June 19, 2014
ሰኔ 04/ 2006
ካርቱም ሱዳን
ካርቱም ሱዳን
ባለፉት ሦስት ፁሁፎቻችን እንደገለፅነው ዛሪም የስደተኛው ችገር በመቀፀሉ የተነሳ ይህንን ፁሁፍ ለመፃፍ ተገደናል አፈሳው ሰሞኑን ጋፕ ብሎ ሰንብቶ ነበር ከሰኔ ሁለት ጀምሮ ግን በጣም ተባብሷል ጭራሽ ህግ አስከባሪ ነን የሚሉ ፖሊሶች ወደ ተራ ዝርፊያ ገብተው ይገኛሉ።
የአሁኑ አፈሳ ባለፉት ፁሁፎቻችን እንደተገለፀው አጠቃላይ የውጭ ዚጋን ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን ብቻ በመሆኑና ለስደተኛው ተቆርቋሪ አካል በመጥፋቱ የተነሳ ህግ አስከባሪ ፓሊሶች እንዲሁም በፍርድ ሂደቱ ላይ የተሰየሙት ዳኞች ከሙያ ሥነ መግባራቸው በተቃራኒ በስደተኛው ላይ አሳፋሪ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።
ቀደም ሲል ከመንገድም ከስራ ቦታና ከመኖሪያ ቤት የታፈሱ ሥደተኞች ወደ እስር ቤት ወስደው ወደ ፍርድ በማቅረብ ያስፈርዱ እንደነበር ይታወቃል። አሁን ግን የታፈስቱን ስደተኞች ከእይታ ውጭ በሆነ አሳቻ ቦታ ፖሊሶች መከናዎቻቸውን አቁመው 400 ብር በማስከፈል መልቀቅ በመጀመራቸው ሊሎቹ ደግሞ ጠያቂ እስከለለ ድረስ እኛስ የማንዘርፍበት ምን ምክኒያት አለ በማለት ካፈሱ በኋላ በስደተኞቹ ኪስ ውስጥ የሚገኝ ብርም ሆነ ሞባይል ባጠቃላይ ሊጠቅም የሚችል ነገር በሙሉ በመዝረፍ ያልታሰበ የገቢ ምንጭ አድርገውታል።
የሚገርመው ዳኞቹ የቀጡትን 400 ብር ደረሰኝ እንኳዋን አይሰጡም የተቀጣው ስደተኛ በቆራጣ ወረቀጥ ነው የሚሸኘው። የመቀጮው ገንዘብም ወደ መንግስት ካዝና አይደርስም አፈሳውን ያከናወነው ፓሊስ ጣቢያና በአፈሳው ላይ የተሳተፉት ፖሊሶች ተካፍለው እንደሚበሉት ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።
ከሦስት ሳምንታት በፊት ወደ ሊቢያ የሚጓዙ ቁጥራቸው 400 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ኢርትራውያን በፖሊስ ክትትል ተይዘው ሁዳ ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት የታጎሩ ሲሆን ቀድም ብለው እዛው እስር ቤት ውስጥ ከነበሩት 300 ስደተኞች ጋር የቀላቀሏቸው ሲሆን እስር ቤት ሲገቡ ሰውነታቸው በውሃ ጥም እና በምግብ እጥረት በጣም የተዳከመ ሰለነበረ በቦታው የነበሩትም የሱዳን ፖሊሶች በቶሎ ውሃ እንዳይደርስላቸው ስለከለከሉ ብዙዎቹ ተዝለፍልፈው ሲወድቁ ነገሩን በቦታው ሆኖ ሲከታተል የነበረ አንድ የትግራይ ተወላጅ በሆነ እስረኛ በኩል ምናልባት በሚችሉት ቋንቋ ቢነገራቸው ሊሰማቸው ይችል ሆናል ተብሎ ወደ ኢምባሲ በመደውል ነገሩን ቢያስታውቅም የተሰጠው ምልስ ግን ጭካኔ የተሞላበት እኛ እናንተን አናውቅም እንደገባችሁበት ተወጡት የሚል መልስ ነበር።
ባንጻሩ ግን የኢርትራ ተወላጅ የሆኑት ግን ወደ ኢምባሲያቸው ደውለው ነገሩን ሲያሳውቁ የኢንባሲው ባለስልጣኖች ሁኒታውን ለሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣኖች በማስረዳት ችግሩን እንዲፈቱ በማሳሰባቸው ሁኒታው የተነገራቸው የሱዳን ባለስልጣናት ጉዳዩ በትክክል መፈጸሙን ለማረጋገጥ ወደ ቦታው ሲሄዱ ያጋጠማቸው ነገር አስደንጋጭ ስለነበር 40 የሚሆኑት በሙቀቱ ምክኔያት እና በውሃ ጥም ራሳቸውን ስተው በመገኘታቻው ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ተደርጓል ሦስቱ እዛው ሂወታቸው አልፏል የተወሰዱበት ሆስፖታል በትክክል ስላልታወቀ አሁን በምን ሁኔታላይ እንዳሉ ለማንም ግልፅ አይደለም።
ሱዳንኖች እንኳን ለተራ ስደተኛ ኢትዮጵያውያኖች ቀርቶ ዲፕሎማት ነን ለሚሉትም ቅንጣት ታክል ክብር እንደሊላቸው ሰኔ ሁለት የተፈጸመው ክህስተት ምስክር ነው። ይሄውም አቶ መሃመድ ቶፍ የሚባል የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በሱዳን ፖሊሶች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ እራሱን እስኪስት ተደብድቦ በቃሪዛ አምቡላንስ ላይ ተጭኖ ወደ ሆስፒታል ተልኳል። ይህ የሆነው ማሃከማ ሱቅ አለ ማሃሊ በሚባል የገቢያ አካባቤ ባለ ፍርድቤት ውስጥ ነው።
ነገሩም የተነሳው ህጋዊ ባልሆነ ርካሽ ሥራ ላይ ማለትም በካፍቴሪያ ስም በሴተኛ አዳሪነት ይተዳደሩ የነበሩ ሴት እህቶቻችን በጥቆማ ተይዘው ወድ እስርቤት ይላካሉ። ይህ ዲፕሎማት ደግሞ የጥቅም ሰውና ከታሰሩት መሃል በውሽምነት የያዛቸው ሴቶች በመኖራቸው መታሰራቸውን እና ዋስ እንዲፈልግላቸው ካልሆነ እሱ እራሱ ዋስ እንዲሆናቸው ደውልው ያስታውቁታል።
ሴት የላከው እንዲሉ ይህ ዲፕሎማት እሴቶቹ ወደተያዙበት ፍርድ ቤት በመሄድ ለፖሊሶች መታወቂያውን በማሳየት ፖሎሶቹ የሰሩት ትክክል እንዳልነበር በቲቢት ተወጥሮ ይናገራል በዚህም አላቆመም ከአንድ ዲፕሎማት የማይጠበቅ ጽያፍ ቃላት በመናገር ጭራሽ ያዙኝ ልቀቁኝ አበዛ በወገኖቹ ላይ የለመደውን እብሪት የተሞላበት ዘለፋ አበዛ በሁኔታው ትግስታቸው ያለቀው የሱዳን ፖሊሶችም በሚያሳዝን ሁኔታ ቀጥቅጠው ሰባብረው ጣሉት በጣም አሳፋሪ ነበር። ይህን ጉዳይ ለማስተባበል ኢንባሲው ውስጥ የተጠራው ስብሰባም በረብሻና በስድብ በድንጋይ ውርወራ ተጠናቋል።ድሮም በኢንባሲው ቂም የያዘው ስደተኛ በጉዳዩ ተበሳጭቶ ማፈሪያዎች እንደሆኑ ነግሯቸው ተበትኗል።
በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በመታወቂያ ምክኔያት ተይዘው በእየስርቤቱ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ምንም መልስ ያልሰጠው ኢምባሲ ከሃገሪቱ ሸሪያ ህግ ጋር የሚጻረር የሰተኛ አዳሪነት ስራ ሲሰሩ ለተያዙት ሴቶች እህቶቻችንን ለማስፈታት ሲሞክሩ የደረሰበት ውርደት ከፍተኛ ነበር።
ኢምባሲው ውስጥ የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ሲደበደቡ ይሄ የመጀመሪያ አይደለም ከዚህ በፊትም ተደብድበዋል። ከመብት በፊት ጥቅምን የሚያስቀድመው ለወያኔ ግን ይሄ ምንም ማለት አይደለም። ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች ግን አሳፍሪ ድርጌት ሆኖ ይቀራል።ወያኔ ሱዳን የጠየቀውን ማንኛውንም ነገር እሽ ከማለት ውጭ ሊላ አማራጭ የለውም። በሚያዘው ተይዟል ይሄው ዲፕሎማት ሰዎችን ህጋዊ ባልሆነ መንግድ ከኢትዮጵያ እያመጣ ለሱዳኖች እንድሚሸጥም በሰፊው ይወራል ወያኔ ስለሆነ ነው እንጅ ጭራሽ ለዲፕሎማትነት ሊያበቃ የሚችል ስነመግባር የለለው የንዋይ ሰው እንደሆነ ነው የሚታወቀው። ለነገሩ ሱዳኖች ኢትዮጵያኖችን መናቅ የጀመሩት አሁን ሳይሆን ያኔ የአጼ ዩኋንስን አንገጥ ቆርጠው ሙዚየም ውስጥ ካስቀመጡበት ዘመን ጀምሮ ነው።
የአባይ ነገር
አባይ ድሮ አፈራችን ጨረስ አሁን ደግሞ ገንዘባችን ጨረሰ በቦንድ ግዥ የተሰቃየው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባባል ነው።
በጣም የሚያስቆጣው ግፍ ሲፈፀምብን አይመለከተንም ያለው በጀት እየመደበ ይታፈሱልኝ የሚለው ወያኔ ለህዳሴ ግድብ ዕርዳታ ለመጠየቅ ከፍተኛ ዝግጅት ካርቱም በሚገኘው የኢምባሲው ክለብ ላይ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህ የእርዳታ ማሳባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ባጃጅና ቲሸርት በተምቦላ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን በልዩ የሙዚቃ ድግስም የታጀበ ነበር። ኢምባሲው ልዝግጅቱ ብዙ ተሳታፊ አገኛለሁ ብሎ በማሰቡ ብውድ ዋጋ የሚሸጡ የለስላሳ መጠጦችና የተለያዩ የምግብ አይነቶች አዘጋጅቶ ነበር።
በልመና ተፀንሶ በልመና አድጎ በልመና እያረጀ ያለው ወያኔ ልመናን በሃሉ አድርጎት በልመና ባለመርካቱ እንደ ማፊያ ወደ ዝርፊያ የገባው ወያኔ በተለያዩ ሃገራት የተለያዩ የለምና ኮሚቴ አቋቁሞ ቢልክም እየተዋረደ እንደተመለሰ ሃገር ያወቀው ፅሃይ የሞቀው መሆኑ እየታወቀ አይኑን በጨው አጥቦ ወደ ካርቱም መጥቶ ቢሞክረም አለተሳካለተም ዝግጅቱ በተሳታፊ ድርቅ የተመታ ሲሆን በተሞበላ የተጫረተው ባጃጅም የደረሰው እዛው ኢምባሲ ውስጥ ለሚሰራ ሰው ነው።
አይገርምም ሎተሪውም ዘር መምረጥ ጀመረ አየ ዘመን አይ ጊዜ! ሆኖም ግን ሻጥር አለው ተብሎ እንዳይጠረጠር ሎተሪው የደረሰው ሰውየ 17.000 ጨምሮ እንዲውስድ ተብሏል ከዛ በኋላ ይክፈልና ይውሰድ በነጻም ይስጡት የሚውቁት ያው በሚስጥራዊ ስራቸው እራሳቸው ብቻ ናቸው።
“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ሲሉኝ ደስ አለኝ” እንዳለው መዝሙረኛው ዳዊት ካርቱም የሚገኘው የመዳህኔአለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ፅሃይ ገ/ስላሴ ወደ ኢምባሲ እንሂድ ሲሉኝ ደስ አለኝ በማለት በአገልጋዮቻቸውና በመዘምራን ታጅበው በኢምባሲው ዝግችት ላይ የታደሙ ሲሆን $ 12.000 (አስራ ሁለት ሺ ዶላር) ለኢምባሲው ገቤ አድርገዋል።
ከፍተኛ ገቢ ያስገባው ኢትዮ ሱዳን ቡቲክ ተብሎ የሚታወቀው ከኢትዮጵያ የተለያዩ ሸቀጦችን እና ቅመማ ቅመም እንዲሁም በሃላዊ አልባሳትን በተጨማሪም የሃዋል አገልግሎት የሚሰጥ በነጻነት የሚሰራ በካርቱም 16 ቅርጫፍ ያለው የንግድ መደብር ሲሆን $ 13.000 (አስራ ሶስት ሺ ዶላር) ገቢ አድርጓል።
ከዚህ ውጭ የጎላ የገንዘብ እርዳታ ያደረገ የለም በ$ 1.000 ዶላር የተበለጡት አባት ግን እንዴት እበለጣለሁ በማለት $ 13.000 (አስራ ሶስት ሺ) እንዲመዘገብና ቀሪውን $ 1.000 እንደሚያመጡ ቃል በመግባት ተሰብሳቢውን አስገርመዋል ሰውየው ከስደተኛው በተለያየ ምክኔት ህጋዊ በሆነም ባልሆነም መንገድ የተሰበሰበውን ግንዘብ ልግል ዝናቸው ሲሉ ያደርጉት አድርባይነትን የተላበስ ከአባትነታቸው ጋር የማይጣጣም መንፈሳዊ መሆኑ ቀርቶ ፖለቲካዊ ስራ ነበር የስሩት።
በነገራችን ላይ እኔህ አባት አባ ፅሃይ ገ/ስላሴ ከአውስትራሊያ የመጡ ሲሆኑ እዛም ሕዝቡን ለሁለት በመክፈል ከፍተኛ የወያኔ ባለሟል መሆናቸውን ያረጋገጡ ዘመኑ ያመጣቸው የአባት ካባ የለበሱ ካድሪ ናቸው።
የሚገረመው እዚህ ካርቱም ያለው የኢትዮጵያ አምባሰደር ስሙ አባዲ ዝሙ ሲሆን በቅርቡ በዊብ ሳይቶች እንዳየነው በ50 ሚሊውን ብር ያሰራው ቪላ በጣም ዘመናዊ መሆኑን በፎቶ አይተናል። የት አመጣው?
እኛ አባይ ለልማት አይዋል አይደለም እያልን ያለነው። ነገር ግን ያለውን ተጨበጭ ሁኔታ ስናጤን ፣ ግድቡ እየተገነባ ያለበትን ቦታ ስናስብ ፣ አንቀጽ 39 የሚባለው ሰይጣናዊ ህግ በውስጡ የያዛቸውን የህግ ክፍተቶች ስናስብ ፣ የወያኔን የሃገር ፍቅር ሲሜት ሚዛን ላይ ስናስቀምጠው ቀደም ሲል የአማራ ብሄርን ከክልሉ እንደአባረሩ ሁሉ አሁን ደግሞ የሊሎች ብሄር ተወላጆች የሆኑትን ከክልሉ ውጡ ከማለት አልፈው ሰሞኑን እንደሰማነው 14 የሚጠጉ ዚጎችን መግደላቸው አብላጫዎቹ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በዚህ የግድያ ጀርባ የክልሉ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት መረጋገጡ ግድቡ የሚሰራበት ክልል ከሱዳን ጋር አዋሳኝ መሆኑና ያካባቢው ተወላጆች ደግሞ የቢኒሻንጉል ብሄረሰብ ተወላጆች ሲሆኑ ወያኔ ስልጣን እንደያዘ የመግባቢያ ቋንቋቸው አረበኛ እንዲሆን የሚጽፉትም የሚያነቡትም በአረበኛ ፈዳላት እንዲሆን አድርጓ አለበበሳቸውም ከሱዳን ጋር በጣም ተመሳሳይ መሆኑ ሱዳኖችም ቢኔሻንጎል የሚባለው ግዛት የሱዳን እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንዲያውም 18 ዓመት በፊት መተማ የትግራይና የቢኒሻንጉል ጉምዝ ማእከል (መገናኛ) እንደምትሆን ይነገር እንደነበር ይታወቃል። ወያኔ እቅድ (2) ብሎ በያዘው አጀንዳ መሰረት ትግራይን ሲገነጥል ይሄን ግድብ ወደሱዳን በማዞር ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የነበረወን ጥቅም ከሱዳን ወደ ትግራይ ሊያዞረው የማይችልበት ምን ምክኔያት አለ? ከወያኔ ታሪካዊ አመጣጥ አንጻር ካየነው።
ለዚህም ነው ግድቡ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ የበለጠ ፖለቲካዊ ጥቅሙ የሚያመዝን ነው ብለው ብዙ ሙሁራኖች የሚስማሙት። ለዚህም ነው በዚሁ ግድብ ስም እርዳታ ሲጠየቅ በዓለም ዙሪያ በነጻነት የሚኖሩት ኢትዮጵያዋያን መልስ የማይሰጡት በእርግጥ ወያኔ እንደፈለገ በሚያደርግበት ኢትዮጵያ ግን የድሃውን ሕዝብ አፍንጭን ይዞ ያስከፍላል።
ካርቱም የተደረገውን የአባይ ግድብ የእርዳታ ማሰባሰቢ ዝግጅት እስፖንሰር ያደረጉት የንግድ ድርጅቶች እነዚህ ናቸው፡
1. አቢሲኒያ ቡቲክ
2. አዲስ ቡቲክ
3. ስታር የወንዶች ሳሎን
4. አፍሪካ ምግብ ቤት
5. ቶፊቅ ኬር ጋራዥ
6. አንበሳ ቡቲክ
7. ሚኪ ቡቲክ
8. ኤደን ምግብ ቤት
9. መቲ የውበት ሳሎን
10. ሃና ምግብ ቤት
11. መሃሪ ምግብ ቤት
2. አዲስ ቡቲክ
3. ስታር የወንዶች ሳሎን
4. አፍሪካ ምግብ ቤት
5. ቶፊቅ ኬር ጋራዥ
6. አንበሳ ቡቲክ
7. ሚኪ ቡቲክ
8. ኤደን ምግብ ቤት
9. መቲ የውበት ሳሎን
10. ሃና ምግብ ቤት
11. መሃሪ ምግብ ቤት
“ኢትዮጵያ አንደነቷ እንደተጠበቀ ለዘላለም ትኑር”!!!
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen