Netsanet: ያለፈው ፅሁፌ ላይ ድንጋይ ሚሊዮን ወይም ቢሊዮን አመታትን ባህር ውስጥ መኖሩ አሳ እንደማያደርገው ፅፌ ነበር፡፡ ይህን የምል ወድጄ አደለም፡፡

Freitag, 6. Juni 2014

ያለፈው ፅሁፌ ላይ ድንጋይ ሚሊዮን ወይም ቢሊዮን አመታትን ባህር ውስጥ መኖሩ አሳ እንደማያደርገው ፅፌ ነበር፡፡ ይህን የምል ወድጄ አደለም፡፡

ያለፈው ፅሁፌ ላይ ድንጋይ ሚሊዮን ወይም ቢሊዮን አመታትን ባህር ውስጥ መኖሩ አሳ እንደማያደርገው ፅፌ ነበር፡፡ ይህን የምል ወድጄ አደለም፡፡ ............................................................................... #EthioMuslimPrisoners #EthioMuslimCommitteeTrial ##Ethiopia #UDJ #Blueparty #Medrek #Ginbot7 #Jiustice #Freedom #ethiopian politics #Eppf #minilik salsawi #አብቢን #ሳምቮድሶን ይድረስ ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም /ኤዲት ያልሆነ እስቲ አንድ ጉዳይ አንስተን ለመነጋገር እንሞክር ዘመዶቼ፡፡ ያለፈው ፅሁፌ ላይ ድንጋይ ሚሊዮን ወይም ቢሊዮን አመታትን ባህር ውስጥ መኖሩ አሳ እንደማያደርገው ፅፌ ነበር፡፡ ይህን የምል ወድጄ አደለም፡፡ በእርግጥ ልምድ ከትምህርታዊ እውቀት የተሸለ ሊያረጋግጥልንና አይናችን ባየውና ጀሯችን በሰማው መሰረት ያለምንም ጥርጥር ነገሮችን እንድንቀበል እንድንተዋቸው ወይም ደግሞ እንድንመሰክርላቸው እንድንፅላቸው አንዲሁም አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንድናደርግላቸው ያደርገናል ከዛ በተረፈ ግን በሁለቱ መካከል ያለው ሰማይና ምድር የሆነ ቋሚ ልዩነት ፈጥሮ አይታይም፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነታም ቢሆን ይሄው ነው፡፡ አንዳንዱ ፐሮፌሰር ሆኖ ምንም ቢባል ነባራዊ እውነታውን አልቀበል ብሎ ማለትም ሆን ብሎ ሳያውቅ ወይም አውቆ ሌላኛው ደግሞ ራሱ ፕሮፌሰሩ ከተፈጥሯዊ ተሰጥኦ እጅግ ሆድና ጀርባ ሆኖ ይወለድና ምንም ሳይገባው አንድ የአምስት አመት ህፃን የገባውን ያህል እንኳን ሳይገባው መመለስ ወዳለበት ይህን ዓለም እየበከለና እየመረዘ ቆይቶ ይመለሳል፡፡ ለዚህም ምስክር መቁጠር ሳያሻን እዚሁ በራችን ላይ የሁለት ዓመቷ ህፃን ኤሊሳ ሮበርትስ በ156 አይኪው ተፈጥራ አለምን ያስደመመችውና ከአንስታይን በአራት አይኪው አንሳ ዓለምን መተንተን ትችላለች፡፡ ይህን ፐሮፌሰር ሆና አደለም ያገኘችው፡፡ ዓለም ላይ እጅግ ደደብ እና ምንም አርቆ የማሰብ ብቃት የሌላቸው ሚባሉ ፕሮፌሰርም ይሁኑ ምንም ያህል ዓመት ዓለምን የጠኙባት ሞልተዋል ለምሳሌ እንውሰድ እንደ ፕሮፌሰር ፕላይት ደደብ ካልተማረ ሰው በታች የሚያስብ ፍጡር የለም፡፡ ዘመዶቼ እንዲህ እንድትትል ምን አነሳሳህ ብላችሁ መጠየቃችሁ ስለማይቀር እስቲ ምክንያቴንና ደሜን ትክን ያደረገውን ጉዳይ ላንሳላችሁ፡፡ አንዱ የሃገራችን እጅግ የተከበሩና የሚደነቁ ፕሮፌሰራችን ናቸው እኔም ለእርሳቸው ያለኝ ክብርና አመለካከት እንዲሁም አድናቆት ወሰን አልነበረወውም ለነገሩ እነዚህ እንኳን ሚቀጥሉ ይመስለኛል፡፡ እና ምን መሰላችሁ እኚህ ፕሮፌሰር ስለ ሰላማዊ ትግልና ትጥቅ ትግል የፃፉት ትን ሽ አንገቴን አስቀረቀረኝና ለምን የራሴን አልሞነጭርም ብ ተነሳሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ሰለማዊ ትግልን በራሳቸው አገላለፅ:: ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው ሲሉ ነው የገለፁት፡፡ እሽ እርሳቸው እንዳሉት ትጥቅ ትግል በጠመንጃ ሁለት ሟቾች የሚያደርጉት ግብግብ ነው እንበል በትንሹም ስለሚመስል፡፡ ሰላማዊ ትግልንም እንዲሁ እርሳቸው እንዳሉት በሁለት ሃይሎች መካከል የስሜት አካላትን ብቻ በመጠቀም አንዱ ቡድን ሟች በሆነ መልኩ ማሸነፍ ወይም መሸነፍ ሂደት ነው ሲጠቃለል፡፡ ታዲያ የኔ ቁጣ የጀመረው 1ኛ. ሰለማዊ ትግል ማለት የሃሳብ ፍጭት ብቻና አንድ ቡድን ሟች ብቻ ያለበት የሚለው ላይና 2ኛ. ትጥቅ ትግል ላይ ደግሞ ሁለት ሟቾች ‹የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› የሚሆንበት ነው ያሉት ላይ 3ኛ. ሰላማዊ ትግል ለምን የሚውል ለስልጣን፣ ለመሞት ብቻ ወይስ ለሰፊው ህዝብ ጥቅምና ለብሄራዊ አንድነት ወይስ መክሰስ ለመሆን 4ኛ. ትጥቅ ትግልስ ለም ለስልጣን የሰፊውን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ እና ለብሄራዊ አንድነት ወይስ ለመጠፋፋት ብቻ ለመተላላቅ እነዚህን ጉዳዮች ለይተው ማየት ካልቻሉ ፕሮፌሰሩ እጅግ የተበላሸ መልዕክት ብቻ እያስተላለፉ እንደሆነ መገመት ለማንም የሚያቅት አይመስለኝም፡፡ እስቲ ከአንደኛው ጉዳይ እንነሳና የፀሃፊውን ፅሁፍ እንተች 1ኛ... ሰላማዊ ትግል ለምን ፕሮፌሰር እርስዎ እንደዛ ያሉለት ሰላማዊ ትግል ለምን እንዲውል ምን ኣላማና ግብ ይዞ የተነሳ ሰላማዊ ሰልፍ ነው እርስዎ ሚደግፉት ለዚህ ምላሽ በሚችሉት ሰዓትና በሚችሉት መልክ ቢሰጡ ደስታውን ልችለውም፡፡ ሰላማዊ ትል ማለት የስሜት ህዋሳት ለስሜት ህዋሳት የሚደረግ የማሸነፍና የመሸነፍ ድራማዊ እውነታ ነው፡፡ በዚህ መሃል ፀሃፊው እንዳሉት መሞት ሊኖር ይችላል፡፡ ምናልባትም በሰላማዊ መንገድ መታገያ መንገዶችን ሲጠቀም ታስሮ ተደብድቦና ተቀጥቅጦ በስቃይ ከሚሞተው እስከ ብስጭት ደርሶበት በተለያዩ በሽታዎችና አካል ጉዳቶች ተዳርጎ ያልጋ ቁራኛ ሆኖ እስከሚሞተውና የተከበረች ነፍሱን በዚህ ሰላማዊ ትል ሰበብ ከርቀት በተተኮሰች ጥይትም ይሁን ምግቡና መጠጠጡ ላይ በተጨመረች የአይጥ መርዝየሚሞተውን ያጠቃልላል፡፡ ዋናወ ጉዳይ ግን ሞት ባለበት ሁሉ የትኛው ነው ሰላማዊ ሊሆን የሚችለው ሰላማዊ ትግል ያለምንም ደምና ሞት ያለምን ኽፀፅ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ማናም ሳይጎዳ የስልፃን ሽግግር መደረግ ሲችል ነው፡፡ በመሰረቱ በርካታ ፀሃፍት እንደሚሉት በዚህ እውነተኛው ዓለም ላይ ምንም አይነት ሰላማዊ ትግል የለም፡፡ እርስዎ የሚሉት ሰላማዊ ትግል የትኛው ነው? በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉት ሁሉ ሰላማዊ ናቸው እንዴ? እርስዎ እንዳሉት ሰላማዊ ትግል አንደኛው ቡድን ማለትም ስልጣን ላይ ያልሆነው ወደ ስልጣን የሚሮጠው የህዝብን መብት አስከብራለው ለራሴ መብትም እታገላለው የሚለው አካል የሚሞትበት ቢሞትም እኳን ሰላማዊነቱን የማይነሽረው ስልጣን ላይ ያለው ደግሞ የእርሱ ማለትም ስልጣን ላይ ያለውና ወደ ስልጣን የሚሄደው ሁለቱም የማይጠፋፉበት ሲሆን ነው ሰላማዊ የሚባለው ካሉ ከዚህ የከፋ ስህተት የለም፡፡ ፕሮፌሰር እዚህ ላይ የኔ ማስተባበያየ ምንድን መሰልዎት? 1ኛ... ሰላማዊ ትግል ማለት እርስዎ እንዳሉት አንዱ ብቻ ከሞተ ማለትም "ተቃዋሚ ወይም ተቀናቃኝ" የሚባለው የሚሞትበት ስልጣን ላይ ያለው የማይሞትበት ግን ሊገድል ሊያስር እንዲሁም ሊያሰቃይ የሚችልበት የትግል ስልት አደለም፡፡ በእርግጥ ይህ ጠፍቶዎት ነው ማለት አደለም ነገር ግን ይህን እርስዎ በገባዎት መልክ ሌሎች ሊገባቸው ይችላል ብሎ ማስፈሩ ዋጋ የሚኖረው አይመስለኝም፡፡ ሰላማዊ ትግል ከሆነ ሰላማዊ ነው ምንም ክርክር የለውም ሰላማዊ ነው፡፡ ተጎጅና ጎጅ የሌለበት ነው፡፡ ፍፁም ነው ግን አላልኩም፡፡ በመሰረቱ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነው ብለው የሚያስቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ ተሳስተዋል፡፡ በእርግጥ እነርሱና ደጋፊና አባሎቻቸው ምንም አይነት ጉዳት አላደረሱም ማድረስም አይፈልጉም አድርሰውም አያውቁም እንበል ስለሆነም ነገር ግን "ሰላማዊ" የሚለው ቃል በሁለቱም አቅጣጫ ነው የሚሰራው፡፡ ከተቃዋሚውም ከገዥውም በኩል ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ሲቀር ነው ሰላማዊ የሚሆነው፡፡ ያለዚያ ግን ተቃዋሚዎች ብቻ ሰላማዊ ናቸው እንጅ የትግል ምህዳሩ ግን ሰላማዊ አደለም፡፡ እንዴት እንዴት ነው የምናስበው ኢህአዴግም እና ተቀጥያ ድርጅቶችም እኮ በዚህ ነው አሞታችን የቀመሱት ወንድነታችን ያበነኑት፡፡ ይህ አስተሳሰብ አንድ ነገር ያስታውሰኛል፡፡ አንድ መሪ ነበር አሉ ድሮ ነው፡፡ እና ሶስት ሚሊዮን የሚጠጋ ጦር አለው፡፡ እና ይህን ጦር ምን ብሎ አሰላው መሰልዎት፡፡ መጀመሪያ ምን ያህል አመት እርሱ መግዛት እንደፈለገ አሰላና 50 ዓመት በቃኝ አለ አሉ፡፡ ከዛም ጠላቶቹ በየስንት ጊዜው እየመጡ አደጋ እንደሚያደርሱበት አሰላና በየየስድስት ወሩ ስልጣኑን እንደሚገዳደሩት አወቀ አሰላ፡፡ ከዚያም በኋላ ሶስት ሚሊዮን ወታደሮቹን ለሃምሳ ዓመታት አካፈላቸው በዓመት ሁለት ጊዜ ጦርነት እንዳለ በማሰብ፡፡ ከዚያም በኋላ ሶስት ሚሊዮኑን ወታደር ለመቶ በማካፈል በሃምሳ ዓመታት የስልጣን እድሜያቸው ውስጥ መቶ ጊዜ ጠለላት እንደሚያጠቃቸው በማሰብ በአንድ ጦርነት 30 ሽህ ወታደሮችን ብቻ ለማሰማራት ለጦር መሪዎቻቸው ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ 30 30 ሽህ ወታደሮቹንም ከፊት ከሁዋላ ከፊት ከኋላ ከፊት