Netsanet: ጂቡቲ በቀን 103 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ከኢትዮጵያ በነፃ እንድታገኝ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

Mittwoch, 4. Juni 2014

ጂቡቲ በቀን 103 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ከኢትዮጵያ በነፃ እንድታገኝ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

ጂቡቲ በቀን 103 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ከኢትዮጵያ በነፃ እንድታገኝ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ
‹‹አዋጁ ለጂቡቲ ውኃ ሳይሆን መሬት የሚሰጥ ነው›› ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ
-የፓርላማ አባላት የኢትዮጵያን ጥቅም ጠይቀዋል
ተጻፈ በ ዮሐንስ አንበርብር (ሪፖርተር)
የጂቡቲ መንግሥት ያለበትን ከፍተኛ የመጠጥ ውኃ ችግር ለመቅረፍ፣ ከድንበሩ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደ ውስጥ ገብቶ በሺኒሌ ዞን በኩሊ ሸለቆ የሚገኝን የከርሰ ምድር ውኃ አልምቶ በነፃ እንዲወስድ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀረበ፡፡
በኢትዮጵያና በጂቡቲ መንግሥታት መካከል የተፈረመውን የውኃ አቅርቦት ስምምነት ለማፅደቅ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ ሰነድ የጂቡቲ መንግሥት ለዜጎቹ ንፁህ የመጠጥ ውኃ በማቅረብ ረገድ ለረዥም ጊዜ የቆየና ሥር የሰደደ ችግር እንዳለበት ይገልጻል፡፡ ለጂቡቲ ከተማ ነዋሪዎች ከሚቀርበው ውኃ ውስጥ 95 በመቶው ከጉድጓድ የሚገኝና በከፍተኛ ደረጃ ጨዋማ መሆኑን የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ባደረገው ጥናት በኢትዮጵያና በጂቡቲ ድንበር አካባቢ በሚገኘው ሺኒሌ ዞን ከፍተኛ የመሬት ውስጥ ውኃ መኖሩ መረጋገጡንና ክምችቱም ከፍተኛ በመሆኑ፣ ከፊሉ ለጂቡቲ ከተማ የውኃ አቅርቦት እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት በሁለቱ መንግሥታት መካከል መፈረሙን ሰነዱ ይገልጻል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ባካሄደው ጥናት እንደተረጋገጠው በኢትዮ ጂቡቲ ድንበር መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በሺኒሌ ዞን በኩሊ ሸለቆ በ210 ካሬ ኪሎ ሜትር ውስጥ በቀን 270 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡ የጂቡቲ መንግሥት ይህንን የከርሰ ምድር ውኃ በማልማት 103 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ለጂቡቲ እንዲቀርብ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተስማምቷል፡፡ በስምምነቱ መሠረት የውኃ አቅርቦቱን ፕሮጀክት ሙሉ ወጪ የሚሸፍነው የጂቡቲ መንግሥት ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ ባለቤትም የጂቡቲ መንግሥት እንደሚሆን ረቂቁ ይገልጻል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የጂቡቲ መንግሥት ለውኃ አቅርቦቱ የዕለተ ተዕለት ሥራዎች የሚመራ ኩባንያ እንደሚያቋቁም ስምምነቱ ያስረዳል፡፡ የውኃ አቅርቦቱ አስተዳደር የሚመራው በሁለቱ መንግሥታት የጋራ ስምምነት በሚወሰን አሠራር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለውኃው አቅርቦት የሚያስከፍለው ክፍያ እንደማይኖርም ሰነዱ ያብራራል፡፡
በፕሮጀክቱ ግንባታ ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለሚፈናቀሉ የሺኒሌ አካባቢ ነዋሪዎች

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen