Netsanet: አሳዛኝ ዜና ሳሪስ ቻይናዊ 3 ተማሪዎች ሕይወት ቀጠፈ

Freitag, 23. Januar 2015

አሳዛኝ ዜና ሳሪስ ቻይናዊ 3 ተማሪዎች ሕይወት ቀጠፈ

አሳዛኝ ዜና ሳሪስ የባቡር ፕሮጀክት ስራ የሚሰራ ቻይናዊ በሎደር ማሽን የፍሬ ሕይወት ት/ቤት አጥር በመደርመስ 3 ተማሪዎች ሕይወት ቀጠፈ

ዛሬ ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሳሪስ ካዲስኮ የባቡር ፕሮጀክት ስራ የሚሰራ ቻይናዊ በሎደር ማሽን የፍሬ ሕይወት ት/ቤት አጥር በመደርመስ በስፖርት ክፍለ ጊዜ ግቢ ውስጥ የነበሩ 3 ተማሪዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ በርካታ ተማሪዎች ከፍተኛና መካከለኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ቦታ ሄደዋል፡፡ በተጨማሪም በቅርብ እርቀት ቡና ቦርድ እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ቻይናው የጥበቃ ሰራተኛውን ሲመታው ለመከላከል ሲል በያዘው አጣና ሲመታው በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች ሁለቱንም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ የሕፃናት ተማሪዎች ያለአግባብ መሞት የፍሬ ሕይወት ተማሪዎች በአስነሱት ከፍተኛ ቁጣ የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ በተማሪዎች ላይ አድርሷል፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው የሕፃናቶች ሞት ሳይታሰብ ቻይናውያንን የፌዴራል ፖሊስ በማጀብ በተዘጋጀላቸው መኪና ወደ ቤታቸው ሲሄዱ የህዝብ መገልገያ በሚመስል ታክሲ በርካታ ተማሪዎች ወደ እስር ቤት ተጉዘዋል፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen