June24/2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ተከሳሽዋ ወ/ሮ አልጋነሽ ገብሩ ባራኪ ይባላሉ። መንግስትን በሃይል ለማፍረስ በማሰብ የአሸባሪነት ተግባር ፈጽማለች ተብላ በትግራይ ክልል መንግስት ተከሳለች። ሁኔታውን በቅርብ የተከታተለው በስፍራው የሚገኘው አብርሃ ደስታ ነው። እንዲህ በማለት ዘገባውን ይቀጥላል።
የእንደርታ እግሪሓሪባ ሰዎች መሬታችን ስላሉ፣ ፍትሕ ስላሉ፣ እነሆ ለሦስት ዓመታት የመንግስት አገልግሎት (ትምህርት የማግኘት መብት፣ ህክምና የማግኘት መብት፣ የፖሊዮ ክትባት ወዘተ) ተከልክለው ቆዩ። መንግስት ራሱ በፈጠረው ችግር አሁን ኗሪዎችን በሽብር ወንጀል (ማንን እንዳሸብሩ እንጃ) ተከሰዋል። አንድ ዳኛ እንደገልፀው የተከሰሱበት የሽብርተኝነት ወንጀል በ97ቱ የቅንጀት መሪዎች የተከሰሱበት ዓይነት ነው።
ከታሰሩ የእግሪሓሪባ ኗሪዎች አንዷ ወይዘሮ አልጋነሽ ገብሩ ትባላለች። የሰማእት ቤተሰብ ናት (ስድራ ስውእ)። አራት ልጆች ብቻዋ ታሳድጋለች (አባታቸው ሞቷል)። ትምህርት የላትም። አርሶአደር ናት። ትንሹ ልጇ የ አምስት ዓመት ህፃን ነው። ምግብ የሚሰጠው የለም። ያከባቢው ኗሪዎች በየተራ ምግብ ያቀብሏቸዋል። መሬታችንን አትንጠቁን ስላለች እነሆ በሽብርተኝነት ተከሳለች። የመንግስት ጥፋት ሁሉ የሷ ሆኗል። መንግስት ያጠፋው ሁሉ እሷ ተጠያቂ ሆናለች።
እስቲ ክሱ አንብቡት። ትገረማላቹ። አራት ገፅ ነው። በቅደም ተከተል ይነበብ። በትግራይ ለ አንዲት ድኻ አርሶደር እንዲህ ይባል እንደሆነ ራሳች ሁ ትጠይቃላቹ። ይሄ ስርዓት ይጠየቅ።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen