Netsanet: 2017

Mittwoch, 15. November 2017

የብሄራዊ ደህንነት ዕቅድ ወይስ የህወሀት የስንብት ደብዳቤ? ( ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

የብሄራዊ ደህንነት ዕቅድ ወይስ የህወሀት የስንብት ደብዳቤ?
መቀሌ
ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ሰዓት መቀሌና ሀራሬ ሁነኛ የፖለቲካ ክስተት ተፈጥሯል። የመቀሌው ይፋ የወጣ አይደለም። በህወሀት አፍቃሪያን ድረገጾች የተተነፈሰ ወሬ ነው። ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመቀሌውን ህንፍሽፍሽ ረግጠው ወጡ የሚለው ከውስጥ አዋቂ ያፈተለከው ዜና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በትክክል ከሆነ የሀራሬው ዓይነት መፈንቅለ መንግስት ልናይ የምንችልበት እድል ሰፊ ነው። የጄነራል/ፕሮፌሰር ሳሞራ የኑስ ቡድን በመቀሌው ስብሰባ ከተሸነፈ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ አይሆንም። በአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባው ህወሀት በአንዳች ተአምር መከላከያውን ከሳሞራ የኑስ እጅ ፈልቅቆ ካልወሰደ በቀር የወ/ሮ አዜብ መስፍን ኩርፊያና ረግጦ መውጣት የሚያስከትለው መዘዝ ለህወሀት ፍጻሜው ሊሆን ይችላል።
ትያትሩን አድፍጦ መከታተሉ ጥሩ ነው። ያም መጣ፡ ይሄም ሄደ ልዩነት የለውም። ለኢትዮጵያ ህዝብ የትኛውም የህወሀት አንጃ አይበጀውም። ህወህት ቢከፈልም፡ ቢሰነጣጠቅም ያው ህወሀት ነው። ከነስሩ ተመንግሎ፡ ተጠራርጎ መወገድ ያለበት እንጂ ክፋዩ፡ ስንጣቂው ቢተርፍና በስልጣን ላይ ቢቆይ ለኢትዮጵያና ህዝቧ ተውሳክ፡ ነቀርሳ መሆኑ የማይቀር ነው።

ሀራሬ
የዙምቧቡዌ ሰማይ ያልተለመደ አየር ነፍሶበታል። የ40 ዓመቱ የሙጋቤ ስዩመ እግዚያብሄር አገዛዝ ፍጻሜውን አግኝቷል። በስልጣን ላይ በመቆየት የዓለምን ክብረወሰን የጨበጡት ሽማግሌው ሙጋቤ ከነሚስታቸው በወታደሩ ክፍል ለጊዜው በማቆያ ይገኛሉ። ብሄራዊው ቴሌቪዥን ላይ የዚምቧቡዌ ጦር መሪዎች መግለጫ እየሰጡ ነው። በአጭሩ መፈንቅለ መንግስት ተካሂዷል። ለዚምቧቡዌ አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል። ሰውዬው በአጥንታቸው ሳይቀር ጨምድደው እየገዟት ያለችው ሀገር በአዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ወጥታለች። ሁኔታዎች በፍጥነት በሚለዋወጡባት ዚምቧቡዌ የሚሆነው ነገር አይታወቅም። ታሪክ ግን ተቀይሯል።
ዚምቧቡዌ በአንድ ስልጣኑን እስከመቃብሩ ድረስ ላለመልቀቅ በወሰነ ሽማግሌ የስንግ ተይዛ ለ40 ዓመታት ቆይታለች። ኢትዮጵያ በዘርና ጎሳ በተቧደኑ፡ በዘረፋና ሌብነት ሀገሪቱን ለመጋጥ በተሰለፉ የአንድ መንደር ልጆች ከሩብ ክፍለዘመን በላይ ደሟ እየተመጠጠ ያለች ሀገር ናት። የዚምቧቡዌ ጦር የዚምቧቡዌ ነው። የኢትዮጵያ ጦር የኢትዮጵያ አይደለም። በዚምቧቡዌ መፈንቅለ መንግስት ቢካሄድ አዲስ ስርዓት በተስፋ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ ግን መፈንቅለ መንግስት የህወሀትን አገዛዝ በመሳሪያ ሃይል የሚያስጠብቅ ሌላ የጨለማ ዘመን የሚያመጣ እንጂ ለውጥ አይኖረውም።
ዕቅድ ወይስ ስንብት?
ለአዲስ ስታንዳርድ በቅድሚያ ምስጋና ይገባዋል። ይህ ሰነድ ወይም ዕቅድ ወይም ኑዛዜ ወይም የስንብት ደብዳቤ ይደርሰን ዘንድ የአዲስ ስታንዳርድ ውለታው ላቅ ያለ ነው። ሰነዱ በጣም ጠቃሚ ነው። በጣምም ወሳኝ ነው። ለነጻነትና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መምጣት ለሚዋደቁ ሃይሎች በተለይም በለውጥ ምጥ ላይ ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ዕቅድ ተስፋን የሚያለመልም ነው። በእስከአሁኑ በዚህ ደረጃ የህወሀት መንግስት ውድቀቱን ያመነበት ሰነድ አላየሁም። የጠቃሚነቱን፡ የወሳኝነቱን ያህል ግን ትኩረት አልተሰጠውም። ኢትዮጵያ እንደዚምቧቡዌ ያረጀውንና፡ የጃጀውን ስርዓት ልትገላገለው በዋዜማው ላይ መሆኗን የሚያበስር ዕቅድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ዝርዝር ዕቅዱ የህወሀትን የወቅቱን ቁመና የሚያሳይ ነው። ውስጣዊ ሁኔታዎች በሚል በ10 ነጥቦች የተዘረዘሩትን ከወሰድን ከአንድ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን። የህወሀት መንግስት በእርግጥም አብቅቶለታል። በተቃራኒው ያለው የለውጥ ሃይል ጠንካራ ባለመሆኑ፡ ወይም፡ በአንድነት ባለመሰለፉ ወይም በሁለቱም ምክንያቶች የተነሳ እየፈራረሰ ያለውን የህወሀት ስርዓት ወደመቃብሩ መውሰድ ባለመቻሉ ህወሀት ለጥቂት ጊዜያትም ቢሆን እድሜው እንዲቀጥል እየሆነ ነው። የህወሀትን ኑዛዜ ዋና ዋና ክፍሎችን እንመልከተው።
ህዝብ ተስፋ ቆርጦብኛል
ህውሀት አልደበቀም። እንደሁልጊዜውም የህዝብ ተስፋ ነኝ የሚል ባዶ ኩሸት መደለቅ አልፈለገም። በዕቅዱ ላይ እንደተናዘዘው ህዝቡ ተስፋ ቆርጦበታል። ህዝብ በህይወት የመኖር ተስፋው እየቀነሰ፡ እየጨለመ መምጣቱን፡ በስርዓቱ ላይ ተስፋ የመቁረጥና ይህ ስርዓት ይቀጥል ይሆን የሚል ብዥታ ውስጥ መግባቱን ይገልጻል። ህዝቡ የሰላም ዋስትና ማጣቱንም ህወሀት አምኗል። ስጋት ውስጥ የተዘፈቀ፡ በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ላይ እምነት አጥቶ ውዥንብር ውስጥ የገባ ህዝብ ሲልም ያስቀምጣል። ህዝቡ ብቻ ሳይሆን ሰራዊቱም ተስፋ እንደቆረጠበት ተናዟል። ለህወሀት ትልቁ አደጋ ይሄ ነው። የጸጥታ ሃይሉ ሰላም የማስከበር አቅሙ መጎዳቱን፡ በመንግስት መቆየት ላይ ጥርጣሬ ውስጥ መግባቱን፡ በአጠቃላይ መሰላቸትና ተስፋ መቁረጥ በሰራዊቱ ውስጥ መከሰቱን አትቷል።
ጸረ-ሰላም ሃይሎች(የለውጥ ሃይሎች)
ይህን ዕቅድ ላነበበ አንድ ነገር ግልጽ ይሆንለታል። በኢትዮጵያ ውስጥ የህወሀትን ስርዓት ገንድሶ ለመጣል የተስለፉ ሃይሎች እግር አውጥተው ረጅም ርቀት እየተጓዙ ለመሆናቸው ትልቅ ማስረጃ የሚሆን ሰነድ ነው። ተቃዋሚዎች የታላችሁ? መሳሪያ የታጠቀ ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ወይ? ለሚሉ ሰዎች የህወሀት ዕቅድ አጥጋቢ መልስ ይሰጣል። በዕቅዱ ላይ እንደተገለጸው አርበኞች ግንቦት ሰባትና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በሀገሪቱ እንደፈለጉ በመፈንጨት ላይ ናቸው። እነዚህ ሃይሎች በፕሮፖጋንዳው ጭምር እንደበለጡትም አምኗል። ሃይላቸው ተጠናክሯል። ህዝብን ከጎናቸው እያሰለፉ ነው። ለጦርነት የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ እየሰበሰቡ ነው። መሳሪያ ግዢው ተጧጡፏል። እነዚህ ሃይሎች መንግስት ተዳክሟል፡ ሀገር ለመምራት አይችልም ከሚል ድምዳሜ ደርሰው ስርዓቱን ሊያፈራርሱ እየተረባረቡ ነው ሲል ህወሀት የመጣበትን አደጋ በግልጽ አስቀምጧል።
ጸረ ሰላም(የለውጥ) ሃይሎች ውስጡን እንደቦረቦሩት ህወሀት በገደምዳሜም ቢሆን ገልጿል። አመራሩ በተለይም መካከለኛውና የታችኛው አመራር በእነዚህ ሃይሎች ፕሮፖጋንዳ ታጥቦ ተወስዷል የሚለው ህወሀት በሀገሪቱ ለተከሰተው አጠቃላይ ቀውስም የራሱ መዋቅር ላይ ጣቱን ቀስሯል። አርበኞች ግንቦት ሰባትና ኦነግ የብአዴን፡ ኦህዴድንና ደኢህዴንን መዋቅር ሰብረው መግባታቸውን በመግለጽ በተለያዩ ጊዜያት ለሚወጡ ጥሬ መረጃዎች ማረጋገጫ የሚሰጥ ኑዛዜ ነው። ህወሀት በዚህ ዕቅዱ የተቃዋሚዎች(የጸረ ሰላም ሃይሎች) መጠናከርን የህዝብ ስጋት የፈጠረ ሲል ይገልጸዋል። በእርግጥ ተቃዋሚዎች በዚህ ደረጃ ማንሰራራትና መጠናከር መቻላቸው ለህዝብ ስጋት አይሆንም። መርዶም አይደለም። ተስፋ እንጂ። ተቃዋሚዎችን ፍለጋ በየሰፈርና መንደሩ የሚሰማውን የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የሚመልስ የወቅቱ ታላቅ የምስራች እንጂ።
ኢኮኖሚው አደጋ ላይ ነው
የህወሀት ኑዛዜ በኢኮኖሚው ላይ ያስቀመጣቸው እውነቶች በተለያዩ የነጻነትና የዲሞክራሲ ደጋፊ ሚዲያዎች ሲባል የነበረውን የሚያረጋግጥ ነው። ህወሀት ግብር መሰብሰብ እንዳልቻለ ገልጿል። መንግስት የለም፡ ግብር አትክፈሉ የሚል ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው ብሏል። በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ሳቦታጅ( ዶ/ር ታደሰ ብሩ አሻጥር ይለዋል) እየተፈጸመ መሆኑን አትቷል። ህዝቡን ለልማት ከማሰማራት ይልቅ የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመ ለግጭትና ለሰላም መደፍረስ ሚና እንዲጫወት እየተደረገ ነው ያለው ህወሀት በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚው ክፉኛ መጎዳቱን አስታውቋል። የውጭ ኢንቨስትመንት ተዳክሟል። የቱሪስት ፍሰት ቀንሷል። የውጭ እርዳታ በከፍተኛ መጠን ወርዷል።
የህወሀት ዕቅድ ላይ እንደተገለጸው ባለሀብቶችና ኢንቨስተሮች ሀብትና ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ ከሀገር እያሸሹ ናቸው። እነማን እንደሆኑ በእርግጥ አልተገለጸም። መረጃዎች የሚያመለክቱት የህወሀት ባለስልጣናትና በዘር መስመር ሀብት ያፈሩ የትግራይ ተወላጆች በዋናነት ሀብት እያሸሹ መሆናቸውን ነው። በነገራችን ላይ ማክሰኞ አንድ ሪፖርት ወጥቷል። የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ከ10ሩ ገንዘብና ሀብት ከሚሸሽባቸው የዓለም ሀገራት ውስጥ አስገብቷታል። በዚህም ምክንያት ከኢትዮጵያ በሚሸሸው ሀብትና ገንዘብ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው። ለ28ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ሰርኩላር ተበትኗል። የህወሀት ባለስልጣናት አንዱ የሀብት ማሸሺያ መስመር አሁን ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ታስሯል። የሼህ አላሙዲን መታሰር በህወሀት መንደር ሽብር የፈጠረው ያለምክንያት አይደለም። እናም ህወሀቶች ለጡረታቸው ያሸሹት ሀብትና ገንዘብ ወጥመድ ውስጥ ገብቷል።
ጄኖሳይድ
የዚህ ዕቅድ አስደንጋጩ ክፍል ይሄው ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን ህወሀት ገልጿል። በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መሃል በተፈጠረው ግጭት ጄኖሳይድ ተፈጽሟል ያለው የህወሀት የደህንነት ዕቅድ እነማን እንደፈጸሙ፡ ምን ያህል ሰዎ እንዳለቀ በዝርዝር አያስቀምጥም። የፖለቲካ ተንታኞች ህወሀት ሌሎችን ለማጥመድ የስነቀራት ምክንያት ልትሆን ትችላለች የሚል ሀሳብ ያቀርባሉ። በተለይም የሁለቱን ክልሎች በዋናነትም የኦሮሚያ ክልል መሪዎችን ለማስበርገግ ሊሆን እንደሚችልም ይገልጻሉ። ሆኖም ህወሀት ሳያስበው ራሱ ላይ ጥይቱን አቀባብሏል የሚሉ ወገኖችም አሉ። ህወሀት በሚቆጣጠራት ሀገር ጄኖሳይድ ተፈጽሞ ከሆነ ይህን የምድረግ አቅም ያለው የህወሀት ጦር በመሆኑ በቀጥታ ተጠያቂ የሚሆነው የህወሀት መንግስት ነው። ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ለመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥሩ ዱላ ነው። ሌሎች በኢትዮጵያ የተፈጸሙና የተደበቁ የጅምላ ግድያዎች የሚነሱበትና ተጠያቂዎች ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ የሚቀሰቅስ ሊሆን ይገባዋል። በኦጋዴናን በአኝዋክ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጽሙትን ጄኖሳይዶች ማን ይረሳቸዋል?
የጦስ ዶሮ
ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩ ቀውሶች ራሱን ተጠያቂ ከማድረግ ተቆጥቧል። ሶስት አካላት ላይ ጣቱተቀስሯል። ግብጽና ኤርትራ በረጅም እጃቸው ኢትዮጵያን እየበጠበጡ ነው የሚል ክስ በህወሀት ቀርቧል። አርበኞች ግንቦት ሰባትና ኦነግ ሀገሪቱን በማመስ ተወንጅለዋል። የስርዓቱ አመራሮች ለቀውስ የተመቸ ሜዳ በመፍጠር ጥርስ ተነክሶባቸዋል። በዕቅዱ ላይ አንድም ቦታ ህወሀት ሃላፊነት አልወሰደም። አሁንም ለኢትዮጵያ ህዝብ መላዕክ መሆኑን ይገልጻል። የጦስ ዶሮዎች እየተፈለጉ ነው። በተለይ በስርዓቱ ውስጥ ያኮረፉት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል። መጠነ ሰፊ እስሮች ከፊት እንደሚኖሩ ይጠበቃል። የዕቅዱ አንድም ግብ እነዚህን አመራሮች ልክ ማስገባት ነው።
የዕቅዱ ግብ ሌሎች ተግባራትንም ያከናውናል። ሰልፎች ታግደዋል። በአስቸኳይ አዋጁ ገደብ የተጣለባቸው መብቶች በተዘዋዋሪ በዚህኛው ዕቅድም ተግባራዊ ይሆናሉ። ዕቅዱ በስም እንጂ በይዘት ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር አንድ ነው። የዕቅዱ ሌሎች ግቦች ከፉከራ ያለፉ አይደሉም። መሳሪያ መንጠቅ፡ ጸረ ሰላም ሃይሎችን መደምሰስ እና የመሳሰሉት ግቦች አሁን ህወሀት ካለበት ቁመና አንጻር የሚሳኩ አይመስሉም።
ማጠቃለያ
የመቀሌው ስብሰባ አልተጠናቀቀም። ህወሀት ሪፎርም ማድረጉንና ከስልጣን የሚያሰናብታቸው አመራሮች እንደሚኖሩ እየተነገረ ነው። It is too late. ምን ዓይነት ሪፎርም? ህወሀት አፈጣጠሩ ለዚህ የሚፈቅድለት አይደለም። ያረጠ ድርጅት ነው። ከተቸነከረበት የስታሊን መስመር ዝንፍ ካለ መጥፊያው ነው። ደግሞም 11ኛው ሰዓት ላይ ሪፎርም አያድነውም። የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሀትን ሊሰናበት ተዘጋጅቷል። ይህ ዕቅድም የስንብት እንጂ የሪፎርም አይደለም። ከመቀሌ የሚጠበቅ ለውጥ አይኖርም። ህወሀት በዕቅዱ እንዳስቀመጠው ህዝቡ መንግስት ይቀጥላል ብሎ አያምንም። ተስፋ ቆርጧል። ስለዚህ ዕቅዱን የስንብት ደብዳቤ ነው ቢባል ያስኬዳል። ኑዛዜም ነው። ይህን ተቀብሎ የማሰናበትና ህወሀትን ከነጥቁር ገጽታው

Freitag, 1. September 2017

ጊዜው "የእምቢ አልገዛም! " "የእምቢ አልከፍልም! " ነው። (በ ዶ/ር ታደሰ ብሩ)

ህወሓት፣ በቀን ገቢ ግምት ግብር ከፋዮች ላይ  ያሰበው መጠነ ሰፊ ዘረፋ ላይ በደረሰበት ሰፊ ተቃውሞ ሳቢያ ቀላል የማይባል ኪሳራ ደርሶበታል። በዚህም ምክንያት የማፈግፈግ ምልክቶችን አሳይቷል። ማፈግፈግ የሥርዓቱ ጊዜዓዊ ማምለጫ ነው፤ ሁኔታዎች ሲረጋጉ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም። እንዲያውም ሌሎች ተጨማሪ የዝርፊያ መስሮችን መክፈቱን የማይቀር ነው። 

አሁን ተግባራዊ መሆን የጀመረ ድሆችን ይበልጥ የማደህያ አንድ መጠነ ሰፊ ፕሮጀክት እነሆ። በወሊሶ ከተማ የቀበሌ ቤቶች ኪራይ በአንድ ጊዜ ከ 40  - 50 ጊዜ እጥፍ መጨመሩ ኢሳት ገልፆ ነበር።

እንዲህ ዓይቱ ጭማሪ በወሊሶ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኦሮሚያ ከተሞች ወስጥ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኗል።. ለምሳል፣ በወር 10 ብር ይከፈልበት የነበረ ዛኒጋባ ብር 500 እንዲከፈልበት፤ መክፈል  የማይችሉ ቤቶቹን እንዲለቁ እንዲደረግ ተወስኗል።

ይህ ውሳኔ በኦሮሚያ ላይ ተወስኖ የሚቀር አይደለም፤ የኦሮሚያው አፈፃፀም ታይቶ ወደሌሎች ክልሎችም መዛመቱ የማይቀር ነው። ስለሆነም ካሁኑ ተቃውሞዓችን አገራዊ መሆን ይኖርበታል።

መጪው 2010 "ለማይወክለን አገዛዝ ግብር ብቻ ሳይሆን ማናቸውንም ክፍያ አንፈፅምም" የሚባልበት ዓመት መሆን ይኖርበታል።

መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ወታደሮችና ፓሊሶች "አንገዛም፣ አንታዘዝም፣ አንከፍልም፣ አንሠራም……" ለማለት ይዘጋጁ።

ጊዜው "የእምቢ አልገዛም! " "የእምቢ አልከፍልም! " ነው።

Freitag, 18. August 2017

የእነ አቶ በቀለ ገርባ መከላከያ የመስማት ሂደት አቃቤ ህጉ እርቦኛል በማለቱ ምክንያት ተቋርጧል። በ ( ጌታቸው ሽፈራው)

የእነ አቶ በቀለ ገርባ መከላከያ የመስማት ሂደት አቃቤ ህጉ እርቦኛል በማለቱ ምክንያት ተቋርጧል።

አቃቤ ህግ ለሚያቀርበው ጥያቄ ተደጋጋሚ መቃወሚያ የቀረበበት ሲሆን መሃል ላይ "አርብ እንደመሆኑ እኛ ለምሳ  መውጣት ያለብን 5:30 ላይ ነው። የምሳ ሰዓታችን ይከበር" ብሎ ባቀረበው ጥያቄ  መሰረት መጠነኛ ክርክር ተደርጓል። ሌላ አቃቤ ህግ ስለነበር ፍርድ ቤቱ ሌላኛው አቃቤ ህግ ራበኝ ያለውን ተክቶ የሚሰራበት አጋጣሚ ስለመኖሩ ቢጠይቅም ራበኝ ያለው አቶ  አንተነህ  የተሰየመው እሱ ብቻ መሆኑን ገልፆአል።

 " እኔም ከጤናዬ አንፃር ሊታሰብልኝ ይገባል።ጨጓራ አለብኝ። መብላት አለብኝ" ብሏል አቶ አንተነህ።

የቀኝ ዳኛው አቃቤ ህጉ ያነሱት ጥያቄ መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጀመር ቢሆን ኖሮ ተገቢ ይሆን እንደነበር  ገልፀው መታገስ እንደሚገባ በመጠቆማቸው  አቃቤ ህጉ " ትክክል ነው። ታግሼ መስራት እንዳለብኝ አውቃለሁ። እዚህ ቦታ ላይ ቆሜ የምሰራው ጤና ሲኖረኝ ነው። ህመሜን እያዳመጥኩ ልጠይቅ አልችልም።" ብሎ የምሳ ሰዓቴ ይከበር የሚለውን ጥያቄ ገፍቶበታል።

አቶ በቀለ ገርባ በበኩሉ "  ይህ ከዚህ ትልቅ  ተቋም የሚጠበቅ አይደለም።  እኛ እየተራብን፣ ብዙ መከራ እያየን ነው ያለነው። ህዝቡም የፍትህ ሂደቱን እንዲያይ ነው። አቃቤ ህግ ከተለየ አካል ትዕዛዝ ሊቀበል ካልሆነ በስተቀር ይህ በምክንያትነት ሊቀርብ አይገባም" ብሏል።

 መሃል ዳኛው" ከዚህ ወንበር ተቀምጠን ትዕዛዝ መስጠት አለብን። ሁለት አቃቤ ህጎች ስላሉ አንዱ ተክቶ ሊሰራ እንደሚችል እንረዳለን። ይህ የትዕዛዝ ጉዳይ አይደለም።" ቢልም ሂደቱ ተቋርጦ ለምሳ ተወጥቷል።
 ይህ የምሳ ሰዓት ይከበር ጥያቄና ክርክር በታዳሚውና ተከሳሾች  ሳቅ የታጀበ ነበር።

Mittwoch, 9. August 2017

እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ በሀሰት እየተመሰከረባቸው እንደሆነ ገለፁ • (በጌታቸው ሺፈራው)

እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ በሀሰት እየተመሰከረባቸው እንደሆነ ገለፁ • ‹‹ህዝብ እውነታውን እንዲረዳልን እንፈልጋለን›› መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ (በጌታቸው ሺፈራው) ቂሊንጦ እስር ቤትን አቃጥላችኋል፣ ንብረት አውድማችኋል እንዲሁም የሰው ህይወት አጥፍታችኋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ማስረሻ ሰጤ ነሃሴ 2/2009 ዓ.ም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በሀሰት እየተመሰከረባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት ሁለት ምስክሮች የቀረቡ ሲሆን አንደኛው ምስክር በ13 ተከሳሾች ላይ ምስክርነት ሰጥቷል፡፡ ምስክሩ እነ ማስረሻ ሰጤ፣ ሰይፈ ግርማ እና ፍቅረማርያም አስማማው የአማራ ብሄር ተወላጆችን እየሰበሰቡ ለግንቦት ሰባት በአባልነት ይመለምሉ እንደነበር ሲገልፅ፣ ወልዴ ሞቱማ፣ አበበ ኡርጌሳና ሌሎች ተከሳሾች የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን በመሰብሰብ ለኦነግ ይመለምሉ ነበር ብሎ መስክሯል፡፡ ሆኖም ምስክሮቹ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ለግንቦት ሰባትና ኦነግ ይመለምሉ ነበር የተባሉት ተከሳሾች ከየትኛው ብሄር እንደሆኑ ሲጠየቁ አናውቅም ብለዋል፡፡ ምስክሮቹ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በቃጠሎው ወቅት የሞቱትን እስረኞች ፎቶ ቀድሞ በማሳየት ለምስክርነት ያዘጋጃቸው መሆኑን ለችሎቱ የገለፁ ሲሆን ተከሳሾቹም በሀሰት እየተመሰከረባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ማስረሻ ሰጤ በበኩሉ በሀሰት እየተመሰከረባቸው መሆኑን በመግለፅ ‹‹በተቋም ደረጃ የሀሰት ምስክርነት እየተሰጠ ነው፡፡ ህዝብ እውነታውን እንዲረዳልን እንፈልጋለን›› ብሏል፡፡ ሌሎች ተከሳሾችም በሀሰት እየተመሰከረባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ዛሬ ነሃሴ 3/2009 ዓ.ም ሁለት ተጨማሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የተሰሙ ሲሆን የምስክር መስማት ሂደቱ እስከ ነሃሴ 12/2009 ዓ.ም ይቀጥላል ተብሏል፡፡ ምስክሮቹ ነሃሴ 28/ 2008 ዓ.ም ተኩስ እንደነበር፣ በጥይት የተገደሉና የቆሰሉ እስረኞች እንዳዩ እንዲሁም ወደ እስረኛው የጭስ ቦንብ እንደተወረወረ ገልፀዋል፡፡ ለቃጠሎው መንስኤ የአስተዳደር ችግር፣ ምግብ መከልከሉና በመታሰር የተፈጠረ ብሶትም እንዳለበትም ተገልጾአል፡፡ ቶፊቅ ሽኩር፣ ሸቡዲን ነስረዲን፣ ኡመር ሁሴን፣ ሸምሱ ሰይድ፣ ከድር ታደለ፣ ተመስገን ማርቆስ፣ አሸናፊ መለስ፣ ሚስባህ ከድር፣ አግባው ሰጠኝ፣ ምትኩ ደበላ፣ ካሳ መሃመድ፣ ከበደ ጨመዳ፣ ጌታቸር እሸቴና ፍጹም ጌታቸው በሁለቱ ቀን የፍርድ ቤት ውሎ ምስክር ተሰምቶባቸዋል፡፡

https://netsanetlegna.wordpress.com/2017/08/09/%e1%8a%a5%e1%8a%90-%e1%88%98%e1%89%b6-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%89%83-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%88%a8%e1%88%bb-%e1%88%b0%e1%8c%a4-%e1%89%a0%e1%88%80%e1%88%b0%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%98/

Dienstag, 1. August 2017

ግብር በአምባገነን አገዛዝ (በዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርሰሞ)

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
*******************************
ግብር በአምባገነን አገዛዝ
-------------------------
በዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርሰሞ
 ስለ አምባገነን አገዛዝና ግብር ሲነሳ መጥቀስ የምወደው የእውቁ ኢኮኖክስ ማንኩር ኦልሰን  Dictatorship, Democracy, and Development ነው።  ከዚህ ጽሁፍ በዛ አድርጌ ልጥቀስ።
===
ዘላን ወንበዴዎች /roving bandits/ ነጥቀው ይሮጣሉ፤ መቼ እንደሚመለሱ አይታወቅም። እነዚህ ወንበዴዎች ነጥቀው በሮጡ ቁጥር የማኅበረሰቡ ሀብት የማፍራት ፍላጎት ስለሚዳከም በሚቀጥለው ዙር የሚዘርፉት ነገር እያነሰባቸው ይመጣል። ቀን ባለፈ መጠን ነጥቆ መሮጥ ራሳቸውን እንደሚጎዳቸው ይገነዘቡና ከተዘዋዋሪ ወንበዴነት ወደ ቋሚ ወንበዴነት /stationary bandit/  ይቀየራሉ። ለንጥቂያቸውም ሥርዓትና ልክ ያበጁለታል፤ ስሙን “ግብር” ይሉታል። ማኅበረሰቡንም፣ ራሳቸውንም ከሌሎች ተዘዋዋሪ ወንበዴዎች ይከላከላሉ። ይህ ሥርዓት ከሥርዓተ አልበኝነት የተሻለ፣ የቅሚያውም መጠንም አስቀድሞ የሚታወቅ ከመሆኑ ጋር ማኅበረሰቡ ለሚከፍለው ተመጣጣኝ ባይሆንም የሚያገኘው ጥቅም (ሰላምና ሌሎችም ማኅበራዊ ምርቶች) ስላሉ ምርት ይጨምራል፣  ዕድገትም ይኖራል።
 ይሁን እንጂ አምባገነን ሰፋሪዎች በተደላደሉ መጠን ፍጆታቸው እየናረ መሄዱ ፈጽሞ የማይቀር ነው። ለጦር ሠራዊቱ፣ ለቤተመንግሥቱ፣ ለማሰልጠኛው፣ ለመታሰቢያ ሀውልቶች ግንባታ፣ ለአዳራሾች ግንባታ፣ ለአምባገነኖች፣ ለተከታዮቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የክብር ልብሶችና ጌጣጌጦች፣ “ለመጠባበቂያ“፣ .....  የሚያስፈልገው ወጪ በጨመረ ቁጥር ሕዝቡ በግብር አሊያም በሌላ መንገድ እንዲከፍል ስለሚገደድ ሥርዓት በመስፈኑ ምክንያት አንሰራርቶ የነበረው የሥራ ፍላጎት እንደገና ያሽቆለቁላል። የሰፋሪ ወንበዴዎችን የሀብት ማጋበስ፣ ምቾትና እዩልኝ ፍላጎቶችን ማርካት አይቻልም።
==
 በማንኩር ኦልሰን ላይ የምጨምረው የለኝም፤ ሁሉንም ብሎታል።
 ወንበዴዎች ሕዝብን ለማስገበር ሁለት ነገሮች ያስፈልጓቸዋል።  አንዱ ጉልበት ነው። ሞኝ ሽፍታ ዘርፎ ይሮጣል፤ ብልጣብልጥ ሽፍታ ደግሞ ቁጭ ብሎ መዝረፍ ያምረዋል።  ብልጣ ብልጥ ሽፍታ ራሱን በመንግሥትነት ሰይሞ ለዘረፋው “የመንግሥት ግብር “ የሚል ስያሜ ሰጥቶ ተዘራፊን አሰልፎ ደረሰኝ እየሰጠ ይዘርፋል።
 ቁጭ ብሎ ደረሰኝ እየሰጡ ለመዝረፍ ግን ከጉልበት በተጨማሪ ለዘረፋ ሰበብ የሚሆኑ ማኅበራዊ ምርቶች (public goods) ማምረት ያስፈልጋል። ካድሬዎች ሕዝቡን “ግብር የምትከፍለው ለመንገድ፣ ለጤና  አገልግሎት፣ ለትምህርት  ...” ብለው መቀስቀስ አለባቸው። ግብር ግዴታ መሆኑ ቢታወቅም ምክንያታዊ እንደሆነ ማብራራት መቻል አለባቸው። በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ ከተሰበሰበው ግብር ምን ያህሉ ወደ ማኅበራዊ ምርት፤ ምን ያህሉ ደግሞ ወደ ባለሥልጣናቱ ኪስ እንደሄደ የሚጠይቅ የለም።  መንገዱም ሆነ ሕንፃው ቢሰራ ለማን፣ ለምን ብሎ የሚሞግት የለም። ሕዝቡ አምፆ እስካላስቀረው ድረስ ደረሰኝ እየተቀበለ ይዘረፋል።
 በህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ ይህ ነው። የህወሓት ሠፋሪ ወንበዴዎች በግብር ስም እያስራቆቱን ነው። ህወሓት የዘረጋው የግብር ሥርዓት ወንበዴው ቁጭ ብሎ ለፍቶ አዳሪውን የሚመጥበት፤ ድሀው ሀብታሙን የሚደጉምበት ነው። እንዲህ እንዳሁኑ አንዳንዴ የሙስና ዜና  ሲኖር ነው በግብር የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደተከማቸ በወሬ ወሬ የምንሰማው።
 ሌላም ላነሳው የምሻ ጉዳይ አለ:  “ግንዛቤ ማስጨበጥ” የሚሉት።
 አገራችን ውስጥ የወር ደመወዝ ተከፋይ ምንም ከግብር ማምለጫ ቀዳዳ የሌለው በመሆኑ ከሁሉ በላይ ተበዳይ እንደሆነ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መጠነኛ እውቀት ያለው ሁሉ የሚያውቀው ሀቅ ነው። የግብር ዕዳን ለማስተካከል ሲባል “ነጋዴ ላይ ግብር መጫን የወር ደመወዝተኛው ኑሮ ያሻሽላል” የሚል “ግንዛቤ ማስጨበጥ”  “እኔ ብጎዳም ያንተ ከኔ ይበልጥ መሰቃየት ያስደስተኛል” ዓይነት ሰይጣናዊ አመክኖ ነው። በነጋዴ ላይ የሚጫን ግብር ውሎ አድሮ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሸቀጦች ዋጋ መተላለፉ አይቀርም።  ይህንን ሽግግር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አያስቀረውም። እናም የወር ደመወዝ ተከፋዩ  የሚጠቀመው በለፍቶ አዳሪው ላይ የግብር ዕዳ በመጫኑ አይደለም። የወር ደመወዝተኛው የሚጠቀመው በለፍቶ አዳሪው ብቻ ሳይሆን በሱም ላይ የተጫነው የግብር ዕዳ  ሲቀንስ ነው።
 ላጠቃለው።
ወገኞቼ፤ ለህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ግብር አልከፍልም ማለት ተገቢ ነው። ለአንባገነን ሥርዓት አልገብርም ማለት ከሥነ ምግባር አንፃር ተቀባይነት ያለው የጽድቅ ሥራ ነው። ለህወሓት አንገብርም ማለት የሚኖርባቸው ነጋዴዎች ብቻ ሳይሆኑ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።

Montag, 10. Juli 2017

አርበኝነት

አርበኝነት

አርበኝነት ማለት ለወገኑ የተሻለ ህይወትና ጊዜዉን ጉልበቱን እዉቀቱን ገንዘቡን  ንብረቱንና ክቡር ህይወቱን መስዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ ሰዉ ወይም የህብረተስብ ክፍል ማለት ነዉ።

ከዚህም በመነሳት ዛሬ ላይ እየተካሄደ ባለዉ የአርበኝነት ትግል አላማችን እንዲሳካ እራአያችን እንድያብብ የምንሻ ሁሉ የግድ ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ ማጤንና መገንዘብ ያስፈልጋል።  የአርበኝነት አላማ ደግሞ ዉጤታማ የሚሆነዉ በእቅድ የሚመራ በተግባር የሚታይና በድርጊት የሚገለጽ  የጥርት ዉጤት ሲሆን ነዉ።
በመሆኑም ድሮ አርበኛ አባቶቻችን በአዋጅ ተሰባስበዉ በራሶችና በደጃዝማቾች የጦር አጋፋሬዎች እየተመሩ ለሃገራቸዉ በነበራችዉ ጥልቅ የሃገራዊ የፍቅር ስሜት አርበኝነትን ተላብስዉ በባዶ እግራቸዉ ወንዝና ሽነተረሩን አቋርጠዉ ዳገት ቁልቁልቱን ወጥተዉ ወርደዉ ከጦርነቱ አዉድማ ሲደርሱ ነጋሪት እየተጎሰመ እንቢልታዉ እየተንፋ ንጉስ ከፈረስ ሳይወርዱ በጦርነተ መሃል ዉስጥ ሆነዉ አዋጅ እያስነገሩ የፊዉታራሬ ጦር ግባ ተብለሃል፥ የቀኝ አዝማች ጦር ግባ ተብለሃል፥የግራዝማች ጦር ግባ ተብለሃል በሚል የአዉደ ዉጊያ የእዝ ሰንሰለት ጊዜዉ በፈቀደዉ የጦርነት ስልት ነበር  በጦር በጎራዴ ተዋግተዉ ደማቸዉን አፍሰዉ ሃገራችን ኢትዮጵያን ከወራሪ  ቅኝ ገዥዎች ያዳኗት።
ዛሬ ላይ ደግሞ ሃገር በቀል ወራሬ የወያኔን ቡድን ለማስወገድ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በሁለገብ የትግል ስልት ከገጠር እስከ ከተማ ሁሉንም የሃገራችነን ክፍል ባከለለ የህዝባዊ እንቢተኝነትና የህዝባዊ አመጽ እንዲጎለብት በማድረግ በቁርጠኝነት በምታገል ላይ ናቸዉ።
እንድሁም አርበኛ ታጋዮቻችን ከነጻነት ሃይሎችና ከህዝቡ ጋር በመሆን የሽምቅ ዉጊያ በማካሄድ ትግሉ ወደ ላቀ ደረጃ እንድሸጋገር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ስለሆነም የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች እንዳ አባቶቻችን የአርበኝነትን  መንፈስ ተላብሰዉ መስዋእትነት በመክፈል ደማችዉን አፍሰዋል።
በአሁኑ ስአትም ደም ገብረዉ ሃገራችንን ከጥፋት ለመታደግ የቆረጡ የህዝብ ልጆች ከአገዛዙ ታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተፋለሙ ናቸዉ።
በሌላ በኩል ግን ወያኔን ለማስወገድ ራሱ ወያኔ በመጣበት የትግል ስልት እና ኢህአፓና ኢድዩ የትጓዙበትን የትግል መንገድ የተከተለ አይደለም ምክኔያቱም ዘመኑ ያለፈበት የትግል መንገድ በመሆኑ።
ወይም እንዳባቶቻችን የደጃዝማች ጦር በቀኝ በኩል ግባ ተብለሃል የፊዉታራሪ ጦር በግራ በኩል ግባ ተብለሃል በሚል በአዋጅ የሚደረግ ጦርነት አይደለም ዘመኑ የቴክኖሎጅ ዘመን ነዉ።ስለዚህ አሁን ያለዉ የአርበኝነት ትግል የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታን ባገገናዘበ በስልትና ሚስጥር በመጠበቅ የሚደረግ የአርበኝነት ትግል ነዉ ።
ይህን ተከትሎ በትጨባጭ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነትን ለማምጣትና ዴሞክራሲን ለማስፈን ለሃገራችን ኢትዮጽያ በጎ ራእይን በመሰነቅ  የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ በሁሉም መስክ ትግሉን እያቀጣጠሉ ይገኛሉ።
 ነገር ግን አንዳድ ወገኖች ከራሳቸዉ የግል ጥቅም በመነሳት እና አሁን ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ባለመረዳት እንድሁም በግንዛቤ እጥረት አራንባና ቆቦ በሆነ አስተሳሰብበ በአዉሮፓና  በአሜሪካ  ካለ የፕረስ ነጻነት ጋር በማመሳሰል እቅዳችን ይሕ ነዉ፥አሁን እንደዚህ እየሰራን ነዉ ፥ወደፊት እንደዚያ ልናደርግ ነዉ የሚል ሪፖርት ወይም ጋዜጣዊ መግለጫ እንድሰጥ የሚፈልጉ የመኖራቸዉን ያክል፥ በሌላ በኩል ደግሞ የሽምቅ ዉጊያ ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ የሚከናወን በመሆኑ አንዳድ ብሄር ተኮር ፖለቲከኞች ለራሳቸዉ የፖለቲካ ስካራ ለግባትነት ለመጠቀም በማሰብ ሆን ብለዉ በተግባር እየተከናወነ ያለዉን ስራ ትቢያ እያለበሱ  ምንም ስራ እንዳልተሰራ በደካማ ጎን በመፈረጅ የወሬ ቋታቸዉን ሲያራግቡ ይስተዋላሉ።
 በጥቅሉ  እነዚህ ግለሰቦች አብሮ ከመታገልና የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ለትግሉ አስተዋጽኦ ከማድረግ ይልቅ ችግሮችን እየፈለጉ በስራ ላይ የሚከሰቱትን ጥቃቅን ስህተቶችን ነቅሶ በማወጣት የሚያናፍሱት ወሪ የአርበኝነት ትግሉን ወደኋላ   የሚጎትት እና የወያኔን የአገዛዝ እድሜ ሊያራዝም በሚያስችል በተሳሳተ መንገድ እየተጓዙ መሆናቸዉ ግልጽ ሆኖ እየታየ ነዉ።
ሃግርን ለምዳን በሚደረገዉ የሞት ሽረት ትግል ዉስጥ ሚና በሌለዉ ለግል ጥቅም አንጋጦ በወሬ ብቻ እራስን ከፍ አድርጎ እንደ ታጋይ በመቁጠር የሚመጣ ለዉጥ የለም ከገደል ማሚቶነት ማስተጋባት የዘለለ ሊሆን የሚችል አይደለም ።
በአንጻሩ ግን ለፖለቲካ ግባትነት ያገለግላል ከሚል መነሻነት አማራ ኦሮሞ በማለት ልዩነትን በማስፋት ትርፍን አስቦ የግል ፍላጎትን ለማሟላት የሚደርግ ሩጫ የወያኔን እድሜ ከማራዘሙም በላይ በህብረተሰቡ መካከል ቅራኒን አስፍቶ ዘመን የማይሽረዉን ጠባሳ ይተክላል ።ስለሆነም በህዝብ ደም ለመነገድ ማሰቡ ሊቆም ይገባዋል። 
የዚህ አይነት አመለካከት ያላቸዉ ግለሰቦች ሊያዉቁት የሚገባዉ መሬት ላይ ያለዉ እዉነታ በርበኞች ግንቦት7 ድርጅት ጥላ ስር የትሰባሰቡ በሃገር ዉስጥም በዉጭም ያሉ አርበኛ ታጋዮች በእንቅስቃሴአቸዉ በተግባር እያከናወኑት ያለዉ የአርበኝነት ትግል አንዱን አገዛዝ አስወግዶ ሌላዉን አገዛዝ ለመተካት አይደለም  ምክኒያቱም በትግሉ ሂደት ዉስጥ ሁሉንም እይነት ፈተና በመቀበልና መስዋእትነት እየተከፈለ ያለዉ ሃግራችን ኢትዮጽያ ከገባችበት የአሮንቃ ማጥ ዉስጥ ለማዉጣት ሲባል ብቻና ብቻ ነዉ።
ስለሆነም ክቡር ህይወትን ከመገበር በላይ ሌላ ምስክርነት የሚስፈልገዉ አይደለም ።
ይልቁንም እንደኔ እምነት የሚሻለዉ መንገድ ሁላችንም ግለሰባዊ ጥቅምን ወደ ጎን በመተዉ እንደ ሃገር በጅምላ የደረሰብንን መከራና ስቃይ ዋየታና እሮሮ ለማስቆም በአንድነት ላይ ቁመን በጋራ ተባብረን በአርበኝነት በመታገል ወራሪ የህዉሃትን ቡድን ለማስወገድ ቅድሚያ ልንሰጠዉ የሚገባ ተግባር ሊሆን ይገባዋል።

ባንዳነት ጌጥ የሆነላቸው (መስቀሉ አየለ)

ባንዳነት ጌጥ የሆነላቸው (መስቀሉ አየለ)
መስቀሉ አየለ
ቡልጋሪያ የምትባል የምስራቅ አውሮፓ ክፍል አለች። ለአራት መቶ አመት ያህል በቱርክ የእሳት ሰንሰለት ተጠፍንጋ የኖረች አገር ናት። የኦቶማን ቱርክን ጦር ቀጥቅጦ ወደ መቃብር የገፋላት የሩሲያ ጦር ነበር። ቡልጋዎች ይህን የነጻነት ቀን በያመቱ ሲያከብሩ የክብር እንግዳው የሚመጣው ከሩሲያ ነበር። ባለፈው አመት ግን ይኽ አልሆነም። በሶፊያ፣ ቡልጋሪያ የሚገኘው የ አሜሪካን አምባሳደር ተቆጣ አሉ፤ ተቆጥቶም አልቀረም ይልቁንም የክብር እንግዳው ከቱርክ መሆን አለበት ብሎ ቀጭን ትእዛዛ ያስተላለፈው ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት ነበር።በጌታና የሎሌ ግንኙነት ወቅት ፕሮቶኮል ትርጉም የለውም።Unpatriotic act
የናዚ ጀርመን ጦር አውሮፓን እንዳይወር በወቅቱ የነበሩት መራሄ መንግስትታ ለሂትለር እጅ መንሻ የመስዋእት ጠቦት አድርገው የሰጡት ፖላንድን ነበር። ክፋቱ ሂትለር እርሷን በልቶ አለማቆሙ ነው እንጂ። ፖላንድን ከናዚ ጦር ነጻ ለማውጣት ስድስት መቶ አምሳ ሺህ የሩሲያ ጦር ነበር ያለቀው። በታሪኩ አሰቃቂ በተባለለት አስቸጋሪ የበረዶ ላይ ከበባ ዋጋ ለከፈሉትና ድፍን አውሮፓን ከናዚዝምና ከፋሽዝም ለታደጉት የሩሲያ ወታደሮች መታሰቢያ በፖላንድ ዋርሳው የቆሙትን ሃውልቶች ዛሬ ከአሜሪካ በላይ አሜሪካዊነት በሚሰማቸው የፖላንድ መሪዎች መፈራረስ በመጀመራቸው የሩሲያ መንግስት የወታደሮቹን አጽም በክብር ወደ አገሩ መልሶ ለማሳረፍ ቃል ገብቷል።ዛሬ ፖላንድ ማለት በምስራቅ አውሮፓ ውስጥ ያለች አንዱዋ የአሜሪካን ላፕዶግ መሆኗን በብዙ አጋጣሚ እያስመሰከረች ያለችበት ሁኔታ ነው ያለው።

በኛም አገር ለአገራቸው በጎ የዋሉ፤ ለማንነታቸው ዋጋ የሰጡና እራሳቸውን የተቀደሰ መስዋእት አድርገው ህዝባቸውን የታደጉ አባቶቻችን አጽመ እርስታቸው የሚያርፈው አዲስ አበባ በሚገኘው ዮሴፍ ቤተክርስቲያን እንደነበረ ይታወቃል። አርከበ እቁባይ የተባለ የባንዳ ልጅ የመናገሻውን ቢሮ በያዘ ሰሞን “የኒህን የነፍጠኞች ምናምንቴ አውጥተኽ ጣልልኝ!” ብሎ ባዘዘው መሰረት የዚያ ሁሉ የአርበኛ አጽም ነበር ድፍን አዲሳቤ በኣይኑ ብረት ቆሞ እያየ በቡልዶዘር ተጠራርጎ የፈረሰው። ከላይ በሌሎች አገሮች ተሞክሮ እንዳየነው ባንዳ ሁሉ ስነ ባህሪያቸው አንድ ነው። ሰሞኑንም የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ፣ መልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬና ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን አጽም አንሡ መባላችን ያው ከላይ በፖላንድ ካየነው እውነት ልዩነት የለውም። እንዲህ በማንነቱ የሚሸማቀቅ፣ የገዛ ታሪኩን የሚያዋርድና ገንዘብ ባየበት ሁሉ እንደ ሴተኛ አዳሪ የሚገለፍጥ የወያኔ አይነት ባህሪ ለምን የምእራባውያንን ልቦና እንደሚያማልል ግልጽ ነው። ዘመኑ የባንዳ ነው።

Sonntag, 2. Juli 2017

የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የሚጥስ አዋጅ አጥብቀን እንቃወማለን!!! (ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)

የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የሚጥስ አዋጅ አጥብቀን እንቃወማለን!!!

    ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ
ህወሀት/ኢህአዴግ በ100 ፐርሰንት አሸንፊያለሁ ብሎ ባወጀ ማግስት በመላ ሀገራችን በሁሉም አቅጣጫ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የነፃነት፣ የእኩልነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን በማንገብ የኢትዮጵያ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው፡፡አገዛዙ ይህንን መሰረታዊ የለውጥ ጥያቄ ለማዳፈን ሲል ለማመን በሚከብድ ሁኔታ አስተዳድረዋለሁ በሚለው ህዝብ ላይ ግድያ፣ የጅምላ እስር እና ማፈናቀል ዋነኛ ተግባሩ አድርጎታል፡፡ በዚህ የአገዛዙ ኢ-ሰብዓዊ እርምጃም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ የለውጥ ጥያቄ ማስቆም ባለመቻሉ በድንጋጤና ባልታሰበበት ሁኔታ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመከፋፈል እና በጥርጣሬ እንዲተያይ ለማድረግ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
ይህ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተረቀቀ የተባለው አዋጅ በጥድፊያ የወጣ፣ግልፅነት የጎደለው፣ህገ መንግስቱን የጣሰ፣በመረጃና በጥናት ላይ ያልተመረኮዘ፣አጠቃላይ የዴሞክሰራሲ መርሆና ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 አላማ ጋር በእጅጉ የተቃረነና ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት አገዛዙ የተነሳበትን የፖለቲካ ትኩሳት ለማብረድ በማሰብ የተቀነባበረ ግልብ ሴራ ነው፡፡
አገዛዙ በተቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን እንደተገለፀው በዚህ አዋጅ የማርቀቅ ሂደት ላይ የተሳተፉት አካለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ኦህዴድ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እንደሆኑ ተገልፅዋል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ አዲስ አበባን ከሚያስተዳድሩትም ሆነ በፌደራል ፓርላማ 100 ፐርሰንት አሸንፊያለሁ ያለው ኢህአዴግና አጋሮቹ ውስጥ እንደ ድርጅት ኦህዴድ ብቻ መሳተፉና ሌሎች ማለትም ብአዴን፣ደህዴንና ህወሃት እንዳይሳተፉ መደረጋቸው በድርጅቱም ውስጥ ታስቦበትና ሙሉ ስምምነት ተደርሶበት የተዘጋጀ ረቂቅ አለመሆኑን እና ተራ የፖለቲካ ሸቀጥ መሆኑን ግልፅ ማሳያ ነው፡፡በዚሁ መግለጫ ላይ አንደተገለፀው በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋት ለተፈናቀሉና ወደፊትም ለሚፈናቀሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈለው ለኦሮሞ ብሄር ተወላጅ አርሶ አደሮች እንደሆነ ተገልጧል፡፡ይህም ማለት በዚህ አዋጅ መሰረት በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋት ምክንያት ለሚፈናቀሉ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ካሳ የማግኘት መብት የላቸውም ማለት ነው፡፡ ይህ አገላለፅ የዜጎችን ተዘዋውሮ የመስራትና ሀብት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብት የሚነጥቅ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተቀባይነት የለውም፡፡
የህገ መንግስቱ አንቀፅ 49/5 ዓላማ የአገልግሎት አቅርቦትን፣የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምናን እና የጋራ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን አፈፃፀም የተመለከተ ሲሆን ይህ ተረቀቀ የተባለው አዋጅ ግን ከዚህ አንቀፅ በተቃራኒው ተለጥጦ የአዲስ አበባን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት በመንጠቅ ኦሮሞነትን በላዩ ላይ በመጫንና ተገዶ እንዲቀበል በማድረግ ኦሮሞ ያልሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ በገዛ ሀገሩ ባይታወርነት እና እንግድነት እንዲሰማው የሚያደርግ ጨቋኝ አዋጅ ነው፡፡
በዚህ ተረቀቀ በተባለው አዋጅ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሰራተኞች ተመዝግበው ቤት የማግኘት መብት እንዲከበርላቸው ይደነግጋል፡፡ በመሰረቱ የኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት ዋና ከተማ አዳማ መሆኗን በ1994 ዓ.ም የተሸሻለው የክልሉ ህገ መንግስት አንቀፅ 6 ይደነግጋል፡፡ይህ ሆኖ እያለ ህወሃት/ ኢህአዴግ በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ አዲስ አበባ ከተማ ላይ በደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት ምክንያት የወቅቱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ በምርጫው ማግስት የኦሮሚያ ክልልን ህገ መንግስት በመጣስ በፖለቲካ ውሳኔ የአዳማ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማነት መብትን በመንጠቅና ወደ ህዝብ የመቅረብ መሰረታዊ የፌደራሊዝም ፅንሰ ሃሳብ በመጣስ ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር አድርገዋል፡፡ይህ ውሳኔ የክልሉን ህገ መንግስት ያላከበረ ስለሆነ ሊፀድቅም ሊፈፀምም አይገባም፡፡
በፌደራሉ ህገ መንግስት መሰረት 9 ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እንዳሉ ሲታወቅ አዲስ አበባ በዚህ ህገ መንግስት በአንቀፅ 49/2  መሰረት ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብትና የራሱን የስራ ቋንቋ የመወሰን መብቱ የአዲስ አበባ ህዝብ እና የሚወክላቸው አካላት ብቻ መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ይህንን ህገ መንግስታዊ መብት በመጣስ የአዲስ አበባ አስተዳድርን የስራ ቋንቋ የሚወስን አዋጅ በፌደራል መንግስት ማውጣት በራሱ በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 9 መሰረት ተቀባይነት የለውም፡፡ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኦሮሞኛን የስራ ቋንቋ ማድረግ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከስራ እድል በማግለል ኦሮሞ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ቅድሚያ ለመስጠት በማስመሰል በዜጎች መካከል አላስፈላጊ የጥቅም ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርግና በህዝብ መካከል ያለውን መስተጋብር የሚንድ መርዘኛ አዋጅ በመሆኑ በፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡    
ከላይ በገለፅናቸው ማሳያ ነጥቦች መሰረት ይህ ተረቀቀ የተባለው አዋጅ የህግም ሆነ የሞራል መሰረት የሌለው ስለሆነ በአስቸኳይ አንዲቆምና የኦሮሚያ ክልል መንግስትም የአዳማን የክልል ርዕሰ ከተማነት ህገ መንግስታዊ መብትን በማክበር አሰተዳደሩን ወደ አዳማ እንዲያዛውርና የአዳማ ከተማ በክልሉ ህገ መንግስት የተሰጠውን የክልል ከተማነት መብት ተከብሮ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚገኙ የኢኮኖሚ፣የፖለቲካ እና የማህበራዊ እድገት ተፈፃሚ እንዲሆን በአፅንዖት እንጠይቃለን፡፡በመጨረሻም ረቂቅ አዋጁ ህወሀት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያን መሰረታዊ የህዝብ ጥያዌ ለመመለስ አቅምም ሆነ ፍላጎት እንደሌለው በግልፅ የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር ለስልጣኔ ይጠቅመኛል  ያለውን ሁሉ በህዝብ ላይ ከመፈም ወደኋል እንደማይል ከድርጊቱ ተገንዝበናል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአዲስ አበባ ህዝብ ይህንን ተረቀቀ የተባለውን ከፋፋይና መርዘኛ ረቂቅ አዋጅ ውድቅ እንዲሆን ጥቃቅን ልዩነቶችን በማሶገድ መሰረታዊ ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት፣እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር አውን መሆን ላይ በማተኮር በአንድነት ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
 
                                ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
                                ሰኔ 25 ቀን 2009 ዓ.ም

Freitag, 30. Juni 2017

ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር --- ክፍል አንድ ( በነጻነት ቡልቶ)

ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር
በነጻነት ቡልቶ

ክፍል አንድ
ጄነራል ጻድቃን፣ “የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ” እና  “የፓለቲካ ችግሮች”

በግሪክ አቴናና በስፓርታ መካከል የተካሄደውን የጦርነት ታሪክና ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ ስትራቴጃካዊ ጽንሰ ሃሳቦች በማፍለቅ ከሚደነቀው ጥንታዊው የታሪክ ጸሃፊ  የቱስዳይስ  The Peloponnesian war  ጀምሮ  እስከ  የጀርመኑ ካርል ቮን ክልሽዊትዝ  On War ፣  የባህር ሃይል  ስትራቲጂ አባት አልፌሬድ ማሃን The influence of Sea Power Upon History፡ ከዘመን ተሻጋሪ  የስትራቴጂ አስተምሮዎች ፈላስፋ ቻይናዊው ከሰን ዡ The Art of War  አንስቶ እሰከ ሉትዋርክ፣ ኮሊንስ የመሳሰሉ የዘመናችን የስትራቴጂና የደህንነት ጥናቶች ታላላቅ ተመራማሪዎችና  ምሁራን  የጻፏቸውንና ያፈለቁዋቸውን የስትራቴጂ ጽንሰ ሃስቦችና ቀመሮች  በጥልቀት ማጥናትና ማወቅ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው፡፡  የሴኪዩሪቲና የስትራቴጂ እውቀቶችን ባካበቱ ምሁራንና ተመራማሪዎች የሚጻፉ የአብይ ስትራቴጂ (Grand strategy) ንድፈ  ሃሳቦችና ጽንሰ ሃሳቦች፣  ከነዚህ የሚመነጩ የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ቀመሮችን ተመርኩዞ  የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲዎችን መንደፍ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተጋረጡባት ድርብርብ የፖለቲካ ችግሮችና ከችግሮቹም የሚመነጩትን ዘርፈ ብዙ የደህንነት አደጋዎችን ለመከላከል የማይናቅ ድርሻ አላቸው። በእነዚህም ዙሪያ  ጥልቀት ያላቸው ጥናቶችን ማድረጉ አስፈላጊ ነው። እነዚህንም የሚያስፈጽሙ አካላት መኖርና መጠናከር ለኢትዮጵያም ሆነ ለማንም ሀገር አስፈላጊ ከሆኑ ተቋማት ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጡ መሆናቸው አይካድም። ከዚህ አኳያ ጄነራል ጻድቃን በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲዎችና ተቋማት ለአንድ ሃገር የሚበጁ እንደሆኑ ወደ አደባባይ ጉዳዩን ማቅረባቸው ያስመሰግናቸዋል።

ነገር ግን በዋነኝነት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ስርአት መሪዎች ባህሪ ፣ የፖለቲካ ታሪካቸው (track record)፣ የሚከተሉት ኣካሄድና የፓለቲካ ፍላጎት በሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ቀዳሚና  ወሳኝ (Decisive) ድርሻ እንዳላቸው ክርክር የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም። ይህንን ቀላል ዕውነት መረዳት የችግሮቻችንን መሰረት ለማወቅ ፣ አውቆም በቀዳሚነት የሚያስፈልገው ያለፈው 26 አመት ህወሃት የዘረጋውን  የፓለቲካ ስርአትና ተከትሎት የመጣውን  ግዙፍ  የደህንነት አደጋዎች ለመገንዘብ ይረዳናል።  ይህን አደጋ ለመቀልበስ ደግሞ ቁርጠኝነትና  የፓለቲካ ወኔ (Political will)  መኖር   ዋናው ቁልፍ ነው። ይህም በመሆኑ ነው “የፓሊሲዎች ቈንጮ የሆነውን የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ” በባለቤትነት፣ በአስፈጻሚነትና በኣስተግባሪነት አሁን ላለው የሀገሪቱ የደህንነት ስጋት ዋና ቀፍቃፊ ምንጭ ለሆነው  የሕወሃት አመራር መስጠት ውሻን ሉካንዳ ቤት እንዲጠብቅ ከማድረግ ይቆጠራል ብዬ የምከራከረው። የብሄራዊ  ደህንነት አደጋዎች አመንጪና አሽከርካሪ (driver) የሆነውን አካል የዚህ ፖሊሲ ባለቤትና አስፈጻሚ ማድረጉ ስርአቱን ትንሽ ጠጋግኖ ለማስቀጠል ይረዳ እንደሆን እንጂ በዘለቄታው የኢትዮጵያን የደህንነትና ተያያዥነት ያላቸውን ዘርፈ ብዙ የፖለቲካ  ችግሮች  ማስወገድ አይቻልም። እንዳውም በተቃራኒው እነዚህ  ዘርፈ ብዙ የሀገሪቱ የፓለቲካ ችግሮች ተወሳስበው መቀጠላቸውና  ሀገሪቱንም ሆነ የአፍሪካ ቀንድን ለከፋ ትርምስና የደህንነት ኣደጋ ማጋለጣቸው አይቀሬ ነው።

ህወሃት የስልጣን ዕድሜውን ማስቀጠያ መርህ ወይም ከልቡ የሚያምንበት ገዢ ሃሳብ ከጠፋበት ሰንበትበት ብሏል። ህወሃቶችንና ኢህአዴጎችን አጣብቆ የሚያቆያቸው መርህ ፍርክርክ ባለበት፤ በተለይ ከቀድሞ መሪያቸው ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በእውር ድንብር በሚሄዱበት፤ በውስጣቸው የሚገኘው ቅራኔና ክፍፍል በጦዘበት፤ ሆኖም ላንሰራፉት የአንድ ብሄር የበላይነትና የዘረፋ ስርአት መሳሪያ የሆነን የመንግስት ስልጣን እንዳያጡ ተጣብቀው የሚገኙበት ሁኔታ ላይ ነው ያሉት። የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያማልሉበት፣ የሚያሳምኑበትና ከጎናቸው የሚያሰልፉበት ሃሳብ እንደሌላቸውም ግልጽ ከሆነ ቆይቷል። ባጠቃላይም በህወሃት የበላይነት ስር የሚገኘው የፖለቲካ ስርኣት የቅቡልነት፣ የህጋዊነት፣ ብሎም የራስ መተማመንና የውህድ አመራር እጦት ድርብርብ ቀውሶች ታማሚ ሆኖ በሚማቅቅበት በአሁኑ ቀውጢ ሰዓት ላይ ጄ/ል ጻድቃን አንድ መላ ይዞላቸው የመጣ ይመስላል።  ምናልባትም “የሕዝብ የአስተሳስብ አንድነት” ሊያመጣ የሚችል ሁሉን አሰባሳቢ ገዢ ሃሳብ ነው ብለው ገምግመው ሊሆን እንደሚችል ከግምት ውስጥም ማስገባት ያስፈልጋል።

“ከህገ መንግስቱ በታች የፓሊሲዎች ቁንጮ” የሆነው የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ በአግባቡ ተቀርጾ፣ ይህንን በቋሚነት የሚሰራ ኣስፈጻሚ አካል ማደራጀት ዋነኛ የኢትዮጵያ የፓለቲካ ችግሮች መፍቻ ምትሃታዊ አቅም (ማጂክ ዋንድ) ወይም የብር ጥይት (ሲልቨር ቡሌት) እንዳለው ተደርጎ በጄነራሉ ሰፊ ትንታኔ የተሰጠበት አይነተኛ ምክንያትም ከላይ የተዘረዘሩትን ግቦች ለማስፈጽም እንዲረዳ ታስቦ ሊሆን ይችላል። በመሰረቱ የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ራሱ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነው። አገዛዙ የሚያራምዳቸው ዘርፈ ብዙ ጸረ-ህዝብና ጸረ -ዲሞክራሲያዊ ተግባሮቹ  በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ችግሮች ዋነኛ ምንጭና ተዋናይ መሆኑን በገሃድ የሚያሳዩ ምስክሮች ናቸው። ለዚህም ነው ጄ/ል ጻድቃን በሰፊው ትንታኔ የሰጠበት የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ መኖር አለመኖር ወይም ይህን ፓሊሲ የሚከታተልና አማራጭ ሃሳቦችን የሚያቀርብ ቋሚ አካል መኖር አለመኖር ሕወሃትን ቀስፎ ከያዘውና ከሚያሰቃየው የውስጥ ደዌው ጋር እምብዛም ተያያዥነት የለውም ብሎ መከራከር የሚቻለው። ጄ/ል ጻድቃን “የፓለቲካ ችግሮች”  በሚል ጥቅል ሀረግ አደባብስው ያለፉዋቸውን ሕወሃት ሰራሽ የሆኑ ችግሮችን እንደሚከተለው ማቅረብ ይቻላል።

ዋናው የኢትዮጵያ የደህንነት ኣደጋ የሀቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት አለመኖር ነው። ትልቁ የደህንነት አደጋ የኢትዮጵያን የብሄር ችግሮች ፈትቷል ተብሎ ከጅምሩ ሕወሃት እንደ ትልቅ ስኬት ሲመጻደቅበት የቆየው ፌዴሬላዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ዴሞክራሲያዊም ፌዴራላዊም አለመሆኑ ነው! የህወሃትን ፍላጎት፣ የበላይነት፣ የዘረፋ፣ የኣድሎአዊነትና የዘረኝነትን ስርዓት ማስጠበቂያና ማስቀጠያ መሳሪያና ጭንብል ከመሆን በዘለለ የተባለውን ሐቀኛ ዴሞክራሲንም ሆነ ፌዴራሊዝምን እውን አለማድረጋቸው ነው።

ህወሃት መራሹ የኢትዮጵ እገዛዝ ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በባርነት ቀንበር ውስጥ ጠፍንጎ ይዞ፣ ስልጣን ከላይ እስከ ታች ድረስ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር አስገብቶ አይን ያወጣ ዘረፋ፣ ግድያና አፈና መፈጸሙና ማስፈጸሙ የህዝብና የዜጎች የዕለት ተዕለት ትእይንት የሆነባት አገር ናት ኢትዮጲያ!  ህዝቦቿ ባዶ እጃቸውን አደባባይ ወጥተው የመብትና የዴሞክራሲን ጥያቄ ባቀረቡ ቁጥር መልሳቸው በአጋዚ ቅልብ ጦርና በፌዴራል ፖሊስ  እንደ ጠላት በጥይት የሚቆሉባት፣ ዜጎቿ በጅምላ የሚታሰሩባት፣ የሚፈናቀሉባት፣ በየአመቱ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቿ የሚራቡባት፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለተሻለ ሕይወት ወደ ስደት ሲሄዱ በባሕር ላይ የዓሳ ነባሪ ቀለብ ሆነው የቀሩባት፣ እህቶቻችን የአረብ ገረዶች ሆነው ለወሲብ ጥቃት የተጋለጡባት፣ ከፎቅ ላይ እየተወረወሩና በፈላ ውሃ እየተቀቀሉ በየቀኑ ሬሳቸው ወደ አገር ቤት የሚጫንባት፣ ነዋሪዎቿ በቆሻሻ ክምር ናዳ የሚያልቁባት አገር ሆናለች ኢትዮጲያ!  ከዚህም በተጨማሪ ዜጎች የመኖር ዋስትና ተነፍጓቸው በሰላም ከቤታቸው ወጥተው በሰላም መግባት የሚችሉበት ሕይወት የሩቅ ዘመን ትዝታ ከሆነ ሰነባብቷል።  እንደ አሸን የፈሉ የስርዓቱ ሰላዮች እስከ ቤተክርስቲያንና መስጊድ ድረስ ሳይቀር ለመሰለልና አለመተማመንን ለመፍጠር  የተሰማሩባት፣ ዘረፋ፣ ውሸት፣ ሌብነትና ማጭበርበር ባህል የሆነበትና ሰዎችን እንደሸቀጥ የማዘዋወር ንግድ እየተንሰራፋ የመጣበት አስደንጋጭ ሁኔታም ተፈጥሯል። እነዚህና ሌሎች እዚህ ላይ ያልተዘረዘሩ ተወራራሽ ችግሮች ህወሃት በሚመራው አገዛዝ የተፈጠሩ ናቸው።

ጄነራል ጻድቃን በእድገትም፣ በዲፕሎማሲም ሆነ በሰላም ማስከበር ወዘተ በአለም ማህበረሰብ ዘንድ የሃገራችን ተቀባይነት ጨምሯል በማለት የህወሃትን አገዛዝ “ስኬቶች” እውቅና በመስጠት ችግሩ በዋነኛነት የውጪና የደህንነት ፖሊሲ ችግር ነው በሚል አገላለጽ  ለማድበስበስ ሞክረዋል። እንዲሁም ብጥብጥና ትርምስ የፈጠሩት የጸረ ሰላም ሃይሎች በቀጥታ ከሻዕቢያ ወይም በሻዕቢያ መንግስት አቀነባባሪነት የተፈጠረ ነው የሚል አንደምታ ያለውም ሃሳብ አስቀምጠዋል። በተለይም ደግሞ ጄነራሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያነሳውን ተደጋጋሚ የመብትና የነጻነት ጥያቄ በሻዕቢያ ተላላኪነት የፈረጇቸው ሽብርተኞችና የጸረ ህዝብ ሃይሎች ሴራ አድርገው ለማቅረብ የሞከሩበት ሂደት በጣም አስገራሚ ነው።

የህወሃት ትግራዮች የበላይነት በሌሎች ህዝቦች ኪሳራ በኢኮኖሚ፣ በፓለቲካ፣ በወታደራዊ፣ በደህንነት ተቋማት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ እንዲኖራቸው መደረጉና ይህም ኢፍትሃዊ አሰራር በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የፈጠረው የበይ ተመልካችነት፣ የባይተዋርነትና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ስሜት በህዝቦች አብሮ የመኖር እድል ላይ አሉታዊ ጥላውን አሳርፏል። ይህም ጤናማና የተረጋጋ ማህበረሰብ ለዘለቄታው ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ላይ የራሱን ሳንካ ማሳረፍ ብቻ ሳይሆን ህዝብ ለህዝብ፣ ብሄር ለብሄር በጎሪጥ ኣንዲተያይ፣ በተቃርኖ እንዲቆምና ወደ ግጭት ምናልባትም ፍጅት ወደሚያስከትል ደረጃ ያደርሰው እንደሁ እንጂ  የብሄራዊ ደህንነትን ወደሚያረጋግጥ፣ የሰላምና መረጋጋትን ዋስትና ወደሚያስቀጥል መንገድ ፈፅሞ ሊመራው አይችልም።

እጅግ ጥልቀት ያለው የደህንነት ፖሊሲ ተቀመረ አልተቀመረ ፋይዳ ቢስ ነው። መሰረታዊ ምክንያቱም ይህ ፓሊሲ ሊከላከላቸው የሚችሉ የደህንነት አደጋዎች መሰረታዊ ምንጫቸው የደህንነት ፖሊሲ አወጣለሁ የሚለው ራሱ ህወሃት የዘረጋው አምባገነናዊ፣ ዘራፊ፣ ዘረኛ፣ አድሎአዊ የአፓርታይድ መሰል ስርአት በመሆኑ ነው! ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ ህወሃት ራሱ የሃገሪቱ ዋነኛ የደህንነት ስጋት ሆኖ ሳለ “በጥልቀት የተጠናና ምልእኡ የሆነ የሃገሪቷን የደህንነት ፖሊሲ አስፈጻሚ/አስተግባሪ ምሆኑ በጣም አስቂኝ ያደርገዋል። ጄነራሉም ቢሆኑ ህወሃትን የሃገሪቷ የደህንነት ስጋቶችና አደጋዎች የሚያመንጭ ኃይል ሆኖ ሳለ ራሱ መፍትሄ ብሎ የሚያስቀምጠውን የደህንነት ፖሊሲ ባለቤትና አስፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል መረዳት የገባዋል። በህወሃት የበላይነት የሚዘወረው አገዛዝ የሃገሪቷ ትልቁ የደህንነት ስጋትንና አደጋ ስለመሆኑ መካካድ አያስፈልግም። ጄነራል ጻድቃን ይህንን ሐቅ ጠንቅቀው የሚረዱት ይመስለኛል።

ከላይ እንደተጠቀሰው እጅግ ከባዱ የኢትዮጵያ የደህንነት አደጋ ህወሃት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያንሰራፈው የትግራይ የበላይነት ወይንም የገዢ መደብነት ስርአት ነው። ይህም ስርዓት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በመንግስታዊ ተቋማት፣ በመከላከያ፡ በደህንነት  “እንወክለዋለን የሚሉትን” የትግራይ የህዝብ ቁጥር ፈጽሞ የማይመጣጠን የአናሳ ብሔር አባላትን የተጠቃሚነት፣ የፈላጭ ቆራጭነት፣ ኢፍትሀዊ በሆኑ መንገዶች ለዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ ሳይሰሩ በአንድ ጀንበር ባለሃብት የሚሆኑበትንና የሚከብሩበትን መንገድ በግልጽና በስውር ያመቻቸ እኩይ ስርዓት ነው። በሌላ በኩልም  በየእስር ቤቶቹ የሌሎች ብሄር ተወላጆች “አንተ አማራ፣ አንተ ኦሮሞ፣ አንተ  ጉራጌ. ሽንታም ” በማለት እያዋረዱ ትግሪኛ ተናጋሪ በሆኑ የሰርዓቱ ሰዎች የሚፈጸሙ እጅግ ዘግናኝ ግፎችና ሰቆቃዎችን እዚህ መዘርዘሩ ለቀባሪው ማርዳት ነው። የዚህ መጥፎ ስርዓት ሰላባ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሃያ ስድስት ዓመታት ያየው፣ የሰማው፣ የደረሰበትና ያንገፈገፈው የግፍ ዋንጫ ነውና! በብዙ መገለጫዎች የሕወሃትን የበላይነት፣ መሰሪነት፣ ስግብግብነት፣ ጭካኔ ማሳየት ይቻላል። ለዚህም ነው ህወሃት የሚዘውረው አገዛዝ ከመቼውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደህንነት ስጋትና አደጋ ተደርጎ የሚቆጠረው። ጄነራል ጻድቃን ይህን ራሱ ስጋት የሆነውን ሃይል ነው እንግዲህ ሃገሪቷን የሚያረጋጋና ከተደቀኑባት የደህንነት አደጋዎችም መጠበቅ የሚያስችል የደህንነት ፖሊሲ እንደሚያወጣና የፖሊሲው ይዘትም ምን መሆን እንዳለበት የተናገሩት!

የኢትዮጵያ ህዝብ በፍትህ ህይወቱን የሚመራበትን፣ የህግ የበላይነት በሰፈነበት ስርአት የሚዳኝበትን፣ ፍትሃዊ የሆነ የስልጣንና የሐብት ክፍፍል፣ ማህበራዊ ፍትህ  የሚሰፍንበትን ስርዓት ከምንም ጊዜውም በላይ ይናፍቃል። ዜጎች በነጻነት አብረው የሚኖሩባት ፣ የዘላቂ ሰላምና ደህንነት ዋስትና የተረጋገጠባት፣ ብዙሃኑ እየተራበ ጥቂቶች በጥጋብ የማያገሱባት፣ ማሕበራዊ ፍትህና ብልጽግና ለሁሉም አካባቢዎች በተግባር የሚተረጎምባትን ኢትዮጲያን ማየት ይመኛል። ሆኖም ከምኞት ባሻገር ለነኚህ የተቀደሱ ዓላማዎች መሳካት ዜጎች ሁሉ ከልብ ሊጨነቁባቸው፣ ብሎም በጽናት ሊታገሉላቸው የሚገቡ ግቦች መሆን አለባቸው። አሁንም እደግመዋለሁ!   ዛሬ  በኢትዮጳያ  ውስጥ የተንሰራፋው የሕወሃት ገዢ መደብ ሁሉንም በባለቤትነትንና በበላይነት  ይዞ በሚገኝበት እጅግ አስፈሪና አሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን።

ይህ ዐይን ያወጣ አድሎአዊና ኢፍትሀዊ የስልጣን፣ የሀብትና የጥቅም ክፍፍል ብሎም ይህ ክፍፍል የፈጠረው አስከፊ የሆነ ብሄሮች የጎሪጥ የሚተያዩበት ሁኔታ ሊካድ አይገባውም። እንደውም የብልህና አርቆ አሳቢ፣ ዘመን ተሻጋሪ፣ ባለራይና  የፓለቲካ መፍትሄ አመንጪነት መነሻ መሆን ያለበት ይህን መራር ሐቅ ከምንም በፊት አስቀድሞ በመቀበልና በመጋፈጥ መሆን ይኖርበታል።፡ ምክንያቱም ይህ ነባራዊ   ሁኔታ ለዘለቄታው የሕዝብ አብሮ መኖር፣ ሰላም፣ መረጋጋትና ባጠቃላይ ለሀገሪቱ ህልውና የሚያሰጋ ትልቁ  የደህንነት ፈተና  በመሆኑ ነው። እናም ይህንን  አደገኛ አካሄድ በትዕግስት፣ በጥበብና በቁርጠኝነት በመቀልበስ  የአገሪቱን ህልውና፣ የሕዝቦችን  በእኩልነትና በሰላም መኖር ለማረጋገጥ መጨነቅና መታገል ሲገባ ነው እንጂ ጄነራሉ እንዳነሱት ሃሳብ የችግሮቹን ዋና ምንጭ ትተው ጉዳዩን ከውጪና ደህንነት ፖሊሲ ጋር  በዋነኘት በማያያዝ አይደለም።አለባበሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዳይሆን።

በኢትዮጵያ ውስጥ መጥቶ የነበረው የጸጥታ ችግር አስቀድሞ ሊታይ ይችል ነበር። በሰው ህይወት፣ በንብረት ላይ ጉዳት ሳያስከፍል፣ የጊዜአዊ ኣስቸኳይ ኣዋጅ ሳያስፈልግ ለመከላከል ይቻል ነበር። ሀገር ተናውጦ “በጊዜያዊ አስቸኳይ አዋጅ ነው የቆመው” ይላሉ ጄ/ል ጻድቃን!  እውን የመጣው የህዝብ ቁጣና አልገዛም ባይነት የፖሊሲ አለመኖር ወይንስ የሕወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሲዎች ጸረ-ህዝብነት ያመጡት ነው ብሎ ለጠየቀ ሰው መልሱ ግልጽና ግልጽ ሆኖ ይታየዋል። በተለያዩ ጊዜያት የተተገበሩ የህወሃት ፓሊሲዎች ያመጡት ድርብርብ ችግሮች መሰረቱ የስርዓቱ ጸረ- ዲሞክራሲያዊና ጸረ- ህዝብነት መሆኑ ላይ ነው። ሌላ ምንም ሚስጥር የለውም! ይህን መሰረታዊ ችግር በደህንነት ፖሊሲ ምሉዕነትና አፈጻጸም ያለመኖር  የመጣ ችግር ነው ብሎ ለማቅረብ መሞከር ሃገሪቱ አሁን የገባችበትን ቅርቃር በሚገባ ባለመገንዘብ ወይንም ኃላፊነት በጎደለው መንፈስ ሆነ ተብሎ ለራስ በሚሰላ ጥቅም አማካኝነት ችላ የማለት ጉዳይ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው።

ጄ/ል ጻድቃን የስርዓቱን ዝቅጠት “የውስጥ የፓለቲካ ችግር” ሲሉ በደምሳሳው ቢገልጹትም የሀገሪቱን የፓለቲካ ችግሮች ዋና ዋና ገጽታዎች ከዚህ በፊት በጻፉት ጽሁፍ በስሱም ቢሆን እንደገለጹት በዚህኛው ቃለ ምልልሳቸው ሊገልጹና ሊዘረዝሩ አልደፈሩም። መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎችና ከላይ የተዘረዘሩት እውነታዎች የሚቀየሩበት መሰረታዊ ለውጦች እስካልመጡ ድረስ “የህዝብ የአስተሳሰብ አንድነት” ሊመጣ ከቶም አይችልም። በሀገሪቱ የሚገኙ ችግሮች ስርአቱ የወለዳቸውና ያሳደጋቸው እንደመሆናቸው መጠን በዚህ ስርአት የህዝብ ጥያቄዎች መልስ ሊያገኙ እንደማይችሉ ያለፉት ሃያ ስድስት አመታት ስለ ስርአቱ ማንነትና ምንነት ብዙ አሳይቶናል፤ ብዙም አስተምሮናል። በዚህ ረዥም ሂደት ውስጥ ህወሃት ይበልጥ ከህዝቡ እየተነጠለ ዛሬ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የስርአቱን መውደቅ የሚናፍቅበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ህወሃት የህዝቡን የአስተሳሰብ አድማስ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለመምራት ቀርቶ የራሱንም ህልውና ለማቆየት ከማይችልበት አዘቅት ውስጥ መግባቱን ለማሳየት  ብዙ መድከም የሚያስፈልግ አይመስለኝም። እንዳውም ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት ““ሕወሃት የወደቀበት አዘቅት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ በሕይወት ይቆይ ይሆን?” የሚለው ይመስለኛል።

በመቀጠልም አሁንም ትልቅ የደህንነት አደጋ  “እያረገዘ ያለ ሊኖር ይችላል” ይላሉ ጄ/ል ጻድቃን። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እነዚህ የተረገዙ ችግሮች የፖለቲካ ስርዓቱ መሰረታዊ ለውጥ እስካላመጣ ድረስ መፈንዳታቸው አይቀሬ ነው። ለማርቀቅና ለማጸደቅ ውይንም ለማሻሻል እያሰቡት ያለው የደህንነት ፓሊሲ ይህን የለውጥ ሱናሜ ሊያቆመው ከቶም አይቻለውም። ሌሎች የስርአቱ ፓሊሲዎች ሁሉ የሚመነጩት ከዚህ የህወሃት መለያ ከሆኑት ስግብግብነቱ፣ ጸረ ዲሞክራሲያዊና ጸረ ህዝብ ባህሪያቶቹ በመሆኑ ነው።”መከለስ ያለበት” የውጪና የደህንነት ፖሊሲም ከህወሃት ጸረ ህዝባዊነትና ጸረ ዲሞክራሲያዊነት የሚመነጭና የስርአቱን እድሜ ለማራዘም ተብሎ የሚቀመር በመሆኑ ከመነሻው ጄነራል ጻድቃን እንደተመኙት የችግሮቹ መፍትሄ ሆኖ ሊመጣ አይችልም።

መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች በመሰረታዊ ለውጦች እስካልተመለሱ ድረስም “የህዝብ የአስተሳሰብ አንድነት” ሊመጣ አይችልም። የሀገሪቱን ዘርፈ ብዙ የፓለቲካ ችግሮች ለመፍታት የማይፈልግ፣ ይህን ካደረግኩ ስልጣኔን አጣለሁ በሚል ስሌት ዘረኛና አምባገነን የሆነውን የህወሃት የፓለቲካና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት ለማስቀጠል የሚተጋ፣ በተንኮልና በመሰሪነት እንዲሁም በጭካኔው የተካነ መሆኑ የተረጋገጠለት ስርዓት የአገሪቱን የጸጥታና የደህንነት ችግሮች ለዘለቄታው ሊፈታ የሚችል ሃይል ሊሆን አይችልም።ከገለማ እንቁላል ጤናማ ጫጩት አይፈለፈልም እንዲሉ! ራሱ የሃገሪቷ የደህንነት ስጋት ስለሆነ ከማንም በላይ የችግሮቹ ምንጭና መንስኤ ነው!

አርበኞች ግንቦት 7ም ሆነ ኦነግ እንዲሁም ሌሎች ጄ/ሉ ያልጠቀሷቸው ሃይሎች ህልውና መሰረት በሃገር ውስጥ ህወሃት የፈጠራቸው ሁኔታዎች፣ ጸረ ህዝብነቱና ጸረ ዴሞክራሲያዊነቱ፣ ራሱ ያወጣውን ህገ-መንግስታዊ መብቶች በተደጋጋሚ በመርገጥ ስላማዊ ህጋዊ ትግልን ለማድረግ ፈጽሞ በማይቻልበት ደረጃ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥፋቱ እንጂ እነዚህን የፓለቲካ ሃይሎች ሚረዱ ሁሉ፡  ኤርትራን ጨምሮ ስለፈለጉ ሊሆን አይችልም። ጭቆና ባለበት ጭቆናን የሚታገሉ ሃይሎች መኖራቸው ተፈጥሯዊ እውነታ ነው። የነዚህን ሃይሎች ተጽዕኖ ለመቀነስና ጨርሶውኑ ለማጥፋት የደህንነት ፖሊሲ አይነቶች ቢደረደሩ ምንም የሚፈጥረው ፋይዳ የለም። የነዚህ ሃይሎች የህልውና መሰረት ስርዓቱ የፈጠራቸው ዘርፈ ብዙ “የፖለቲካ ችግሮች“ ናቸው። የስርዓቱ ጸረ ህዝብነትና ጸረ ዲሞክራሲያዊነት እስካለ ድረስ በየፊናው የሚደረገው ትግል እያደገና እየሰፋ እንደሚሄድና ህዝቡ ከዚህ አስከፊ ቀንበር ነጻ ለመውጣት ምንም አይነት መስዋዕትነትን ከመክፈል ወደኋላ እንደማይል ጄኔራሉ የሚጠፋቸው አይመስለኝም።

 (ይቀጥላል)

ነጻነት ቡልቶን ቀጥሎ ባለው የኢሜልና ፌስቡክ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ

Netsanetbulto2017@gmail.com                                             https://www.facebook.com/netsanet.bulto.58

ሌ/ጄነራል ጻድቃን፣ ህወሃት፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር ( በነጻነት ቡልቶ)

#ETHIOPIA | #ERITREA | ሌ/ጄነራል ጻድቃን፣ ህወሃት፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር

በነጻነት ቡልቶ

ክፍል ሁለት

ጄነራል ጻድቃን “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሀይል መሆን አለባት” የሚል አስገራሚ ሃሳብ አንስተዋል። “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሀይል መሆን አለባት” የሚለው ማደናገሪያ  ሃሳብ ሕወሃቶች ያዳከሙትን የኢትዮጵያን ብሄረተኝነት ስሜት ለማነሳሳት ይጠቅመናል በሚል ስሌት በእነ ጄ/ል ጻድቃን በኩል ነገሮችን ለማጥናት እየሞከሩ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል ። እንደሚታወሰው ቀደም ሲልም በአረብ ጸደይ (ኣረብ ስፕሪግ) ወቅት የአረቡን አለም ያናወጠው የለውጥ ማዕበል ወደ ኢትዮጵያ ይዛመታል የሚል ስጋት ውስጥ ገብቶ የነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ አባይን የመገደብ ፕሮጀክት በማስተዋወቅ የህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ- ውሱን በሆነ መልኩም ቢሆን- አስተዋጽዖ አድርጎላቸው ነበር ። አሁን ደግሞ ስርዓቱ ከገባበት አጠቃላይ ቀውስ ለመውጣት ባለተራው “የቀይ ባህር ሀይል” ሆኖ የመውጣት ጥያቄን ማራገቡ ያዋጣል የሚል መደምደሚያ ላይ  ደርሰውም ሊሆን ይችላል። በዚህ “ገዢ ሃሳብ” የ”ህዝብ የአስተሳስብ አንድነት” ይመጣል ከሚል እሳቤ የተሰላ ይመስላል።  በተጻራሪው ከዚህ አመለካከትና ኣቋም የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በግብጽ ወይንም ባጠቃላይ በአረብ  “ቅጥረኛነትና ተላላኪነት” ይፈረጃሉ  ማለት ነው፡፡ የደርግ ስርዓት ሻዕቢያን፣ ወያኔንና ሌሎች ተቃዋሚዎችን በዘመኑ ከፈረጀው ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ ማለት ነው። ደርግና ሕወሃት በዚህ ተቃዋሚዎችን ከመክሰስና ከመፈረጅ አኳያ ተመሳሳይነት እንዳሏቸው ማጤን ያስፈልጋል።

ብሔራዊ ጥቅም ወይንም “ናሽናል ኢንተረስት”  ከሚለው መርህ በመነሳት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ብሄራዊ ደህንነት ሊጠበቅ የሚችለው” የቀይ ባህር ሃይል መሆን ሲቻል ነው” የሚለውን ኣዲስ መዝሙር በማስተዋወቅ  እንደ ጄ/ል ጻድቃን አገላለጽ “የህዝብን የኣስተሳሰብ አንድነት’’ እናመጣለን ፣ የህዝቡንም ትኩረትና የሚጠይቃቸውን መሰረታዊ የፍትህ፣ የነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ የሃቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ምስረታ፣ እንዲሁም የስርአት ለውጥ ጥያቄዎች ወደ በስተኃላ መቀመጫ ይገባሉ ማለት ነው። በዚህም ስሌት የኢትዮጵያ ህዝብ ስርዓቱ የወለዳቸውን ዘርፈ ብዙ  የፓለቲካ ችግሮቹን ወደ ጎን ትቶ ቀይ ባህር ላይ  እንዲያንጋጥጥ ልናደርገው እንችላለን በማለት ሊሄዱበት እየተዘጋጁ ሊሆን ይችላል። የዚህ አመለካከትና ሂደት ዋነኛ ግብም  በህወሃት ስር የምትገኘው ኢትዮጵያ የአካባባዊ ሃይል የምትሆንበትና ህወሃት ያንሰራፋው የትግራይ የበላይነት  የስልጣን እድሜ የሚቀጥልበትና  የሚረጋገጥበትን ስርዓት ማጠናከር ነው። ይህንኑም እውን ለማድረግ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ማናቸውም ተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎች  የሚመቱበት፣ እንደ ጄኔራሉ አገላለጽም በመንግስት “ቁጥጥር ስር የሚውሉበት”፣ እነዚህን ሀይሎች ይደግፋል በሚል የሚከሰሰው “የኢሳያስ ኣፈወርቂ  የኤርትራ መንግስት” የሚወገድበት ሁኔታ ይመቻቻል ማለት ነው።

ለመሆኑ የሕወሃት አገዛዝ የቀይ ባህርንና የባህር በርን ጉዳይ ለማሳካት ጀ/ል ጻድቃን እንደሚለው በወታደራዊ መንገድ ኤርትራን ለማጥቃትና ያለውን መንግስት ለማስወገድ ወታደራዊ ብቃቱና አቅሙ አለውን?

በዚህ ጥያቄ መነሻነት የተወሰኑ ነጥቦችን አፍታተን ብናየው መልካም ይመስለኛል።

ህወሃት ስትራቴጂክ አመራር ሊሰጥ የሚችል ወታደራዊ አዛዦች የለውም። የሕወሃት ጄነራሎች መከላከያውን ባለፉት ሀያ አመታት 95 በመቶ፣  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከ70 በመቶ በላይ በስትራቴጂክና ከዚያም በታች ባሉ እርከኖች በአመራርነትና በአዛዥነት ለ26 አመታት ተቆጣጥረውታል። የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች አሁን ያሉበትን የስልጣን ቦታ የያዙት በብቃት፣ በእውቀትና በክህሎት መስፈርቶች ሳይሆን በፓለቲካና በመጡበት የትግሬ ብሄር ተወላጅነታቸው ወይንም የሕወሃት ታጋዮች በመሆናቸው ብቻ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። መሰረታዊ በሚባል ደረጃ አለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ የመደበኛ ሰራዊት ማለትም የምድር፣ የአየርና ልዩ ልዩ ሃይሎችን አስተባብረውና አቀናጀተው ለመምራት የሚያስችል እውቀትም፣ ትምህርትም ሆነ ክህሎት እንደሌላቸው በድፍረት መናገር ይቻላል። ይህንንም ሃቅ ጄነራሉ ጠንቅቀው ያውቁታል።

የወያኔ ሰራዊት ሞራል በጣም የዘቀጠ መሆኑን ጄ/ል ጻድቃን የሚጠፋቸው አይመስለኝም። ሰራዊቱ በብሄር እንዲያስብና እንዲከፋፈል መደረጉ ከፍተኛ ለሆነ የስነ ልቦና ክስረት ዳርጎታል። የሰራዊቱ ጓዳዊ ግንኙነት በጣም የላላና በጎሪጥ የሚተያይ ሆኗል። ከላይ እሰከ ታች ማለትም ከስትራቴጂክ እዝ እስከ ታክቲካል የሚንቀሳቀሰው በወታደራዊ ዕውቀት፣ ብቃትና ክህሎት ሳይሆን በፓለቲካዊ ታማኘነትና በህወሃት ትግሬነት የተደራጀ እዝና ቁጥጥር (Command and control) ባለበት ሁኔታ መሆኑም ያደባባይ ሚስጥር ነው። የመከላከያ ተቋሙ የሰራዊቱ አዛዦች በተለይም የህወሃት ምርጦች  የሰራዊቱን የስንቅ አቅርቦት በማጭበርበርና በኮንትሮባንድ ንግድ የሚከብሩበት (በተለይም በሶማሊያና በኦጋዴን)፣  ለሰራዊቱ ከውጭ የሚመጡ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን፣ አውሮፕላኖችንና  መለዋወጫዎችን በመሸጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ኪሳራ እየደለቡ ያሉበትና በሙስና የተጨማለቁ አመራሮች የተሰገሰጉበት ሆኗል!  ሰራዊቱና የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ዕውነት በሚገባ እያወቀው፣ ሰራዊቱን ተማምኖ  በፈረንጆቹ በ2000 ዓ/ም እንዳደረገው የሕወሃትን የበላይነት በኢትዮጵያ ህዝብና በአካባቢው ሀገሮች ላይ ለማስቀጠል ኤርትራን በወታደራዊ ጡንቻ አዳክማለው ወይንም “የኢሳያስ እፈወርቂን መንግስት” አስወግዳለሁ ብሎ አጉል ቢጋበዝ  ለዳግም ለቅሶና ውርደት ሊዳርገው የሚችል አካሄድ መሆኑን ጄ/ል ጻድቃን ሊጠፋቸው  የማይችል ሃቅ ነው።

በአሁን ሰአት ጦርነት ቢነሳ በኤርትራ በረሃና ተራራማ ቦታዎች ውስጥ ዘልቆ ማዋጋት የሚችል ከፍተኛ የጦር አዛዦች የሉም። የሰራዊቱ የሰው ሃይል በጣም አነስተኛ ነው። በአሁኑ ሰአት የመደበኛ ተዋጊው ሃይል በጣም በዛ  ቢባል ከ120,000 አይበልጥም። በህወሃት ስር የሚገኘው ሰራዊት 18 ክፍለ ጦር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6ቱ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ነው። የተቀረው 12ቱ እግረኛ ክ/ጦር ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ሰራዊቱ ከመከላከያ እየከዳ መጥፋት የእለተ ተሌት ክስተት ሆኖ በአዛዦች ደረጃ የሚጠፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየተበራከቱ መጥተዋል። በአሁኑ ሰአት በአንድ እግረኛ ክ/ጦር ውስጥ ቢበዛ 6,000 ሰራዊት ነው ያለው። በሜካናይዝድ ክ/ጦር ደግሞ ቢበዛ ከ 2500 አይበልጥም። በዚህም መሰረት በሕወሃት ስር የሚገኘው ሰራዊት ሌላን አገር መውረር ቀርቶ ከሌላ አገር ጥቃት ቢሰነዘርበት እንኳ ያንን መመከት የሚችል የሰራዊት ብዛትም ሆነ አቅም በጭራሽ የለውም።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የህዝብ ተቃውሞ በተለይ በአማራና በኦሮሚያ አካባቢዎች ያለው ተቃውሞ በተፋፋመበት ሁኔታ ህወሃት ወደ  ኤርትራ ጦርነት ቢጀምር  መሃል አገሩ ክፍት ስለሚሆን ህወሃትን ለማስወገድ ወደ ኤርትራ ጦርነት መክፈቱ ለተቃዋሚዎች ትልቅ የምስራች ተደርጎ እንደሚወሰድ ህወሃት ራሱ ያውቀዋልና ድንበር አካባቢ ለማስቀየሻ  ካልሆነ  በስተቀር ህወሃት በኤርትራ  ላይ ሙሉ ጦርነት አይከፍትም። ነገር ግን በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተቅበዝብዞ ሙሉ ጦርነት ከከፈተም የራሱን የመቃብር ጉድጓድ መቆፈር ይሆናል።

በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት (በፈረንጆቹ 1998-2000)  ወቅት ከመረጃ አንጻር ትልቁን ሚና ሲወጡ የነበሩት የቀድሞ የደርግ አገዛዝ ስር ያገለገሉ የሰራዊት አባላት ነበሩ። አብዛኛው የቀድሞ ሰራዊት በኤርትራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በግዳጅ የቆየ በመሆኑ የኤርትራን እያንዳንዱን አካባቢና ክፍል እንደ እጅ መዳፉ ያውቁ ነበር። በዚህም ሁኔታ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት እነዚህን የቀድሞ ሰራዊት አባላትን በመጠቀም ህወሃት የነበረበትን የመረጃ ክፍተት ጭምር ለመሙላት ጥሯል። ይህም በጦርነቱ ሂደት ተጠቅሞበታል።

አሁን ባለበት ሁኔታ ግን ህወሃት ኤርትራን በሙሉ  ልውረር ቢል የትኛው የህወሃት የጦር አዛዥ ነው የኤርትራን ተራራማ የውጊያ ቀጠናዎች በአግባቡ ሊያውቅ የሚችለው? እንደሚታወቀው አብዛኛዎቹ የህወሃት የጦር አዛዦች መሰረታዊ የሚባለውን የካርታ ንባብ እንኳን የማያውቁ ናቸው። ከመረጃ ጋር ተያይዞ  ህወሃት በኤርትራ ውስጥ ስላለው አጠቃላይ ሂደት አንድን ጦርነት ለማከናወን የሚያስችል በቂ መረጃ እንደሌለው በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ውስጥ የሚሰሩ አካላት ሁሉ የሚያውቁት እውነታ ነው።

ህወሃት ኤርትራ ላይ ሙሉ ወረራ እፈጽማለው ቢል እንኳን እኔ ባለኝ ግርድፍ ግምት በትንሹ 200,000 መስዋዕት የሚሆን ሰራዊት ያስፈልገዋል ። ሙሉ ወራራ ከታቀድም  ቢያንስ ቢያንስ 3 እጥፍ በትንሹ  ከ600,000 በላይ ሰራዊት ማሰለፍ ሊኖርበት  ከዚህ ውስጥም ቢያንስ 200,000 ሰራዊት ጭዳ፣ ፈንጂ ረጋጭና የጥይት ማገዶ በማድረግ ነው አስመራ ሊገባ  የሚችለው። እኔ እስከሚገባኝ ዋናው የጦርነት ቀጠና ደግሞ አስመራ አይደለም። ደርግ 17 አመት ለፍቶ ናቅፋን መያዝ ያልቻለውን ህወሃት ከአስመራ፣ ከረን እስከ ናቅፋ የተዘረጋውን ሰፊ  የጦርነት ቀጠና ለመወጣት ምን ያህል ሰራዊት ያስፈልገዋል ስንል ጉዳዩ ምን ያህል ውስብስ እንደሆነ እንረዳዋለን። በተለያየ ምክንያት ይህን ያህል ቁጥር ሰራዊት ማሰባሰብ ቢቻል እንኳን ከስትራቴጂክ ጉዳዮች እስከ ታክቲካል ደረጃ ያሉ የውጊያ ሂደቶችን መምራት የሚችሉ የጦር አዛዦች የሉም። ይሄ ማለት ጄኔራል ጻድቃን ያሰቡት ጦርነቱ ሳይጀመር በሽንፈት መጠናቀቁን የሚያሳይ ይሆናል።

ሌላ ትልቅ ነጥብ እናንሳ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዊያን በኢትዮ-ኤርትራ (ከፈረንጆቹ 1998-2000) እነ ጀ/ል ጻድቃን በመሩት ጦርነት ህይወታቸውን ገብረዋል። እኔ ባለኝ መረጃ በጦርነቱ 92,450 በላይ የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ህይወታቸውን መሰዋት አድርገዋል። ለከባድ እና ቀላል የአካል መቁሰል የተዳረጉ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤት ይቁጠራቸው። እንግዲ ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው ድንበር አካባቢ በተደረገ የአውደ ውጊያ ቀጠና ነው። ወደ ኤርትራ ውስጥ እየዘለቁ የሚኬድ ቢሆን ኖሮ የጉዳቱ መጠን ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። በኢትዮጵያውያን ላይ እንደደረሰው ጉዳት ሁሉ ያ ጦርነት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የኤርትራ ወጣቶችን ህይወትም የቀጠፈ ጦርነት ነበር። በኤርትራ ምድር ልጁን ያላጣ አካባቢ መኖሩ ያጠራጥራል። በኤርትራ ምድር ለሚሰማው ሀዘን፣ ቁጭትና፣ ከፍተኛ ምሬት ለጦርነቱና ለተከፈለው የህይወትና የንብረት ውድመት ኪሳራ ተጠያቂ የሚያደርጉት ህወሃትን ነው። እንዲያውም ወረድ ሲል በኣንዳንድ አካባቢዎች እነዚህ  “ትግሬዎች” በደርግ ዘመንም ሰላዮች ሆነው ልጆቻችንን  ሲያሳስሩ፣ ሲያስገርፉና  ሲያስገድሉ ነበር የሚል ሮሮ የሚሰማ ሲሆን አሁንም የልጆቻቸውን ህይወት የቀጠፈውን የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት  በተመሳሳይ መንገድ የሚተረጉሙ በሚልዮኖች እንዳሉ መታወቅ ይኖርበታል። ጦርነቱን ተከትሎ ለትግራይ ማህበረሰብ ያለው ጥላቻ እንዲ በቀላሉ የሚታይ አይመስለኝም። በመሆኑም የህወሃትን ወረራ ደግፎ በእልልታ የሚቀበል ኤርትራዊ ለማገኘት ለህወሃት ትልቅ አቀበት እንደሚሆንባቸው የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በሽምቅና በደፈጣ ውጊያም ይሁን በመደበኛ ጦርነት  የህወሃትን ወረራ ሊመክት የሚችል በርካታ ቁጥር ያለው ኤርትራዊ እንደሚሳተፍና እስከመጨረሻው የደም ጠብታው እንደሚፋለማቸው  ጄ/ል ጻድቃንም ሆነ ሌሎቹ የህወሃት የጦር አበጋዞች በትዕግስት ሊያጤኑት የሚገባ እውነታ ነው።

“የአይናቸውን ቀለም ካላማረን እናባርራለን” በሚል ትብኢት  መለስ ዜናዊ ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢዎች በግፍ እንዲባረሩ የተደረጉት ኤርትራዊያን ከዚያም በኋላ በህወሃት ትግራዮች ሀብት ንብረታቸውን ተቀራምተውታል። ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራና ልዩ ልዩ ሀገሮች እንዲሰደዱ የተገደዱት እነዙህ  በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ኤርትራውያን የህወሃትን የኤርትራ ወረራ  አቅፈውና  እልል ብለው የሚቀበሉ ናቸው ብሎ ማሰብ “የወጋ ቢረሳ ፣ የተወጋ አይረሳም” የሚለውን ብሂል መርሳት እንደሚሆን በወቅቱ የጦር ሃይሎች ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሌ/ጄነራል ጻድቃን የሚጠፋቸው አይመስለኝም።

ባለፈው ጦርነት የሃይል ሚዛኑ በ11ኛው ሰኣት ወደ ኢትዮጵያ እንዲያጋድል ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶችን በማንሳት ጀነራሉን ማስታወስ ጠቃሚ ይመስለኛል ።  1ኛ) ሲንኳስሰ የነበረውን የኢትዮጵያን ብሄረተኝነት ስሜት ለህዝቡ “ሀገራችን ተጠቃች ተወረረች” በሚል የህወሃት አገዛዝ  ራሱን በኢትዮጵያዊነት ካባና ሰንደቅ አላማ ስር በመወሸቁና  ቀደም ሲል በህወሃት ስርአት ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የነበረውን በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የነበረውን ኢትዮጵያዊ በተወሰነም ደረጃ ቢሆን በማጭበርበሩና ከጎኑ በማሰለፉ የተገኘ ነበር። 2ኛ) ለውርደትና ለችግር የዳረጋቸውን የቀድሞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የአየር ሃይል አብራሪዎች፣ የመስመር መኮንኖችና ልዩ ልዩ የጦር ስልትና ቴክኒክ ባለሙያዎች እየለመነ በገፍ ስላስገባቸው እንጂ እንደ ጅምሩ በሕወሃት ኮነሬሎችና ጄኔራሎች የተመራው ጦር በበርካታ ዙር ውጊያዎች ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የሞራል ውድቀት ደርሶበት እንደነበርና በወቅቱ የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹም የነበሩትን ሌ/ጄነራል ጻድቃንን ለለቅሶ እንደዳረጋቸውም ጄኔራሉ የሚያስታውሱት ይመስለናል። በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩና በህወሃት ስርአት ተማረው ስርአቱን የከዱ  ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ይህንን ሚስጥር አጋልጠዋል።

ሌላም ማሳያ  እንመልከት።  በ1969 የሶማሊያ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ አየር ሃይል 25 የሶማሊያ ሚግ 21 ጀቶችን በአየር ላይ ዶግ አመድ አድርጓል። በተቃራኒው ከመሬት በተተኮሰ ተወንጭፊ ሚሳኤል ኢትዮጵያ የወደሙባት ጄቶች ሁለት ብቻ ነበሩ ። ከ 1998 – 2000 በተደረገ የ“ኢትዮ ኤርትራ” ጦርነት ወቅት በህወሃት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው አየር ሃይል በጎረቤትት ሀገሮች በስደት ይኖሩ የነበሩና ሀገር ውስጥ ለእስር፣ እንግልትና ውርደት ህወሃት ዳርጓቸው የነበሩ የቀድሞ ስርዓት አብራሪዎችንና ቴክኒሻኖችን በልመና አስገብቶ ነው በተወሰ ደረጃም ቢሆን  በአየር ኃይሉ ላይ ነፍስ የዘራበት።  እንዲያም ሆኖ ጦርነቱና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ 25 አይሮፕላኖችና ሄሌኮፕተሮች ወድመዋል። በርካታ ድንቅዬ አብራሪዎችም ተሰውተዋል። በህወሃት ሙሉ ቁጥጥር ስር የነበረው የመከላከያ  ሰራዊት በታጠቀው  የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል የተመቱ የወገን አይሮፕላኖችም ነበሩ። ለምሳሌ መ/አ እንደገና ታደሰ  የሚያበረው ጄት ሁለት ጊዜ በወገን የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል ተመትቶ ነበር። መጀመሪያ የሚያበረው ሚግ 21 ጄት ቢመታም በፓራሹት ወርዶ ሊተርፍ ቢችልም ሁለተኛ ጊዜ የሚያበረው L 39 የተባለ  ተመትቶ መስዋዕት ሆኗል። በኤርትራ  በኩል 2 ሚግ 29 ጄቶች የተመቱ ሲሆን እነዚህን ጄቶች የጣሉትም የኢትዮጵያ አብራሪዎች ሳይሆኑ የራሺያና የዩክሬን ቅጥረኛ ነበሩ ኦሌግ እና አሌክስ የተባሉ አብራሪዎች ናቸው።

አሁን የማዕከላዊ አየር ምድብ አዛዥ የሆነው ኮ/ል ሰለሞን ገ/ስላሴ አንድ ጆሮው የማይሰማ ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፊት በድሬዳዋ ኤል 100 ( L – 100 ) የተባለ ግዙፍ የእቃ ማመላለሻ አይሮፕላን ከስክሷል። በአንድ ስልጠና  ላይ የእስራኤል አብራሪዎች በሚያሰለጥኑበት ጊዜ አይተውት አንተ እንኳን ማብረር አይሮፕላን ውስጥም መግባት የለብህም ብለውት እንደነበር ይታወሳል። እንደዚህ አይነት አብራሪዎችን ይዞ ጦርነትን ማሰብ እብደት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም አይባልም። አሁን ያሉት የህወሃት አብራሪዎች የአየር ላይ ጦርነት የማድረግ ምንም ልምድና ብቃት የሌላቸው ስለመሆናቸው በቂ መረጃዎች አሉ ። በአሁኑ ሰአት የአየር ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄነራል አደም መሃመድ እና ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ሃላፊ የሆኑት ብ/ጄነራል ማዕሾ ሃጎስን ጨምሮ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ላይ ምን አይነት ተሳትፎ ያልነበራቸው ናቸው። በተቃራኒው ስልጣን እና ማዕረግ በላይ በላዩ  የሚደርቡት ግን እነርሱ ናቸው። ምክንያቱም አየር ኃይሉም ሆነ ጠቅላላ ስርዓቱ በብቃትና በእውቀት ላይ የተገነባ ሳይሆን በዘርና በፓለቲካ ታማኝነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።  በኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት ላይም በዋናነት የተሳተፉት የቀድሞ አየር ሃይል አባላት ናቸው። እነዚህ አብራሪዎች ከጦርነቱ በኃላ በተለያየ  መንገድ ከአየር ሃይሉ እንዲባረሩ በመደረጉ በአሁን ሰአት ጦርነት ቢነሳ ብቃት ባለው ሁኔታ አየር ሃይሉ ምንም አይነት ምላሽ የሚሰጥበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው። በአሁን ሰአት ሃገሪቷ እየተጠበቀች ያለችው በራሺያና እና በዩክሬን ቅጥረኞች ነው። እነዚህም ሱ 27 ( SU 27 ) የሚያበሩ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ አየር ክልል ወጥተው ጥቃት መሰንዘር አይችሉም። የተዋዋሉት ውል በሃገር ውስጥ ብቻ ለመብረር ነው። ከኢትዮጵያ አየር ክልል ወጥተው ለመብረርና ጥቃት ለመሰንዘር የመጡበት ሃገር ህግ አይፈቅድላቸውም።

ኢትዮጵያ በአሁን ሰአት ካሏት MI 35 ሂሊኮፕተር ውስጥ ግዳጅ መውጣትና መስራት የሚችሉት 5 ብቻ ናቸው። እንዲሁም MIG 23 ቦምብ ጣይ ጄቶቹም ያረጁና በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውሉ አይደሉም። ለደህንነትም ( Safety )  አስተማማኝ አይደሉም። በብልሽት ምክንያት በተደጋጋሚ ሲከሰከሱ ተስተውለዋል። እንዲሁም ከ17 ሱ 27 ወሰን ተከላካይ ጄቶች ( SU 27 Intercepters)  ውስጥ በሚገባ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ሰባቱ ብቻ ናቸው። ካሉት 3 ሱ 25 ( SU 25 ) ጄቶች ውስጥ በሚገባ መስራት የሚችለው አንዱ ብቻ ሲሆን ይህንንም አይሮፕላን በሚገባ የሚያበረው የለም። አየር ሃይሉ በመለዋወጫ ድርቅ ከተመታ ቆይቷል። በቅርብ ጊዜ የሱ 27 ጀት መለዋወጫ ለመግዛት ተኪዶ ሃገሪቷ የሌላት የሚግ 29 ጀት መለዋወጫ ተገዝቶ መምጣቱና የሃገር ሃብት መባከኑ የአየር ሃይል አባላት በቁጭት የሚያነሱት ጉዳይ ነው። ላሉ አይሮፕላኖች መለዋወጫ እንኳን በአግባቡ መግዛት የማይችል ተቋም በምን ሁኔታ ውጊያዎችን አቅዶና በተግባር አውሎ ጦርነትን ማሸነፍ እንደሚችል ጄነራል ጻድቃን የሚጠፋቸው አይመስለኝም። ጄነራል ጻድቃን ስለአየር ሃይል ለማወቅ ከፈለጉ ወደዚያ ጎራ ብለው ቢያዩት ሃገሪቷ አየር ሃይል የሚባል እንደሌላት በቀላሉ መረዳት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ።

አየር ሃይሉን በአመራርነት እየመሩ ያሉ ከፍተኛ አዛዦች የአየር ሃይል የውጊያ ዘመቻዎችን በአግባቡ መምራት የሚችሉ አይደሉም። የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነትንም በዋናነት ሲያስተባብሩና በሙያዊ ብቃታቸው ውጤት ያስመዘግቡ የነበሩት  አለም የመሰከረላቸውና ያደነቃቸው የቀድሞ አየር ሃይል አባላት ነበሩ። እነዚህ ከፍተኛ ብቃት ያላቸው የቀድሞ አየር ሃይል አባላት በአሁኑ ሰአት በአየር ሃይል ውስጥ የሉም።

ለመሆኑ እንደዛም ሆኖ ለኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት በድንበር አካባቢ ብቻ በተደረጉ ውጊያዎች ከዘጠና ሁለት ሺ አራት መቶ ሃምሳ (92,450) በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን ገብረው ምን ተገኘ? ጦርነቱ ምን ፈየደ? መልሱ ምንም ነው!  የህወሃትን እድሜ ከማስቀጠልና የኢትዮጵያዊያንን ስቃይ ከማራዘም በስተቀር ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ አንዳች የፈየደው ነገር የለም። ጸረ ኢትዮጲያዊው የህወሃት ቡድን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሲያብጠለጥለውና ሲዘልፈው በነበረው ኢትዮጵያዊነት ካባና ሰንደቅ አላማ ስር መደበቁና ህዝቡንም በዚህ ብልጣ ብልጥ ስልቱ ማጭበርበሩ ረድቶታል።  በእነ ጄ/ል ጻድቃን አመራር በተካሄደው በዚህ ጦርነት ውስጥ በአብዛኛው ምናልባትም አለማጋነን  95 በመቶ  የሚሆነውና የተቀበረ ፈንጂ እየረገጠ የፈንጂ አምካኝ እንዲሆን የተፈረደበት የሌላ ብሄር ተወላጅ ሆኖ ሳለ ጦርነቱን ይመሩና ትዕዛዝ ይሰጡ የነበሩት ግን 95 በመቶው ከወታደራዊ ሳይንስ ጋር የማይተዋቁና መደበኛ ጦርነት እንዴት መምራት እንዳለባቸው ምንም እውቀቱ የሌላቸው የሕወሃት ጄኔራሎች ነበሩ ። እሁንም በኤርትራ ላይ የጠነሰሰው ወታደራዊ ጥቃት እነዚሁ በችሎታና በብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ታማኝታቸውና በትግሬነታቸው ለ26 አመት የሰራዊቱን ላብና ደም እየጠጡ ራሳቸውን ትላልቅ ባለሀብት ያደረጉ የህወሃት ጄኔራሎች የሚመራ እንደሆነ እሙን ነው። ነገር ግን ተዋጊውና ለመትረየስ አጨዳ የሚጋለጠው ብሎም የፈንጂ አምካኝ ሆኖ አሰቃቂና ከንቱ ሞት እንዲሞት የሚፈረድበት የሌላው ብሄር ተወላጅ  እንደሚሆን የህወሃት የቅርብ ታሪክ ደጋግሞ አሳይቶናል።

በዚሁ ከባድ መስዋዕትነትን ባስከፈለው የሁለት ዓመት ጦርነት ( 1998-2000) ውስጥ በርካታ ዙር አውደ ዉጊያዎች  ከለቅሶና ዋይታ አልፎ የህወሃትን ህልውና ራሱን ከባድ አደጋ ላይ ጥሎት እንደነበርና የስልጣን እድሜውንም የሚፈታተን ደረጃ አድርሶት እንደነበርም ይታወሳል። ይህ ያለፈ ክስተት ለዛሬው እውነት ትልቅ ትምህርት ሰጪ መሆኑን እነ ጄ/ል ጻድቃን በይፋ አይናገሩት እንጂ ከእነሱ የተሰወረ የሚሆን አይደለም። ለመሆኑ የመለስንና የህወሃትን የመጨረሻ ደረጃ መሰሪነትና ውለታ ቢስነት ጄ/ል ጻድቃን ያስታውሱት ይሆን?  ጄ/ል ጻድቃንን ጨምሮ ብዙ የህወሃት ድኩማን የጦር መኮንኖች በተደጋጋሚ በኤርትራ ጦር የደረሰባቸውን አዋራጅ ሽንፈቶች ተከትሎ ለቀጣዩና የመጨረሻ  የመልሶ ማጥቃት  ጦርነት ዝግጅት ወቅት በልመና ያመጧቸውን የቀድሞ ሰራዊት ምርጥ ጄኔራሎች፣ የመስመር መኮንኖችና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሰራዊት አባላትን መለስ ዜናዊ “እነዚህ አባታቸው የሞተባቸውን ማን ነው ያመጣቸው? ይባረሩ!”’ በማለት ህወሃት ከኤርትራ ጋር ባደረገው የመጨረሻው መልሶ ማጥቃት ጦርነት ላይ  ከተጠቀመባቸው በኋላ  እንደ ቆሻሻ በገፍ እንዲባረሩ መደረጉን በጊዜው የመለስ ዜናዊን “አይናቸውን ማየት ኣልፈልግም” ትእዛዝ አስፈጻሚ የነበረው ኤታማጆር ሹሙ ጄ/ል ጻድቃን ሊዘነጋው አይችልም። ሁሉም ኢትዮጲያዊ በተለይ ለዳግም ውርደት በህወሃት የተዳረጉትና በጦርነቱ ትልቅ ሚና የነበራቸው የቀድሞ ሰራዊት አባላትና ቤተሰቦች በቁጭትና በምሬት የሚያስታውሱት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው። ባጭሩ “ የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” እንደማለት ነው።

ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኃላም ቢሆን  ሌላ የህወሃትን መሰሪነትና በአካባቢው የደቀነውን  የሰላም ጠንቅነት በሚመለከት ህወሃት የሄደበትን ብዙ ርቀት እንመልከት። ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ በሶማሊያ ደሙን ሲያፈስና የአልሻባብ እሳት ራት እየሆነ ለአመታት የዘለቀውና ህይወቱን በ10,000 ሺዎች በላይ የገበረው የመከላከያ ሰራዊት ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች የመጣ  ሲሆን ኣሁንም በላዩ ላይ በአዣዥነት ተጭነውት እያዘመቱ  በአልሻባብ የሽብር ጥይት ያስቆሉት፣ ሬሳውን ክብር አሳጥተው መሬት ለመሬት ያስጎተቱትና ደመ ከልብ አድርገው ያስቀሩት  እነዚሁ በሶማሊያ ውስጥ በሚካሄድ የኮንትሮባንድ ንግድ የተዘፈቁና  በሙስና የተጨማለቁ  የህወሃት የጦር አበጋዞች መሆናቸው ጸሃይ የሞቀው ሐቅ ነው። በሶማልያ ውስጥ  በህወሃት ጀነራሎች አዝማችነት  በተሰነዘረው ወረራ የዛሬው በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሜ/ጀነራል  በወቅቱ ኮ/ል ገብሬ ዲላና በኮ/ል ወዲ አባተ (ሁለቱም የሕወሃት ትግሬዎች) ኣዛዥኝነት ስር ይመረሩ የነበሩት 43ኛና 44ኛ  ከፍለ ጦሮች በሶማሊያ ወስጥ በተደረጉ ጦርነቶች  ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ መደምሰሳቸው ይታወቃል።

ሌላው አሳዛኝ ክስተት በMI 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በሚወነጨፉ ሮኬቶች የመከላከያ ሰራዊቱ በራሱ አየር ሃይል እየተደበደበ በብዙ ሺ የሚቆጠር ሰራዊት ማለቁ ነው። ለዚህ ጥፋት ተጠያቂ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የአየር ሃይል ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ሃላፊ የሆነው ብ/ጄነራል ማዕሾ ሃጎስ ነው። ይህ የጦር አዛዥ ህወሃት በመሆኑ የሚነካው የለም። እንደውም ስልጣን በስልጣን ላይ እየጨመረ አየር ሃይልን እንደፈለጉ ከሚዘውሩ ሰዎች አንዱ ሆኗል። ጄነራል ጻድቃን ይህን እውነት አጠገቦ ካሉ የህወሃት ጄነራሎች ጠይቀው ማወቅ እንደሚችሉ በዚህ አጋጣሚ ልጠቁሞት።

በጣም የሚያሳዝነውና ለእነ ጄ/ል ጻድቃን አይነቶቹ እምብዛም የማያስጨንቃቸው ሶማሊያ ውስጥ ህወሃት ባደረገው ጣልቃ ገብነት ህይወታቸውን የገበሩ ከ10,000 በላይ የሌሎች ብሄር ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መጨረሻው ምን እንደሆነ ለቤተሰቦቻቸው እንኳን እስካሁን አለመነገሩ ነው። አገዛዙ በሶማሊያ ኣስካሁን ባደረገው ጦርነት ምን ያህል ኢትዮጲያዊያን  እንደተሰው ለፓርላማ ተብዬውም ሆነ ለህዝብ የተገለጸ አለመሆኑን ከጄ/ል ጻድቃን የተሰወረ ነው የሚል ግምት አይኖርም። የህወሃት ስርዓት ለኢትዮጲያውያን ክብር፣ ለሰው ልጆች ህይወት ዋጋ የማይሰጥ መሆኑን ለማሳየት አንድ ሺ ኣንድ መገለጫና ማስረጃዎች ቢኖሩም ይህ የሶማሊያ ዘግናኝ ታሪክ ሌላው ማጠናከሪያ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ ይችላል።

ይህ ብቻም አይደለም። ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በህወሃት የጦር መኮንኖች አዝማችነት የተመራው መከላከያ ሰራዊት በፈረንጆች 2006 ወደ ሶማሊያ ሲገባ በየመንደሩ በየመስጊዱ እየገባ ባደረገው ጭፍጨፋ ሶማሌዎች ዘመን ሊሽረው የማይችል ጥላቻን በኢትዮጵያ ላይ እንዲኖራቸው አድርጓል። በአንጻራዊነት ለዘብተኛውን የእስላማዊ ኮርት ጣልኩ ባለ አክራሪው አልሻባብ በአጭር ጊዜ ውስጥ በምድረ ሶማሊያ ተስፋፍቶ እንዲጠናከር ማድረጉ ህወሃቶች በኢትዮጵያ ላይ የፈጠሩት ትልቅ የደህንነት ስጋትና አደጋ ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ውስጥ እየሰፋ ለመጣው ትርምስ የህወሃት አገዛዝ ትልቅ አሉታዊ ሚና ተጫውቷል በሚለው ድምዳሜ ብዙዎች የሚስማሙት። ይህም የመነጨው የህወሃት የማንነት መገለጫ ባህሪው መሰሪነት፣ ውንብድናና  ስግብግብነት ከመሆኑ የተነሳ ብቻ ሳይሆን ከአፍንጫው ስር በላይ ማየት የማይችል ከታክቲካል ስሌት ብቻ የሚነሳ በመሆኑ ነው።

በአንጻሩ ህወሃቶች ከእነሱ ሌላ ምንም ጥሩ ጎኖች እንዲሌላቸው በተደጋጋሚ የሚያብጠለጥሏቸው የቀድሞው የአጼ ሃይለ ስላሴና የኮ/ል መንግስቱ መንግስታት ከሶማሊያ የተቃጡ ሁለት ወረራዎች (1953 እና 1969) በአመርቂ ሁኔታ ከመከቱ በኃላ ወደ ሶማሊያ ምድር ዘልቀው ያሻቸውን ማድረግ ይችሉ ነበር። ከወታደራዊ አቅምና በወቅቱ ከነበረው የጦርነቱ ሂደት ሙቀት ( Momentum ) አኳያ በ 1953 ጄ/ል አማን አንዶምም ሆነ በ1969  የነበሩት ጄኔራሎች  እነ ደምሴ ቡልቶ፣ ሙላቱነጋሽ፣ መስፍን ገብረ ቃል ኣንዲሁም ሌሎች የወቅቱ ጀነራሎች ስትራቴጅካዊ እዝ ስር የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሞቋዲሾን ከመያዝ የሚያግዳቸው እምብዛም ችግር አልነበረም። ነገር ግን የወደፊቱንና የሩቁን በማሰብ ሶማሊያ ውስጥ ገብቶ በሃይል ግዛቶችን መያዝ ለወደፊቱ የአካባቢያዊ ሰላም ጠንቅ ሊሆን እንደሚችል በሳል በሆነ የፓለቲካና  የዲፕሎማሲ  ስሌት በማሰባቸው ነበር ከዚህ የወረራ እርምጃቸው የተቆጠቡት።

ጄ/ል ጻድቃን ቀይ ባህርን የመቆጣጠር አባዜ ቢያንሰራራበትና ለጥቆም “የባህር በር ማጣት አልነበረብንም” በሚል ጸጸት በስተርጅና የመጣ ቢመስልም  እሱም ሆነ ድርጅቱ  ህወሃት ለዚህ የኢትዮጲያን ያለ ባህር በር መቅረት ሃላፊነቱን አንድ ጊዜም ቢሆን ወስደው አያውቁም። “መለስ ዜናዊ ስለ አሰብ መደራደር ይችል ነበር” በማለት ሀርማን ኮኸን በበርካታ መድረኮች ላይ ምስክርነቱን ሰጥቷል። በስትሪቴጂካዊ አስተሳሰብ ደደብነት፣ ርዕዮተ ዓለማዊ መደናበርና በተለይም ደግሞ  በሕወሃት ጸረ ኢትዮጵያዊ  ኣቋም ሳቢያ የመጣ ጉዳት ነው። የህወሃት መሪዎች ለዚህ ሃላፊነት ወስደው አያውቁም። “አሰብን ግመሉን ውሃ ያጠጣባት! ” ነበር ያለው መለስ ዜናዊ። ቀጠል አድርጎም “ወደብ እንደማንኛውም ሸቀጥ ነው” በሚል ነበር የተራቀቀው። የስትራቴጂካዊ  ድድብናውን በዓለም መድረክ ያረጋገጠው ብልጣ ብልጡ መለስ ዜናዊና እሱ የሚመራው ህወሃት የወሰዱት አቋም ይህ እንደነበር ጄ/ል ጻድቃን ለመቀበል ዝግጁ እንዳልሆኑ ግልጽ ነው።

ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የተነሳ የሕወሃት አመራሮች ስለባህር በርና የቀይ ባህር ጥያቄን በማንሳትና  በማራገብ ህዝብን ለማጭበርበር አይችሉም። ስለዚህ ጉዳይ ለማንሳት  ምንም  አይነት የሞራል ልዕልና የላቸውምና! ህወሃት የባህር በር ጥያቄን አንስቶ መደራደርና ዘላቂና ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ያልቻለው በጸረ ኢትዮጵያ ኣቋሙ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብና የቀደሙት መንግስታት የኢትዮጵያን የባህር ሃይልና የባህር ወደቦችን ለማቋቋምና ለማሳደግ በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ሃብት በኤርትራ ውስጥ አፍስሰዋል። የምጽዋንና የአሰብ ወደቦችን ለማዘመንና  ለማስፋፋት ብዙ ኢትዮጲያዊያን (ኤርትራውያንን ጨምሮ)  በጊዜው የዕውቀት፣ የላብ፣ የደምና የገንዘብ መስዕዋትነት ከፍለዋል። ከአሰብ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው  በሃሌብ ደሴት 3ኛ ወደብ፣ ዘመናዊ የጀልባ ፋብሪካ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ በባህር ነክ ቴክኒክና ሌሎች ሙያዎች የሚያስመርቅ የባሕር አካዳሚ ( Marine Acadamy)፣ ዘመናዊ የመርከብ ማደሻ ግንባታዎች በጅምር የነበሩበት፣ ያለቁበትና የተገባደዱባቸው በርካታ ሌሎች ፕሮጄክቶችም በኤርትራ ምድር ተሰርተዋል። እነዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት የፈሰሰባቸው ነበሩ።  

ኤርትራን በሚመለከት ብዙ ስህተቶችን በፈጸሙ ሁለት መንግስታት ስር ሰለባ ይሁን እንጂ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ጀግና ልጆች አይተኬ መስዕዋትነትን መክፈላቸው የሚካድና የሚለወጥ ሃቅ ኣይደለም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ “ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ነች” አንድ ኢትዮጵያ ብለው ህይወት፣ ደምና አጥንት በኤርትራ ምድር ገብረዋል። ይህ ነው ተብሎ የማይዘረዘር መስዋእትነት ከፍለዋል። የኢትዮጵያ እናቶች የደም ዕምባ እንደ ጎርፍ ፈሷል። እናት ኣባት ልጆቻቸውን ተነጥቀዋል። ሚስቶች ባሎቻቸውን፣ ልጆች ኣባቶቻቸውን በኤርትራ ምድር ላይ በተደረገ ከ30 አመታት በላይ በፈጀው ጦርነት አጥተዋል። ከ60ሺ በላይ ኤርትራውያን በ30 አመቱ ትግል ተሰውተዋል። በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ኣካለ ጎዶሎ ሆነዋል። ለስደት፣ ለእንግልት፣ ለእስርና ለሰቆቃም ተዳርገዋል።  ልክ እንደ ኢትዮጵያ እናቶች ሁሉ የኤርትራ እናቶችም ልጆቻቸውን በእሳት ተነጥቀው የደም እምባ አልቅሰዋል። ሚስቶች ባሎችቻቸውን፣ እህቶች ወንድሞቻቸውን፣ ልጆች አባቶቻቸውን አጥተዋል።

በኤርትራ ምድር ለተካሄደው ጦርነት፣ በሁሉም ወገን ለተከፈለው የህይወት መስዋእትነት፣ ይህ ነው ለማይባል የወደመ ንብረት፣ ለተገበረው ህይወት፣ ለተከሰከሰው አጥንት፣ እንደጎርፍ ለወረደው ደም፣ እንደ ዥረት ለፈሰሰው የሚሊዮኖች ዕምባ በዋነኛነት ተጠያቂዎቹ በጊዜው የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት ናቸው። የአለም አቀፍ ህግን በመጣስ የኤርትራን ፌዴሬሽን ከማፍረስ (ባለራዪው የኢትዮጵያ ባለውለታ ጸሃፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ቀጣይ የሚያመጣው ቀውስ ቀድሞ ታይቷቸው ፌደሬሽኑ እንዳይፈርስ ቢማጸኑም) ጀምሮ የኤርትራን ህዝብ በፊዴሬሽኑ ያገኛቸውን ልዩ ልዩ መብቶች እስከመግፈፍ፣ በቀጣዩም አመታት የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡና በሰላማዊና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመያዝና  ለመፍታት አለመቻላቸው እንደነበር ሌላው ሊካድ የማይገባው የታሪክ እውነታ ነው።

ይህ ግን  የተዘጋ የታሪክ ምዕራፍ ነው። አሁን ኤርትራ ነጻና ሉዓላዊ ሀገር ናት። የኢትዮጵያ ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ ጋር የሚኖረው የወደፊት ግንኙነት ይህን ሐቅ፣ ይህን እውነታ ከልብ በመቀበል ይጀምራል።  የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄም ሆነ  ከቀይ ባህር ጋር የተያያዙ የኢኮኖሚ፣ የደህንነት፣ የወደብና ሌሎች ጥቅሞችም ሆኑ ስጋቶች ሊነሱና ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት የህወሃት አገዛዝ  በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የጫነው የአንድ ብሄር የበላይነት ኣፓርታይድ የፖለቲካ ስርአት ሲገረስስ ብቻ ነው!! ለሁሉም ብሄሮች ፍትሃዊ የሆነ፣ ለሁሉም ዜጎች ነጻነት፣ መብቶችና ጥቅሞች የሚቆም ሀቀኛ የዴሞክራሲያዊ ስርአት ሲመሰረት ብቻ ነው!! በውጭ ሀይሎች የአይዞህ ባይነትና የተላላኪነት ሚና፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አልፎም በአካባቢው ላይ ያለውን የበላይነት ለማስቀጠል የህወሃት አገዛዝ በሚፈጽማቸው ዘርፈ ብዙ  የመሰሪነትና የውንብድና ታክቲካዊ ስሌቶች ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ፣ ስትራቴጂካዊና ሁለንተናዊ  ግንኙነቶች ላይ የተማከሉ፣ የአካባቢውን ህዝቦች የጋራ ዘለቄታዊ ጥቅም የሚያረጋግጡ፣ በእኩልነትና በመከባበር መርሆዎች ላይ የተመሰረቱና  በአለም አቀፍ ህጎች አግባብ መሰረት የሰጥቶ መቀበል ውይይቶችና  ድርድሮች ሲደረጉና ሲፈቱ ብቻ ነው!!

የኢትዮጵያና የኤርትራ  ህዝቦች ዘላቂና ስትራቴጂካዊ ሽርክና “Partnership” የሚረጋገጠው በሰላማዊና የአለም አቀፍ ሕግን በተከተሉ ውይይቶች፣ ድርድሮችና ስምምነቶች ላይ በተመረኮዘ የጋራ ውሳኔ ላይ ሲደረስ ነው። ከዚህም ባሻገር በረጅም ዘመን ታሪክ ውስጥ ተገንብቶ የቆየውንና አሁን በሕወሃት ሳቢያ እየተሸረሸረ የመጣውን ጥልቅ ተጋምዶ፣ ትስስሮችና ዝምድና የሚያንሰራራ፣ የሁለቱን ህዝቦች ወንድማማችነት የሚያጠናክር፣ የሁለቱንም  ሀገሮችና ህዝቦች  ስትራቴጂካዊ  ጥቅም  ባመከለ መልኩ  በሚከወን ግልጽና ፍትሃዊ ሂደት ብቻና ብቻ ነው።  በሰላምና በድርድር ሁሉንም ግዙፍ ጉዳዮች ማለትም የሁለቱንም ሀገሮች ህዝቦች ዘላቂ የሆኑ የደህንነት፣ የጋራ የኢኮኖሚ ብልጽግና ማሕበራዊና ሌሎች ትስስሮችን አጠናክሮ፣  ከባህር በርና ወደብ ጋር ተያይዞ የሚነሱትንም ጨምሮ  ለዘለቄታው የሚያስቀጥሉና የሚያረጋግጡ ድርድሮችና ስምምነቶች የማይስተናገዱበትና የማይፈቱበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ከሁለቱ ሀገሮች አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን የጋራና ዘለቄታዊ ሰላም፣ ደህንነትና እድገት ለማረጋገጥም ቢሆን አለም አቀፍ ሕግን የተከተሉ፣ ግልጽና ፍትሃዊ  አካሄዶችና የፖለቲካና  የፖሊሲ አቅጣጫዎች ሲቀመጡ ብቻ ነው። ለዚህ  ሁሉ ራዕይና ግብ በተግባር አለመተርጎም ትልቅ ጋሬጣ ሆኖ ያስቸገረው የህወሃት መሰሪና ዘረኛ አምባገነናዊ አገዛዝ ነው።

በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ለሚገኙ ችግሮችም ሆነ ከኤርትራ ጋር ላለፉት ረዥም አመታት የተደነቀረው ጦርነትም ሰላምም የሌለበት ሁኔታ “No war, no peace” ተጠያቂው የህወሃት ዘረኛና ዘራፊ አምባገነናዊ አገዛዝ ነው። ባጭር አነጋገር ሕወሃት ተቆርጦ መጣል ያለበት የምስራቅ አፍሪካ ካንሰር ነው! ከመቶ ሺ በላይ የድሀ ኢትዮጵያውያን  ልጆች ደም ከተገበረበት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማግስት በሄግ ላይ የተሰየመው የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ባድሜን ለኤርትራ  በይኖላት ሳለ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ህወሃቱ አቶ ስዩም መስፍን  “ባድሜ ለኢትዮጲያ ተወስኗል” የሚል ያደባባይ ቅጥፈት ተናግሮ እንደነበር የሚረሳ አይደለም። ዛሬም ድረስ  ባድሜ ራሱ ህወሃት በተስማማበት የአልጀርሱ ስምምነትና የሄግ የድንበር ኮሚሽን የበየነውን “ባድሜ የኤርትራ ግዛት” መሆን አልቀበልም ብሎ የኤርትራን ግዛት በህይል ተቆጣጥሮ እስክአሁን ድረስ  አለም አቀፍ ሕግን ኣሻፈረኝ ያለው የህወአት አገዛዝ እንጂ “የእቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት” እንዳልሆነ ህሊና ያለው ሁሉ መፍረድ የሚችለው ነው። ጀ/ል ጻድቃንም ሃቁ ይህ በመሆኑ ከኤርትራ ጋር ላለው No war , no peace “ ሁኔታ ተጠያቂና  የሰላም ነቀርሳ የህወሃት ኣገዛዝ መሆኑን መቀበል ባይፈልጉ አይፈረድባቸውም።  ህወሃትነታቸው አሁንም  ይጎትታቸዋልና።

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ላይ የበላይነትን ለማረጋገጥና  ለማስቀጠል ሲል ሕወሃት የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ መሰሪ ጥረቱን አምርሮ እንደሚገፋበትና ምናልባትም እስካሁን ያልታዩ የጭካኔና የውንብድና ተግባሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ማወቁና መዘጋጀቱ አዋቂነት ነው። የአለፈው ታሪኮቹ የሚመሰከሩበት ከዚህ ውጭ ሊያስብና ሊተገብር የማይችል እኩይ፣ እጅግ አደገኛ ሀይል መሆኑን ይመሰክሩበታልና። በመሆኑም የአብሮ መኖር፣ የደህነትና የሰላም ጠንቅ የሆነው ህወሃት ዘረኛ፣ አድሎአዊ፣  አፓርታይዳዊ አገዛዝ የስልጣን እድሜ በተራዘመ ቁጥር የኢትዮጲያ ህዝብ አብሮ የመኖሩ ጉዳይም ሆነ የኢትዮጵያን ህልውና እ

Donnerstag, 29. Juni 2017

​የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ጥላሁን አበጀን ጨምሮ በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት የተጠረጠሩ 77 ተካሳሾች ፍርድ ቤት ቀረቡ!!!

​የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ጥላሁን አበጀን ጨምሮ በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት የተጠረጠሩ 77 ተካሳሾች ፍርድ ቤት ቀረቡ!!!
(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ) 

በፌደራል ዐ/ህግ እራሱን አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል በመሆን እና ኤርትራ ሀገር በመሄድ የሽብር ቡድኑን ታጣቂዎች በመቀላቀል አባላትን በመመልመል፣የሽብር ቡድኑ ገቢ ማስገኛ የጉልበት ስራ ላይ በመሳተፍ፣አደምዳሚት ሀሬና እና ዊአ በተባሉት የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በመግባት የቡድኑን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና ወስደው በማጠናቀቅ በቡድኑ በታጣቂነት፣በአሰልጣኝ እና በአመራርነት ተሳትፈዋል በሚል የሽበር ክስ የቀረበባቸው 77 ተከሳሾች ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀረቡ፡፡ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ተከሳሾች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ የዓቃቢ ህጉን መልስ ለመቀበል ቢሆንም ዓቃቢ ህግ አሟልቶ ባለመቅረቡ በድጋሜ ለሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ 
45ቱ ተከሳሾች ከጎንደርና ጎጃም
12ቱተከሳሾች ከኤርትራ
13ቱ ተከሳሾች ፀገዴ፣ወልቃይት፣ቃፍታ ሁመራ
4ቱ ተከሳሾ ከአርባ ምንጭና ጉራጌ ዞን
2ቱ ተከሳሾች ከደብረ ዘይትና ሙነሳ እና 
1 ተከሳሽ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 
የተከሳሾች ስም ዝርዝር 
1.ሚፍታህ ሼክሱሩር መሀመድ
2.ግርማ ፈቃደ ሞላ
3.እሸቴ ዘለቀ መኮነን
4.ለሚ እሸቴ ዘገደ
5.አብርሃም ደርበው መኮነን
6.መስፍን ሁሬሳ ተክሌ
7.ሸጋው ፈንታ አድማሱ
8.ጸጋዬ እሸቴ መኩሪያ
9.አማረ አወቀ ሲሳይ
10.ልጅሸት ኪዴ ገብሬ
11.ገረመው ጌታቸው ዘለለው
12.አራገው ቸኮል አስማማው
13.ደሳለኝ ንጉሴ ሙላቱ
14.ሀብሉ አንገሶ ውንዴሳ
15.በዛ ሞላው ውነህ
16.ቴዎድሮስ ይግዛው አራጌ
17.እማዋየው ዘላለም እጅጉ
18.አንቼ ተረፈ አላሜ
19.ምስጋና ይርጋ አስፋው
20.ደሴ ሀይሌ ጣሰው
21.አወቀ አደመ አባተ
22.ጀጀው አብርሃም መኮነን
23.ባባይ እንደሻው ካሳዬ
24.መሰረት ዘየደ ሞገስ
25.ግደይ ፀሀዬ ይግዛው
26.ሰለሞን እሸቴ ጌታሁን
27.አንተነህ ጌታቸው አላምረው
28.ተካልኝ መንግስቱ መና
29.ፀጋዬ አስፋው ኡሃይ
30.ማማዬ በርሄ አባይ
31.ጋሻው ቢትወደድ ጎዶ
32.ሸጋው ፈለቀ ቀስቅሶ
33.ሀፍቶም ማማይ ተስፋዬ
34.የሻንበል አጥናፉ ማሙ
35.ደመቀ ነጋ መኩሪያ
36.እንግዳው አዲሱ አምባው
37.እሸቴ ይስማው አዲስ
38.ገብረኪዳን መልካሙ አያሌው
39.ባዬው ሀብተው ሽፈራው
40.መንግስቴ ትዕዛዙ ነጋ
41.አትርሳው ፈረደ ክንፈ
42.ሲሳይ መኮነን በቀለ
43.ወንድፈራው አደራጀው ካህሳይ
44.ሻንቆ ክብረት ይፋ
45.ሙሉዬ አስማማው ካሳው
46.ዝናብ ጥጋቡ ሞላ
47.መላኩ ነገሰ አውላቸው
48.ፈጠነ ማሞ መርሻ
49.ላመነው ማሞ አለፍ
50.ድረስ ጌታ ታዬ
51.አሳምነው ደጉ ታለማው
52.አባይ አዳነ ታከለ
53.ፍሬው ሞኝነት ካሳ
54.ደስታው ሞላ ዳኘው
55.ፋንታሁን አለልኝ ዳምጤ
56.ሰላሞን አያሌው ዘነበ
57.ዮሃንስ ታረቀኝ ሞገስ
58.እንዳለ ብርሌ ሽፈራው
59.ዳዊት ቀለምወርቅ ወረቅ
60.ጥላሁን አበጀ
61.አዲስ አገኘው ደርበው
62.ሙሴ ታሪኩ ጥበብ
63.ፈለቀ አድባብ ወ/ኪሮስ
64.አልፈቴ ፋሲካው ውብነህ
65.ምትኩ ኡዴሳ አብዲሳ
66.ቃቃይ ንጉሴ ረታ
67.ሐፍታለም መሳፍንት አግደው
68.ሐብታሙ መለሰ ይረና
69.አለሙ አለልኝ ብርሀኑ
70.ዘማሪያም ለገሰ አንዳርጌ
71.ወርቁ ሞገስ ድረስ
72.አትርሳው ደሴ መንግስት
73.ነጋሽ መሀመድ ሀቢብ
74.ፈረደ ክንድሻቶ ይርጋ
75.አሸናፊ አብርሃ ይርጋ
76.ረ/ሳ መኳንንት አለሙ 
77.ውበት ጨለው ጉቤ ናቸው፡፡

በእስር ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ/ ኦፌኮ/ መሪዎች የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የልማታዊ መንግስትና የአውራ ፓርቲ አስተሳሰቦች ቦታ ለቀው አዲስ ሥርዓት እንዲፈጠር በመጠየቅ መግለጫ አወጡ።

በእስር ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ/ ኦፌኮ/ መሪዎች የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የልማታዊ መንግስትና የአውራ ፓርቲ አስተሳሰቦች ቦታ ለቀው አዲስ ሥርዓት እንዲፈጠር በመጠየቅ መግለጫ አወጡ።
የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮን መሪዎች አሁን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በተሐድሶ ስም የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተግባራዊ የማይሆንና ሕዝብን ለመደለል የሚደረግ ሙከራ ነው ብለዋል።

እስረኞቹ “በአሮጌ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አይጨመርም” በሚል ያወጡት መግለጫ እንደሚያመለክተው ጥልቅ ተሐድሶ በሚል በገዥው ፓርቲ የሚሰበከው አስተሳሰብ ተግባራዊ ሊሆን የማይችልና የነበረውን የሚደግም እንቅስቃሴ ነው ብለዋል።
የሀገሪቱ ተቋማት ማለትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዋና ኦዲተር፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የፀረ ሙስና እንዲሁም የእንባ ተቋማት ጠባቂ መስሪያ ቤቶች አደረጃጀታቸውና አፈጣጠራቸው በኢህአዴግ አስተሳስብ የቃኙ በመሆኑም ፋይዳ የላቸውም ብሏል መግለጫው።
ተቃዋሚዎችን በገፍ በማሰርና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገጉ የሕዝብን እንቅስቃሴ ማፈን እንደማይቻልም በእስር ቤት የሚገኙ የኦፌኮ አመራሮች በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
ባለፉት 26 የአገዛዝ ዓመታት ሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ የኢኮኖሚ ዘረፋና የፖለቲካ ጭቆና የተፈፀመ መሆኑንም መግለጫው አስታውሷል።
በተለይ ደግሞ ከሕዝብ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ በተወሰደው የኃይል እርምጃ አገዛዙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደሞቱ እንዲታሰሩ እና ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ እንዲፈፀምባቸው አድርጓልም ብለዋል።
በጥልቅ ተሐድሶ ስም የሚስተካከል ነገር ስለማይኖር በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን መንግስት ስለተቀየረ መፍትሄ እንደማይኖርና ትግሉም እንደሚቀጥል መግለጫው አሳስቧል።
በሽብርተኝነትና አመፀ በመቀስቀስ ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራሮች ጉዳያቸው በፍርዱ ሂደት ላይ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በቀጠሮ መራዘም ምክንያት ውሳኔ እንዳላገኙ ይታወቃል።

Mittwoch, 28. Juni 2017

​”በአፋን ኦሮሞ” አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር !! (~ Ermias Legesse Wakjira)

“በአፋን ኦሮሞ” አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር !!

~ Ermias Legesse Wakjira
#ETHIOPIA | ህውሃት ለሁለት የተሰነጠቀ ሰሞን ጐልተው ከታዩ ባህሪያት አንዱ የኦህዴድ ካድሬዎች “የኦሮሞ ብሔርተኝነት ” ካርድ የመዘዙበት ነበር። እነ ኩማ ደመቅሳ እና ግርማ ብሩን ጨምሮ በመዘዙት ካርድ “የትግራይ የበላይነት ሊውጠን ነው” በማለት ወደ ስልጣን ጫፍ ( ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጨምሮ) ለመቆጣጠር የተጉበት ነበር። 
    እናም በእነ ግርማ ብሩ የተመራው ቡድን የኦሮሞ ብሔርተኝነት ይቀሰቅሳል ብሎ ያሰበውን እቅዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ አደረገ። ከእነዚህ ተግባራት አንዱ በአዲሳአባ የሚሰሩ ሥራዎች ተለይተው የቀረቡበት ነበር። ከስራዎቹም  ውስጥ አንዱ ” በአዲሳአባ አምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 28 ወረዳዎች በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ 28 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች መክፈት” የሚል ነበር። በነገራችን ላይ በወቅቱ አዲሳአባ በአምስት ዞኖች እና 28 ወረዳዎች የተከፈለችበት ነበር።
     እነዚህ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እስኪያልቁ አምስቱም ዞኖች በአጣዳፊነት ነባር ትምህርት ቤቶችን በመለየት ለጐልማሶች የማታ፣ ለህጻናት እና ታዳጊዎች የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በክረምት ኢ_መደበኛ ትምህርት እንዲጀመር ጥብቅ ኦህዴዳዊ ትእዛዝ ተላለፈ። በድርጅት ቋንቋ መደብ ወረደ። መደቡን ለማስፈፀም ደግሞ የአዲሳአባ ካቢኔ የነበሩት  ሊቀመንበር አሊ አብዶ ፣ ሀይሉ ደቻሳ ፣ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ( የአፈ ጉባኤ ደግፌ ቡላ ባለቤት እና በኋላ ላይ በአዜብ መስፍን ከም/ል ሚኒስትርነት የተባረረች የምንወዳት እህታችን)  እና አምባሳደር ሰለሞን ተመደቡ። ተግባሩ በቁልፍ ደረጃ በመቀመጡ ስራውን ያንጠባጠበ ካድሬ በኦህዴድነት መቀጠል እንደማይችል ተገለፀ። 
      በየቀበሌው የሚገኝ ካድሬ ቤት ለቤት እያሰሰ የኦሮሞ ዘር አለው የሚለውን አዲስአበቤ እንዲመዘግብ አደረገ። እንደ መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ፍቃደኛ ያልሆነውን ማስገደድ ተጀመረ። በደርግ ጊዜ ዝነኛው ቆምጬ አምባው ” አስኳላ የማይሄድ ቡዳ ነው!” ያለውን በተሞክሮ በመውሰድ የአዲሳአባ ኦህዴድ ካድሬዎች ” አፋን ኦሮሞ የማይማር የነፍጠኛ ተላላኪ ነው!” የሚል ማዕከላዊ መልእክት ቀርፀው በጥቅም ላይ አዋሉ።
     ስራው በተጀመረ የመጀመሪያው ወር የተመረጡት አምስት ትምህርት ቤቶች በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ከጠቅላላው አዲሳአባ በአማካይ 500 ተማሪ ተገኘ። ቅዳሜ እና እሁድ በተዘጋጀው የህጻናት፣ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ክፍለጊዜ በአማካይ አንድ ሺህ የሚጠጋ ተገኙ። የኦህዴድ አብዮታዊ ካድሬዎች አጀማመሩ ጥሩ እንደሆነ ገመገሙ። 
      ስራው በተጀመረ ሶስተኛው ወር የምሽቱ 60 ፣ የሰንበቱ ወደ 90 ተማሪ ብቻ ቀረ። አምስቱ ትምህርት ቤት ታጥፈው በዞን ሁለት ውስጥ ወደ ሚገኘው ተግባረ እድ ትምህርት ቤት እንዲጠቃለል ተደረገ። በአራተኛው ወር እንደ ኮንደሚኒየም ወደ 40/60 ተቀየረ። አካሄዱ አስደንጋጭ የሆነበት ኦህዴድ ” ሁሉም ዜሮ ዜሮ” መመዝገቡ በፊት ትምህርቱ ባልተገለፀ መመሪያ እንዲቀር ተወሰነ። 
      ከሁሉም የሚገርመው ነገር አዲሳባ የሚኖር አንድም የኦህዴድ ባለሥልጣን ልጆቹን አፋን ኦሮሞ እንዲማሩለት አልሰደደም። በክረምቱ ክፍለጊዜም ሆነ በሰንበት ባለሥልጣናት ልጆቻቸውን የሚልኩት የእንግሊዘኛ እውቀታቸውን የሚሳድጉበት ከ3ሺህ ብር በላይ የሚከፈልባቸው ውድ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች ነበር። አንዳንዶቹ ከቋንቋው በተጨማሪ ልጆቻቸው እንዲዝናኑ የሚልኩት ወደ ትውልድ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ነበር ። አሁንም የተቀየረ ነገር ያለ አይመስለኝም። እንደውም እየሰማን ያለነው በሌብነት እና መሬት ችብቸባ ኪሳቸው ያበጠ የኦሮሚያ ዞን እና ወረዳ ካድሬዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት አዲሳባ ቤት ተከራይተው እጅግ በጣም ውድ በሆነ ” ከእንግሊዘኛ ውጭ መናገር ክልክል ነው!” የሚል ማስታወቂያ የተለጠፈበት ትምህርት ቤት እንደሆነ ነው። ተወደደም ተጠላ መሬት ላይ ያለው እውነታ ይሄ ነው። 
   ከአዲስአባ አወቃቀር አኳያም የተቀየረ ነገር የለም። አዲስአበቤ እንኳን በሕውኃት ድርጅታዊ መመሪያ የተላከለትን ቀርቶ ሌላውንም ቢሆን በጥሞና የሚመለከት አስተዋይ ህዝብ ነው። (” ወርቅ ህዝብ ነው!” ብዬ ልገልፅ ነበር፣ ኩረጃ ይመስልብኛል ብዬ ተውለኩት።) ያለማጋነን አዲስአበቤ የህውሓትን አካሄድ እና አላማ ከመገንዘብና ከመታገል አኳያ የቀደመው የለም። 
  እናም ዛሬ ” የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ” በሚለው አባይ ፀሐዬና በረከት ስምኦን የፃፈው አዋጅ ላይ ” አስተዳደሩ በአፋን ኦሮሞ ልጆቻቸውን ማስተማር ለሚፈልጉ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ማደራጀት አለበት” የሚል ተፅፎ ስመለከት የተሰማኝ ከላይ የተገለጠው ነው። እነ አባይ በዚህ አዋጅ አማኸኝተው ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር ማስገባታቸው እንዳይታወቅ “የዶሮን ሲያታልሏት” ማታለያ ይዘው ብቅ ማለታቸው እርስ በራስ ለማጋጨት ነው። ሌሎች  የህጉ እሳቤዎች መሰረታዊ ምንጫቸው ይሄ እና ይሄ ብቻ ነው።

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም አለው! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሕወሓት ሀገር ከፋፋይ ቀጣይ አጀንዳ አካል ነው

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም አለው! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሕወሓት ሀገር ከፋፋይ ቀጣይ አጀንዳ አካል ነው

(የጉዳያችን ማስታወሻ)

ጉዳያችን / Gudayacnhn

ሰኔ 21/2009 ዓም (ጁን 28፣2017)

++++++++++++++++++++

ዛሬ ሰኔ 20፣2009 ዓም የሕወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራት ጥቅም በሚል ርዕስ ውሳኔ ማሳለፉ እና የሕወሓት ኢህአዴግ  99% አሸነፍኩ ወዳለበት ምክር ቤት እንደሚመራ ተነግሯል። ጉዳዩ ልዩ መብት የሰጠ የመሰለው ካለ እርሱ ከ26 አመታት በኃላም ገና ፖለቲካ ሀ ሁ እያለ እንደሆነ መረዳት ያለበት ይመስለኛል።

1/ ልዩ ጥቅም የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?



ልዩ ጥቅም የሚለው አባባል በእራሱ የመከፋፈል አላማ ያነገበ አባባል ነው።አንድ ሰው ልዩ ጥቅም ለማግኘት ዋናው መሰረት ሊሆን የሚገባው በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ የታሪክ የበላይነት ወይንም የዘር መሰረቱ ወይንም የተለየ አነጋገር በመናገሩን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ከሆነ መከፋፈል ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከኢትዮጵያ ምድር በመውጣቱ ነው።ከጃፓን ወይንም ብራዚል የመጣ ሰው የማይኖረው ልዩ ጥቅም ኢትዮጵያዊ ሊኖረው ይገባል።ይህ ማለት ኦሮሞው አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያዊነቱ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ አዲስ አበቤውም በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ኦሮሞው በመቀሌ ላይ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ የአክሱሙም ሰው በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የወለጋው ገበሬ በጎንደር ላይ ልዩ ጥቅም እንዳለው የራስ ዳሽን ገበሬም በነቀምት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ይህ ሁሉ ልዩ ጥቅም የሚመነጨው እንደ ህወሓት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በከፋፋይ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሙሉ መብት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ እና መሬት በሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የኦሮምያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የሚለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ  በእራሱ ከፋፋይ የሆነው  የስርዓቱ አጀንዳ ቀጣይ ምዕራፍ ነው።

2/ የውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ አገልግሎት አይደለም እንዴ?

 “የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በአዲስ አበባ ዙርያ ላሉ የኦሮምያ ክልሎች ያካተተ ይሆናል” ይላል ከአዋጁ አካል ውስጥ አንዱ።አሁንም ውሃ የማግኘት ልዩ መብት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ነው።ይህ አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያዊነቱ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልሎች የውኃ አገልግሎት ላያገኙ ነበር? የውኃ ፍሳሽ አገልግሎት ለማግኘት የልዩ ጥቅም አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያውነታቸው የማግኘት መብት የላቸውም ነበር? ይህ በእራሱ ከፋፋይ አቀራረብ ነው።በአዲስ አበባ ዙርያ ያለ የኦሮሞ ሕዝብ ውሃ ለማግኘት ልዩ አዋጅ መጠበቅ ነው ያለበት ወይንስ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያገኘው መብት ነው መሆን ያለበት? ለአዲስ አበባ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ወጪ የሚሸፈነው  ቀረጥ  ከኦሮምያ የሚመጣ ገንዘብም ጭምር መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያረሳሳን ነው ? እናስ የአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ገና ለገና ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር አብሮ ይነሳብኛል ልከፋፍለው በሚል እሳቤ ውሃ በልዩ ጥቅም አዋጅ መሰረት ይዘረጋልሃል የሚል አዋጅ ረቂቅ አንድ ሐሙስ የቀረው እና የታመመ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካልሆነ ማን ያወጣዋል?

3/ የጤና አገልግሎትስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?



በአዋጁ ረቂቅ ላይ “አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ በከተማዋ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የክልሉ ተወላጆችን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል” ይላል። የጤና አገልግሎት የኢትዮጵያዊነት ልዩ ጥቅም ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍልል ቢኖር የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱ ነው።በእዚህ ረቂቅ ላይ አዲስ አበባ እና ኦሮምያ የተለያዩ ሀገሮች ይመስል በአዲስ አበባ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙርያ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ታሳቢ ያደርጋል ሲል ዛሬ ተነስቶ ልዩ ጥቅም የሰጠ አስመስሎ ሕዝብ የመከፋፈል አላማ ለማሳካት ብቻ የተገለፀ ነው።

4/ የአዲስ አበባ ሕዝብ እና የኦሮምያን ሕዝብ ከህወሓት በበለጠ ይተዋወቃል

በእዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአዲስ አበባ ስም በፊንፊኔ፣የከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች እና አደባባዮች በኦሮምያ ታሪክ ይቀየራሉ የሚል ሃሳብ የያዙ አረፍተ ነገሮች እንዲሁም ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር የስራ መጠቀምያ ይሆናል ይላል።ኦሮምኛ የስራ መጠቀምያ መሆኑ አማርኛ እስካልገባው ድረስ ኦሮምያ የተወለደ ኢትዮጵያዊ በኦሮምኛ አገልግሎት ማግኘቱ ሙሉ መብቱ ነው።ዛሬ ህወሓት እንደ ልዩ ጥቅም አድርጎ ማቅረቡ ነው የማይመቸው። ይህ እንዴት ልዩ ሆኖ ይቀርባል? ኢትዮጵያዊ መብቱ በሚለው ስር የሚገባ ነው።አንድ የጋምቤላ ተወላጅ አዲስ አበባ መጥቶ አማርኛ ካልገባው በጋምቤላ አነጋገር አገልግሎት የማግኘት መብቱ ኢትዮጵያዊነቱ ያጎናፀፈው መብት ነው እንጂ ልዩ መብት ሊባል ያችልም። ሕወሓት ለመከፋፈል ስትፈልግ ልዩ መብት ብላ ትርክት መጀመሯ አስቂኝ ነው። የአዲስ አበባ ስያሜ መቀየር እና የከተማዋን ታሪካዊ ቦታ ከመቀየር አንፃር የተነሳው አገላለጥ በእራሱ የተደናበሩ ሰዎች ያወጡት ረቂቅ አዋጅ ነው። በመጀመርያ ደረጃ በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰጡት ስሞችም ሆኑ የአዲስ አበባ የእራሷ ስያሜ እውን ታሪካዊ አመጣጥ የሌለው ባዶ ትርክት ከነበረ የታሪክ ሰዎች ይንገሩን እና እንመን።በሐሰት ታሪክ ግን የትም ሀገር ስም አይቀየርም። ይህንን ልሞክር የሚል ካለ የመስቀል አደባባይ እና የአብዮት አደባባይ ስያሜን ማስታወስ ነው።በሕልም እና በስሜት ሕዝብ ያጋጭልኛል ከሚል እሳቤ ብቻ ሕወሓት ይህንን ማሰቧን እራሱ የኦሮሞ ሕዝብ እና የአዲስ አበባ ነዋሪ ጠንቅቆ ይረዳል።

ባጠቃላይ ልዩ ጥቅም በሚል ቡልኮ የተሸፈነው የህወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን የተለያዩ ሀገር በማስመስል የአዲስ አበባ እና ዙርያዋን ያሉት የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ግንኙነት ኢትዮጵያዊ የሆነ የጋራ እሴት ሳይሆን የጥቅም ግንኙነት ብቻ ያላቸው  አስመስሎ የማቅረብ ሙከራ ነው።መንግስት የተባለ አካል የመጀመርያ ስራው ዜጎቹን በእኩልነት የማስተዳደር፣ሕግ የማውጣት እና የማስፈፀም አቅሙን የማስመስከር  መሆን ይገባው ነበር።ከእዚህ ውጭ አንዱን አስነስቶ በእዚህ አካባቢ ልዩ ጥቅም አለህ።አንተኛው ግን በምትኖርበት ከተማ ከእርሱ ያነሰ ጥቅም ነው የምታገኘው የሚሉ አባባሎች በእራሳቸው ህዝብን ለመከፋፈል የሚደረጉ አጀንዳዎች የማስቀጠል ሥራ አካል ካልሆኑ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። አዲስ አበባ እና ኦሮምኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል አትሞክሩ።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ሕዝብ የምታገለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ልዩ ጥቅም እንዲኖረው ነው።

ይህንን ፅሁፍ የምደመድመው አንድ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አክቲቪስት በተናገረው ንግግር ነው። አባበሉ አሁን ሕወሓት እየዳከረበት ካለው የመከፋፈል ከንቱ ሥራ ፍሬ እንደሌለው በሚገባ ያሳየ ነው። አክትቪስቱ ያለው እንዲህ ነበር

“ሕወሓት የኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ያለውን ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በመቶዎች በሚቆጠሩ  ዓመታት ውስጥ ያለፈ እና ጠንካራ የደም ትስስር መሆኑን ህወሓት በደንብ ያወቀው አይመስለኝም።እነርሱ ራቅ ካለ አካባቢ ስለመጡ የእዚህ አይነቱ ጠንካራ ግንኙነት ታሪክ በደንብ የገባቸው አልመሰለኝም።የኦሮሞ ሕብረተስብ አሁን ሕወሓት እለያይበታለሁ እያለ የሚያቀርባቸው አጀንዳዎችን የመለያያ አጀንዳዎች እንደማይሆኑ ጥንት በሰራቸው ስርዓቶች ካፈረሳቸው ቆይቷል።ሕወሓት ትልቅ የመረጃ ክፍተት ላይ እንዳለ መረዳት አለብን” ነበር ያለው።

Dienstag, 27. Juni 2017

እነ ለገሰ ወ/ሃና የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው!!! በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ሳይቀርቡ ቀሩ!!!

እነ ለገሰ ወ/ሃና የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው!!!
በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ሳይቀርቡ ቀሩ!!!
(በሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
በሶስት መዝገቦች ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 49 ሰዎች ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ቀረቡ፡፡
፨ሁለት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባላትን  ጨምሮ አስር ሰዎች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ፣38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3/1/ እና/4/ ስር የተመለከተውን በመተላላፍ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ከሚገኙ የአርበኞች ግንቦት ሰባት  አባላት ጋር የትጥቅ ትግል እናካሂዳለን በሚል ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት 2009 ዓ.ም ድረስ በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ ከሚገኙ በህቡዕ ከሚንቀሳቀሱ አባሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለአመፅ  ለማነሳሳት የሽብር ተልዕኮና የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል የጦር መሳሪያ ቦንብ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በመግዛት በተለያዩ ጊዚያት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፡-
ክንዱ ዱቤ
ዘመነ ጌቱ
ደበበ ሞገስ
ዘርዓይ አዝመራው
ገብረስላሴ ደሴ
መርጌታ ዲበኩሉ ሰማረ
ሀብታሙ እንየው
ብርሀኑ አያሌው
መላኩ አለም
ለገሰ ወልደሀና ናቸው፡፡

 ፨በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ለዛሬ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበሩ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ዛሬም አለቀረቡም፡፡ዓቃቢ ህግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የተካሰሾች ጠበቆች በበኩላቸው ተደጋጋሚ ጊዜ በመቀጠሩ የደንበኞቻቸውን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን የሚያሰጣ በመሆኑ ዓቃቢ ህግ ምስክሮችን ማቅረብ እንዳልቻለ ተቆጥሮ በቀረበው ማስረጃ ብይን እነዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ፍርድ ቤቱም ዓቃቢ ህግ ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ለመጨረሻ ጊዜ ለሀምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የቀረበባቸው ንግስት ይርጋ፣በላይነህ አለምነህ፣ቴድሮስ ተላይ፤አለምነው ዋሴ፣ያሬድ ግርማ እና አወቀ አባተ ናቸው፡፡

፨በተመሳሳይ  የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ፣38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 7/1/ እና አንቀፅ 4 ስር የተመለከተውን ተለልፈው የሽብር ወንጀል ፈፅመዋል በሚል 35 ሰዎች ላይ የሽብር ክስ መስርቶባቸዋል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፡-
1ኛ. ተሻገር ወ/ሚካኤል ላቀው
2ኛ. ነጋ ዘላለም መንግስቴ
3ኛ. ተስፋሁን ማንዴ ሰላምሰው
4ኛ.  አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም ካሴ
5ኛ. አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት
6ኛ. ሰኢድ ኑርሁሴን ኑርሰይድ
7ኛ. በለጠ አዱኛ መንግስቱ
8ኛ. ተስፋሚካኤል  አበበ ላቀው
9ኛ. እንዳለው ፍቃዴ አበበ
10ኛ. ስለሽ ግርማይ ነጋሽ
11ኛ. ይታይ ክብረት አታላይ
12ኛ. አዛናው ሲሳይ ገዛኸኝ
13ኛ. ዮሃንስ አየሁ ዘለቀ
14ኛ. አለማየሁ መኳንንት ካሴ
15ኛ. አሸናፊ ዮሃንስ ዘሪሁን
16ኛ. እዮኤል  በሪሁን ይማም
17ኛ. ዓለምሰገድ ዋኛው በሪሁን
18ኛ. አበበ አበጀ ሽመልስ
19ኛ. መንግስቴ ተስፋሁን አረጋ
20ኛ. ሰለሞን ፀኃይ እንግዳ
21ኛ. አዝመራው ተሰማ አዕምሮ
22ኛ. ነበቡሽ ደሳለኝ መንግስቴ
23ኛ. ታደሰ ይግዛው ገብሬ
24ኛ. ቢራራ ልጃዓለም አብርሃም
25ኛ. አብርሃም ድረስ አለሙ
26ኛ. አማረ ገ/ሚካኤል ገ/ስላሴ
27ኛ. ሲሳይ ተስፋ ደሴ
28ኛ. አራጋው እንዳለ አሰፋ
29ኛ. ፍቅሬ ግርማይ ምትኩ
30ኛ. ደጀኔ ደምሴ ወርቅነህ
31ኛ. ሙላቱ ፍስሃ ገብሩ
32ኛ. ማርሸት አሰፋ ባዬ
33ኛ. ክንድሽህ ሀጎስ ታዬ
34ኛ. መንግስቴ አማረ ያዜ
35ኛ. ተስፋሁን ሙሌ መኮንን ናቸው። የክስ መቃወሚያ ለማቅረብ ለሀምሌ 11/2009 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡

Montag, 26. Juni 2017

አድርባይነት (Tadesse Biru Kersmoe )

አድርባይነት

1. ትርጓሜ

አድርባይነት ለገዛ ራስ ጥቅም እንጂ ለህሊና ዳኝነት፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት ላላቸው የሥነ ምግባር መርሆዎች፣ ለሌሎች ሰዎች፣ ቡድኖች፣ ትውልድና ሀገር ግድየለሽ መሆን ነው።  የግል ዝናውን፣ የግል ሀብቱን ወይም የግል ምቾቱን ለመጨመር ሲል ማድረግ የነበረበትን ማድረግ እየተቻለ ሳያደርግ የቀረ፤ ወይም ማድረግ ያልነበረበትን ያደረገ ሰው፣ ቡድን ወይም ድርጅት አድርባይ ይሰኛል።

አድርባይ የሆነ ሰው ወይ ድርጅት የሥነ ምግባር ልጓም የለውም፤ የሚናገረውን ሆኖ አይገኝም፤ ዋዣቂና ወላዋይ ነው፤ ለምንም ነገር መታመን አይችልም፤ ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ ማዶ ነው፤  ከፍ ያለ ዋጋ ላቀረበ ሁሉ ሊገዛ የሚችል ሸቀጥ ነው። አድርባይ ሰው ወይም ድርጅት ነገሮችን ሁሉ የሚመዝነው ከራሱ ጥቅም አንፃር ብቻ  ነው። አድርባይነት በመልካም ማኅበረሰብ የተጠላ፣ የተናቀ፣ የማይፈለግ ብቻ ሳይሆን በህገወጥነት የሚያስቀጣም ባህርይ ነው።

2. አድርባይነትን የት እንፈልገው?

1.  ሥልጣን:  ተጠያቂነት የጎደለው ሥልጣን ባለበት አድርባይነት ሊኖር እንደሚችል እንጠብቅ። ያልተገደበ ሥልጣን አድርባይነትን ያፋፋል።
2.  ጥቅም:  ጥቅም (በተለይም ገንዘብ) ባለበት ቦታ ሁሉ አድርባይነት የመኖሩ እድል ከፍተኛ  ነው። አድርባዮች ያለአግባብ ሲበለጽጉ የዳር ተመልካቾች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በማለት ሊቀላቀሏቸው ይችላሉ።
3.  ሁኔታ:  ሰዎች አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ ወኔ ሊከዳቸው ይችላል። ለምሳሌ ሰቆቃ (ቶርቸር) የበዛበት ሰው ወይም ከገመተው በላይ ማባበያ የቀረበለት ሰው ህሊናው የሚያዘውን ብቻ የመፈፀም አቅም ሊያጣ ይችላል።  “እኔ ባላደርገውም ሌላ ሰው ያደርገዋል” የሚለው ስሜትም ለአድርባይነት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው።
4.  ጋርዮች:  ለጋራ ጥቅም በኅብረት መሠራት በሚኖርበት ጊዜ አድርባዮች ከሥራው ድካም ተሸሽገው ከጥቅም ለመጋራት ግን ከሁሉ ቀድመው ይገኛሉ። አድርባዮች “ከጋራ ሀብት በጋራ ኃላፊነት ስሜት መጠቀም” የሚባል  ነገር አያውቁም።
5.  መረጃ: የመረጃ፣ የእውቀትና የግንዛቤ እጥረት ባለበት አድርባይነት ይፋፋል።  ነገሮች ግልጽ ባልሆኑት፤ የትኛው ህግ በሥራ ላይ መዋል እንዳለበት ያለየበት እና ብዥታ የበዛበት ሁኔታ ለአደርባይነት ምቹ ነው። አድርባዮች አውቀው መረጃን በማዛነፍ ለራሳቸው የተመቸ ሁኔታን ይፈጥራሉ።
6.  ውድድር:  የተፋፋመ ውድድር፣ ፉክክር ወይም ደግሞ ጦርነት ባለበት ሁኔታ ማጭበርበር፣ መዋሸት፣ ማታለል ተራ ነገር ይሆናል።  ለማሸነፍ አሊያም ከሽንፈት ለመዳን ሰዎች በሌላ ጊዜ የማያደርጓቸውን መጥፎ ነገሮች ያደርጋሉ። የተከበሩ የሥነምግባር መርሆዎች ይጣሳሉ።  አድርባዮች ውድድሮችን ተለማምጠውም ሆነ አጭበርብረው ይቀድማሉ።
7.  ስኬት:  ከመጠን ያለፈ ለስኬት መጓጓት ለአድርባይነት መንገድ ይከፍታል። ለምሳሌ ዝናን፣ መታወቅን ከመጠን  በላይ መሻት።   ለግል ስኬቱ ከመጠን በላይ የሚጨነቅ ሰው በሌላ ጊዜ ህሊናው የማይፈቅድለትን ሥራ  ሊሠራ ይችላል።

3.  “ወይን ለመኖር”

ለጥቅም ብሎ የኢሕአዴግ ድርጅቶች (ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴግ) ወይም አጋር ድርጅቶች (አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ) አባልነት ፎርም መሙላትና በህወሓት ፈቃድ ማደር  “ወይን ለመኖር” የሚል ስላቃዊ ስያሚ ተሰጥቶታል። “ወይን ለመኖር” በአሁኑ ሰዓት አገራችን እያዋረደ ያለ የአድርባይነት ዓይነት ነው።

ሁሉን ጠቅላይ  (totalitarian) አገዛዝን በማስፈን “ወይን ለመኖር” ለህወሓት ከፍተኛ ጥቅም ያስገኘ ስልት ነው። የወይን ለመኖር ዓላማ ዜጎችን መቆጣጠር ነው። “ወይን ለመኖር” ኢትዮጵያዊያን የህወሓትን ኃይል በመጠን በላይ አግዝፈው፤ የራሳቸውን ደግሞ አንኳሰው እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል። “ወይም ለመኖር” በርካታ ወገኖቻችን በብአዴን፣ ኦህዴግ፣ ደኢህዴግ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ... ውስጥ ገብተው እራሳቸውን እያዋረዱ፤ ወገናቸውን እያሳረዱ፣ አገራችውን ዘርፈው ለዘራፊው ህወሓት እንዲያስረክቡ እና ማኅበረሰባዊ ቀውስ እንዲፈጥሩ አድርጓቸዋል።

4. ምን ይደረግ?

1.  ከሁሉ አስቀድሞ ለራሳችን ክብር እንስጥ፤ ለጥቅም ወይም በፍርሃት ምክንያት የኢሕአዴግ አባልነት ፎርም በመሙላት ባርነትን አንቀበል።
2.  ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዜጎች ነፃነት መሠረት መጣል የሚቻለው አድርባይነትና አድርባዮችን በመታገል መሆኑን እንቀበል። አገር በአድርባዮች እንደማትገነባ ማወቅ።
3.  በማናቸውም ምክንያት ራሳቸውን ኢሕአዴግ ውስጥ ያገኙ የሕዝብ ወገኖች እዚያው ውስጥ ሆኖ ኢሕአዴንግ የማፍረስ ሥራ እንዲሠሩ ማበረታታት።  የኢሕአዴግ መዋቅር ራሱ ኢሕአዴን ለማዳከሚያነት መጠቀም።
4.  “ወይን ለመኖር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያዋረደ፤ ለትውልድ የሚተርፍ የስነልቦና ኪሳራ ያደረሰ ማኅበራዊ በሽታ እንደሆነ እውቅና ተሰጥቶት ጥንቃቄ ማድረግ።
ዶክተር ታደሰ ብሩ