የኮካኮላ ተወካይ በኢትዮጵያ አቶ ምስክር በድንገት ባልታወቀ ምክንያት ሃሳቡን በመቀየሩ ቴዲ አፍሮ ከኮካኮላ ጋር ሰርቶት የነበረው የዓለም ዋንጫ ዘፈን ሳይለቀቅ በመቅረቱ አርቲስቱ ከፍተኛ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ደጋፊዎቹ የኮካኮላን ምርቶችን ያለመጠቀም ዘመቻ (#boycottcocacola) በማህበራዊ ድረገጾች ከፍተው ሰንብተዋል።
ይህ ሁኔታ ያሳሰበው ኮካኮላ መናገር የጀመረ ሲሆን የቴዲ አፍሮ ጉዳይ በሶስተኛ ወግን “ማንዴላ ሊሚትድ” በተባለ ኩባንያ አማካኝነት ተይዞ እንደነበርና በስምምነታቸው መሰረት የቴዲ አፍሮ ስራም ሙሉ ለሙሉ የኮካኮላ ነብረት ሆኖ ይኖራል ብሏል።
ቴዲ አፍሮ ለሰራው ስራ ተገቢው ክፍያ እንደተከፈለው ያስረዳው ኮካኮላ የቴዲ አፍሮ ስራ ለምን እንዳልተለቀቀ ግን ከማብራራት ተቆጥቧል።
ኮካኮላ በዓለም ዋንጫ ዋዜማ በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥቆ ምርቶቹን ሲያስተዋውቅ ከርሞ በሞቃታማዎቹ የብራዚል ከተሞች ኮካኮላን በገፍ ለመሸጥ እየተሰናዳ ባለበት ሁኔታ ነው የኢትዮጵያውያኑ ያልተጠበቀ ተቃውሞ የማህበራዊ ድረ-ገጾችን ማጥለቅለቅ የያዘው። ይህ ሁኔታ ኮካኮላን በእጅጉ ቢያሳስበው የሚደንቅ አይደለም። #ethiopia #teddyafro
Coca-Cola under fire for dropping Teddy Afro’s World Cup Anthem
June 4, 2014
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen