#DW
እሥራኤልና የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ተስማምተዉበታል የተባለዉ ተኩስ አቁም ታዉጆ ሳያበቃ ተኩሱ ቀጥሏል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ሁለቱ ወገኖች ለጋዛ ሕዝብ ሠብአዊ ርዳታ እንዲደርስ ለሰባ-ሁለት ሰዓታት ተኩስ ለማቆም ተስማምተዉ ነበር።ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን በቃል አቀባያቸዉ በኩል ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ተኩስ አቁሙ ለተጨማሪ ድርድር በር ይከፍታል የሚል ተስፋም ነበር።

«ይሕ ለሠብአዊ ርዳታ ሲባል የተደረገዉ ተኩስ አቁም በሐገሬዉ አቆጣጠር አርብ ነሐሴ 1 2014 ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስካልተራዘመ ድረስ ለ72 ሠዓታት የሚቆይ ነዉ።በዚሕ ጊዜ ዉስጥ ተዋጊዎች በያሉበት ይቆያሉ።የእስራኤልና የፍልስጤም መልዕክተኞች በግብፅ መንግሥት ጋባዥነት ዘላቂ ተኩስ አቁም ለማድረግ ለድርድር ባስቸኳይ ወደ ካይሮ ይጓዛሉ።በዚሕ ድርድር የሚካፈሉት ወገኖች ሁሉንም ጉዳይ ያነሳሉ።»
የዓለም አቀፉ ድርጅት መገለጫ ተሠራጭቶ ሳያበቃ ተኩስ አቁሙ ተጥሶ ጋዛ እንደመሰንበቻዉ መንደድ ይዛለች።ለተኩስ አቁሙ መጣስ እሥራኤልና የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች አንዳቸዉ ሌላቸዉን እያወገዙ ነዉ። የእስራኤል ጦር ራፋሕ በተባለችዉ ከተማ አጠገብ በፈፀመዉ ድብደባ ብቻ ሐምሳ ሰዎችን ገድሏል።ከሁለት መቶ በላይ አቁስሏል።የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ደግሞ ሁለት የእስራኤል ወታደሮች ገድለዋል፤ አንድ ማርከዋል።የእስራኤል ጦር ጋዛን መደብደብ ከጀመረበት ካለፈዉ ሐምሌ አንድ ጀምሮ የገደላቸዉ ፍልስጤማዉያን ቁጥር 1500 ደርሷል።አብዛኞቹ ሠላማዊ ሰዎች ናቸዉ።የፍልስ ጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ስልሳ-ስድስት እስራኤላዉያን ገድለዋል።ሠላማዊ ሰዎቹ ሰወስት ብቻ ናቸዉ።

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen