ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት እሑድ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ቅፅ ፪ ፣ ቁጥር ፳፯
ሰሞኑን ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም «ሸገር» ከተሰኘ በኤፍ.ኤም. 102.1 (FM 102.1) ከአዲስ አበባ መርኃግብሩን ከሚያሠራጭ የሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ «ዐማራ» የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ አለመኖሩን ልባቸውን ነፍተው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ፕሮፌሠር መሥፍን በዚህ ቃላቸው፣ በ፲፱፹፫(1983)ዓ.ም. ከሟቹ የትግሬ-ወያኔዎች መሪ መለስ ዜናዊ ጋር በቴሌቪዥን ቀርበው ስለ ዐማራው ነገድ ያለመኖር ያንጸባrmቁትን አቋም አፅንዖት በመስጠት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ዐማራ የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ ውስጥ «አለ» ወይስ «የለም» ብሎ፣ በላ! ልበልሃ! ወደሚል እጅግ የወረደ ክርክር የሚገባ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት ክርክር ውስጥ የሚገባ ሰው፣ ኃሣቡ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የማይችል የፕሮፌሠር መሥፍን ዓይነቱ ሰው ብቻ ነው። ለነገሩ በዚህ የቀን ቅዠት አቋም የሚፀና ካለ ከፕሮፌሠር መሥፍን ሌላ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ይገኛል ተብሎ አይታሰብም። የፕሮፌሠር መሥፍንም ክርክር ጭፍን ክህደት ወይም መሣት (መጃጀት) አልያም ቀቢፀ-ተስፋ የተሞላው ቁጭት ከመሆን አያልፍም። የፕሮፌሠር መሥፍን አቋም የክህደት ከሆነ፣ ወላጅ አባታቸውን ዕውቁን ሊቅ አለቃ አስረስ የኔሰውን ክደዋልና የዐማራ ነገድን ኅልውና ከመካድ የሚያግዳቸው የኅሊና ልጓም ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ከመሣት(መጃጀት) የመነጨ ከሆነ ግን አያድርስ! እንዲህ እስኪሆንስ ፈጣሪን «አታቆዬን» ከማለት ሌላ ምን ይባላል። ከቁጭት ከሆነ ነገሩ ሌላ ነው። በቁጭት የአንድን ታላቅ ሕዝብ መኖር ኅልውና ክዶ ስለዚያ ሕዝብ መከራከር እና መጮህ አይቻልም። የቁጭት ተገቢ መገለጫው «አሻፈረኝ! በቃኝ! ተነስ! ዱሩ ቤቴ በል!» በማለት እንጂ «የለህም! የሚያጠፉህ ሳትኖር ነው!» በማለት አይደለም። የሌለ፣ ኅልው ያልሆነ፣ ሊያደርገው የሚችለው ምንም ነገር የለምና!
ፕሮፌሰር መሥፍን «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» ከሚል መደምደሚያ የደረሱት፣ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ከሦሥቱ በአንዱ ወይም በሁሉም ተያያዥነት እንደሆነ ቀደም ካሉት ድርጊቶቻቸው መገንዘብ ይቻላል። የመጀመሪያው በ፲፱፹፫(1983) ዓ.ም. ከሟቹ መለስ ዜናዊ ጋር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባደረጉት ውይይት ዐማራን እና ክርስቲያንን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን በመዘንጋት፣ ወይም ሆን ብለው «ክርስቲያን እንጂ፣ ዐማራ የሚባል የለም» ብለው ተከራክረው ስለነበር ያ አቋማቸው ያልተለወጠ መሆኑን እና ዛሬም «በዚያው አቋማቸው የጸኑ ናቸው» ለመባል ከማሰብ የመነጨ፣ ከስህተት ወደ ስህተት የመጓዝ አስተሳሰብ ነው። ሁለተኛው ፕሮፌሠር መሥፍን ክህደት የመታወቂያ ባሕሪያቸው ስለሆነ ትናንት የካዱትን ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላም በክህደቱ የቀጠሉ መሆኑ የሚያመለክት ነው። ይህም ሌላው ግትርና «ያለ እኔ ዐዋቂ የለም» የሚለው የገነገነ አስተሳሰባቸው መገለጫ ነው። ሦስተኛው ከክህደት ባሕሪይ በተጨማሪ በዕድሜ መግፋት ምክንያት የመጣ፣ የኋላን ያለማዬት እና የመሣት አባዜ የገጠማቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። አራተኛው በዘመነ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በዐማራው ላይ በተከታታይ እየተፈጸመበት ያለው መገደል፣ መታሠር፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ከአገር መባረር፣ መዋረድ እና መጎሳቆል እጅግ በዝቶ የግፉ ጽዋ ሞልቶ የሚፈስበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሆኖም ዐማራው «አሻፈረኝ» ብሎ ወያኔን ግብግብ ከመግጠም ይልቅ የሚሣየውን ሆደ ሠፊነት ከኢዮብ ትዕግሥት በላይ ሆኖ ስላገኙት፥ «ዐማራ የሚባል ነገድ ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ ጥቃት እና ውርደት ሲፈጸምበት ዝም ብሎ አይመለከትም ነበር! ሌሎቹ እንደሚያደርጉት ኃይሉን አስተባብሮ ጥቃቱን ይቋቋም ነበር! ባለመኖሩ ነው ይኸ ሁሉ ጥፋት የሚፈጸምበት» ከሚል ቁጭት የደረሱበት ድምዳሜ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል።
ይህ ግን ከዐማራው ባህል፣ ዕምነት፣ አኗኗር፤ ማኅበራዊ ግንኙነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ጋር አጣምሮ ለሚያይ ሰው፣ ዐማራው በወያኔ የደረሰበትን ሁለንተናዊ ግፍ እና በደል በአርምሞ በመመልከት ላይ ያለው፣ በደሉ ሳይሰማው ቀርቶ አይደለም። እንዲያውም «የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች» እንዳይሆንበት የትግሬ-ወያኔዎችን ግፍ ለመበቀል ሲል በደልን በበደል መመለስ፣ የትልቂቱን አገሩን የኢትዮጵያን ኅልውና እንዳያፈርስ ኅሊናውን ገዝቶት፣ በሆደ ሠፊነት እና በትዕግሥት ማየቱ፥ ብልኅነቱን፣ አስተዋይነቱን፣ «አድሮ እንየው» ማለቱን፣ ውሽንፍርን እና ጥምዝምዝን አጎንብሶ ማሳለፍ ባህሉ መሆኑን፣ እንጂ፤ ጥቃትን እስከ ዝንተ ዓለሙ የሚቀበል አለመሆኑ ታሪኩ ያስረዳል። «ዐማራ ሰንበሌጥ ነው፤» የሚባለውም እኮ ለዚህ ነው። ማንም እንደሚያውቀው ሰንበሌጥ ኃይለኛ ወዠብ (ነፋስ) ሲመጣበት ለጥ ብሎ ያሳልፋል፣ ወዠቡ ሲያልፍ ይነሣል። ዐማራውም በተደጋጋሚ እና በተከታታይ ሊያጠፉት የተሰለፉትን ኃይሎች ሁሉ ተቋቁሞ እስካሁን የዘለቀው በዚህ መንገድ ነው። ጠላቶቹን የሚያሸንፋቸው በመበቀል ሣይሆን በይቅርታ እና በፍቅር መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አያስፈልግም። የኢትዮጵያዊነት ማገር፣ ዋልታ እና ጭምጭም ሆኖ ለዘመናት የዘለቀውም የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት ስሜቱ የዳበረ በመሆኑ ነው። ይህም በመሆኑ ነው የዐማራው ሥነልቦና በድል ጊዜም ሆነ በጥቃት ላይ እያለ የበላይነቱን እንደጠበቀ እንዲዘልቅ ያደረገው።
ዛሬ ወያኔን እና መሠል ቡድኖችን ያስጨነቃቸው ይኸው የዐማራው የኢትዮጵያዊነት ሥነልቦና የበላይነት አልሰበር በማለቱ ነው። እኒህን ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሌት ተቀን የሚያባንናቸው ዐማራው ኢትዮጵያዊነትን ማተቡ፣ ዕምነቱ እና የእሱነቱ መገለጫ፤ ሠንደቅ ዓላማውንም ልብሱ፣ ትራሱ እና መጌጫው አድርጎ በዓለም አደባባይ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የሚያሰማው ድምፅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያስገመገመ በመጓዙ ነው።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ይህን መግለጫ ለማውጣት የወሰነው በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን አብዛኛው ሰው የሚያምነው የሚያየውን ብቻ ሣይሆን የሚሰማውንም ጭምር በመሆኑ ነው። እንዲያውም ሰው ከሚያየው ይልቅ የሚሰማውን ይበልጥ አምኖ ይቀበላል። ስለሆነም «ፕሮፌሠር መሥፍን እኮ ዐማራ የሚባል ነገድ የለም ብለዋል» ብሎ የሚቀበለው እና የሚያምነው ሰው ቁጥር ቀላል ስለማይሆን፣ ለዚህ ዓይነቱ አድማጭ ዕውነታውን ማሣወቅ አስፈላጊ ይሆናል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ፥ ምንም እንኳን ጊዜ እየከዳቸው ያሉ ቢሆንም፣ እስትንፋሳቸው እስካለ ድረስ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሌሎች የክህደት ንግግሮችን ከመናገር ስለማይቆጠቡ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «ዐማራ የለም» ሲሉ የካዱትን ክህደት በተጨባጭ መረጃዎች በማሣዬት ለወደፊት አድማጫቸው እና አንባቢያቸው ከሃዲነታቸውን ከወዲሁ እንዲገነዘብ ለማድረግ ነው። ከዚህ አንፃር የዐማራን ነገድ ከኢትዮጵያ ምድር አልፎ በዓለም ዙሪያ ተሠራጭቶ የሚኖር መሆኑን የሚከተሉት መረጃዎች ያረጋግጣሉ። እነርሱም፦
፩ኛ አካላዊ (ነባራዊነት)፣
፪ኛ አማርኛ የተሰኘ ቋንቋ በኢትዮጵያ መኖር እና በስፋት መነገር፣ እንዲሁም
፫ኛ የጽሑፍ፣ የቃል (ድምፅ) እና የምሥል ማስረጃዎች ናቸው።
፩ኛ. አካላዊ (ነባራዊነት)
አካላዊ ወይም ነባራዊነት ስንል፥ በእጅ የሚዳሰስ፣ በዐይን የሚታይ፣ ግዙፍ፣ ራሱን «ዐማራ ነኝ» ብሎ የሚገልጽ ሰው የተሰኘ ፍጡር በኢትዮጵያ ምድር በስፋት ተሰራጭቶ የሚኖር ሕዝብ ማለታችን ነው። ይህ ሕዝብ ቀደም ሲል ክርስትና ወደ አገራችን ሲገባ ቀድሞ የተቀበለ በመሆኑ ከክርስትና ኃይማኖት ጋር አያይዞ የራሱን ማንነት የሚጠራ፤ ሌሎችም «ዐማራ» ሲሉ «ክርስቲያን የሆነ» ማለታቸው እንደሆነ አድርገው የሚገልጹት፣ በኋላም በጊዜ ሂደት ወደ አገራችን የገቡ ዕምነቶችን ሳይቃወም፣ መቻቻልን መርሑ አድርጎ የተቀበለ እና ከእርሱም ውስጥ የተወሰነው ክፍል የክርስትና ኃይማኖቱን በመተው ሌሎች ዕምነቶችን በመከተል የኖረ፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ነገዶች በቁጥር ከፍተኛውን መጠን የያዘ ማለታችን ነው።
ማንም በግልጽ ሊገነዘበው እንደሚችለው፣ ቋንቋ ከሰው በፊት አልተፈጠረም። ቋንቋ ከሰው ልጅ ኅልውና በኋላ የተከተለ የሰዎች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው። ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይዳብራል፣ ይሞታል የሚባለውም ከሰዎች መኖር ጋር በጥብቅ የተሳሰረ በመሆኑ ነው። በሌላም በኩል ቋንቋ ባህልም ነው። ከጥንት ጀምሮ የቁጥር መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሄደ እና ራሣቸውን «ዐማራ ነኝ» በሚሉ ተወላጆች የጋራ ማንነት የተገነባ ነገድ አለ። እኒህ ሰዎች አፋቸውን በአማርኛ ቋንቋ የፈቱ፣ ካለ አማርኛ ቋንቋ ሌላ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በመሠረቱም የአማርኛ ቋንቋን መግባቢያ እና መገልገያ ያደረገ ሕዝብ ሣይኖር የአማርኛ ቋንቋ ሊኖር አይችልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም ነገዶች እና ጎሣዎች አንድ ተብለው መቆጠር ሲጀምሩ በቅድሚያ በማንም ሰው አዕምሮ ውስጥ ድቅን የሚለው ዐማራ ነው። ስለዚህ በማንነቱ ከኢትዮጵያ ኅልውና ጋር በጥብቅ የተሣሰረ «ዐማራ» የሚባለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ኅልውና መካድ ኢትዮጵያን ከመካድ ተለይቶ አይታይም።
ሌላው አካላዊ ማስረጃ «ዐማራ ሳይንት» የተባለው እና በላኮመልዛ(ወሎ) ክፍለሃገር የሚገኘው የአውራጃ ስም ነው። «ዐማራ» የሚባል ነገድ ሳይኖር፣ በዐማራ ስም የሚጠራ የቦታ ስም ሊኖር አይችልም። በሌላም በኩል ከጥንት ጀምሮ በጌምድርና ስሜን(ጎንደር)፣ ጎጃም፣ ሸዋ እና ላኮመልዛ(ወሎ) የተሰኙ የኢትዮጵያ መልከዐ-ምድር አካል የሆኑ ክፍለ-ሀገሮች አሉ። የነዚህ ክፍለ-ግዛቶች አብዛኛው ነዋሪ ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ «ዐማራ የሚኖርባቸው» ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘመነ ትግሬ-ወያኔ «የዐማራ ክልል» በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ክፍል ኅልውናውን ካስቆጠረ ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሆኗል። ስለዚህ ይህን ሁሉ እንዴት መካድ ይቻላል? ለፕሮፌሠር መሥፍን የክህደት መንገዳቸው ማጠናከሪያ አድርገው የሚያቀርቡት «ስለ ዐማራ አጥንቻለሁ» የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይህ አጥንቻለሁ የሚሉት ጥናት ዕውነት ከሆነ፥ ባለፉት ዘመናት «የዐማራ ገዥ መደብ፣ ጨቋኝ የዐማራ ብሔር፣ ነፍጠኛ ዐማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔር/ብሔረሰቦች ደመኛ ጠላት፣ ወዘተርፈ» እየተባለ ሲወገዝና የመከራ ዓይነቶችን ሲቆጥር ለምን ዝም አሉ? ኢትዮጵያውያን ዐማሮች ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች፥ «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው፤ ከደቡብ፣ ከሐረርጌ፣ ከአርሲ፣ ከባሌ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቡር፣ ከሶማሌ፣ ከቤንሻንጉል-ጉምዝ እንዲሁም ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲባረሩ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «እነዚህ እኮ ዐማራ አይደሉም፣ የሌላ ነገድ አባሎች ናቸው፤» አላሉም? «እንዲያውም ዐማራ የምትሉት ሰው በምድረ-ኢትዮጵያ የለም፤» ብለው ማስተባበል እንዴት ተሣናቸው? እኒህ ሰው የሌሎችን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ኅልው መሆን ሲቀበሉ እንዴት የዐማራ ነገድን ኅልውና ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ ዳዳቸው? ማንን ለማስደሰት ይሆን?
በደርግ የአገዛዝ ዘመን ስለኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች በኢትዮጵያ የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም በተደረጉት የጥናት ውጤቶች መሠረት፣ የዐማራ ነገድ ከኢትዮጵያ ነገዶች አንጋፋው፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ተሠራጭቶ የሚኖር፣ እንዲሁም በቁጥርም ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያሉ።
ሌላው የዐማራን ነገድ ኅልውና የሚያረጋግጠው ደረቅ ማስረጃ በኢትዮጵያ የተደረጉት የሕዝብ ቆጠራ ውጤቶች ናቸው። ለምሣሌም ያህል፦ በ፲፱፻፸፮ (1976) ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ፵፪(አርባ ሁለት) ሚሊዮን ያህል እንደነበረ ይታወቃል። ከጠቅላላው የአገሪቱ ሕዝብ (42 616 876) ውስጥ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት 12 055 250 (አሥራ ሁለት ሚሊዮን ሃምሣ አምሥት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ) ነበር። ይህም ከአጠቃላይ የአሪቱ ሕዝብ 28.288 ከመቶ እንደነበረ ያሣያል። በሥርጭት ረገድም፥ በሸዋ 23.1 በመቶ፣ በአዲስ አበባ 47.86 በመቶ፣ በወሎ 79.86 በመቶ፣ በጎንደር 84.83 በመቶ፣ በጎጃም 87.58 በመቶ፣ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ነበሩ፣ በግለሰብ ደረጃም ሰዎች ማንነታቸውን «ዐማራ ነን» ብለው ማረጋገጣቸው በውል ታይቷል። ዐማራው በሌሎች የአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮችም በበቂ መጠን ተሰራጭቶ እንደሚገኝ የቆጠራው ውጤት አሣይቷል። በዚህም መሠረት በሐረርጌ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በወለጋ፣ በጋሞጎፋ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በአሰብ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንደነበረ መረጃው ያስረዳል። በዚያ የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኦሮሞን ቁጥር ከፍ፣ የዐማራን ቁጥር ግን ዝቅ ለማድረግ ሆን ተብሎ የቁጥሮች ጨዋታ የተሠራ መሆኑ ቢታወቅም፣ ዐማራው በቁጥር በአገሪቱ ከሚገኙ ነገዶች እና ጎሣዎች በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን ያረጋግጣል (ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን፣ ታኅሣሥ ፲፱፻፹፫ (1983) ዓ.ም.)።
በሁለተኛ ደረጃ በ፲፱፻፹፯(1987) ዓ.ም. በተደረገ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 53 499 248 መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ 13 834 297 ያህሉ ዐማሮች መሆናቸውን ያሣያል። በንፅፅር ሲታይ በትግሬ-ወያኔ ዘመን በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት በ፲(አሥር) ዓመታት ውስጥ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ቁጥር የጨመረው በ1,779,047 ብቻ ነው። ይህም የቆጠራው ውጤት የወያኔን ዐማራን የማጥፋት የፖለቲካ ዓላማ በጉልህ የሚያሣይ ነው። ሆኖም የዐማራ ነገድ በቁጥሩ ብቻ ሣይሆን በሥርጭትም ጭምር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በብዛት የሚገኝ መሆኑን የቆጠራው ውጤት አላስተባበለም። በመሆኑም ወያኔ «የዐማራ ክልል» ብሎ በከለለው ውስጥ ከሚኖረው 13 834 297 ሕዝብ መካከል ዐማራው 81.5 ከመቶ መሆኑን፣ በ«ትግራይ ክልል» ከሚኖረው 3 136 267 ሕዝብ መካከል የዐማራው ነገድ 2.6 ከመቶ በመያዝ በክልሉ በሕዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ታውቋል። በ«ኦሮሚያ ክልል» ከሚኖረው 18 732 525 ሕዝብ መካከል 9.1 ከመቶ የሚሆነው የዐማራ ነገድ መሆኑን እና ይህም በ«ክልሉ» ከሚኖሩት ነገዶች መካከል ከኦሮሞው ቀጥሎ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያል። አርባ አምሥት(፵፭) ነገዶች እና ጎሣዎችን ባጠቃለለው የ«ደቡብ ክልል» ዐማራው በቁጥር በስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚህ «ክልል» 10 377 028 ሕዝብ እንደሚኖር ቆጠራው አሳይቷል። ወያኔ «ሐረሪ» ብሎ የመንግሥትነት ዕውቂያ ከሰጣቸው ክልሎች አንዱ የሆነው የሕዝቡ ቁጥር 131 139 ነው። ከዚህ የ«ሐረሪ ክልል» ነዋሪ ሕዝብ መካከል 52.3 ከመቶው ኦሮሞ ሲሆን፣ 32.6 ከመቶው ዐማራ ነው። ሐረሪዎቹ 7.1 ከመቶ ብቻ ናቸው። እንግዲህ ለእነዚህ አናሣ ቁጥር ለያዙት ነው የአብዛኛውን የኦሮሞ እና የዐማራ ነገዶች ተወላጆች ዕጣ ፋንታ እንዲወስኑ ወያኔ የመንግሥትነት መብት የሰጣቸው። ይህንንም «ዲሞክራሲ ነው» እያሉን ነው። በሶማሌ ክልል 3 439 860 ሕዝብ እንደሚኖር በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. የተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ያመለክታል። ከዚህ መካከል በዚያ ክልል ዐማራው 0.69 ከመቶ በመያዝ በሦስተኛነት ደረጃ ላይ ይገኛል። ለሁሉም ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት እንዲቻል የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንመልከት።
በ፲፱፻፹፯(1987) እና በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. በተደረጉት የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ውጤቶች *መሠረት የክልሎችና የአስተዳደሮች ሕዝብ የብሔር /ብሔረሰብ ሥርጭት እና ብዛት
ክልል ወይም አስተዳደር | የክልሉ ሕዝብ ብዛት | ከአገሪቱ ሕዝብ (በመቶኛ) | በክልሉ የሚኖሩ ብሔር/ብሔረሰቦች | የየብሔረሰቡ ብዛት | ከክልሉ ሕዝብ (በመቶኛ) | መግለጫ |
ትግራይ | 3 136 267 | 5.6 | ትግሬ | 2 971 738 | 94.75 | ከ10 ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው |
ዐማራ | 81 297 | 2.59 | ||||
ሣሆ/ ኢሮብ | 22 858 | 0.73 | ||||
አፋር | 1 060 573 | 1.99 | አፋር | 968 018 | 91.27 | ከ2 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው |
ዐማራ | 46 534 | 4.39 | ||||
አርጎባ | 9 673 | 0.91 | ||||
ትግሬ | 8 460 | 0.8 | ||||
ኦሮሞ | 8 055 | 0.76 | ||||
ዐማራ | 13 834 297 | 25.91 | ዐማራ | 12 615 160 | 91.19 | ከ20ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው |
አገው | 417 373 | 3.02 | ||||
ኦሮሞ | 416 883 | 3.01 | ||||
ቅማንት | 172 291 | 1.23 | ||||
ትግሬ | 44 609 | 0.32 | ||||
አርጎባ | 37 626 | 0.27 | ||||
ኦሮሞ | 18 732 525 | 35.1 | ኦሮሞ | 15,709 474 | 83.86 | ከ50 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው |
ዐማራ | 1 684 128 | 8.99 | ||||
ጉራጌ | 246 895 | 1.32 | ||||
ጌዲኦ | 180 215 | 0.96 | ||||
ሶማሌ | 107 811 | 0.56 | ||||
የም | 103 823 | 0.55 | ||||
ትግሪ-ወርጂ | 67 456 | 0.36 | ||||
ኩሎ | 67489 | 0.36 | ||||
ሶማሌ | 3 198 514 | 5.99 | ሶማሌ | 3 011 453 | 94.15 | ከ3 ሺ በላይ ሕዝብ የያላቸው |
ኦሮሞ | 70 506 | 2.21 | ||||
ዐማራ | 20 951 | 0.66 | ||||
ጉራጌ | 4 085 | 0.13 | ||||
ቤንሻንጉል ጉምዝ | 464 590 | 0.86 | ጀብላዊ | 115 602 | 25.12 | ከ10 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው |
ጉምዝ | 107 495 | 23.35 | ||||
ዐማራ | 102 061 | 22.17 | ||||
ኦሮሞ | 58 833 | 12.78 | ||||
ሽናሻ | 32 105 | 6.97 | ||||
አገው | 17 928 | 3.89 | ||||
ደቡብ ብሔር/ ብሔረሰቦች | 10 377 028 | 19.43 | ሲዳማ | 1 820 030 | 17.539 | ከ50 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው |
ጉራጌ | 1 646 925 | 15.871 | ||||
ወላይታ | 1 210 235 | 11.662 | ||||
ሐዲያ | 874 468 | 8.427 | ||||
ጋሞ | 679 540 | 6.549 | ||||
ከፊቾ | 521 223 | 5.023 | ||||
ጌዴኦ | 549 351 | 4.423 | ||||
ከምባታ | 459 351 | 4.423 | ||||
ዐማራ | 443 525 | 4.274 | ||||
ኩሎ | 312 929 | 2.631 | ||||
ጎፋ | 273 089 | 2.320 | ||||
ኦሮሞ | 240 749 | 1.986 | ||||
ቤንች | 206 244 | 1.663 | ||||
ኦሪ | 17 ,611 | 1’488 | ||||
ኮንሶ | 154 381 | 1.362 | ||||
አላባ | 141 375 | 1.132 | ||||
ኮይራ | 117 449 | 1.014 | ||||
ጠምባሮ | 105 244 | 0.818 | ||||
የም | 84 918 | 0.586 | ||||
ጋምቤላ | 181 862 | 0.39 | ኑዌር |
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen