የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአገሪቷ ሕግ እውቅና አግኝቶ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድት የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። ዜጎች በተሰማቸው አጀንዳን ዙሪያ የመጻፍ፣ የመናገር ፣ ሰላማዊ ሰልፎች የማድረግ ምብት እንዳላቸው ሕገ መንግስቱ በግልጽ አስቀምጧል። በሕገ መንግስቱ መሰረት የደብረ ማርቆስ ሕዝብ ድምጹኝ ማሰማት ይችል ዘንድ፣ የአንድነት ፓርቲ ሰኔ አንድ ቀን ሰልፍ ጠርቷል። በሕጉ መሰረት የከተማዋን አስተዳደር ያሳወቀ ሲሆን፣ ከአስተዳደሩ የ እውቅና ደብዳቤ አግኝቷል።
እንደዚያም ሆኖ ግን በደብረ ማርቆስ፣ የአንድነት ቀስቃሾች ሕዝቡ ስለ ሰልፉ ያውቅ ዘንድ የለጠፋቸውን ፖስተሮች ፣ የኢሕአዴግ ካድሬዎች እየቀዳደዱ ሕግ ወጥ ተግባራት ፈጽመዋል። በአንድ በኩል ባለስልጣናት እውቅና ሰጥተው፣ በሌላ በኩል ፣ በተለየ መመሪያ ሰልፉን ለማጨናገፍ የሚደረገው ሙከራ ምን ያህል አገዛዙ እራሱ ለሕግ ከበሬታ እንደሌለው የሚያሳይ ነው።
በድብረ ማርቆስ ያሉ ካድሬዎች ይየቀደዱትን አንድ ፖስተርና አንዱን የአንድነት አስተባባሪ ላይ መዛታቸዉን የሚያሳይ መረጃ ይመልከቱ።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen