Netsanet: Oktober 2018

Sonntag, 21. Oktober 2018

21/10/2018 አላማጣ በአላማጣ እየተካሄደ ባለው የራያ ህዝብ ተቃውሞ በትግራይ ልዩ ኀይል 4 ሰዎች ተገደሉ

ዜና አላማጣ

በአላማጣ እየተካሄደ ባለው የራያ ህዝብ ተቃውሞ እስካሁን 4 ሰዎች በትግራይ ልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውን እንዲሁም ከ15 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን  ከስፍራው ያነጋገርናቸው ሰዎች ተናግረዋል። ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው። ፊልሙ ከስፍራው የሚገኙ ተወላጆች የላኩልን ነው።






Samstag, 20. Oktober 2018

የለውጥ ሀይሉ እውነተኛ ከሆኑ ስራቸውን ይስሩ እኛም ስራችን እንስራ:: ማገዝ የሚለውን ቃል አልወደውም ::(በ ርዕዮት አለሙ)

በ ርዕዮት አለሙ

የለውጥ ሀይሉ እውነተኛ ከሆኑ ስራቸውን ይስሩ እኛም ስራችን እንስራ:: ማገዝ የሚለውን ቃል አልወደውም :: ምንድን ነው ማገዝ ማለት ለመሆኑ ? እኔ እኮ ኢትዮጵያ ሀግሬን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ድሮ ያኔ ለትግል ስነሳ ዶር አብይ የሚባል ሰው ከነመፈጠሩም አላውቅም ::

  የ  ትግሌ አላማ እና ግብ ዶር አብይን ለማገዝ አይደለም አይሆንምም... አላማየ ኢትዮጵያ ሀግሬን ዲሞክራሲት የማድረግ ትልቅ ራዕይ ነው:: እኔ ይህ አላማየ እስኪሳካ ትግሌን እቀጥላለሁ:: በዚህ የ ትግል ጎዳና ላይ እያለሁ ዶር አብይ የሚባል ሰው ከ ኢህአዴግ ወጥቶ አይ እየሄድንበት ያለው መንገድ ልክ አይደለም ብሎ ኢትዮጵያን ለመቀየር ከተነሳ  እሽ ጥሩ ...ይህ ከሆነ ትክክለኛ ስሜቱ ደግ ነው::  እኔም ትግሌን እቀጥላለሁ መንገድ ላይ እንገናኛለን:: ነገር ግን እየሆነ ያለው ነገር ይህን አያሳይም::
 
    በ ግልፅ በ አደባባይ ሀገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሀቅ ግን ተስፋ ሰጭ አይደለም ...እንደተባለለትም ወደ ዲሞክራሲ እየሄድን አይደለም...አንድ አንዶች ይህን ጥሬ ሀቅ እያዩ ዶር አብይን ከማገዝ ውጭ ምን ምርጫ አለ ለምትሉ መልሴ ምርጫ ካሳጡ በሗላ ምን ምርጫ አለ ይባላል እንዴ ? እየሆነው ያለው እኮ ምርጫ የማሳጣት ነገር ነው::

     ለምሳሌ አሁን የተፈጠረውን ችግር ከስሩ እንመልከተው:: የ አዲስ አበባ ወጥቶች ለምን ለመደራጀት ተነሱ ብሎ መጠየቅ ደግ ነው?  ሆሮሞሳ ፊንፊኔ በሚል ስም የተደራጁ ወይም እንዲደራጅ ያደረጉ ሰወች እኮ በ አደባባይ የ ጥላቻ ንግግር ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው ይህም ይታወቃል:: እነዚህ ሰወች ተሰብስበው ምን ነበር ሲያወሩት የነበረ ? የ ሚያቃቅር የሚያጣላ የምያጋጭ አይደለም ን? እነዚህ ሰወች ተደራጅተው የፍለጉትን እንዲናገሩ እየተደረገ ነው :: እንዲህም እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል::

    በሌላ በኩል ይህን አደጋ የተገነዘቡ የ አዲስ አበባ ወጣቶች የ አዲስ አበባን ወጣት ለማደራጀት ሲሞክሩ አንጠልጥለው እስር ቤት ወረወሯቸው::  እነዚህ ወጥቶች ሄኖክ እና ማይክ ወንጀላቸው ምንድን ነው ?  ወንጀላቸው መደራጀት ነው ተባለ ...

   ይህ ግልፅ መድሎ ነው ! ለ አንዱ መፍቀድ ሌላውን መከልከል ብቻ እንኳ አይደለም  ልትደራጅ ነው ብሎ ማሰር !  እዚህ ውስጥ  የ ዶር አብይ እጅ የለበትም ብሎ ነገር አይጥመኝም... ጥሩ ጥሩውን ለ ዶር አብይ  እንዲህ አይነት ግፍ እና በደሉን ለ ለውጥ ቀልባሾች መስጠት ትክክል አይደለም::

  ሲጀመር የለውጥ ሀይሉ የ ለማ ቲም የሚባለው ቁጥራቸው ስንት ነው እነማን ናቸው የሚባለው ነገር ግልፅ አይደለም::

   ሌላው የሚገርመው ነገር  የ ቤተመንግስቱ የ ወታደሮች ሁኔታ ነው:: በ እለቱ ዶር አብይ ወጥተው ከ ደሞዝ ጋ የተያያዘ ነው አሉን ከዛም ከዚህ በተቃራኒ መረጃ አለን ያሉትን ሰወች ውሸታማሞች አስባሉ::

   አሁን ወጥተው አይ ያን ጊዜ የነገርኳችሁ እውነት አይደለም ሌሎች ያሉት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ትክክል ነበረ አሉን ::  እንግዲህ ከሁለቱ የቱን እንመን ሲባል ያንም ይህንም እመኑኝ የሚሉት ነገር ነው::  እኔ ያ ነው ይህ ነው የሚል ክርክር ውስጥ አልገባም ነገር ግን ሁለቱንም እመኑኝ የሚሉት ነገር ትክክል አይደለም:: ስለ ሰበታ ለጋጠፎ እና ቡራዮ የተናገሩት ነገር የሚገርም ነው ! እውነት እየመጡ ነበር የሚለው ነገር እንዳለ ሁኖ  ለማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ምንድን ነው ብሎ መጠየቅ ግድ ይላል :: እኔ የሚታየኝ ድራማ ነው ለምን እንዲህ አይነት ድራማ ለመስራት ተፈለገ::

  ማሳስቢያ::
ይህን ፅሁፍ የ ፃፍኩት ርዕዮት አለሙ በ ኢሳት እለታዊ ያደርገችውን ውይይት ተመርክዤ ቢሆንም ንግግሩን ወደ ፅሁፍ ሲገለብጥ ትንሽ  ማጣፈጫ ተጠቅሚያለሁ::
CC Eskedar Alemu Gobebo

Donnerstag, 18. Oktober 2018

ጊዜው የእኛ ነው በሚሉ የብሄር አቀንቃኞች ዜማ መደነስን መርጠዋል። ( ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

አቶ ታዬ ዳግም መስመር ስተዋል። ለተቀመጡበት ወንበር የሚመጥን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የብሽሽቅ ፖለቲካ ውስጥ ተነክረዋል። እልህ ሲተናነቃቸው ፌስቡክ ከፍተው እንዳለ እንደወረደ ይዘረግፉታል። ትላንት የረገሙትን ወገንተኝነት ዛሬ እሳቸው ያቀነቅኑት ጀምረዋል። ትላንት የተጠየፉትን ኢፍትሀዊነት ቋንቋ ሳይቀይሩ እንዳለ ገልብጠው እያሳዩን ነው። ጊዜው የእኛ ነው በሚሉ የብሄር አቀንቃኞች ዜማ መደነስን መርጠዋል። ማዳላት አይበጅም እያሉ በማዳላት ተጠምደዋል። እሻጥርን እያወገዙ በአሻጥር የተንቆጠቆጠ የፖለቲካ መስመር ላይ ሽምጥ እየጋለቡ ነው። በግማሽ መላጣ ሆነው ጎፈሬውን እያብጠለጠሉት ነው። 'ህገወጥነት' ብለው የሚከሱትን አካል በህገወጥ መስመር ለማረም ወገባቸውን ታጥቀው ተነስተዋል። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት የመንግስትን ትልቁን ሃላፊነት ተሸክመው ነው። ያውም ፍትህን በእኩልነት ያሰፍናል ተብሎ በሚጠበቅ የሃላፊነት ወንበር ላይ ተቀምጠው።

አቶ ታዬ በዚሁ መቀጠል የሚገባቸው አይመስለኝም። ስሜታቸውን መቆጣጠር ካቃታቸው፡ ነጻ ግለሰብ ሆነው እንደፈለጋቸው ሀሳባቸውን የሚያስተላልፉበትን፡ አቋማቸውን የሚያንጸባርቁበትን፡ ወገኔ ለሚሉት አካል የሚቆሙለትን ሌላ መንገድና ቦታ ቢፈልጉ ለእሳቸውም፡ ለጤናቸውም፡ ለድርጅታቸውም፡ ለመንግስታቸውም የሚበጅ ይሆናል። ከተቀመጡበት ወንበር እኩልነትን እንጠብቃለን። ከጨበጡት ሃላፊነት ሚዛናዊ ፍርድ እንሻለን። ተራ ብሽሽቅ ውስጥ ተነክረው፡ የቃላት ጦርነት ላይ መጠመዳቸውን ያቁሙት። ቢያንስ ለወንበራቸው ክብር ዘብ ይሁኑ።

አንድ ተጨማሪ ወንድማዊ ምክር። እንዲህ እልህ ሲተናንቅዎት ከፌስ ቡክ አከባቢ ይራቁ። ሰውነትዎን ላላ አድርገው፡ ቀዝቃዛ ውሃ ፈልገው ትንሽ ጎንጨት ይበሉ። እርስዎ ዘንድ ያለው አይበገሬነት ሌላውም ጋር መኖሩን እንደማይዘነጉ ተስፋ አደርጋለሁ። የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለም። ጊዜው የእኛ ነው የሚለው ጋርዮሻዊ አስተሳሰብ ብዙ ርቀት አይወስድም። የህወሀት ባለሟሎች የትዕቢት ተራራ እንዴት እንደተናደ ከእርስዎ የተሰወረ አይመስለኝም። ትዕቢት የሰነፎች ጊዜያዊ ጉልበት ነው።

ቤተመንግስት የሚገኘው የለውጥ ሃይል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ደረጃ የሚተላለፉ መልዕክቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርግ ዘንድ ይጠበቃል። ዜጎችን በእኩል አይን መመልከት የሚገባቸው የመንግስት ሃላፊዎች ደምና አጥንት እየቆጠሩ ፍርድ የሚሰጡ ከሆነ ውጤቱ ለሁላችንም አይበጅም። የህወሀት መሪዎችም እኮ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ያወገዝናቸው፡ የታገልናቸው፡ እኩል ስለማያዩን ነበር። ውድቀታቸውን በጸሎትና በእልህ አስጨራሽ ትግል እንዲመጣ የናፈቅነው እኮ የበላይና የበታች መሆንን ተጠይፈን፡ አንገሽግሾን ነው።

ስሜታቸውን በማይቆጣጠሩ፡ ከሀሳብ ይልቅ ዘርና ብሄር እየጠሩ የሚሰብኩ፡ የሚፈርዱ መሪዎችን አደብ ማስገዛት የመንግስት ሃላፊነት ነው።