Netsanet: የስብሃት ነጋ እህት ቅዱሳን ነጋ “ቀጭን” ትእዛዝ፦

Donnerstag, 14. August 2014

የስብሃት ነጋ እህት ቅዱሳን ነጋ “ቀጭን” ትእዛዝ፦


የስብሃት ነጋ እህት ቅዱሳን ነጋ ይባላሉ። የቅዱሳን ባል ደግሞ ፀጋይ በርሄ ሲሆኑ ሃለቃ ፀጋይ የፌዴራል ደህንነት ዋና ሹም ናቸው። የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የሆኑት ቅዱሳን ነጋ ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ውጭ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ነበር። የእጅ ስልካቸውን በማንሳት ስልክ ይመታሉ፤ የደወሉት በወቅቱ የኢ.ቲቪና ራዲዮ ስራ አስኪያጅ ለነበረው ዘርአይ ነበር። ቅዱሳን እንዲህ አሉ፥ « በትላንትናው ዕለት በትግርኛ ቲቪ ፕሮግራም ላይ የቀረበውን ዝግጅት ያሰናዳው ጋዜጠኛ በአስቸኳይ ከባድ ቅጣት እንድትጥልበት። አሁን ወደ ውጭ እየሄድኩ ነው፤ ስመለስ ያልኩህን እርምጃ ወስደህ ካልጠበቅከኝ.. ቅጣቱ ወደአንተ ይዞራል» ሲሉ ያንባርቁበታል። ዘርአይም « እሺ የተባለውን እፈፅማለሁ» ሲል መለሰ። ጋዜጠኛው ትግራይ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ ችግር በማቅረቡ ነበር በቅዱሳን የቅጣት ትእዛዝ የተላለፈበት። አሁን ከስልጣን የተነሳው የአቶ መለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ ካድሬው ዘርአይ ጊዜ ጠብቆ በስልክ የተላለፈችውን የቅዱሳን “ትዕዛዝ” በስልኩ ድምጿን ቀርፆት ኖሮ በቅርቡ ለሚቀርባቸው የፓርቲው ሰዎች ሲያስደምጥ እንደነበረ ማወቅ ተችሏል። ..መብት፣ ነፃነት፣ ህግና ህገ መንግስት..ወዘተ ቦታ የላቸውም። ወረቀት ላይ የሰፈሩ – ነገር ግን በተግባር የሌሉ ናቸው። ጋዜጠኞች የሚታሰሩት፣ ሌሎች ወገኖች የሚደበደቡትና የሚንገላቱት እንዲህ በስልክ ባለስልጣናት በሚሰጡት “ቀጭን” ትእዛዝ ነው። አይ አገሬ!…
እየሩሳሌም አርአያ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen