Netsanet: ሥርዓቱ የፈቀደውን ሌብነት ያካሂዱ ዘንድ ዕድሉን አትከልክሏቸው፡፡የሁላችንም የጋራ ሀብት ሌብነት ነው።

Freitag, 6. Juni 2014

ሥርዓቱ የፈቀደውን ሌብነት ያካሂዱ ዘንድ ዕድሉን አትከልክሏቸው፡፡የሁላችንም የጋራ ሀብት ሌብነት ነው።

ሥርዓቱ የፈቀደውን ሌብነት ያካሂዱ ዘንድ ዕድሉን አትከልክሏቸው፡፡የሁላችንም የጋራ ሀብት ሌብነት ነው።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎Corruption‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Medrek‬#EthioMuslimPrisoners ‪#‎EthioMuslimCommitteeTrial‬ ##Ethiopia #UDJ #Blueparty #Medrek ‪#‎Ginbot7‬ ‪#‎Jiustice‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎ethiopian‬ politics ‪#‎Eppf‬ ‪#‎minilik‬ salsawi ‪#‎አብቢን‬ #ሳምቮድሶን
ህዝብ “ወይ አገሬ!” የሚል ቁጭት ቢያሰማ አይገርምም፡ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በድህነት ላይ ሙስና ተጨምሮ የት እንደሚያደርስ ማንም ጅል አይስተውም፡፡ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” ነው፡ከተማ ኢኮኖሚዋን በኮንትሮባንድ ላይ ከመሰረተች፤ አይዟችሁ፤ የጉምሩክም ሰራተኞች የደምቡን ጉርሻ ብቻ ነው የሚወስዱት እያለ ይሳለቃል ፀሀፊ ፡፡ ድርሻ ድርሻችንን ከወሰድን በኋላ፤ አገራችን እያደገች ነው ብሎ መለፈፍ ምን ያህል ቀላል እንደሚሆን መተማመን አያዳግትም፡፡ ትላልቆቹ አሳዎች የበሉትን በልተው ትናንሾቹ አሳዎች ላይ ቢላክኩ፤ የ “አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ” ታሪክ ያህል አስገራሚ ነው፡፡ (እርግጥ ትናንሾቹ አሳዎችም ትርፍራፊ አልለቃቀሙም ማለት አይደለም፡፡) ህዝብም ያንን አይቶ “ወይ አገሬ!” የሚል ቁጭት ቢያሰማ አይገርምም፡፡ ቁጭቱን ሲለማመደው ግን “እገሌ ከበላው፣ እገሌ የበላው ይበልጣል፤ እንወራረድ!” እያለ የዕለት ኑሮ ያደርገዋል፡፡
እያንዳንዳችን ግራና ቀኝ ማየት፤ አርቆ ማስተዋል፤ ግትር አለመሆን ይጠበቅብናል፡፡ አንድና አንድ ነገር ላይ ብቻ አተኩረን፣ እሱም ላይ ግትር ሆነን አንችለውም፡፡ ምክንያቱም ከየአቅጣጫው የሚቦረቡሩንን ችግሮች ስራዬ ብለን ስለማናያቸው አወዳደቃችን አያምርምና ነው፡፡ የምናደንቀውና የምናወራለት ነገር ሳናስበው ከወደቀ “ወርቅ ከዛገ ብረት ምን ሊሆን ነው?” እንዳለው ፤ “ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ” ይሆንብናል፡፡በፈጣሪ እጅ የተሰራው ፍፁም ነበር፡፡ እሰው እጅ ሲገባ ይነክታል ይነትባል ወይም በእኛ ቋንቋ “ይቸከላል!”፤ ወይም የድሮው መሪ መንግስቱ ሃይለማርያም እንዳሉት “ብታምኑም ባታምኑም ሞተናል!” ያሉት ዓይነት ነገር ይሆናል፡፡በማይሰማ ማህበረሰብ መካከል የቴክኖሎጂ ፋይዳ ምን ያህል እንደሆነ ሳይጠቁመን አይቀርም፡፡
ሙስና ቁመቱና ዐርቡ እንዲሁም ስፋቱ ሃገራችንን ያጥለቀለቀ ነው፡፡ እንደተስቦ ድንበርተኞቹን አገሮች ያዳርሳል፡፡ የእኛ ውስጥ ውስጡን በተምችም፣ በምችም፣ በምሥጥም ጀምሮ አሁን አሁን መስረቅም ሆነ መንጠቅ አሊያም መዝረፍ፤ ወደ ብዝበዛ ተሸጋግሮ እንደ ናይጄሪያና ኬንያ ዐይን-ያወጣ የሆነበት ደረጃ ለመድረስ አንድ ሐሙስ የቀረን ይመስላል፡፡ ብዙዎቻችን የምንስማማበት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም በኢትዮጵያ ሙስናን ማጥፋት አዳጋች ሥራ መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ዋናው ጣጣ፤ የማይቻል ዓላማ ማለማችን ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ የታችኛውን ሌባ የሚያስረው የላይኛው ሌባ መሆኑ ነው” ይለናል፡፡ ሥርዓቱ የፈቀደውን ሌብነት ያካሂዱ ዘንድ ዕድሉን አትከልክሏቸው፡፡ የሁላችንም የጋራ ሀብት ሌብነት ነውና ብንልም ያስኬዳል፡፡
ዛሬ መታሰርም እየቀለለ መጥቷል ይባላል፡፡ አንድ የአሥር ዓመት ፍርደኛ ያሉት ነገር እዚህ ላይ ተጠቃሽ ነው፡፡ “አይዟችሁ ብትታሠሩም የሰረቃችሁት ገንዘብ ያኖራችኋል፡፡” አንድ የዱሮ ባለሥልጣን እሥር ቤት ሲጎበኙ፤ “ይህ እሥር ቤት መታደስም፣ መስፋፋትም ይገባዋል፡፡ የወደፊት ቤታችን‘ኮ ነው!” አሉ፤ አሉ፡፡ አሉ ነዋ ነገራችን ሁሉ፡፡
ገዢዎቹ ስለዕድገት፣ ስለልማት ጧት ማታ እያወሩ፣ ስለመልካም አስተዳደርና የሕግ የበላይነት እያወሩ፤ ላይና ታች ሳይባል በየዕለቱ የሚሰማው የሙስና ጀብድ፤ አሳዛኝም አስደንጋጭም እየሆነ ነው፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የሚወሳለት ዕድገት በዘረፋ ታጅቦ በዚህ ሁሉ ሙስና ማህል አቋርጦ እንዴት እንደሚሸጋገር አሳሳቢ ነው አዲስ አድማስ፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen