያቀብላል።
ወድ ኢትዮጽያዊ እነዚህ ለሆዳቸው ያደሩ አሳልፈው እንደሰጡህ ይታወቃል ሌሎችም አንድ ለአምስት በሚል በወያኔ የስላላ መረብ የተጠረነፉ እንደተለከፈ ውሻ በየስደተኛው ቤት የሚክለፈለፉ በአማራ በትግሬ በኦሮሞ በጉራጌ በደቡብ መሀበራት ስም የተደራጁ እንዳሉ ይታወቃል እነዚህ ወገን ሀገርን የሚሸጡ ደላለዎችን በማንኛውም መልኩ ከማንኛወም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ማድረግ አለብን። ከአሁን በሆላ በስደተኛው ስም መነገድ እንዲያቆሙ ልንነግራቸው ይገባል። እንደማይራሩሉልህ ይታወቃልና ስለዚህ በይሉኝታ መብታችን ና የኢትዮጽያን ክብር ከአሁን በፊት አሳልፈን የሰጠነው ይብቃል እንበላችው ! በጋራ እንዋጋቸው !!!
ይህንን በረሪ ወረቀት ኮፒ እያደረክ ያላነበበው እንዲያነበው ትብብርህን አንጠይቃለን !
ለመብትህ ለክብርህ ተነስ !!!

አቶ አባይ ፀሐዬ ቤተክርስቲያን የግል ፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ መመሪያ መስጠታቸው ተጋለጠ

(ዘ-ሐበሻ) ከሁለት ወራት በፊት አቶ አባይ ጸሐዬ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ መመሪያ ማስተላለፋቸውን የዘ-ሐበሻ የቤተ-ክህነት ምንጮች አጋለጡ። እንደምንጮቹ ገለጻ ቤተክርስቲያኗ ይህን መመሪያ ከተቀበለች በኋላ የተለያዩ ክሶችን በፕሬሶች ላይ አዘጋጅታ የነበረ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሎሚ መጽሔት ላይ የታሰበው ክስ ጋዜጠኞቹ በመሰደዳቸው የተነሳ ክሱ ሊቀር ችሏል።
(ሎሚ መጽሔት ሊከሰስበት የነበረው ጽሑፍ ይህ ነበር)
(ሎሚ መጽሔት ሊከሰስበት የነበረው ጽሑፍ ይህ ነበር)

የቤተክህነት ምንጮቻችን ዜናውን ሲያደሱን “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን በሎሚ መጽሄት ላይ ልትመሰርት የነበረውን ክስ ሰረዛዋለች።” ካሉ በኋላ “ከትላንትና በስቲያ በንብረኡድ ኤሊያስ አብርሃ ለሕግ ክፍል በደረሰ የስልክ ትእዛዝ መሰረት የሎሚ መጽሄት ባልደረቦች ስለተሰደዱ እና ጹሁፉን ጻፈ የተባለው ግለሰብም የሚኖረው በአውሮፓ ሞናኮ መሆኑን የመንግስት አካላት ባደረስን መረጃ ክሱ ዝግጅቱ ቢጠናቀቅም እንዲሰረዝ በስልክ በንበሩድ ኤሊያስ ተነግሮናል።” ብለዋል። እነዚሁ ምንጮች እንዳሉት “ክሱ እንዲመሰረት የተፈለገው “ዜጎችን ያልታደጉ ቆባቸውን ያውልቁ ” በሚል ርእስ ስር የተጻፈው የሃይማኖት መሪዎችን መብት ይጋፋል እንዲሁም የእምነት ነጻነትን በማደፍረስ ሕዝቡ በሃይማኖት መሪዎች ላይ ታማኝነት እንዳይኖር ያደርጋል ..ወዘተ በሚሉ ተያያዥነት ካላቸው ጉዳዮች ጋር ሰበብ እና አቃቂር በመፍጠር መጽሄቱን እና ጸሃፊውን ለመክሰስ ታስቦ ለሕግ ክፍሉ ተጠንቶ ክሱ እንዲዘጋጅ ትእዛዝ ተላልፎልን የነበረ ቢሆንም ከመንግስት በተገኘ በሚል መረጃ መሰረት በንብረኡድ ኤሊያስ አብርሃ ተሰርዟል።” ብለዋል።
ምንጮቹ ጨምረውም ከሁለት ወራት በፊት በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ሁሌም ጣልቃ የሚገቡትና በአንድ ወቅትም ቤተክርስቲያን አንድ ልትሆን በተቃረበችበት ወቅት “ውጭ ያለውን ሲኖዶስ በቅርብ ቀን በአሸባሪነት እንከሳለን፤ ስደተኛው ሲኖዶስ ሀገር ቤት የሚመጣው መንግስት ለመገልበጥ ነው” በሚል አባቶችን ማስፈራራታቸው በሚዲያ የተለቀቀባቸው አቶ አባይ ጸሃዬ ቤተክርስቲያኗ በፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ የሰጡትን መመሪያ ተከትሎ በሌሎች ፕሬሶች ላይም ክስ ለመመስረት ዝግጁ ናቸው።

ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም በዐማራው ቁስል ላይ ጨው ነሰነሱ! የ«ዐማራ የለም» አቋም የክህደት ወይስ የመሣት?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት       እሑድ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺህ፮  ዓ.ም.      ቅፅ ፪ ፣ ቁጥር ፳፯
ሰሞኑን ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም «ሸገር» ከተሰኘ በኤፍ.ኤም. 102.1 (FM 102.1) ከአዲስ አበባ መርኃግብሩን ከሚያሠራጭ የሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ «ዐማራ» የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ አለመኖሩን ልባቸውን ነፍተው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ፕሮፌሠር መሥፍን በዚህ ቃላቸው፣ በ፲፱፹፫(1983)ዓ.ም. ከሟቹ የትግሬ-ወያኔዎች መሪ መለስ ዜናዊ ጋር በቴሌቪዥን ቀርበው ስለ ዐማራው ነገድ ያለመኖር ያንጸባrmቁትን አቋም አፅንዖት በመስጠት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ዐማራ የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ ውስጥ «አለ» ወይስ «የለም» ብሎ፣ በላ! ልበልሃ! ወደሚል እጅግ የወረደ ክርክር የሚገባ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት ክርክር ውስጥ የሚገባ ሰው፣ ኃሣቡ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የማይችል የፕሮፌሠር መሥፍን ዓይነቱ ሰው ብቻ ነው። ለነገሩ በዚህ የቀን ቅዠት አቋም የሚፀና ካለ ከፕሮፌሠር መሥፍን ሌላ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ይገኛል ተብሎ አይታሰብም። የፕሮፌሠር መሥፍንም ክርክር ጭፍን ክህደት ወይም መሣት (መጃጀት) አልያም ቀቢፀ-ተስፋ የተሞላው ቁጭት ከመሆን አያልፍም። የፕሮፌሠር መሥፍን አቋም የክህደት ከሆነ፣ ወላጅ አባታቸውን ዕውቁን ሊቅ አለቃ አስረስ የኔሰውን ክደዋልና የዐማራ ነገድን ኅልውና ከመካድ የሚያግዳቸው የኅሊና ልጓም ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ከመሣት(መጃጀት) የመነጨ ከሆነ ግን አያድርስ! እንዲህ እስኪሆንስ ፈጣሪን «አታቆዬን» ከማለት ሌላ ምን ይባላል። ከቁጭት ከሆነ ነገሩ ሌላ ነው። በቁጭት የአንድን ታላቅ ሕዝብ መኖር ኅልውና ክዶ ስለዚያ ሕዝብ መከራከር እና መጮህ አይቻልም። የቁጭት ተገቢ መገለጫው «አሻፈረኝ! በቃኝ! ተነስ! ዱሩ ቤቴ በል!» በማለት እንጂ «የለህም! የሚያጠፉህ ሳትኖር ነው!» በማለት አይደለም። የሌለ፣ ኅልው ያልሆነ፣ ሊያደርገው የሚችለው ምንም ነገር የለምና!
ፕሮፌሰር መሥፍን «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» ከሚል መደምደሚያ የደረሱት፣ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ከሦሥቱ በአንዱ ወይም በሁሉም ተያያዥነት እንደሆነ ቀደም ካሉት ድርጊቶቻቸው መገንዘብ ይቻላል። የመጀመሪያው በ፲፱፹፫(1983) ዓ.ም. ከሟቹ መለስ ዜናዊ ጋር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባደረጉት ውይይት ዐማራን እና ክርስቲያንን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን በመዘንጋት፣ ወይም ሆን ብለው «ክርስቲያን እንጂ፣ ዐማራ የሚባል የለም» ብለው ተከራክረው ስለነበር ያ አቋማቸው ያልተለወጠ መሆኑን እና ዛሬም «በዚያው አቋማቸው የጸኑ ናቸው» ለመባል ከማሰብ የመነጨ፣ ከስህተት ወደ ስህተት የመጓዝ አስተሳሰብ ነው። ሁለተኛው ፕሮፌሠር መሥፍን ክህደት የመታወቂያ ባሕሪያቸው ስለሆነ ትናንት የካዱትን ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላም በክህደቱ  የቀጠሉ መሆኑ የሚያመለክት ነው። ይህም ሌላው ግትርና «ያለ እኔ ዐዋቂ የለም» የሚለው የገነገነ አስተሳሰባቸው መገለጫ ነው። ሦስተኛው ከክህደት ባሕሪይ በተጨማሪ በዕድሜ መግፋት ምክንያት የመጣ፣ የኋላን ያለማዬት እና የመሣት አባዜ የገጠማቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። አራተኛው በዘመነ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በዐማራው ላይ በተከታታይ እየተፈጸመበት ያለው መገደል፣ መታሠር፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ከአገር መባረር፣ መዋረድ እና መጎሳቆል እጅግ በዝቶ የግፉ ጽዋ ሞልቶ የሚፈስበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሆኖም ዐማራው «አሻፈረኝ» ብሎ ወያኔን ግብግብ ከመግጠም ይልቅ የሚሣየውን ሆደ ሠፊነት ከኢዮብ ትዕግሥት በላይ ሆኖ ስላገኙት፥ «ዐማራ የሚባል ነገድ ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ ጥቃት እና ውርደት ሲፈጸምበት ዝም ብሎ አይመለከትም ነበር! ሌሎቹ እንደሚያደርጉት ኃይሉን አስተባብሮ ጥቃቱን ይቋቋም ነበር! ባለመኖሩ ነው ይኸ ሁሉ ጥፋት የሚፈጸምበት» ከሚል ቁጭት የደረሱበት ድምዳሜ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል።
ይህ ግን ከዐማራው ባህል፣ ዕምነት፣ አኗኗር፤ ማኅበራዊ ግንኙነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ጋር አጣምሮ ለሚያይ ሰው፣ ዐማራው በወያኔ የደረሰበትን ሁለንተናዊ ግፍ እና በደል በአርምሞ በመመልከት ላይ ያለው፣ በደሉ ሳይሰማው ቀርቶ አይደለም። እንዲያውም «የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች» እንዳይሆንበት የትግሬ-ወያኔዎችን ግፍ ለመበቀል ሲል በደልን በበደል መመለስ፣ የትልቂቱን አገሩን የኢትዮጵያን ኅልውና እንዳያፈርስ ኅሊናውን ገዝቶት፣ በሆደ ሠፊነት እና በትዕግሥት ማየቱ፥ ብልኅነቱን፣ አስተዋይነቱን፣ «አድሮ እንየው» ማለቱን፣ ውሽንፍርን እና ጥምዝምዝን አጎንብሶ ማሳለፍ ባህሉ መሆኑን፣ እንጂ፤ ጥቃትን እስከ ዝንተ ዓለሙ የሚቀበል አለመሆኑ ታሪኩ ያስረዳል። «ዐማራ ሰንበሌጥ ነው፤» የሚባለውም እኮ ለዚህ ነው። ማንም እንደሚያውቀው ሰንበሌጥ ኃይለኛ ወዠብ (ነፋስ) ሲመጣበት ለጥ ብሎ ያሳልፋል፣ ወዠቡ ሲያልፍ ይነሣል። ዐማራውም በተደጋጋሚ እና በተከታታይ ሊያጠፉት የተሰለፉትን ኃይሎች ሁሉ ተቋቁሞ እስካሁን የዘለቀው በዚህ መንገድ ነው። ጠላቶቹን የሚያሸንፋቸው በመበቀል ሣይሆን በይቅርታ እና በፍቅር መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አያስፈልግም። የኢትዮጵያዊነት ማገር፣ ዋልታ እና ጭምጭም ሆኖ ለዘመናት የዘለቀውም የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት ስሜቱ የዳበረ በመሆኑ ነው። ይህም በመሆኑ ነው የዐማራው ሥነልቦና በድል ጊዜም ሆነ በጥቃት ላይ እያለ የበላይነቱን  እንደጠበቀ እንዲዘልቅ ያደረገው።
ዛሬ ወያኔን እና መሠል ቡድኖችን ያስጨነቃቸው ይኸው የዐማራው የኢትዮጵያዊነት ሥነልቦና የበላይነት አልሰበር በማለቱ ነው። እኒህን ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሌት ተቀን የሚያባንናቸው ዐማራው ኢትዮጵያዊነትን ማተቡ፣ ዕምነቱ እና የእሱነቱ መገለጫ፤ ሠንደቅ ዓላማውንም ልብሱ፣ ትራሱ እና መጌጫው አድርጎ በዓለም አደባባይ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የሚያሰማው ድምፅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያስገመገመ በመጓዙ ነው።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ይህን መግለጫ ለማውጣት የወሰነው በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን አብዛኛው ሰው የሚያምነው የሚያየውን ብቻ ሣይሆን የሚሰማውንም ጭምር በመሆኑ ነው። እንዲያውም ሰው ከሚያየው ይልቅ የሚሰማውን ይበልጥ አምኖ ይቀበላል። ስለሆነም «ፕሮፌሠር መሥፍን እኮ ዐማራ የሚባል ነገድ የለም ብለዋል» ብሎ የሚቀበለው እና የሚያምነው ሰው ቁጥር ቀላል ስለማይሆን፣ ለዚህ ዓይነቱ አድማጭ ዕውነታውን ማሣወቅ አስፈላጊ ይሆናል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ፥ ምንም እንኳን ጊዜ እየከዳቸው ያሉ ቢሆንም፣ እስትንፋሳቸው እስካለ ድረስ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሌሎች የክህደት ንግግሮችን ከመናገር ስለማይቆጠቡ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «ዐማራ የለም» ሲሉ የካዱትን ክህደት በተጨባጭ መረጃዎች በማሣዬት ለወደፊት አድማጫቸው እና አንባቢያቸው ከሃዲነታቸውን ከወዲሁ እንዲገነዘብ ለማድረግ ነው። ከዚህ አንፃር የዐማራን ነገድ ከኢትዮጵያ ምድር አልፎ በዓለም ዙሪያ ተሠራጭቶ የሚኖር መሆኑን የሚከተሉት መረጃዎች ያረጋግጣሉ። እነርሱም፦
፩ኛ      አካላዊ (ነባራዊነት)፣
፪ኛ      አማርኛ የተሰኘ ቋንቋ በኢትዮጵያ መኖር እና በስፋት መነገር፣ እንዲሁም
፫ኛ      የጽሑፍ፣ የቃል (ድምፅ) እና የምሥል ማስረጃዎች ናቸው።
፩ኛ.    አካላዊ (ነባራዊነት)
አካላዊ ወይም ነባራዊነት ስንል፥ በእጅ የሚዳሰስ፣ በዐይን የሚታይ፣ ግዙፍ፣ ራሱን «ዐማራ ነኝ» ብሎ የሚገልጽ ሰው የተሰኘ ፍጡር በኢትዮጵያ ምድር በስፋት ተሰራጭቶ የሚኖር ሕዝብ ማለታችን ነው። ይህ ሕዝብ ቀደም ሲል ክርስትና ወደ አገራችን ሲገባ ቀድሞ የተቀበለ በመሆኑ ከክርስትና ኃይማኖት ጋር አያይዞ የራሱን ማንነት የሚጠራ፤ ሌሎችም «ዐማራ» ሲሉ «ክርስቲያን የሆነ» ማለታቸው እንደሆነ አድርገው የሚገልጹት፣ በኋላም በጊዜ ሂደት ወደ አገራችን የገቡ ዕምነቶችን ሳይቃወም፣ መቻቻልን መርሑ አድርጎ የተቀበለ እና ከእርሱም ውስጥ የተወሰነው ክፍል የክርስትና ኃይማኖቱን በመተው ሌሎች ዕምነቶችን በመከተል የኖረ፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ነገዶች በቁጥር ከፍተኛውን መጠን የያዘ ማለታችን ነው።
ማንም በግልጽ ሊገነዘበው እንደሚችለው፣ ቋንቋ ከሰው በፊት አልተፈጠረም። ቋንቋ ከሰው ልጅ ኅልውና በኋላ የተከተለ የሰዎች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው። ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይዳብራል፣ ይሞታል የሚባለውም ከሰዎች መኖር ጋር በጥብቅ የተሳሰረ በመሆኑ ነው። በሌላም በኩል ቋንቋ ባህልም ነው። ከጥንት ጀምሮ የቁጥር መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሄደ እና ራሣቸውን «ዐማራ ነኝ» በሚሉ ተወላጆች የጋራ ማንነት የተገነባ ነገድ አለ። እኒህ ሰዎች አፋቸውን በአማርኛ ቋንቋ የፈቱ፣ ካለ አማርኛ ቋንቋ ሌላ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በመሠረቱም የአማርኛ ቋንቋን መግባቢያ እና መገልገያ ያደረገ ሕዝብ ሣይኖር የአማርኛ ቋንቋ ሊኖር አይችልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም ነገዶች እና ጎሣዎች አንድ ተብለው መቆጠር ሲጀምሩ በቅድሚያ በማንም ሰው አዕምሮ ውስጥ ድቅን የሚለው ዐማራ ነው። ስለዚህ በማንነቱ ከኢትዮጵያ ኅልውና ጋር በጥብቅ የተሣሰረ «ዐማራ» የሚባለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ኅልውና መካድ ኢትዮጵያን ከመካድ ተለይቶ አይታይም።
ሌላው አካላዊ ማስረጃ «ዐማራ ሳይንት» የተባለው እና በላኮመልዛ(ወሎ) ክፍለሃገር የሚገኘው የአውራጃ ስም ነው። «ዐማራ» የሚባል ነገድ ሳይኖር፣ በዐማራ ስም የሚጠራ የቦታ ስም ሊኖር አይችልም። በሌላም በኩል ከጥንት ጀምሮ በጌምድርና ስሜን(ጎንደር)፣ ጎጃም፣ ሸዋ እና ላኮመልዛ(ወሎ) የተሰኙ የኢትዮጵያ መልከዐ-ምድር አካል የሆኑ ክፍለ-ሀገሮች አሉ። የነዚህ ክፍለ-ግዛቶች አብዛኛው ነዋሪ ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ «ዐማራ የሚኖርባቸው» ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘመነ ትግሬ-ወያኔ «የዐማራ ክልል» በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ክፍል ኅልውናውን ካስቆጠረ ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሆኗል። ስለዚህ ይህን ሁሉ እንዴት መካድ ይቻላል? ለፕሮፌሠር መሥፍን የክህደት መንገዳቸው ማጠናከሪያ አድርገው የሚያቀርቡት «ስለ ዐማራ አጥንቻለሁ» የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይህ አጥንቻለሁ የሚሉት ጥናት ዕውነት ከሆነ፥ ባለፉት ዘመናት «የዐማራ ገዥ መደብ፣ ጨቋኝ የዐማራ ብሔር፣ ነፍጠኛ ዐማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔር/ብሔረሰቦች ደመኛ ጠላት፣ ወዘተርፈ» እየተባለ ሲወገዝና የመከራ ዓይነቶችን ሲቆጥር ለምን ዝም አሉ? ኢትዮጵያውያን ዐማሮች ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች፥ «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው፤ ከደቡብ፣ ከሐረርጌ፣ ከአርሲ፣ ከባሌ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቡር፣ ከሶማሌ፣ ከቤንሻንጉል-ጉምዝ እንዲሁም ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲባረሩ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «እነዚህ እኮ ዐማራ አይደሉም፣ የሌላ ነገድ አባሎች ናቸው፤» አላሉም? «እንዲያውም ዐማራ የምትሉት ሰው በምድረ-ኢትዮጵያ የለም፤» ብለው ማስተባበል እንዴት ተሣናቸው? እኒህ ሰው የሌሎችን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ኅልው መሆን ሲቀበሉ እንዴት የዐማራ ነገድን ኅልውና ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ ዳዳቸው? ማንን ለማስደሰት ይሆን?
በደርግ የአገዛዝ ዘመን ስለኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች በኢትዮጵያ የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም በተደረጉት የጥናት ውጤቶች መሠረት፣ የዐማራ ነገድ ከኢትዮጵያ ነገዶች አንጋፋው፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ተሠራጭቶ የሚኖር፣ እንዲሁም በቁጥርም ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያሉ።
ሌላው የዐማራን ነገድ ኅልውና የሚያረጋግጠው ደረቅ ማስረጃ በኢትዮጵያ የተደረጉት የሕዝብ ቆጠራ ውጤቶች ናቸው። ለምሣሌም ያህል፦ በ፲፱፻፸፮ (1976) ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ፵፪(አርባ ሁለት) ሚሊዮን ያህል እንደነበረ ይታወቃል። ከጠቅላላው የአገሪቱ ሕዝብ (42 616 876) ውስጥ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት 12 055 250 (አሥራ ሁለት ሚሊዮን ሃምሣ አምሥት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ) ነበር። ይህም ከአጠቃላይ የአሪቱ ሕዝብ 28.288 ከመቶ እንደነበረ ያሣያል። በሥርጭት ረገድም፥ በሸዋ 23.1 በመቶ፣ በአዲስ አበባ 47.86 በመቶ፣ በወሎ 79.86 በመቶ፣ በጎንደር 84.83 በመቶ፣ በጎጃም 87.58 በመቶ፣ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ነበሩ፣ በግለሰብ ደረጃም ሰዎች ማንነታቸውን «ዐማራ ነን» ብለው ማረጋገጣቸው በውል ታይቷል። ዐማራው በሌሎች የአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮችም በበቂ መጠን ተሰራጭቶ እንደሚገኝ የቆጠራው ውጤት አሣይቷል። በዚህም መሠረት በሐረርጌ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በወለጋ፣ በጋሞጎፋ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በአሰብ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንደነበረ መረጃው ያስረዳል። በዚያ የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኦሮሞን ቁጥር ከፍ፣ የዐማራን ቁጥር ግን ዝቅ ለማድረግ ሆን ተብሎ የቁጥሮች ጨዋታ የተሠራ መሆኑ ቢታወቅም፣ ዐማራው በቁጥር በአገሪቱ ከሚገኙ ነገዶች እና ጎሣዎች በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን  ያረጋግጣል (ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን፣ ታኅሣሥ ፲፱፻፹፫ (1983) ዓ.ም.)።
በሁለተኛ ደረጃ በ፲፱፻፹፯(1987) ዓ.ም. በተደረገ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 53 499 248 መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ 13 834 297 ያህሉ ዐማሮች መሆናቸውን ያሣያል። በንፅፅር ሲታይ በትግሬ-ወያኔ ዘመን በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት በ፲(አሥር) ዓመታት ውስጥ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ቁጥር የጨመረው በ1,779,047 ብቻ ነው። ይህም የቆጠራው ውጤት የወያኔን ዐማራን የማጥፋት የፖለቲካ ዓላማ በጉልህ የሚያሣይ ነው። ሆኖም የዐማራ ነገድ በቁጥሩ ብቻ ሣይሆን በሥርጭትም ጭምር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በብዛት የሚገኝ መሆኑን የቆጠራው ውጤት አላስተባበለም። በመሆኑም ወያኔ «የዐማራ ክልል» ብሎ በከለለው ውስጥ ከሚኖረው 13 834 297 ሕዝብ መካከል ዐማራው 81.5 ከመቶ መሆኑን፣ በ«ትግራይ ክልል» ከሚኖረው 3 136 267 ሕዝብ መካከል የዐማራው ነገድ 2.6 ከመቶ በመያዝ በክልሉ በሕዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ታውቋል። በ«ኦሮሚያ ክልል» ከሚኖረው 18 732 525 ሕዝብ መካከል 9.1 ከመቶ የሚሆነው የዐማራ ነገድ መሆኑን እና ይህም በ«ክልሉ» ከሚኖሩት ነገዶች መካከል ከኦሮሞው ቀጥሎ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያል። አርባ አምሥት(፵፭) ነገዶች እና ጎሣዎችን ባጠቃለለው የ«ደቡብ ክልል» ዐማራው በቁጥር በስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚህ «ክልል» 10 377 028 ሕዝብ እንደሚኖር ቆጠራው አሳይቷል። ወያኔ «ሐረሪ» ብሎ የመንግሥትነት ዕውቂያ ከሰጣቸው ክልሎች አንዱ የሆነው የሕዝቡ ቁጥር 131 139 ነው። ከዚህ የ«ሐረሪ ክልል» ነዋሪ ሕዝብ መካከል 52.3 ከመቶው ኦሮሞ ሲሆን፣ 32.6 ከመቶው ዐማራ ነው። ሐረሪዎቹ 7.1 ከመቶ ብቻ ናቸው። እንግዲህ ለእነዚህ አናሣ ቁጥር ለያዙት ነው የአብዛኛውን የኦሮሞ እና የዐማራ ነገዶች ተወላጆች ዕጣ ፋንታ እንዲወስኑ ወያኔ የመንግሥትነት መብት የሰጣቸው። ይህንንም «ዲሞክራሲ ነው» እያሉን ነው። በሶማሌ ክልል 3 439 860 ሕዝብ እንደሚኖር በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. የተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ያመለክታል። ከዚህ መካከል በዚያ ክልል ዐማራው 0.69 ከመቶ በመያዝ በሦስተኛነት ደረጃ ላይ ይገኛል። ለሁሉም ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት እንዲቻል የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንመልከት።
በ፲፱፻፹፯(1987) እና በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. በተደረጉት የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ውጤቶች *መሠረት የክልሎችና የአስተዳደሮች ሕዝብ የብሔር /ብሔረሰብ ሥርጭት እና ብዛት
ክልል ወይም አስተዳደርየክልሉ ሕዝብ ብዛትከአገሪቱ ሕዝብ (በመቶኛ)በክልሉ የሚኖሩ ብሔር/ብሔረሰቦችየየብሔረሰቡ ብዛትከክልሉ ሕዝብ (በመቶኛ)መግለጫ
ትግራይ3 136 2675.6ትግሬ2 971 73894.75ከ10 ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው
ዐማራ81 2972.59
ሣሆ/ ኢሮብ22 8580.73
አፋር1 060 5731.99አፋር968 01891.27ከ2 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ዐማራ46 5344.39
አርጎባ9 6730.91
ትግሬ8 4600.8
ኦሮሞ8 0550.76
ዐማራ13 834 29725.91ዐማራ12 615 16091.19ከ20ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
አገው417 3733.02
ኦሮሞ416 8833.01
ቅማንት172 2911.23
ትግሬ44 6090.32
አርጎባ37 6260.27
ኦሮሞ18 732 52535.1ኦሮሞ15,709 47483.86ከ50 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ዐማራ1 684 1288.99
ጉራጌ246 8951.32
ጌዲኦ180 2150.96
ሶማሌ107 8110.56
የም103 8230.55
ትግሪ-ወርጂ67 4560.36
ኩሎ674890.36
ሶማሌ3 198 5145.99ሶማሌ3 011 45394.15ከ3 ሺ በላይ ሕዝብ የያላቸው
ኦሮሞ70 5062.21
ዐማራ20 9510.66
ጉራጌ4 0850.13
ቤንሻንጉል ጉምዝ464 5900.86ጀብላዊ115 60225.12ከ10 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ጉምዝ107 49523.35
ዐማራ102 06122.17
ኦሮሞ58 83312.78
ሽናሻ32 1056.97
አገው17 9283.89
ደቡብ ብሔር/ ብሔረሰቦች10 377 02819.43ሲዳማ1 820 03017.539ከ50 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ጉራጌ1 646 92515.871
ወላይታ1 210 23511.662
ሐዲያ874 4688.427
ጋሞ679 5406.549
ከፊቾ521 2235.023
ጌዴኦ549 3514.423
ከምባታ459 3514.423
ዐማራ443 5254.274
ኩሎ312 9292.631
ጎፋ273 0892.320
ኦሮሞ240 7491.986
ቤንች206 2441.663
ኦሪ17 ,6111’488
ኮንሶ154 3811.362
አላባ141 3751.132
ኮይራ117 4491.014
ጠምባሮ105 2440.818
የም84 9180.586
ጋምቤላ181 8620.39ኑዌር

በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!

ኢትዮጵያዊያንን በዘር እና በሀይማኖት ለያይቶን እርስ በርስ እያጋጨን በመግዛት ላይ ያለውን ወያኔን ለማሸነፍ እና ከምትኩም ከራሷ ጋር የታረቀች፤ ፍትህ የሰፈነባት፤ እኩልነት የተረጋገጠባት እና በኃያላን አገሮች እርጥባን ሳይሆን በራሷ አቅም የምትተማመን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎት መተባበር እንዳለባቸው ሲነገርና ሲወተወት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በህወሓት የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ እና በፓለቲካ ባህላችን ኋላቀርነት ምክንያት እስካሁን የተደረጉ የትብብር ጥረቶች የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ቀድሞ የተደረጉት ጥረቶች የተጠበቀውን ውጤት አለማስገኘት ተስፋ ሳያቆርጠን ከእያንዳንዱ ጥረት ልምድ እየወሰደን የኢትዮጵያዊያን አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ የትብብር ጥረቶችን ማድረግ ያለብን መሆኑ ያምናል። በዚህም መሠረት የትብብር መርህ ነድፎ ትግል ውስጥ ካሉ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲነጋገር እና ሲደራደር ቆይቷል። እንደሚታወቀው የንቅናቄዓችን አበይት የትብብር መርሆች ሁለት ናቸው። መርህ አንድ፣ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገለው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ መሆኑ ማመን ነው። መርህ ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የሚገባው በሕዝብ ነፃ ምርጫ ብቻ መሆኑን መቀበል ናቸው።
በምድር ላይ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ኃይሎች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ሁለቱንም መርሆዎች የሚያሟሉ ናቸው። እነዚህ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ከንቅናቄዓችን የተለየ አቋም የላቸውም። በአለፉት ሁለት ዓመታት ድርጅቶቹ ተቀራርበው እንዲሠሩ በመደረጉ ከአመራር አልፎ አባላት መካከል መልካም ወዳጅነት መመሥረት ተችሏል። የነፃነት ትግላችን የደረሰበት ደረጃ እና የድርጅቶቹም ቅርርብ በመገምገም ሶስቱ ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ መዋሃዳቸው ትግሉን ያራምዳል ተብሎ ታምኖበታል። በዚህም መሠረት ሶስቱ ድርጅቶች ለመዋሃድ ተስማምተን ስምምነታቸንን ይፋ አድርገናል። ድርጅቶቹን የማዋሃድ ዝርዝር ሥራም ተጀምሯል።
ከስትራቴጄ አንፃር የትብብር ጥረታችን በዚህ አያበቃም። በዓላማ የምንቀራረብ ሆኖ የአደረጃጀት ልዩነት ያለን የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጥምረት እየሠራን ድርጅቶቻችን ይበልጥ ለማቀራረብ ጥረት እያደረግን ነው። በዚህ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ነው። ንቅናቄዓችን ከትህዴን ጋር ከፍተኛ በሆነ መቀራረብና መተማመን ይሠራል። ይህ መቀራረብና መተማመን ጎልብቶ አንድ የጋራ አመራር የሚፈጥርበት ጊዜ እንዲቀርብ ጥረት እናደርጋለን። ምድር ላይ ከሚገኙ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋርም በመደጋገፍ እንሠራለን። በመጨረሻም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ካሉ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር ለመወያየት ዝግጁዎች መሆናችንን ደግመን እናረጋግጣለን። ልዩነቶቻችን ማጥበብ እንኳን ባንችል የምንተባበርባቸው መንገዶች ይኖራሉ ብለን እናምናለን።
የጦር ኃይሉንና የስለላ መዋቅሩን ዘረኛ በሆነ መንገድ የገባውንና የኢትዮጵያን ሀብት በመዝረፍ የደረጀው ህወሓትን ለማሸነፍ ትብብር ወሳኝ ጉዳይ ነው። ከወያኔ አገዛዝ ውድቀት በኋላ ወደ ተረጋጋ ሰላምና ልማት ፊታችንን የምናዞር መሆናችን ዋስትና የሚሰጠን በአንድ እዝ የሚመራ የአገር አድን ሠራዊት ማደራጀት ስንችል ነው። የአሁኑ ውህደት የዚህ አገር አገር አድን ሠራዊት ጥንስስ ሊሆን ይችላል ብለን እናምናለን።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ በኋላ የሚመጣው ምን እንደሆነ ባለማወቅ ሥጋት ውስጥ ሊገባ አይገባም። በዋና ዋና የአገሪቱ የፓለቲካ ድርጅቶች ውህደት እና ቅንጅት የተዋቀረ በአንድ ማዕከላዊ አመራር ሥር የሆነ አገር አድን ሠራዊት በተቻለ ፍጥነት ሊገነባ ይገባል።
ሶስቱ ድርጅቶች ለማድረግ በወሰነው ውህደት የዚህ የአገር አድን ሠራዊት ምሥረታን ጀምረናል። ስለኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ላለ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ደህንነት ያገባናል የምትሉ ወገኖቻችን ሁሉ በዚህ አገር አድን ሠራዊት ምሥረታ ላይ እንድንነጋገር አበክረን እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ሕዝብም የትብብሩ መንፈስ አገርን የማዳን ግብ ያለመ መሆኑን በመገንዘብ ከተባበረው ድርጅት ጎን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን። የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጉዳይ የሚያገባው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀለንና እንዲያግዘን ጥሪዓችንን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ምን ያህል እንዳከረረ (ክፍል 1) – ግርማ ካሳ

የ «ጌታቸውን » የአቶ መለስን ራእይ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በትጋት እየፈጸሙት እንደሆነ በስፋት እያየን ነው። የአቶ መለስ ራእይ ጭቆና፣ አምባገነንነት፣ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር፣ ሜዲያዉን መጨፍለቅ ነው። የአቶ መለስ ራእይ በእርቅና በፍቅር አገርን ማሳደግ ሳይሆን፣ ማክረር በዜጎችን ላይ መጨከን ነው።

cartoon_691የፍቅርና የሰላም መጽሀፍን (መጽሐፍ ቅዱስን) በየቀኑ አነባለሁ በሚሉት በአቶ ኃይለማሪያም አገዛዝ ግን፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በመለስ ጊዜ ከነበረው በባሰ ሁኔታ በጣም እያከረረ መጥቷል። በርግጥም አቶ ኀያለማሪያም የአቶ መለስስ ፎቶ እየተሳለሙ ቃል እንደገቡት፣ የአቶ መለስን ራእይ በትጋት እያስፈጸሙ ናቸው።
ምን ያህል አገዛዙ እንዳከረረ የሚያሳይ አንድ ጉልህ ማስረጃ፣ በተለይም በሜዴያዉ አንጻር እንዳቀርብ ይፈቀድለኝ። በምንም አይነት ሕወሃት/ኢሕአዴግ እንዲነገርና እንዲጻፍ ከሚፈለገው ውጭ መጻፍ እንደማይቻል እያየን ነው። ኢቲቪ የመሳሰሉቱ ደግሞ እንደ ሰዉ ለሰው ድራማ ያሉትን ከማየት ዉጭ፣ አስቀያሚ ሜዲያዎች ሆነዋል። በጣም አስቀያሚ !!!!! እነ ሪፖርተር፣ አዲስ ፎርቹን የመሳሰሉቱ፣ የአገዛዙ ቱጃሮች ማስታወቂያ የሚያወጡበት፣ በአገዛዙ እየተደገፉ የሚንቀሳቀሱ፣ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ኮድን የማይተገብሩ፣ በአጋር ጋዜጠኖች ላይ የሚደርሰው ግፍ የማይሰማቸውና የማይቆረቆሩ፣ ለይስሙላ የሜዱያ ነጻነት አለ ለማስባል ለአገዛዙ የፖለቲካ ፍጆታ የሚዉሉ፣ በአደርባይነት የተሞሉ ፣ ጋዜጠኖች ሊባሉ የማይገባ ጋዜጦች ናቸው።
በአቶ መለስ ጊዜ የታሰሩ ጋዜጠኖች
1. ርዮት አለሙ (የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ)
2. እስክንደር ነጋ
ከ2002 ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ጊዜ የተሰደዱ ጋዜጠኖች
1. አብይ ተከለማሪያም ( አዲስ ነገር)
2. መስፍን ነጋሽ (አዲስ ነገር)
3. ታምራት ነገራ (አዲስ ነገር)
4. አቤ ቶኪቻው (አዉራምባ ታይምስ)
5. ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ተሰዶ ነበር ፣ አሁን ሰላም ነው ብሎ ተመልሷል
ከ2002 ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ጊዜ እንዳይታተሙ ወይም ክስ የተመሰረተባቸው ጋዜጦች
1. አዲስ ነገር
በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ወደ ወህኒ የተወሰዱ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች (ሁሉም በሽብተኘት የተከሰሱ)
1. ተስፋለም ወልደየስ
2. አጥናፉ ብርሃኔ
3. ዘላለም ክብረት
4. ኤዶም ካሳዬ
5. ናትናኤል ፈለቀ
6. ማህሌት ፋንታሁን
7. አቤል ዋበላ
8. በፍቃዱ ኃይሉ
9. አስማማዉ ወልደጊዮርጊስ
በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኖችና ብሎገሮች
1. ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ( የሎሚ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
2. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
3. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር)
4. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ (የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ)
5. ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)
6. ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)
7. ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
8. አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሮዝ አሳታሚ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ )
9. አቶ ኢብራሃም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ)
10. እንዳለ ተሺና (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ )
11. ሀብታሙ ሥዩም (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ዓምደኛ)
12. ዳዊት ሰለሞን (ታዋቂ ብሎገር)
13. ዘሪሁን ሙሉጌታ ( የሰንደቅ ጋዜጣ ረፖርተር)
በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ሕተመታቸው የተቋረጠ ወይንም ክስ የቀረበባቸው
1. ፍትህ ጋዜጣ
2. ፍኖት ነጻኘት ጋዜጣ
3. የአዲስ ጉዳይ መጽሔት
4. የፋክት መጽሄት
5. የሎሚ መጽሄት
6. የጃኖ መጽሄት
7. የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