ከኋላ አሰለፉ፡፡ አንዱ ካላለቀ በስተቀር ሌላኛው ሰልፍ አይንቀሳቀስም፡፡ ይህን አሰላልና አሰላለፍ ያወቀው ጠላት ለአንዱ የመሪው አሰላለፍ በሶስት እጥፍ ማለትም ለአንድ ወታደር ሶስት የራሱን ወታደር ሶስቱ ወታደሮች በመተጋገዝ አንዱን እንዲያጠፉ በሚል ስሌት ገጠሙ፡፡ ከዚያም የዛ መሪ ወታደሮች አንድ ባንድ የጠላታቸውን አንድ አስረኛ እንኳን ሳያጠፉ ሙሉ በሙሉ ወደሙ እናም የጠላቱ 90 ሽህ ብቻ ወታደር ሶስት ሚሊዮኑን የመሪውን ጦር ደመሰሰው፡፡ አያችሁ የመሪው ድክመት፡፡ ይህ መሪ ያሰላው በርካታ ሞር ስላለው ብቻ ያንን ከስልጣኑ ጋር ብቻ ያጣጣመ መስሎት ነው ጉድ የሆነው አንደኛው ሲያልቅ እቅድ እቅድ ነው ስለዚህ ሌላኛው ሰልፍ ሂደህ አግዝ ጠላትህን አጥፋ በሚል አደልም የሚታዘዘው፡፡ በዚህ ምክንያትም ጉድ ሆነ ተሸነፈ፡፡ ገና ለገና አንድ ሁለት አመራሮቻችን ታሰሩ ተገረፉ ተገደሉ ይህም የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል ነው ብለን ካሰብን ሞኝነት ነው፡፡ ያንን መሪ መሆነ ነው፡፡ ሁሉም አባላትና ደጋፊዎች ሁሉም አመራሮች ታስረው ተገርፈው ተገድለው እስኪያልቁ ማየት ራሱ ከተጠያቂነት አያድንም ታዲያ ከዚያ በኋላ ማንን በሰላማዊ መልኩ አታግለን ልንል ነው፡፡ ይህ የድሮው ትውልድ ፍልስፍና ብቻ ነው፡፡ እንደእኔ እምነት ሰላማዊ ከተባለ ሰላማዊ ነው፡፡ ማንም መታሰር መገረፍ መሰቃየት መገደል የለበትም፡፡ ማንም በስነልቦና መጎዳት የለበትም፡፡ አማራጭ አቅራቢ ቅን ዜጋ ብቻ ሆኖ ብቻ ካልተቆጠረ ይህ ሰላማዊ ሳይሆን ነውጥ የሞላበት ለመሞት ብቻ ለመስዋዕትንት የተዘጋጁ ሰላማዊ አታጋዮች ያሉበት የሞኞች ስብስብ ነው የሚሆነው፡፡ በአጠቃላይ አንድ ሃገር ውስጥ አምባገነናዊ ስርዓት ገዥ መደብ በለበት ሁናቴ ሰላማዊ ትግል አለ ብሎ ማውራት ዘበት ነው፡፡ የለም!!!!! የለም፡፡ እነአንዷለም እነ እስክንድር ኤልባና ሌሊሳ በቀለ እንዲሁም ሌሎች ምርጥ ታጋዮቻችን እስር ቤት ታጉረው፡፡ በርሃብ በግርፋትና በሞት እየተቀጡ ይህ በምን ሂሳብ ነው በሰላማዊ የትግል ምህዳር የሚፈጠረው? እሽ አነርሱ በእጃቸው ምንም አይነት ጉዳት ማድረስ የማይችሉ በመሆናቸው ሰላማዊ ናቸው ምንም አያወላዳም ገዥው መደብ ካልሆነስ ሰላማዊ ትግል ነው እየተደረገ ያለው፡፡ ትግል በአንድ ወገን ብቻ አደልም የሚካሄደው ሁለት የሚላተሙ የሚፋጩ ሃይሎች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም ሰላማዊ ካልሆኑ ትግሉ ሲጀመር ጀምሮ ሰላማዊ አደለም፡፡ ትግሉ ስልጣን ላይ ያልሆኑት ወይም ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ብቻ ለመሞት ይሰመርበት ለመሞት የተዘጋጁበት ዕቃ ዕቃ ነው፡፡ ስለዚህ እርስዎ ያሉት ሰላማዊ ትግል ሳይሆን ተቀናቃኞች ሰልጣን ላይ ያልወጡት ብቻ ለመሞት፤ ከተቻለም ሳንሞት ስልጣን ላይ ወጥተን የሰፊውን ህዝብ መብት እናስከብራለን እናከብራለን የሚሉበት ይህንን አውቀው ወደው የሚገቡበት ራስ መሃላ በመሆኑ ይህ ሰላማዊ የአንድ ቡድን ታጋይ ብቻ ያለበት የባዶ እጅ ጦርነት እጅ ሰላማዊ ትግል ነው ሊያስብለን አይችልም፡፡ ይህ የተቃዋሚ ሰላማዊነት እስኪሞት ይሰመርበት እስከሞት ሳይሆን እስኪሞት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ጫፉ ሞት እንደሚሆን አውቆ ሰላማዊ ትግል አካሂዳለው ይህ አካሄድ የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል ነው ብሎ ለመሸንገል መሞከር ከገዳዮች ጋር መሰልፍ ነው የሚሆነው፡፡ ያ ምስኪን ያወቀም ያላወቀም ደጋፊና አባልማ ይህን ተቀብሎ አምኖ እንደሚሞት ሳያውቅ እስከ ፅዋው እለት ድረስ መታገሉ ጥፋት አይሆንበትም መንገድ የጠፋው እና መንገዱን ያላወቀ መሪ እንደሚከተለው መንገደኛ ብቻ ነው ሊፈረጅ የሚችለው፡፡ ይሕን ፕሮፌሰር እርስዎን የማከብረዎን እጅግ ለኢትዮጵያ ያሉ የሌሉ ብየ የምወድዎትን አንድም የቀለም አባቴን ሁለትም የትግል አስተማሪየን ለማሳነፍ ወይም ክብር ለመንሳት ብየ አደለም ግን ይህ እሳቤ ነው፡፡ በመሆኑም ፕሮፌሰር ሰላማዊ ትግል ጫፉ አስር፣ ግርፋት ስቃይ በየትኛውም ደረጃ እንዲሁም ሞትና ከሞት የሚብሱ ነገሮች መሆናቸው እየታወቀ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንችላለን ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ እናም ሰላማዊ ትል ብቸኛው መፍትሄ ብቻ ሊሆን እንደማይችል መገመት አለብን፡፡ ስዎች ሰው በመሰረቱ ናና እንዲህ አድርግ ከሚባል ራሱ በስሜት በብሽቀት በንዴት ወይም በወቅቱ በተፈጠረ ጉዳይ እንደምላሽ ብሎ የሚወስደው አፀፋ ትክክል ሆኖ የሚገኝበት ሰዓት እንዳለ መገመት ብልህነት ነው፡፡ ሰው ሊገድለው የመጣን እንካ ምታኝ ብሎ ይሄዳል ማለት ዘበት ነው ወይመ አጉል ውዳሴ ከንቱ ነው፡፡ ማንም ሊያጠፋው የመጣ ሳየቀደም ማጥፋት ይፈልጋል፡፡ ከቻለም ያጠፋል፡፡ ነገር ግን ይህ ይሁን ማለት አደልም፡፡ ግን ማመዛዘን፡፡ ሲመዛዘንም ይህ ሰላማዊ ታጋይ ከታንክ ጋር ከክላሽንኮቭ ጋር የገጠመ ሰው ከትክሻው ላይ ያለው የሰፊው ህዝብ ጥያቄና የመብትም ይሁን ሌላ መሰረታዊ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ ከበድ ካለለት እርሱ አፀፋው መግደል ቢሆን ስዕተት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክን|ነቱም ሰውየው ማለትም በእርስዎ አገላለፅ ይህ ሰው የተሸከመው ሃላፊነት የህዝብ እስከሆነ ድረስ ወይም ትክክል እስከሆነ ድረስ ጠላት ሊነሳበት ተቃዋሚ ሊነሳበት የሚችል በስዕተት ብቻ በመሆኑ ቢያጠፋ በምንም መልኩ ምድራዊ ሃጢያት አደለም፡፡ ትክክል ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው ያለው አማራጭ ሁለተኛው ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰላማዊ ታጋዩ መጨረሻው እስራት ግርፋት ወይም ሞት እና መሰሎቹ መሆኑን ቀድሞ አውቆ ከሁለቱ አንዱን መምረጡ ትክክል ነው፡፡ መጨረሻው አስራት ግርፋትና መሰሎቹ ሞትና መሰሎቹ ካልሆነ ሰላማዊ ነው ትግሉ ማለት ስለሚቻል መታገል፡፡ ይሕ ካልሆነ ግን ሰላማዊ ትግል ስላልሆነ ትጥቅ ትግል ምንም አማራጭ የለውም፡፡ ይህ ሲባል ተጥቅ ትግል ጥፋት የለውም ማለት አደልም ግን ትርፍ ካለውሰ? 2ኛ.... "የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ" ፕሮፌሰር ይህ አባባል መች ለመጀመሪያ ጊዜ ለምን እንደተባለ ባውቀው ወዴትስ እንደተባለ መረጃ ባገኝ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር ግን አላውቀውም፡፡ ለማንኛውም እርስዎ ካሉት ተነስቼ ልሞንጭር፡፡ እስቲ እርስዎ በሶስተኛ ደረጃ ያሉትን እንይ ቃል በቃል ሦስት፣ የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር፣ ብረት ከብረት ጋር ይጋጠማል፤ የሰው ልጅ ለእርድ ይቀርባል፤ በሕይወታቸው በልተው ያልጠገቡ ምስኪኖች ለጥቂት ሰዎች የሥልጣን ጉጉት ይታረዳሉ፤ ያለቀባሪ በጅብና በአሞራ ይበላሉ፤ ዕድለኞች የሚባሉት እጆቻቸው፣ ወይም እግሮቻቸው ተቆርጠው፣ ወይም ዓይኖቻቸው ጠፍተው፣ ወይም ከዚህ ሁሉ የባሰ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የሚቀሩት ናቸው፤ ከነዚህ በሕይወት በቀሩት የጦር ጉዳተኞችና በጦርነቱ ላይ በሞቱት መሀከል የትኛው የተሻለ አንደሆነ የሞቱት ባይናገሩም ጉዳተኞቹ ይናገራሉ፤ ‹የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› እያሉ። ፕሮፌሰር ምንድን ነበር ያሉት? የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር እርስዎ እንዳሉት ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር ብረት ከብረት ጋር ብለው መግለፅዎት ትክክል አይመስለኝም፡፡ በመሰረቱ ጦርነት አማራጭ ከሌለ ሰላማዊ ትግል በላይ ውጠየታማ ነው፡፡ እነዚህ ስዎች ጉልበተኞች ሳይሆኑ አማራጭ ያጡ ርሃብና ጥም ሳይበግራቸው እንደስዎቹ ቦርጫቸውን አንገፍተው በየሴታዳሪና በየቡናቤቱ የሚዞሩ ምቾት ወቢ ያስተፋቸው ሳይሆኑ የሰላማዊ ትግል አማራጭ ያጡ የሰላማዊ ትግል መጨረሻውን ጠንቅቀው ያወቁ ድንቅ የብሄራዊ ኩራትና ሁለተኛ ህጋዊ ያልሆኑ /በገዥው መደብ ማለቴ ነው/ መከላከያ የብሄራዊ ክብር መመኪያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፡፡ እርስዎ እንዳሉት ጉልበት የደላቸው አደለሉም ፕሮፌሰር!!! ጉልበታቸው ሃገራዊ ፍቅር ህዝባዊ ፍቅር ነው፡፡ ሞት የማያስፈራው ጉልበት ማንም የማይበግረው ጉልበት ይህ ነው የህዝብና የሃገር ፍቅር ያኔ ነው መስዋዕትነት ያለው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለ ሞት ሞት ነው፡፡ የእነርሱ ግን መስዋዕትነት ነው፡፡ ለሚወዱት ህዝብና ሃገር፡፡ ለሚኖሩለት እውነት መሞትን ያህል ክብር የለም፡፡ የያዙት እውነት ነው ብረት ነው ግን ሰውን አደለም የሚገድሉበት አውሬን እንጅ፡፡ ወያኔ አቢዮተኛ ብሎ ራሱን ከጠራ በኋላ ትጥቅ ትግልን ማድረጉ ስህተት ነው የሚል ካል ትክክል አደለም፡፡ ትክክል ነው ወያኔ ያኔ መብቴን በሃይል አስከብራለው፡፡ ማለት ስህተት አደልም፡፡ ትክክል ነው አማራጭ ሲታጣ፡፡ ስለዚህ ወያኔ ይህን ማድረጉ ብርቅ ያደርገዋል በዚህም ጀግኖች ናቸው፡፡ ስእተቱ ምንድን ነው? ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ የመጣው ጭራቅነት የሞቱለት ዓላማ መና ሲቀር ነው፡፡ ያኔ ነው የሞቱለት ቀርተው የገደላት በላ ሊባል የሚችለው፡፡ ለዛም ነው ይህ አባባል አሁን ለወያኔ ኢህአዴግ የሚገጥመው፡፡ ያኔ አፈር በጥብጠው በልተው ጤዛ ልሰው ከፊታቸው ላይ ላይ እንደሸኮለለ እንኮይ ክብልል ደፋ ብለው የቀሩት ጀግኖችን አጥንት የሚያስወቅሱት ያኔ ነው፡፡ ለዚህም ነው ነባር ቅን ታጋዮች አሁን የሚንገበገቡት የሞቱለት ጓዶቻቸውንና ስንት ምሁራን ወንድም እህቶቻቸውን ያጡበትን ዓላማ ወና ሲበለው ሲያዩ ከንቱ ሲቀር እያዩ ይህኔ ያውም እነርሱና ሟቾች የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የሚሉት፡፡ እውነታው ይህ ስለሆነ እንጅ ትጥቅ ትግል በራሱ ያን አያስብልም፡፡ ጥያቄው እኮ ያለው በትጥቅ ትግል የመጣው ከአሁን በፊት በነበረው ታሪክ ተነስተን የምንተነብየው ጋር እንጅ ትጥቅ ትግል የህዝብ መብትን ማስከበሪያ ሃይልን በሃይል የሚለውን እውነታ አያጣምመውም፡፡ በርካታዎቹ የአፍሪካ ሃገራት በዚህና በመፈንቅለ መንግስት የሚታወቁ መሆናቸው ራሱ የተማረውም ያልተማረውም ከስልጣን በኋላ ያለውን ስርዓት በማየት ብቻ ትጥቅ ትግል አያዋጣም ወደሚል መደምደሚያ ይወስዳል ግን አሜሪካና አውሮፓዎችስ በዚህ ተለዋውጠው ቢሆን እንል ነበር ወይ ይህን ሳያደርጉ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ማድረጋቸው በራሱ አማራጩ ያ ብቻ እንደሆነና ትጥቅ ትግል ስኬታማ አደለም የሚለውን እውነታ ሊያፈርሰው አይችልም፡፡ መችም ይህን ስል የልጅ ነገር እነደማይሉኝ አስባለው፡፡ ካሉም ምን አደርገዎታለው፡፡ እናም ትጥቅ ትግል በራሱ ስዕተት አደለም አማራጭ ግን ነው፡፡ ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላማዊ ለውጥ ቢኖር ጥሩ ነው፡፡ ግን ይህ ካልሆነ ትጥቅ ትግልን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ትጥቅ ትግል ካልሆነ ግን መፈላሰፍ ይጠይቃል፡፡ ለቀጣይ እንያዘው፡፡ 3ኛ. ሰላማዊውም የትጥቅ ትግልም ለምን መዋል አለባቸው ለምን ከመዋላቸው በመነሳት ጠቃሚም ጥቅም አልባም ይሆናሉ በመሰረቱ ጉዳት ማድረስ ጥቅምን ማሳጣት ወይም መጎዳት አደለም ባይ ዲፎልት፡፡ ዋናው ጉዳይ ሁለቱም የትግል ስልቶች ለምንድን ነው የሚውሉት? ይህ ጥያቄ በአግባቡ በተግባርም ሆነ በቲዎሪ ከተመለሰ አማራጩ የትኛውም ቢሆን ትክክል ነው፡፡ ቢያንስ በዛ ሰዓት የተሸለ አማራጭ የለም፡፡ መች ትክክል ይሆናሉ የሚሉትን እንይ አንድ ባንድ ሰላማዊ ትግል ትክክል የሚሆነው 1... ሰላማዊ ትግል አስፈላጊ ነው ወይ የሚለው ሲመለስ 2... ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎች አሉ ወይ 3... ምንም አይነት ሰላማዊ ትግል አድራጊ መታሰር የለበትም 4... ምንም አይነት ሰላማዊ ታጋይ መታሰርና መሰሎቹ በደሎች ሊፈፀሙበት አይገባም 5... ምንም አይነት ግድያ እና ተመሳሳይ በደሎች የማይደርሱበት ከሆነ 6... ሰለማዊ ታጋዩ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት 7... ምንም አይነት አድልኦና አስተዳደራዊ በደሎች ካልደረሱለትና ልክ ስልጣን ላይ እንዳልወጣ ግን እንደ ገዥ መደብ እንክብካቤና ባለቤትነት ስሜቱ ከተከበሩለት 8... ዜጎች የሰላማዊ ታጋዮ ተመሪ ደጋፊና አባል መሆን መብታቸው እና በነሱ ፍላጎት ብቻ መሆን ሲችል 9... የትናውም ዜጋ የፈለገው ፖለቲካል ፓርቲ ደጋፊ መሆን ሲችል 10.... ፖለቲካል ፓርቲው የራሱን አማራጭ የገቢ ምንጮች ማመቻቸት ሲችል 11... ምርጫ አለመጭበርበር ሲችል ከብዙ በጥቂቱ ናቸው እነዚህን ሌሎችም ያልተጠቀሱ ግን ለሰላማዊ ትግል አስፈላጌ የሆኑ መመዘኛዎች ካልተሟሉ ሰላማዊ ትግል አለ ሳይሆን ታጋዮቹ እስኪያልቁ እንደ ዳይኖዘር ከምድረገፅ እስኪያልቁ እየተላተሙ ነው ቢባል ይሻላል፡፡ ስለዚህ ቀጣዩ አማራጭ ትጥቅ ትግል ይሆናል፡፡ በመሰረቱ ሰው እጅግ ካልከፋው እንዴት ሞትና እሳት ከሚቀልቡበት ሜዳ ይገባል? እንዴ ሞኝማ አንሁን፡፡ አንድ ግልፅ የሆነ ለታጋዮቹ ለፕሮፌሰር ግን ምንም ግልፅ ያልሆነላቸው ወይም ደግሞ አውቀው የተውት ወይም ደግሞ መቸም ከአሁን በኋላ እዛ ሆኜ ልታገልና ላታግል አልችልም ከሚል ተስፋ መቁረጥ የተውት ጉዳይ አለ፡፡ እርሳቸው እንዳሉት እርሳቸው እርጅና ጉልበታቸውን ያሳጣቸው እለት እና ወደዛ ቦታ መሄድም መምራትም መመራትም እንደማይችሉ ሲሰማቸው መናገር ፈልገው ካልሆነ በስተቀር እንጅ መቸም የትጥቅ ትግልን ያህል ፈታኝ ያለጉልበተኛነት በደካማ አቅም ብቻ ደፋ ቀና የበዛበት የወንድ ልጅ ፈተና ቦታ የለም፡፡ ይህንን ግን እርሳቸው ከህዝብ ጉያ ጠፍተው የማያውቁት ከሚናገሩት አረመኔው ወያኔ ቢናገር ይሻላል፡፡ ትጥቅ ትግል ምን ያህል ፈታኝ ነው? ትጥቅ ትግል ምን ያህል ጉልበት የሚያሳጣ ሞትን እንደ ምግብና ውሃ ቀን በቀን እየጎበኙ የሚኖርበት ቦታ ነው? እንደምን በረሃብ በበረሃ በውሃ ጥም በእርዛትና በአሾህ እንደሚለበለቡ የማይገባው ይገኝ ይሆን፡፡ ግን ልብሳቸው ምግባቸው መጠጣቸው ሞራላቸውና ጉልበታቸው አንግበውት የወጡት ዓላማ እና አደራ እንደሆነ በታወቀ፡፡ ለነገሩማ እርሳቸው ይሆናሉ እንጅ ማንም የኣለም ዜጋ ያውቀዋል፡፡ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም፡፡ ይህን ስል አሁንም ሰላማዊ ትግል ግን የመጀመሪያው አማራጭና ተወዳዳሪ የማይገኝለት የመጀመሪያው አማራጭ ነው፡፡ ይ ካልሆነ ግን መቸስ ምን ይደረጋል፡፡ ፒኤችዲም ቢሆን ተይዞ ይገባል፡፡ አስቡት ፒኤችዲና ክላሽንኮቭ ፒኤችዲና መትረየስ አንድ ላይ በብዕር ጦርነት ቆመ ማለት ግን አይቻልም ሁለቱም ግን አንድ ላይ ይሄዳሉ፡፡ ሁለተኛ ከዛ በኋላ ግን አማራጭ ሌላ ሊገኝለት አይቻልም ማለት አይቻልም፡፡ ለማንኛውም ትጥቅ ትግል የሚከተሉት ሁሉ ከሆኑ አማራጭነቱ ትክክል ነው 1... ሰላማዊ ትግል ሳይቻል ሲቀር 2... የሰላማዊ ትግል ቁልፍ ቁልፍ መመዘኛዎች ብቻ ሳይሆነ ሰላማዊ ትግልን ሰላማዊ የሚያደርጉት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል ደረጃው ይነስ ይብዛ እንጅ ወደ ትጥቅ ትግል የሚወስዱት መስመሮች ይበቅላሉ ይህም ተፈጥሯዊ ነው፡፡ 3.... ትጥቅ ትግል ለማድረግ ማሰልጠኛ ቦታዎችና ስትራቴጅካሊ ወሳኝ የሆነ ቦታ ሲያዝ ወይም ሲገኝ 4... የገቢ ምንጮች ላይ እርግጠኛ መሆን ሲቻል 5... የተለያዩ አቅርቦቶችን በምን መልክ እንዴት በየት በማን በኩል እንዲሁም መቅረብ ይችላሉ ወዘተ ሲመለሱ 6... ራስን እየቀናነሱ እንደዛ መሪ ላለማስጨረስ የራስ ስትራቴጅ ሲዘጋጅና ሙሉ ስምምነት ላይ ሲደረስ ወዘተ… በአጠቃላይ ሰላማዊ ትግል አልሆን ሲልና የሰላማዊ ትግል መጨረሻው ወደ ድል እና ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሳይሆን ወደ ጥፋትና ኪሳራ የሚመራ ሲሆን ትጥቅ ትግል መሄዱ ምንም ጥያቄ አያስፈልገውም፡፡ ትክክለኛ አማራጭ ነው፡፡ ከዛ ቀጥለውም በአራትኛ ደረጃ አድርገው ያቀረቡት ሁለቱ የትግል ስልት ዓይነቶች በባሕርይ የተለዩ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን የሚደግፍ አይደለም፤ ሰላማዊ ትግል የትጥቅ ትግልን ለመደገፍ ሰላማዊ የሚለውን ስያሜ መጣል አለበት፤ የትጥቅ ትግልም ሰላማዊ ትግልን ለመደገፍ ትጥቅ የሚለውን ስያሜ መተው አለበት፤ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል አራማጆች ድል ቢያደርጉ ማን ወንበሩ ላይ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ጠመንጃ የያዘው ሥልጣኑን ሲይዝ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል! ያውም ከተፈቀደለት! በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አርበኞች ሳይቀሩ በሩ ተዘግቶባቸው ለደጅ ጥናት እንደተዳረጉ አይተናል፤ መልኩን ለወጥ ቢያደርግም ደርግን ከተፋለሙት ውስጥ በአዲስ አበባና በአስመራ ወንበሮች ላይ ሲወጡ የተሸነፉት ወይ ለወያኔ ገብረው ሎሌነት ገቡ፤ ወይም በአሜሪካ መሽገው ያቅራራሉ፤ ዘመኑ እንዳለፈባቸውም ገና አልተረዱም። ብለዋል፡፡ እዚህ ላይም እኔ የተለየ አመለካከት አለኝ፡፡ ሁለቱም በባህሪ ቢለያዩም መድረሻቸው ግን አንድ ነው፡፡ ስለዚህ በዛም ሆነ በዚህ አንድ ዓላማ ይዘው ነው የሚሄዱት ይህ አላማቸውም የጋራ ጠላት እንዲኖራቸውና ይህ የጋራ ጠላታቸውን ለማጥፋት በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚሰሩት ሁሉ ለተመሳሳይ አላማቸው ስለሚውል ተመጋጋቢ የማይሆኑበት ምንም አይነት እውነት የለም የበለጠ እንዲያውም ሙሉ ያደርጋቸዋል እንጅ፡፡ እንዲያውም ፕሮፌሰር አንድ ጉዳይ ልንገርዎት ሰላማዊ ትግል ያለትጥቅ ትግል አነስ ባለ ድግሪ እና በተለይ ትጥቅ ትግል ግን ያለሰላማዊ ትግል እንደ እርስዎ አባባል አይሆኑም ቢሆኑም በርካታ ዓመታትን ከማራዘም አንግል ይወልዳል፡፡ በመሆኑም ትግል ትግል ነው የቅፅበት መዘናጋት ይጥላል፡፡ ትግል ትግል የሚሆነው በግራም በቀኝም ግጥም ተደርጎ ሲያዝ ነው፡፡ አንድ የኛ ፖለቲከኞች ረሱት ጉዳይ ቢኖር ዓላማን ማለትም ፖለቲካዊ እና ሃገራዊ ዓለማን ለማስፈፀም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ አንድ አካል ስልጣን ያስፈልገዋል፡፡ ለምን መሸፋፈን እንደሚያስፈልግ አይገባኝም፡፡ እኛ ሃገር ላይ አንድ የፖለተካ ድርጅት እኔ ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ መብት መከበር ለብሄራዊ ልዕልና ምናምን…ነው የምንታገለው ገለመሌ ይላሉ፡፡ ይህ ግን ስዕተት ነው ባትነግሩንም እኛ ስለምናውቀው አትሸውዱን ለስልጣን ነው፡፡ ቀድሞ ነገር ስለሚያስፈልግ ነው፡፡ ስልጣን ካልፈለጋችሁ ለቀቅ አድርጉን ተጣቂዎቹም ይሁን ሰላማዊዎች ለስልጣንላይ መውጣት ካልቻሉ ማን ሊወጣ ነው፡፡ ይህን በምን ማስተካከል ይቻላል መሰላችሁ…. ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እንደ አማራጭ የሚያመጣን ብቁ ፖለቲካዊ ድርጅት ስልጣን ላይ እንዲወጣ እንታገላለን ቢሉ ይሻላል፡፡ ቆይ ኢህአዴግ ሰለማዊ ትግሉን ወይስ ትጥቅ ትግሉን የሚፈራ ይመስላችኋል፡፡ ያለምንም ጥርጥር ትጥቅ ትግሉን ይፈራል ይሀ ሲባል ሰላማዊ ያገር ውስጡን ትግልም አይፈራም ለማለት አደለም፡፡ ሁለቱ አማራጮች ግን በተመሳሳይ ሰዓት እንዲጠነክሩበትም ሆነ እንዲፈጠሩበት አይፈልግም፡፡ ለምን? ሰው ማንኛውም ሰላማዊ ታጋይም ይሁን በትጥቅ ትግል የሚያምን አማራጮች ተቀምጠውለታል ስለዚህ በምንም ሳያመካኝ ወደፈለገው ይሄዳል፡፡ ሰላማዊ ትግልን መንግስት በሃይል መደምሰስ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ይህ ኢላማን እንደመምታት ነው የሚቆጠረው ባዶ እጁን ያለን ህብረተሰብ በመትረየስ መግጠም ግዳይን በጥይት እንደመደብደብ ያህል ቀላል ነው፡፡ መንግስት እንደሆነ የትኛውንም ዓለማቀፋዊ ሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አይፈራም ከጥቅማቸው እንደማያስበልጡን ያውቃል፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ 100 ገድሎና አስሮ የትኛውንም ያህል ቢሊዮን ዶላር ጥቅም የሚያስገኝ ብሄራዊ ጥቅም ይለግሳል በጎን ይበደራል በጎን ተቃዋሚ የሚላቸውን ከምድረገፅ ለማጥፋት በቢሊዮን ያወጣል ለጥቃቅኑ ሁሉ ጥቅመኛ መንግስት ስለሆነ፡፡ ይህና ሌሎችም እንጅ ስህተተቶቹ ወያኔ ትጥቅ ትግሉ ከምንም በላይ ትክክል ነው፡፡ በመሰረቱ ፕሮፌሰር ከአሁን በኋላ ፖለቲካውን ሁሉ ፕሮ ነፃነት ፈላጊ ካልሆናችሁ በቃችሁ ራሳችሁን ጦሬታ አውጡ መንገዳችን ላይ ዞር በሉልን፡፡ ለህዝብ ከየትም ሆነው የሚጮሁ ወገኖቻችን አታስቀይሙብን፡፡ ተውን አቦ!! አስቲ ወጣቱና የህዝብ ጥያቄን የሚያስተጋቡትን ሁሉ የሚደግፉትን አካላት ሁሉ ሳይጣንም ቢሆን ለጊዜው መደገፍ ሚችል ስራ ብቻ ስሩ፡፡ የወቅቱ ጥያቄያችን የፍላጎቶቻችን ማለትም የኢህአዴግ ስልጣን መውረድ ጥያቄ ነው፡፡ ያዋረደን ያደኸየን ያጣጣለንንን ሁሉ ተንከባክቦ የያዘ መንግስት ማፊያ ቡድን ወድቆ ማየት ይህንን ስልጣን መረከብ የሚችል አካል ጎን ለጎን መመስረት ነው፡፡ ስለዚህ እባካችሁን ውድ ከህዝብ ጎን የቆሙ ዲያስፖራዎቻችንን ተውልን እናንተ በቅናት አብዳችሁ ብታረክሷቸውም እኔና መሰሎቼ ግን እንፈልጋቸዋለን፡፡ ምንም ስንሆን የሚጮኹልን እና ድምፃቸውን የሚያስተጋቡልን እነርሱ ናቸው፡፡ ይህ ሲባል እንደ ሰማያዊ እና አንድነት አይነት ምርጥ ፖለቲካዊ ፓርቲዎቻችንም አትንኩብን፡፡ እዛው ቤት ውስጥ ማለቅ ያለበትን ሚስጥር ለህዝብ ጥሩ ታማኝ መስሎ ለመታየት በግላጭ ለጠላት አውጥታችሁ ተስፋችን አታጨልሙብን፡፡ ፕሮፌሰር እርስዎ እጅግ ትልቅ አስተዋፅኦ ለህዝብዎት አድርገዋል፡፡ ለዚህም እናመሰግናለን ያየንም ያላየንም፡፡ ነገር ግን ከአሁን በኋላ አስረክቡን እርስዎ ከሰሩት ሁሉ ብየ ማለት ባልፈልግም በውጭው ዓለም የሚኖሩት ሁሉ ግን ለኢትዮጵያ ያላቸውን ሞራልና ልዩ ፍቅር በእንባም አጅበው ሳይ ነው ኢትዮጵያዊነቴን የማውቀው፡፡ ስለዚህ እነርሱ ለሃገራችን ህዝብ ዘብ ናቸው ታዲያ በተቃዋሚች ጥንካሬ ነው እንዴ እኛ ዓለማቀፋዊ አጀንዳ መሆን የጀመርነው፡፡ እዚህ ውስጥ የአንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች አስተዋፅኦ እጅግ ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን ሳልገልፅ አላልፍም፡፡ በአምስተኛ ደረጃ እርስዎ ያነሱት ጉዳይ ም እንዲሁ ለኔ የተዋጠልኝ ጉዳይ አደለም፡፡ እንደ እርስዎ አባባል ከሆነ እስቲ ያሉትን ደግመው ይዩት፡፡ … ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል ሁለቱም ብርቱ ቃል ኪዳንን ይጠይቃሉ፡፡ የቃል ኪዳናቸው ልዩነት አንዱ እስከሞት ለመታገል፣ ሌላው ደግሞ እስከመግደልና እስከመሞት ለመታገል መሆኑ ነው፡፡ ለሰላማዊው ትግል ከፍተኛ መንፈሳዊ ወኔ የሚያጎናጽፈው ለመግደል ያለው ተቃውሞ ነው፡፡ ሕይወትን ለማልማት ሕይወትን መቅጠፍ የአስተሳሰብም የመንፈስም ጉድፍ ያለበት ሥራ ነው። የሰላማዊ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ ሕዝብን ለሥልጣን ባለቤትነት ማብቃት ነው፤ ሥልጣንን ለመያዝ አይደለም፤ ስለዚህም ኢላማው ሕዝብ ነው፤ በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያሉት የሰላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነው፤ ሰላማዊ ትግሉ የሚያተኩረው በሕዝቡ ጆሮ፣ አእምሮና ልብ ላይ ነው፤ አገዛዙ በበኩሉ ጸጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛለት ሕዝብ እውቀቱ ዳብሮ፣ መብቶቹን ሁሉ ተገንዝቦ፣ በሕግ ለሕግ እንጂ ለሰው አልገዛም በማለት ልቡ እንዳይሸፍት አፈናውንና ማነቆውን በማጠናከር እያደነቆረ ለመግዛት ይፈልጋል፤ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስተምሩና በአገዛዙ አካላት የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ድርጅቶችን ማዳከም ወይም ማጥፋት ለአገዛዙ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፤ ኢሳት የሚባለው የቴሌቪዥንና የራድዮ ፐሮግራም ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት የሆነበት ለዚህ ነው፡፡ ቃል ኪዳናቸው እስከሞት አደልም እስከ ህዝባዊ ኣላማቸው ነው፡፡ ይዘውት ወደ ትግል እስከሚገቡለት ዓላማ ነው፡፡ በእርግጥ እርስዎ እንዳሉት ቃልኪዳኑ ብርቱ ነው፡፡ ምናልባትም ሚስጥራዊ አለትነቱን ይህ ቃል ላይገልፀው ይችላል፡፡ ሞት እዚህ መሃል መነሳት ያለበት ጉዳይ አደለም ሞት ሞት የሚሆነው የህዝብን ፍላጎት የህዝብን ዓላማ በከንቱ በነገ ነገ ሲያስረግጡ ነው፡፡ ሞት ሞት የሚሆነው በህዝብ ስም ሲነግዱበት እንጅ የህዝብን ጠላትማ ሲያጠፉና ለዛ ሲጠፉ ሞት ሳይሆን መስዋዕትነት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ትልቅ ማንም ማይፈታውና የማያስማማው ልዩነት አለ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ትግሎች ህዝብን ስልጣን ላይ ለማውጣት መሆን ሲችሉ ነው ትክክክል ሚሆኑት፡፡ ያለዚያ ግን ዜሮ ድምር ጨዋታ ነው ሚሆነው ያውም ኪሳራ የሞት ሞት ያ ነው፡፡ በየትኛውም የትግል መስመር መጨረሻው ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ መሆን አለበት፡፡ ይህ ሲባል መቸም ግልፅ ጉዳይ ነው ህዝብን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲሳተፍ እንዲመርጥና እንዲመረጥ ማድረግ መቻል ነው ከዚያም በሰላም ስልጣንን መረከብና ማስረከብ መቻል ማለት ነው፡፡ እርስዎ ትጥቅ ትግልን የሚገልፁት ከታሪክ ብቻ አይን በማየት መሰለኝ ይህ አግባብ አይመስለኝም፡፡ ትጥቅ ትግል ሲታሰብ በዚያ ትግል ወቅት ሊያመጣ የሚችለው ትርፍና ኪሳራም ብቻ አደለም መታየት የሚገባው፡፡ ምክንያቱም ትጥቅ ትግሉ ማለትም ከሃይል ሚዛን ማስደፋት አስከ ስልጣን መብቃት ድረስ ያለው የፈጀውን ፈጅቶ ስልጣን ላይ ያለው አካል ትንሽ ቢቆይ ኖሮ ሃገሪቱን ድራሽዋን ሊያጠፋት ከነበረ ትጥቅ ትግሉ አስፈላጊነቱ ምንም አያወላውልም፡፡ ይህንንም ከሁሉም ሴክት አንግል ማስላት ያስፈልጋል፡፡ ኢሳት የዲያስፖራው እና የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑንም ባለመርሳት ለዲያስፖራዎች ያለዎትን አመለካከት ቢያስተካክሉ መልካም ይመስለኛል፡፡ ሌላውን ሌላ ጊዜ… ኢትዮጵያ ለዘላልም ትኑር አመሰግናለው!! #EthioMuslimPrisoners #EthioMuslimCommitteeTrial ##Ethiopia #UDJ #Blueparty #Medrek #Ginbot7 #Jiustice #Freedom #ethiopian politics #Eppf #minilik salsawi #bitania alemayehu #HAna abebe# abrha desta# አብቢን #አብቢን

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen