Netsanet: April 2014

Mittwoch, 30. April 2014

''የፈሪ ዱላው አስር'' ኢህአዲግ ፈርቷል።ለመሆኑ ኢህአዲግ ያሰራቸው ምንም አይነት ድብቅ አላማ የሌላቸው የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው?

April 29/2014

ፍርሃት የማያሰራው ነገር የለም።ኢህአዲግ በከፍተኛ የፍርሃት ማጥ ውስጥ ነው።ሁሉንም ይፈራል።አይዞህ አትፍራ ቢሉትም የሚችል አይመስልም።በሕዝብ ላይ የሰራቸው ሕዝብ የሚያውቃቸው እና የማያውቃቸው ብዙ ድብቅ ስራዎች ስላሉት የመፍራት ደረጃው ከዕለት ወደ ዕለት እየባሰበት እንጂ እየተሻለው አልሄደም። የሚደግፉትም ልያፅናኑት አልቻሉም።ከሚገባው በላይ ፍርሃት ሲያንቀጠቅጠው ሲመለከቱ እነርሱም ይብሱን ፈሩ።ብዙ የስርዓቱ ደጋፊዎች እና በሀብት የደለደሉቱ ሀገር ጥለው እየወጡ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህ ደግሞ ሌላው የፍርሃት ገፅታ ነው።

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሌሎች ሰሞኑን የተያዙት ጋዜጠኞች ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ግን ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር ያሉ በእዚህም መስረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ እየጠቀሱ የሃሳብ የመግለፅ መብታቸውን የተጠቀሙ፣የሚሰሩት በመንግስት መስርያቤቶች የሆነ፣የሚፅፉት አይደለም ምን በልተው ከማን ጋር ውለው እንዳደሩ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሕዝብ የሚያውቃቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው።ከእዚህ በፊት በሃሳብ የሞገቱትን ሁሉ ''ህገ መንግስቱን እና ስርዓቱን ለመናድ የተንቀሳቀሱ'' እያለ ሲያስራቸው የነበረው መንግስት ዛሬ እራሱ ህገ መንግስቱን አክብረው ሕግ እየጠቀሱ የፃፉትን በ20 ዎቹ እድሜዎች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ''ሃገርን በውጭ ከሚኖር ድርጅት ጋር ተመሳጥረው ሊያሸብሩ'' እያለ ፌዝ አይሉት ቀልድ መሰል ክስ አቅርቦ ማዕከላዊ እስር ቤት አስገባቸው።ምንም አይነት ወንጀል እንደሌለባቸው እራሱ ኢህአዲግ ያውቀዋል።ግፍ መስራት የማይሰለቸው እና በፍርሃት የተዋጠ መሆኑ ግን የእዚህ አይነቱን ተግባር እንዲቀጥልበት አድርጎታል።

''የፈሪ ዱላው አስር'' እንዲሉ የኢህአዲግ አባላት ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ የግብፅ፣የየመንን በቅርቡ ደግሞ የዩክረንን የህዝብ ንቅናቄ እያዩ በሰላም መተኛት አልቻሉም።ያ ቀፎው እንደተነካ ንብ የሚተመው ሕዝብ አንድ ቀን እኛም ላይ ይነሳል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።ለእዚህም ማስረጃው ኢቲቪ ባለፈው ሰሞን ያሳየው የዩክሬንን አመፅ የተመለከተ ፊልም መጥቀሱ ይበቃል።ፍርሃታቸውን ደግሞ እነ ሚሚ ስብሃቱ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ገብቶ እንደሚንዘፈዘፍ ሰው እየተንቀጠቀጡ ሲናገሩ ሕዝብ ታዝቦ ''ወይ ፍርሃት'' ብሏል።ግንቦት 20 ስመጣ ጀግና እንደነበሩ ከሃያ ዓመት በፊት የነበሩ አሮጌ ታንኮች ያሳየናል።መለስ ብለው ደግሞ በፈስ ቡክ እና በጡመራ ፈራን ይላሉ።አጀብ ነው።

ኢህአዲግ ፈራሁ ብሎ ያሰራቸው ንፁሃን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው? የወጣቶቹን የስራ መስክ ግልፅነት እና ሙያ ተመልክታችሁ ፍረዱ።ለፈሪዎችም እዘኑላቸው።

1/ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
ለተባበሩት መንግሥታት ዜና አገልግሎት ኢሪን ለረጅም ጊዜ የሰራ የእንግሊዝኛው 'ፎርቹን' ጋዜጣ አምደኛ እና ዘጋቢ

2/ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ
  አዲስ ጉዳይ መፅሄት ከፍተኛ ኤዲተር
3/ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ
በአካባቢ ጥበቃ የሰለጠነች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በቀድሞው 'እንቢልታ' ጋዜጣ ዘጋቢ
4/ በፍቃዱ ኃይሉ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ብሎገር እና ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ በሙያው የሚሰራ
5/ አቤል ዋበላ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የአየር መንገዱ 'ግራውንድ ቴክኒሻን'
6/ ማህሌት ፋንታሁን
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰራተኛ
7/ አጥናፍ ብርሃኔ
የ25 ዓመት ወጣት በፌስ ቡክ ሃሳቡን የሚገልፅ በብሎጉ ላይ ሃሳቡን የገለፀ
8/ ናትናኤል
የ 26 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ባለሙያ፣'የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር' አባል
9/ ዘላለም ክብረት
የሕግ ባለሙያ፣ማስተርሱን ከሰራ ገና ሳምንታት የሆነው በአምቦ ዩንቨርስቲ የሕግ ትምህርት መምህር ናቸው።

ምንጭ - ከጦማርያኑ ውስጥ በውጭ ሀገር የሚገኙት እንዳልካቸው እና ሶልያና ለቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሚያዝያ 20/2006 ዓም ከሰጡት መግለጫ የተገኘ።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 21/2006 ዓም

ዓባይ እንደ ዋዛ–ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ ዓባይን ለመታደግ ይቻላልን?

April 29, 2014

አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ክፍል ሁለት

Click here for PDF

“ውኅ እየጠማው ያባዪን ልጅ
እሚያዘጋጅለት ቢጠፋ

እሚያበጃጅ ለልማት የሚያመቻች ዓባይን
አኮላሽቶለት ፈንጂውን”

ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው፤ ዐባይ–ፈንጅ የቀበረ ውሃ
ኢትዮጵያ ታላቅና ሃብታም ለመሆን የምትችል አገር ናት። የተፈጥሮ ሃብቷ፤ አቀማመጧና የሕዝብ ስርጭቷ ለታላቅነቷ የማይገኙ ምሰሶዎች (Social Pillars) ናቸው። ሆኖም፤ ይህ የአገርና የማህበረሰብ ታላቅነት መሰረት ጎሳዊና አምባገነናዊ የሆነ ስርዓት ባመጣው ጦስና ቀውስ እየባከነ ነው። ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ የተካውን መንግሥትና ሌሎችን በማዋረድ፤ በማጋለጥ፤ በማጥላላት፤ በማሰር፤ በመግደልና ከሃገር በማባረር ሃያ ሶስት ዓመት ገዝቷል። የጥቂቶችን ኪስ በሚያሳፍር ደረጃ ሞልቶ፤ ቢያንስ ሃያ አምሥት ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ተዘርፎ ወደ ውጭ ሃብታም አገር ባንኮች እንዲዘዋወር አድርጓል። ይኼን ሲያደርግ ደጋግሞ የሚነግረን ተግባሩ ሁሉ ለጭቁን ሕዝቦች፤ ለድሃዎች ጥቅም የሚል ፕሮፓጋንዳ እየተጠቀመ ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን፤ ጠበብቶች፤ ሰራተኞች፤ አገር ወዳዶች ወዘተ አገር ብትሆንም ዛሬ የተማረና አገሩን ለማልማት የሚችል የተማረና የሰለጠነ የሰው ኃይል ድሃ ሆናለች። በሃያ አንደኛው መቶ ክፍል ዘመን ተቀባይነት የሌለው በኢትዮጵያ ተከስቷል። ገዢው ፓርቲ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ እየከፋፈለ፤ እያሰረ፤ እያባረረ፤ እያደኼየ፤ ኃይላቸውን እያባከነ፤ ተስፋ እያስቆረጠ፤ መብታቸውን እየገገፈፈ፤ ተሰደው የውጭ ምንዛሬ እንዲልኩ እያደረገ ከሕንድ፤ ከቻይናና ከሌሎች አገሮች የሰው ኃይል፤ የቀን ሰራተኞች ጨምሮ፤ ይሽምታል። ኢትዮጵያውያን ሊሰሩት የሚችሉትን በውጭ አገር ሰዎች ያሰራል። አገሪቱ የማትችለውን ደሞዝና አበል ይከፍላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተማረውና ያሰለጠነው የሰው ኃይል፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በአገሩ የመስራትና የስራ እድል የመፍጠር አቅምና መብቱ ስለታፈነ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፤ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ወዘተ ይጎርፋል። የሳውዲ፤ በቅርቡ የኩዌት መንግሥትና ሌሎች በኢትዮጵያውያን የቀን ሰራተኞች ላይ የወስዱት አሳፋሪ እርምጃ በግልፅ ያሳየን አስደናቂ እድገት ታሳያለች የምትባለው አገራችን የኢትዮጵያውያንን የስራ፤ የገቢና የኑሮ ፍላጎት ለማሟላት አለመቻሏን ነው። በተደጋጋሚ እድገቱ የጥቂቶች መጠቀሚያ ሆኗል የምለው ለዚህ ነው።
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኑሮው፤ በመብቱ፤ በመንግሥቱና በተፈጥሮ ሃቡቱ ለማዘዝ አይችልም። በአገር ቤት መሬት ለመመራት፤ ቤት ለመግዛት፤ የግል ተቋም ለመመስረት የሚችለው ገቢና አቅም ያለው ዲያስፖራ፤ በአብዛኛው የገዢው ፓርቲ አጋር ሆኗል ለማለት ይቻላል። በዓለም ድሃ፤ የሕዝባቸው ጤና ያልተጠበቀበትና ኋላ ቀር ከሆኑ አገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይል ድሃ መሆኗን በአንድ ምሳሌ አቀርበዋለሁ። የካናዳው ኩሶ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት ከ1990-2006 ዓም ባለው ጊዜ ብቻ ኢትዮጵያ ካሰለጠነቻቸው 3,700 የህክምና ባለሞያዎች 700 ብቻ አገር ቤት ይሰራሉ። ሶስት ሽህ የሚሆኑት ወጥተው ሌሎች ሕብረተሰቦችን፤ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያገለግላሉ። በሌሎች ሞያዎች የተሰማራነውም ተመሳሳይ ሚና አለን። ገዢው ፓርቲ ፈቃድና ፓሥፖርት በመስጠት ቀልጣፋ ነው። መብትን በመግፈፍ የሰለጠነ ነው። የሚፈልገውን ያገኛል። የሚፈልገው ሁለት ነገሮች አሉ። አንድ የውስጥ ተወዳዳሪና ተቃዋሚ እንዳይኖር። ሁለት ወደ ውጭ የሚጎርፈው የሰው ኃይል የውጭ ምንዛሬ እንዲልክና ለገዢው ፓርቲ ደጋፊ እንዲሆን። ብንቀበልም ባንቀበልም ይህ እቅድ እየሰራ ነው። የእድገቱ አድናቂ ከሆኑት ውስጥ ሃብትና ቤት ያለው ዲያስፖራ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል። ከመቶው ዘጠናው የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፍስ ወከፍ ገቢ ዓለም ባንክ ካወጣው በቀን አንድ ዶላር ከሃያ አምስት ሳንቲም በታች መሆኑን ረስቶታል ወይንም አያየውም። ስለዚህ ነው፤ “ዓባይ ዓባይ ዓባይ” የሚለው አነጋጋሪ አርእስት ከስርዓቱ አፋኝነት ጋር አብሮ መታየት አለበት የምለው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
The Nile is a major north-flowing river in northeastern Africa

ሴቶችን አብዝቶ የሚፈራው መንግሥት

April 29, 2014

ቹቸቤJailed Ethiopian female bloggers, activists and journalists መነሻቸው ግልብ ጎጠኛነት መድረሻቸው መንደረተኛነት በመሆኑ በዘረፋ እየከበሩ በመለስ ራዕይ እያጨናበሩ ከመኖር ያለፈ ከእውነት ጋር ፊት ለፊት ተያይተው መኖር ያልቻሉት የትግራይ ጉጅሌዎች በወጣቶች ላይ የሚፈጽሙት ሰቆቃ አሳፋሪ ነው። በህጻናትና በሴቶች ላይ የሚበረቱ የማስተዋል ድርቅ የመታቸው፣ የእውቀት ረሀብ ያደነዛቸው ፍርሃት እንቅልፍ የነሳቸው ናቸውና ድፍረት ያላቸው ህጻናት ያስፈሯቸዋል እውነት የያዙ ሴቶች ያስደነግጧቸዋል። ለዚህ ነው የወጣቶችን ግንባር በምንደኛ ጦር ሲነድሉ ወጣት ሴቶችን ሲደፍሩ ሲያስደፍሩና ሲያዋርዱ ደስታን የሚያገኙት።
አብዛኞቹ በዚህ ጎጠኛ ቡድን የሚንገላቱት ወጣቶች ወያኔ በገባበት ዘመን የተወለዱ ወይም ገና ድክድክ የሚሉ ህጻናት ነበሩ። ሲነገራቸው የኖረውና ህይወታቸውን ሙሉ የተመለከቱት ኢትዮጵያ ስትዋረድ የሀገሪቱ ጀግኖች ሲሰደቡና ዘር በዘር ላይ ሀይማኖት በሀይማኖት ላይ የሚያነሳሳ ታሪክ ሲማሩ ነበር ያደጉት። ሬድዮ፣ ቴሌቭዥን ጋዜጣና መጽሄቱ ሁሉ የሰሩት የወያኔን ፕሮፓጋንዳ ነበር። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊነት ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየገነነ፣ ለነፃነት የሚደረገው ትግል እየጠነከረ መምጣቱ ይልቁንም አፍራሹ ፕሮፓጋንዳና ድርጊት ጠንካራ ወጣት ወንዶችና ወይዛዝርቶችን ቁርጠኛ ታጋይ እንዲሆኑ አደረገ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ሲሞት አላየንም።
ከዚህ መማርና መለወጥ የሚቻል ቢሆንም ኢትዮጵያዊነትን ያሟጠጠ አእምሮው በጥላቻ የሰከረን መመለስ እንደማይቻል መመልከት አሳዛኝ ነው። “የሚያድግ ልጅ አይጥላህ” የሚባለው ተረት የሚያስተምር ቢሆን በወጣቶች ላይ የሚሰራውን ግፍ ቀነስ ማድረግ በተቻለ ነበር። እኒህ ወጣቶች ይቅር ባይ እንጂ ቂመኛ እንዳይሆኑ ግን ምኞቴ ነው።
እነዚህ ክፉዎች በየቀኑ የሚተክሉት የጥላቻ ችግኝና የእልቂት ድግስ የመቶ አመቱን በደል አስታውሶ ከሚያጫርሰው በላይ ዛሬ የሚደርሰውን ግፍና በደል አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ የታች አምናውን ሳይሆን የትናንቱን የወያኔን ሕዝብ ከመኖርያ ማፈናቀል፣ ገበሬዎችን መበተን፣ የሀገር ድንበር መቁረስን፣ በአማራና ኦሮሞ ላይ እየተኪያሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት እያስታወሰ የሕዝብ ሃይል መልሶ ጠራርጎ እንደሚያጠፋቸው አለማወቅ የግብዝነትና የድንቁርና ምልክቱ ነው። በዘመነ ደርግና በንጉሳውያኑ ዘመን ከሆነው ሁሉ የበለጠ ግፍና በደል የተፈጸመው በነዚህ ጎጠኞችና የሀገር ጠላቶች እንደሆነ ለመናገር እዚያው ትግራይ ያለውን ተቃውሞ ምሳሌ ማድረግ ይበቃል። ጎጠኞቹ ልብ ያላሉት የታቀፉት የእባብ እንቁላል እነሱኑ ቀድሞ እንደሚነድፍ ነው። ይህ እንደሚሆን ለማወቅ በሀገሪቱ ከተበተኑት ሰላዮች መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን እውነት እንዲናገሩ ብቻ ቢፈቅዱላቸው እንኳ ያንዣበባቸውን አደጋ ባወቁት ነበር።
ርዕዮት አለሙ ጽንፈኛና አሸባሪ ልትባል የምትችልበት ምንም መረጃ የለም። ወያኔዎችን ያስፈራው እውነትን መያዝዋና ድፈረቷ ብቻ ነው። ርዕዮትን ማሸማቀቅ ሌሎችን ለማስፈራራት የተወሰደ እርምጃ ነበር ግን ውጤቱ በተቃራኒው ሆነ። እናም አነሆ ወይዛዝርቶቹ ተነሱ! ስለወያኔ ክፋት ሳይሆን ስለሕዝባችን ብርታትና መነሳሳት የምናወጋውም በኩራት የሚሆነው ለዚህ ነው።
ሴቶች ትግሉን አልተቀላቀሉም፣ ብዙዎቹ ወደሁዋላ ይላሉ እንላለን ጥቂት ግን በጣም ጥቂቶቹ ደፍረው ሲወጡ ከጎናቸው ልንቆምና በየአቅጣጫው ልንታገልላቸው ይገባል። ርዕዮት እድሜዋ ገና ሰላሳዎቹ ውስጥ ያለች ወጣት ትዳር ያልመሰረተችና ልጅ የሌላት ብዕረኛ ናት። ትዳሩ ይቅር ልጅም አይኑራት ነገር ግን ለህይወትዋ አስጊ በሆነ የጤና ችግር ላይ መሆንዋ እየታወቀ ህክምና እንዳታገኝ ማድረጉ አሰቃይቶ የመግደል እኩሌታ ነው። ይህ የግፍ ጽዋ ሞልቷል። ወጣቱ ቆርጦ ተነስቷል።
ምስላቸው ከዚህ ጽሁፍ ጋር የሚታየው ወጣቶች የእስርቤት ሰለባ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ በጣም ያሳዝናል። ይሁን እንጂ ሁላቸንንም የሚያበረታቱ የጣይቱ የዘር ግንድ የጀግኖች የዜግነት ውርስ በዚህ ትውልድ ደም ውስጥ መፍሰሱን ስለሚያመለክቱ ተስፋ ይሰጡናል ብርታትም ይሆኑናል። እኒህ ወጣቶች ከታሰረው ከሰፊው ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው ለነጻነት ለሚደረገው ትግል አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ተባብረን እንነሳ! ከትንሹ እስር ቤት ወደ ትልቁ ይመጡ ዘንድ ድምጻችንን እናሰማ። አብረንም ሆነን የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ። ኢትዮጵያችንንም ነፃ እናውጣ!
ኦህ ኢትዮጵያ ባንቺ ተሰፋ አይቆረጥም… ልጆችሽ የነጻነት ዐየርን ይተነፍሱ ዘንድ በጀግንነት እንታገላለን… ሁሌም የመከራ ገፈት የሚቀምሱትና የበደል ጫና አንገት ያስደፋቸው የሀገራችን ሴቶች በሀገራቸው ኮርተው አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ የድርሻችንን ሁሉ እናበርክታለን።

የኢህአዴግ መንግስት በሚቃወሙትና በሚተቹት ላይ እየወሰደ ያለውን አፈና እና እስር የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን!!!

April 29, 2014

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ፓርቲያችን አንድነት አበክሮ በተደጋጋሚ እንደገለፀው ኢህአዴግ ያነበረው አምባገን እና ክፉ ስርዓት ዜጎች በተለያየ ጊዜ የሚያነሱትን የሰብዓዊ መብት፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ የሚቀለብሰው ወታደራዊ አቅሙን በመጠቀም ነው፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ አካሄዱም ስርዓቱን ይቀናቀናሉ የሚላቸውን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎችና በግለሰብ ደረጃ ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎችን የተለያየ ስም እየሰጠ ወደ እስር ቤት አውርዷል፡፡ እያወረደም ይገኛል፡፡ በርካታ ዜጎች የአስከፊው ስርዓት ሰለባ ሆነዋል፣ እየሆኑም ነው፡፡ ሀገራችን በመነጋገርና በመደማመጥ ችግራችንን የምንፈታባት እንዳትሆን ሆን ተብሎ ለዘላለም መንገስ በሚፈልጉ ባለጊዜዎች የፊጥኝ ታስራ፤ ዜጎቿ እንደቀደመው ስርኣት ሁሉ በእስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡UDJ/Andinet party logo
እንደዜጋም በታላቋ ሀገራችን በሰቆቃ እንድንኖር ተፈርዶብናል፡፡ ኢህአዴግ ዛሬም ከመንገድ አፍሶ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ማሰቃየቱንና ማንከራተቱን ገፍቶበታል፡፡ ከጊዜና ሁኔታዎች እንደመማር ዛሬም ለስርዓቱ አደጋ ናቸው የተባሉ ወጣቶች ሰበብ እየተፈጠረ ወደ ማሰቃያ ስፍራ እየተጋዙ ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ አፈ-ቀላጤ በሆኑ ሚዲያዎች የታሰሩት ክስና ወደፊት የሚታሰሩት እነማን እንደሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ወጣት አመራሮቻችንና አባላትን የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራም ነው-ስራ ከሆነ፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ሰሞኑንም በግል ተነሳሽነታቸው ለሀገራቸው አስተዋፅኦ ለማድረግ ወስነው በብዕራቸው የሰብኣዊ መብት እንዲከበርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲረጋገጥ በሚወተውቱ የነበሩ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደው የእስር ርምጃ የሚያመለክተው በቀጣዩ አመት የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ የተወሰደ የማሸማቀቅና የወጣቶችን ጥያቄ ለመቀልበስ የሚፈልገው የአምባገነኑ ስርዓት ተግባር ነው፡፡
ፓርቲያችን ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁትን ወጣት ጋዜጠኞች ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚሸረሽር እንደሆነ እናምናለን፡፡ አፈናው ግን ሌሎችን በሺዎች የሚቆጠሩ ብሎገሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንደሚፈጥር አንጠራጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት የከፈተው የእስር ርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆምና የታሰሩትም ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲጣራ፤ መንግስት ያሰረበትን ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡ ፓርቲያችን ዘላቂው መፍትሄ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል አፋፍሞ መቀጠልና በሰላማዊ ትግል አምባገነኑን ስርኣት ማስወገድ ብቻ እንደሆነ ያምናል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
ሚያዚያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ከዞን ዘጠኖች አንዱ ከጆን ኬሪ ጋር

April 29th, 2014

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የታሰሩ ብሎገሮች ጉዳያቸው በአስቸኳይ ታይቶ እንዲፈቱ በቀጥታ የኢትዮዮጵያን መንግስት መጠየቃቸው ቃለ አቀባይዋ ሚሲስ ፕሳኪ ገለጹ።

የኢትዮጵያ መንግስት በሕገ መንግስቱ የተደነገጉትን መብቶች ማክበር እንዳለበት፣ አሜሪካ ጠንካራ አቋም እንደሆኑ የገለጹት ሚሲስ ፕሳኪ፣ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ጆን ኬሪ በአፍሪካ ጉብኘት ባደረጉበት ጊዜ ሁሉ የሰባአዊ መብት ጉዳይ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደሚያነሱ ለመጠቆም ሞክረዋል።

ከታሰሩ ብሎገሮች መካካል አንዱ ናትናኤል ፈለቀ፣ ከአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ ጋር የተነሳዉን ፎቶ ይመልከቱ።

Imageአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ፣ በኢትዮጵያ ጉድያ ላይ ከተናገሩት ጥቂቱን ከዚህ በታች ማንበብ ይችላሉ።

State Department Daily Briefing regarding Secretary Kerry’s visit to Ethiopia.
MS. PSAKI: Sure, I can. We are aware that six independent bloggers and three independent journalists were detained by Ethiopian police April 25th through 26th. We urge the Government of Ethiopia to expeditiously review the cases of these detainees and promptly release them. We have raised these concerns on the ground directly with the Government of Ethiopia.
And we, of course, reiterate our longstanding concern about the abridgment of the freedom of press and the freedom of expression in Ethiopia, and urge the Government of Ethiopia to fully adhere to its constitutional guarantees. And certainly while the Secretary is there as part of his trip to Africa, he often raises, at every opportunity, issues surrounding human rights, whether it’s media freedoms or equal treatment, freedom of speech, and I expect that will be the case this time as well.


Dienstag, 29. April 2014

የአባቶች ስንብት … (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )

April 29, 2014

ከ97ቱ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የ2002ቱ ምርጫ የቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል፤ ከመቼውም በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን ያጠበበው ገዢው ግንባር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን የምረጡኝ ክርክር እንደ 97ቱ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍም ሆነ በአዳራሹ ታዳሚዎችና ታዛቢዎች እንዲገኙ አልፈቀደም፤ በዚህ ክርክር ላይ ኢህአዴግ እንደተለመደው ለመጀመሪያ ጊዜ ካቀረባቸው ጥቂት አፈ-ቀላጤዎቹ መካከል የተመልካችን ትኩረት በመሳብ ጎልማሳው የወራቤ ፍሬ ሬድዋን ሁሴንን የሚተካከል አልነበረም፡፡ ሬድዋን ዕድሉን ካገኘ እንደ ‹‹ጓድ›› መንግስቱ ኃ/ማሪያም ለሰዓታት ሳያቋርጥ ቃላቶችን እንደ መትረየስ አከታትሎ ማንጣጣት ጎልቶ የሚታወቅበት ባህሪው ነው፤ ‹ከሎጂክ› ይልቅ የተዋቡ አረፍተ ነገሮችን መደርደር ይቀናዋል፤ በየመሀሉም የመድረክ ተወካዮችን ‹‹ራዕይና የጠራ ፖሊሲ የሌላቸው››በማለት ይዘልፋል፤ መልሶ ደግሞ ‹ፀረ-ኢትዮጵያዊና ፀረ-ሰላም ናቸው›› ሲል ይኮንናል፡፡ በየሰከንዱ በአስደንጋጭ እና በአደገኛ(Inflammatory) የቃላት ሰይፍ ይመትራቸዋል፡፡ ይህ ‹‹ታጋይ››ነቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በጉምቱ የድርጅቱ ሰዎች ዘንድ ሞገስን አስገኝቶለታል፡፡ ይሁንና ከዕለታት በአንዱ ቀን በዛው አድናቆት በተቸረበት የክርክር መድረክ፣ እንደልማዱ ቃላት ስንጠቃው ላይ ተጠምዶ የነገር ጦሩን ሲያወናጭፍ ድንገት አዳልጦት ታላቅ ‹‹ስህተት›› ፈፀመ፡፡Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
የሬድዋን ‹‹ስህተት›› ድርጅቱ-ኢህአዴግ አፄ ምኒሊክን፣ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የሚያብጠለጥልበትን የታሪክ ንባብ ገልብጦ መተንተኑ ነበር፡፡ እንደሚታወቀው ግንባሩ ንጉሡ ዐድዋ ላይ ጣሊያንን ድባቅ ከመቱት በኋላ እግር እግሩን ተከትለው እያሳደዱ መረብን በመሻገር፣ ከምድረ-ኤርትራም ጠራርገው ለማስወጣት አለመሞከራቸው፤ በአካባቢው ተወላጆች ዘንድ ለተፈጠረው የተገንጣይነት ስሜት ገፊ-ምክንያት አድርጎ መስበክ የጀመረው ከበረሃው ዘመን አንስቶ ነው፡፡ ይሁንና ከተማ ውስጥ በአቋራጭ የተቀላቀላቸው አዲሱ ‹‹ካህን›› ሬድዋን ሁሴን ፕሮፓጋንዳው እንደ በረኸኞቹ ‹‹ካህናት›› ከደም-አጥንቱ ጋር በደንብ አልተዋህደምና ምኒሊክ ከአድዋ ድል በኋላ ጦርነቱን እስከ መረብ-ምላሽ ድረስ ልግፋው ብለው ወደፊት ቢቀጥሉ ኖሮ ለአሰቃቂ ሽንፈት ከመዳረጋቸውም በላይ፣ በሺዎች መስዋዕትነት የተገኘውን ድልም አሳልፈው በመስጠት ትርጉም አልባ ያደርጉት እንደነበረ በመሞገት፣ ስለወቅቱ የንጉሡ ውሳኔ ትክክልነት ኢህአዴግን ወክሎ በተገኘበት መድረክ ላይ በይፋ መሰከረ፡፡ ይህ ከድርጅቱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹ቅዱስ መጽሐፍ› የሚጣረስና አለቆቹንም ያስከፋ ‹‹ስህተት››፣ በቀሪዎቹ የክርክር መድረኮች ላይ እንዳይሳተፍ እግድ አስጣለበት፡፡
ዘፍጥረት
ገዥው-ፓርቲ፣ በድል አድራጊነት መንግስታዊ ሥልጣኑን ጠቅልሎ ከያዘ በኋላ፣ መናፍቃውያን መሪዎቹ ባዘጋጇቸው ‹‹የታሪክ ድርሳናት››፤ በውይይት መድረኮች እና በቁጥጥሩ ስር ባዋላቸው መገናኛ ብዙሀን አማካኝነት ኢትዮጵያ የምትባለዋ የ3 ሺህ ዓመታት ቀደምት ገናና ባለታሪክ ሀገር፣ በተሟላ ቅርፅ የተፈጠረችው በግንቦት ሃያው ‹‹ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች›› ድል አድርጎ የሚያቀርበውን የፈጠራ ታሪኩን እንደ እውነት ለማስረፅ በርካታ ድንጋዮችን ፈነቃቅሏል፤ ተራሮችን ቧጥጧል፡፡ ለዚህ ስሁት ስብከቱም በደጋፊ ማስረጃነት የሚያቀርበው የማዕከላዊ መንግስቱን ምስረታ የዘመናት ሂደት ሲሆን፤ ሂደቱንም ‹‹ታገልኩለት›› ለሚለው ዘውግ ተኮር ፖለቲካ ቅቡልነት ሲል ለዘረፋ እና ለወረራ (ለቅኝ ግዛት) የተደረገ አስመስሎ እስከ ማቅረብ ያደረሰው ዘመንና ታሪክ ሽቀባ ውስጥ ገብቷል፡፡ እነሆ የዚህ ውጤትም ዛሬ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ላንዣበበው ጊዜ አመጣሽ የእርስ በእርስ ግጭት መነሾ ሆኗል፡፡
ምዕራፍ አንድ
ኢህአዴግ-መሩ መንግስት ከአንድነት ይልቅ፣ በተናጠል ማንነት ላይ በተመሰረተ አዲስ ታሪክ እንዲቆሙ ያስገደዳቸው ህዳጣን ጨምሮ፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዘውጎችንም በራሱ የታሪክ ብያኔ አፍርሶ እንደ አዲስ ለመስራት አሀዱ ያለው ገና የሥልጣን እርካቡን እንኳ አደላድሎ ባልረገጠበት ጊዜ እንደነበር የትላንት ትውስታችን ነው፡፡ በተለይም ሰፊው ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪን፣ ራሱን የባለፈው ዘመን ብቸኛ የጥቃት ሰለባ አድርጎ በመውሰድ እንዲብሰለሰል ሲገፋ፤ አማርኛ ተናጋሪውን ደግሞ በቀደሙት አባቶቹ ታሪክ የሚያፍርና የሚሸማቀቅ ሆኖ እንዲቀር ለሁለት አስርታት ያልከለሰው ድርሳን፤ ያልደመሰሰው መዛግብት አልነበረም፡፡
አብዮታዊ ግንባሩ በታገለለት የዘውግ ፖለቲካ የሚበየነው ስርዓት ህልውናን ለማስረገጥ፤ በደምና አጥንት የቆሙ የአንድነት አምዶችን አፈራርሷል፤ የሕዝብ ለሕዝብ መስተጋብርን ለዘመናት ያፀኑ ቅፅሮችን ለመንደር ፖለቲካው ትግበራ ሰውቷል፡፡ ለከፋፋይ አስተዳደሩም በሀገር አቅኚነት ራዕይ ስር የተፈፀሙ የማንነት ጭፍለቃዎች፣ የራስ ገዝ አስተዳደር መናድ፣ የጦር ሜዳ እልቂቶች፣ የንብረት ውድመቶችን…
እያጎነ ትልቁን ምስል ለማደብዘዝ ያለመታከት ሰርቷል፡፡ ለዚህ አይነቱ አፍራሽ ዓላማም እንደማቀጣጠያ የተጠቀመው የ‹‹ታሪክ ተጎጂ›› ወይም ‹‹ሰለባ›› እንደሆኑ ቀን ከሌት የሚሰብካቸው ህዳጣን በጥቂት ልሂቃኖቻቸው ግፊት ያቀነቀኑትን የ‹‹ተረሳን›› አጀንዳ፤ እንዲሁም በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሐረር የተለያዩ
ከተሞች የአፄ ምኒልክ ሠራዊት ያደረጋቸውን የአንድነት ዘመቻዎች ማሳካትን ተከትሎ የተከሰቱ የእርስ በርስ ጭፍጨፋዎች እና የባሕል ተፅእኖዎችን ነው፡፡
ከዚህም ሌላ ሥርዓቱ ለእንዲህ አይነቱ የኑፋቄ ትርክት ያመቸኛል ብሎ የመዘዘው የታሪክ ሰበዝ በጊዜው አማራጭ ያልነበረውን ጠንካራው፣ ደካማውን ጨፍልቆና አስገብሮ አሀዳዊ ሀገር የመገንባት ሂደትን በማንሸዋረርና ፈጠራ በመጨመር ለመሆኑ በርካታ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ‹‹የጊዜ እንጂ የሰው (የብሔር) ጀግና የለውም›› እንዲሉ፤ ኢህአዴግ ጨቋኞቹ-ተጨቋኝ፤ ተጨቋኞቹ ደግሞ ጨቋኝ የሚሆኑበት ጊዜ እንደነበር ትንሽ እንኳ ግንዛቤ ለመውሰድ ጥቂት የታሪክ መዛግብትን ብቻ ማገለባበጥ በቂ መሆኑን በሚገባ ቢያውቅም፤ ታሪካዊ ተጠያቂነቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ አንድ ዘውግ እስከ መወርወር ደፍሯል፡፡ በግልባጩ በዚህ አይነቱ ታግሎ የመጣል ትንቅንቅ ከዛላንበሳ እስከ ቦረና፤ ከቋራ እስከ ኡጋዴን የሚመተረው የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ወሰን መፈጠሩን ሲክድ ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ነውረኛ የፖለቲካ ጨዋታ አመንጪዎቹ አቶ መለስ ዜናዊ እና ጓዶቹ ማዕከላዊ መንግስትን ለመመስረት የሚደረጉ መተጋግሎች ከነፍጥና መስዋዕትነት በቀር የተሻለ አማራጭ እንደሌላቸው፣ በዓለም ታሪክም የእነምኒሊክ የመጀመሪያው አለመሆኑን፤ እንደ አሜሪካንና አውሮፓውያንም ያሉ ታላላቅ ሀገራት በዚህ መሰል የእርስ በእርስ ደም መፋሰስ ውስጥ አልፈው፣ ዛሬ እኛም ጭምር በምኞትና በስደት የምንቀላውጠውን ነፃነትና ብልፅግና የተትረፈረፈበት ሀገር መገንባት መቻላቸውን ጠንቅቀው የማወቃቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፡፡ እናም ሌላ ሌላውን ትተን ከእነአሰቃቂው ጭፍጨፋ ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ጅማሮ የተከፈለውን ውጣ-ውረድ ብናስተውል፣ ሙት ወቃሽ የሆንባቸው በተከታታይ የመጡ ነገሥታትን ውለታ እንዲህ በቀላሉ ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም ብዬ አምናለሁ፡፡
ምዕራፍ ሁለት
ኢህአዴግ ያለፉትን ሁለት አስርታት ያለመንገራገጭ ማለፍ የቻለው በጠብ-መንጃ፣ እንደ አሸን በፈሉ ሰላዮቹ፤ እንዲሁም ከሊቅ እስከ ደቂቅ፤ ከኃይማኖታዊ እስከ ዓለማዊ ማሕበራት ውስጥ በዘረጋው የካድሬ ጥርነፋ ብቻ ሳይሆን፤ ለርዕዮተ-ዓለሙ ሳጋና-ማገር ያደረገው የሀገሪቱን ታሪክ ከልሶ፣ ደልዞ እና ፈጠራ አክሎበት በመስበኩም ጭምር መሆኑ በግላጭ የሚታይ እውነታ ነው፡፡ መቶ እና ሁለት መቶ ዓመት ወደኋላ ተጉዞ የትላንት ስህተቶችን የዛሬ አስመስሎ ከማቅረብም ተሻግሮ፣ በፖለቲካው ቦታ ታሪክን ተክቶ እየሄደበት ያለው ዕርቀት ሰሞኑን ግንባታው አልቆ እስከተመረቀው የአኖሌ መታሰቢያ ሐውልት ያደረሰው መሆኑን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል (ቁልቢ ገብሬኤል አካባቢ እየተሰራ ያለው የጨለንቆ ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልትም በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል)፡፡ ግና፣ ይህ በሰይፍ በተቆረጠ የእንስት ጡት ምስል የተሰራው ሐውልት፣ እንዲነግረን የታሰበውን ያህል ነውረኛ ድርጊቱ ተፈፅሟል፣ አልተፈፀመም የሚለው መከራከሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በዚህ ተጠየቅ የምንፈትሸው ከመቶ ሃያ አራት ዓመታት በኋላ፣ በቀልን የሚሰብክ ሐውልት መገንባቱ ማንን ለመጥቀም ተብሎ ነው? የሚለውን ነውና በዛው ላይ እናተኩራለን፡፡
የርካሹ የፖለቲካ ስልት ጅማሮ የበረሃው ዘመን ቢሆንም፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የታየው የዘውግ አጥር ያላገደው ትብብርና የአትንኩኝ ባይነት ንቅናቄ፣ አገዛዙ በተወሰነ መልኩም ቢሆን፣ ከልዩነት ይልቅ አንድነት ላይ የሚያተኩሩ ጉዳዮችን ለማጉላት እንዲሞክር አስገድዶት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና በ1997 ዓ.ም የተካሄደው ምርጫ ውጤት የፈጠረበት ድንጋጤ ግን ከቀድሞውም በከፋ ሁኔታ ከፋፋይ ፖለቲካውን ወደማጎኑ እንዲመለስ አድርጎታል፡፡ ያ እንደዋዛ የምናነሳው፣ አቶ በረከት ስምኦን ‹‹ናዳ›› ሲል የገለፀው ምርጫ ብዙሃኑን ሕዝብ የልዩነትን ደጃፍ አሻግሮ ከአም-ባገነኑ ሥርዓት በተቃራኒ በአንድነት እንዲቆም ማስቻሉ መንግስትን ከዘላለማዊነት ማማው አውርዶ፣ የሥልጣን ዕድሜውን በቀናት እንዲወሰን እየገፋው ስለመሆኑ በሴራ ከተካኑት የድርጅቱ መሪዎችም ቢሆን የተሰወረ አልነበረም፡፡ እናም ከ‹‹ናዳ›› ጋር ባነፃፀሩት የምርጫ ውጤት ልባቸው የከፋ ቂም በመቋጠሩ መደብዘዝ ጀምሮ የነበረው የ‹‹ከፋፍለህ ግዛ›› ስልታቸው ይበልጥ አቆጥቁጦ፣ የዘውግ ልዩነቱ ወደከፋ ጥላቻ እንዲቀየር ቀን-ተሌሊት እየሰሩ መሆኑን ለማስረገጥ ሰሞኑን መነጋገሪያ ከሆነው የአኖሌ ሐውልት ግንባታ በተጨማሪ ጥቂት ማሳያዎችን አቀርባለሁ፡፡
የመጀመሪያው በምርጫው ማግስት በየዓመቱ ህዳር 29 ‹‹የብሔር ብሔረሰብ ቀን›› ተብሎ በከፍተኛ ወጪ እንዲከበር አዋጅ እስከ ማውጣት መድረሱ ነው፡፡ ምናልባትም የኢህአዴግን አምታች ፕሮፓጋንዳ በፍፁም ልቦና በማመን ይህ ጉዳይ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጥበቅና የልምድ ልውውጥ ለማካበት ታስቦ የተዘጋጀ የሚመስላቸው የዋሃን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ግና፣ ደጋግመን እንደተመለከትነው የበዓሉ ዋነኛ ማድመቂያ ከምዕተ-ዓመት በፊት ‹‹ተፈፀሙ›› የተባሉ አገዛዛዊ በደሎች፣ ዘውግ-ተኮር ጥቃት መስለው እንዲቀርቡ በማድረግ ላይ ያነጠጠረ መሆኑን ነው፡፡ ሁሌ በየክብረ-በዓሉ ሰሞን አንዳንድ ፀጉራቸው ላይ ላባ የሰኩና ቆዳ ያገለደሙ ሰዎች በቴሌዥቪን እየቀረቡ ያለፉት ሥርዓታት ምን ያህል በደል እንዳደረሱባቸው እንባ እየተናነቃቸው ከገለፁ በኋላ፣ ዛሬም ቢሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች በብሔር ብሔረሰቦች ትግል ወደተሸነፈው አገዛዝ ለመመለስ የሚሰሩ መሆናቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ ሕዝብ በንቃት እንዲከላከልና የተገኘውን ድልም ነቅቶ እንዲጠብቅ ሲመክሩ ማድመጣችን ከበዓሉ ጀርባ ያለውን ቴአትር ያጋልጣል ብዬ አምናለሁ፡፡
ሁለተኛው ማሳያ ደግሞ በ2001 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ለሚገኙ ዞኖች በደብዳቤ ከተላለፈ አንድ ትዕዛዝ ጋር ይያያዛል፡፡ የደብዳቤው ፍሬ ሀሳብ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ብሔሮች የየራሳቸውን ታሪክ አጥንተው እንዲያቀርቡ የሚያዝ ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ይሆን? ብለን ስናንሰላስል የምናገኘው ምላሽ፣ ከዚህ ቀደም በበቂ ደረጃም ባይሆን በተለያዩ የታሪክ ምሁራን የተዘጋጁ መዛግብትና የተጠኑ ሰነዶች ተደምስሰው፤ ፖለቲከኞቹ እንደ አዲስ የብሔራቸውን ታሪክ ቀምረው የአንድነቱን መስተጋብር ጨፍልቀው፣ በተናጠል ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ማንነት እንዲኖራቸው ማስቻል የሚል ይሆናል፡፡ ከዚህም አኳያ ይመስለኛል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚገኙ አንዳንድ ዘውጎችን በተመለከተ የሚወጡ ‹‹ጥናቶች›› በፀረ-ነፍጠኛ የተጋድሎ ታሪኮች ዙሪያ ሲዳክሩ የምንታዘበው፡፡ ዳሩ! የሥርዓቱ ተጠቃሚ ፖለቲከኞች የራሳቸውን ታሪክ እንዲጽፉ ሲታዘዙ፣ ለእውነትና ለሕሊና መታመንን መጠበቅ ቂልነት ይመስለኛል (በነገራችን ላይ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮችን በተመለከተ እየቀረበ ያለው የፈጠራ ታሪክ ‹‹ነፍጠኛ›› የሚሉትን ሥርዓት ብቻ የሚኮንን አይደለም፤ ይልቁንም ወላይታውን ከሲዳማ፤ ሀድያን ከአላባ፤ ጉራጌን ከስልጤ፤ ጉርጂን ከጉጂ… የሚያቃቅር እንደሆነ ፍንጮች እየታዩ ነው) በሶስተኛነት የምጠቅሰው በስውር ሴራ ከዝግመተኛ ሞቱ ጋር እንዲፋጠጥ የተደረገውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ክፍልን ነው፡፡ በ1956 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ ደረጃ ሥልጠና መሰጠት የጀመረው ይህ ክፍል፣ ላለፉት አምስት አስርታት ከየትኛውም የምሁራን ጥናት በላይ፣ የሀገሪቱን ታሪክ ተሸክሞ ዛሬ ላይ ያደረሰ ታላቅ ባለውለታ መሆኑ አይዘነጋም፡፡
በአናቱም በርካታ አጨቃጫቂና የተደበቁ ታሪካዊ ጉዳዮችን በማጥናት በማስረጃ አስደግፈው ያቀረቡ እና በዚህ አበርክቶአቸው አለም ሳይቀር ያመሰገናቸው፡- ፕ/ር መርዕድ ወ/አረጋይ፣ ፕ/ር ታደሰ ታምራት፣ ፕ/ር ባሕሩ ዘውዴ፣ ፕ/ር መሀመድ ሀሰን፣ ፕ/ር ሽፈራው በቀለ፣ ፕ/ር ሁሴን አህመድ፣ ፕ/ር ሹመት ሲሳይ፣ ዶ/ር ጉልማ ገመዳ፣ ዶ/ር ዳንኤል አያና፣ ዶ/ር ህዝቅኤል ገቢሳ እና መሰል ጉምቱ ምሁራን ከዚሁ ክፍል የተገኙ እንጂ፤ የሥርዓቱ አገልጋይ እንደሆኑት ከላሽ ‹‹ምሁራን›› (የግንቦት ሃያ ፍሬዎች) አለመሆናቸው ማንም ይመሰክርላቸዋል፡፡ በርግጥ ይህ እውነታ የትምህርት ክፍሉን በአገዛዙ መዓት ዓይን እንዲታይ አድርጎ ለዚህ አብቅቶታል ወደሚል ጠርዝ ቢገፋንም፤ አንጋፋውን ተቋም ስልታዊ በሆነ ጥቃት ከአገልግሎት ውጪ ከመሆን ልንታደገው አለመቻላችን ግን ያስቆጫል፡፡ ከዚህ ድርጊት ጀርባ ግዙፉ መንግስታዊ እጅ መኖሩን የሚያሳየን፤ ትምህርት ክፍሉ የተዘጋበት ምክንያት ‹‹የታሪክ ተማሪዎች ስለሌሉ›› የሚል መሆኑ ነው፡፡
ኧረ ለመሆኑ! ከመቼ ጀምሮ ነው ተማሪ በራሱ ቀጥታ ምርጫ ወደሚፈልገው ‹ዲፓርትመንት› የሚገባው? ይህ ጉዳይ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ የሚተገበር መሆኑ ተዘንግቶ ነውን? አሊያም የታሪክ ትምህርት ክፍልን ከጥቂት ዓመታት በፊት የከፈተው መቀሌ ዩኒቨርስቲ ለ2006 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን 300 (ሶስት መቶ) የዘርፉ ተማሪዎች ሲመደቡለት፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው አንድም አለማግኘቱስ ምን ይሆን የሚነግረን? በጥቅሉ እነዚህ የአደባባይ እውነታዎች በብሔር-ብሔረሰቦች ስም ታሪክን ለመቀልበስ የሚደረጉትን በርካታ ማሳያዎች ሳናካትት ሀገሪቱን ታሪክ የሌላት ለማስመሰል የሚሸረበውን ሴራ በጨረፍታም ቢሆን ያመላክታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ታሪክ ያሌለው ሕዝብ ደግሞ ስለሀገር የማይጨነቅ ደንታቢስ መሆኑ አይቀርም፡፡ እናሳ! ከእንዲህ አይነቱ ትውልድ ማን የሚጠቀም ይመስላችኋል? ሀገር ወይስ ህወሓት…
ምዕራፍ ሶስት
‹‹የአባቶች ስንብት›› የሚለው የዚህ ጽሑፍ ርዕሰ-ሃሳብ የተመረጠው፣ ‹‹ሮም በአንድ ጀንበር አልተገነባችም›› እንዲሉ፤ ለዛሬዋ መልክአ-ኢትዮጵያ እልፍ አእላፍ የዘውግ አጥር ያላገዳቸው አባትና እናቶች ከመሪነት እስከ ተራ ወታደርነት በመሰለፍ የማገልገላቸውን ሀቅ ያሳያል በሚል ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ በቀላል ምሳሌ ከሚያስረዱ ታሪካዊ ገድሎች መካከልም የዐድዋ ድል አንዱ ነውና እስቲ አሰላለፉን በጨረፍታ እንጥቀሰው፡፡ እንደሚታወቀው ዳግማዊ ምኒልክ ዛሬ የሚወቀሱባቸውን በርካታ አካባቢዎች ሀገር በማቅናት ዘመቻ ከማዕከላዊ መንግስቱ ጋር የቀላቀሉት ከዐድዋው ጦርነት በፊት ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ የተቆረጠ ጡት ሐውልት ለመታሰቢያነት በቆመለት አኖሌ የተደረገው ውጊያ ከዐድዋው ድፍን አስር ዓመት የቀደመ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ በአካባቢው የጎሳ መሪዎች ከነበሩት መካከል ሱፋ ኩሶ እና ዳሙ ኩሶ በሰላማዊ መንገድ የንጉሱን አስተዳደር ለመቀላቀል ሲወስኑ፤ የተቀሩት ደግሞ ሀሳቡን ውድቅ በማድረጋቸው ጦርነት መቀስቀሱን በርካታ የታሪክ ድርሳናት አትተዋል፡፡ እንዲሁም ወደ ሌቃ ነቀምት፣ ሌቃ ቀለም፣ ጅማ፣ ሀድያ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ወለጋ፣ ከፋ፣ ሐረር… የተደረጉት ዘመቻዎች በሙሉ ከዐድዋው በፊት ነው፡፡ እዚህ ጋ የሚነሳው ቁልፍ ጥያቄም፡- በዚህ መልኩ ከድሉ በፊት የማዕከላዊ መንግስት አካል የሆኑት የነዚህ አካባቢ ነዋሪዎች በዐድዋው ጦርነት ከምኒሊክ ጎን እንዲሰለፉ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድር ነው? የሚለው ነው፡፡ …መቼም ለዚህ ጥያቄ የህወሓት የታሪክ ባለሙያዎች ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠየቁ ‹እንደ ደርግ ዘመኑ የብሔራዊ ውትድርና በግዳጅ እንዲዘምቱ ስለተደረገ› ብለው መቧለታቸው አይቀርም፡፡ አሊያማ ‹‹ምኒሊክ ኤርትራ ድረስ ዘልቀው ለምን አልገቡም›› በማለት የሚከስሰው ድርጅታቸው፤ ወደ ደቡብ እና ኦሮሚያ ያደረጉትን ዘመቻ ‹‹የቅኝ ግዛት›› ብሎ በድፍረት ሲኮንን፣ ምላሻቸው ዝምታ ባልሆነ ነበር፡፡
ግና፣ እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- በርካታ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች እና የማንነት ጭፍለቃዎች የማንክደው የታሪካችን አካል ቢሆኑም፣ ሀገር በመታደግ ዘመቻው በመሰለፍ ዛሬ ኢትዮጵያችንን-ኢትዮጵያ ያደረጓት ከራስ አሉላ አባነጋ እስከ ራስ ጎበና ዳጬ፤ ከፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ እስከ ፊታውራሪ ገበየሁ፤ ከራስ መኮንን እስከ አሚር አብዱላሂ፤ ከደጃዝማች ባልቻ ሰፎ እስከ ራስ መንገሻ ዮሐንስ… በዐድዋ የፈጸሙት አኩሪ ጀብዱ ነው፡፡ በአናቱም እነዚህን ጀግና አባቶች ለአንድ ዓላማ አንድ ግንባር ያዋላቸው ሀገራዊ አጀንዳ እንጂ፣ ንጉሳዊ ፍቅር ወይም አድርባይነት አለመሆኑ ከማናችንም ባይሰወርም፤ በህወሓት የኑፋቄ ስብከት ተነድተን በአንድነት የሚያቆሙንን መስተጋብሮች አፍርሰን፣ የተናጥል ማንነትን የምንሻ ከሆነ፣ አባቶቻችንን አሰናብተን፣ አዲስ ማንነት ፈጥረን ወደ ገደሉ አፋፍ መገፋታችን የጊዜ ጉዳይ ብቻ ከመሆን የሚታደገው አለመኖሩን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡
በ1928ቱ ዳግማዊ የጣሊያን ወረራም ቢሆን የታየው ሀገር የመታደግ ትብብር እና መነቃቃት፣ በአኖሌ ሐውልት በኩል ሊተላለፍ ከተፈለገው ኢህአዴጋዊ የጥላቻና የበቀል ፖለቲካ የተሻገረ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ከጃጋማ ኬሎ እስከ ዘርአይ ደረስ፤ ከአቡነ ጴጥሮስ እስከ አብረሀ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም፤ ከበላይ ዘለቀ እስከ ራስ ስዩም መንገሻ፤ ከደጃዝማች መሻሻ እስከ ራስ ደስታ ዳምጠው…. እያልን ዘርዝረን የማንዘልቃቸው የሀገር ባለውለታዎች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ሆኖም ሁሉንም መጥቀስ ባይቻልም ወረራውን በመፋለም ታሪካቸውን በደማቁ ቢጽፉም፣ የአበርክቶአቸውን ያህል ያልተዘመረላቸው ሁለት ጀግኖችን ለአብነት አስታውሳለሁ፡፡ አብዲሳ አጋ እና አብቹ፡፡
ሰኔ 7 ቀን 1911 ዓ.ም ወለጋ ነጆ ከተማ የተወለደው አብዲሳ አጋ ተገቢውን ክብር አለማግኘቱ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሰው በጠላት ጦር ተማርኮ ወደ ጣሊያን ሀገር ከተወሰደ በኋላ በናፖሊ ከተማ ከሚገኘው አኞኖ እስር ቤት አንስቶ፣ ቦጆያሊ፣ ካምቦ አንተርናቴ እና ካራ ቤኜር በተባሉ ማጎሪያዎች ከፍተኛ ስቃይ ደርሶበታል፡፡ ይሁንና በእስር ላይ በነበረበት ጊዜያት ካጋጠሙት ሁሉ የሚያስደንቀው ከለታት በአንዱ ቀን፣ ከእስረኛ ጠባቂ ወታደሮች አንዱ በጫማው ሲረግጠው፤ በምላሹ በቡጢ መትቶ መሬት ላይ መጣሉን ተከትሎ፣ በርካታ ዘቦች ተረባርበው ከፍተኛ ድብደባ ካደረሱበት በኋላ፣ ከፎቅ ላይ በጭካኔ ወርውረውት ለጉዳት መዳረጉን አስመልክቶ በአንድ ወቅት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ እንዲህ በማለት የገለፀው ነበር፡-
‹‹እኔስ ማን ነኝና? ኢትዮጵያውያን ለክብራችን ከርሱ የበለጠ ስሜት እንዳለን ገና አልተገነዘበውምና ከእስር ውጪ በነበረ እጄ ትምህርት እንድሰጠው ኢትዮጵያዊነቴ አስገደደኝ፡፡ …በዚያን ጊዜ የደረሰብኝን የዚያን ቁስል ጠባሳ እስከዛሬ ሳይ ሀዘንና ሐሳብ ውስጥም እገባለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ፡፡››
ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሰጠው ሀገር ወዳዱ አብዲሳ አጋ፣ የደቡብ ጣሊያን ተራሮች በአድናቆት የተመለከቱትን ጀብዱ የፈፀመው ከባዕድ ሀገር እስር ቤት ከዩጎዝላቪያዊው መቶ አለቃ ጁሊዮ ኢታችክ ጋር ካመለጠ በኋላ ነበር፡፡ አብዲሳና ጓደኛው በዚህ መልኩ ነፃነታቸውን አውጀው ብቻ ተሸሽገው አልተቀመጡም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ ሀገራት ተወላጆችን አስተባብረው እስር ቤቶችን በመስበር ሐበሾችን ጨምሮ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የዩጎዝላቪያ ሰዎችን እስከማስፈታት አኩሪ ጀግንነት ፈፅመዋል፡፡ እንዲሁም የቃል ኪዳኑ ጦር የሮማ መንግስትን እስከተቆጣጠረበት ጊዜ ድረስ፣ ለሁለት ዓመታት ያህል በጣሊያን ተራሮች ላይ ጥቂት የማይባሉ ሀገራት ዜጐችን እየመራ ከፋሽስት ወታደሮች ጋር በአደረጋቸው በርካታ ውጊያዎች ላይ እጅግ በጣም አስገራሚ ጀብድዎችን አከናውኗል፡፡ ለዚህ ገድሉም ከቃል ኪዳኑ የጦር አዛዦች የአድናቆት እና የምስጋና ሰርተፍኬቶች ተበርክተውለታል፡፡ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀም በኋላ ዜግነቱን እንዲቀይር እንግሊዛውያን ላቀረቡለት ጥያቄ እንደሚከተለው መመለሱን ከላይ በጠቀስኩት ቃለ-መጠይቅ ላይ መናገሩ ይታወሳል፡-‹‹የሀገር ፍቅርና የራስ ጥቅም ምን እንደሆነ ስለማውቅ ጥያቄውን አልተቀበልኩም፡፡ ወደሀገሬም ገባሁ፡፡››
እነሆም ‹‹ብሶት›› የወለደው ኢህአዴግ፣ አብዲሳ ዋጋ የከፈለላትን ኢትዮጵያ፣ በአንድ ዘውግ የበላይነት የተመሰረተች አድርጎ በመቀስቀስ ለእርስ በእርስ ፍጅት ጡንቻችንን እንድናፍታታ እያመቻቸ ነው (ይህ የጀግናው ታሪክ ‹‹ተራሮቹን ያንቀጠቀጠ ቅፅ 5›› መጽሐፍ ላይ በስፋት የቀረበ መሆኑን አስታውሳለሁ)፡፡
ሌላኛው የዛን ዘመን ያልተዘመረለት ጀግና የሰላሌው አቢቹ ነው፡፡ የአቢቹ ታላቅ ገድል ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የተሰማው፣ አዶልፍ ፓርለሳክ በተባለ የቼክ ሪፖብሊክ ተወላጅ ተጽፎ፣ በተጫነ ጆበሬ መኮንን ‹‹የሃበሻ ጀብዱ›› በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ በተተረጎመው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ በሰላሌ የወረጃርሶ ፊት-አውራሪ የነበሩ ሁለት ታላላቅ ወንድሞቹን ተከትሎ በ16 ዓመቱ ሀገሩን ከወራሪ ለመከላከል ስለዘመተው አቢቹ፣ ጻሐፊው ‹‹እነሆ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ፈረንሳይ ሀገር ለከፍተኛ ትምህርት ተጓዥ ነበር›› ሲል ገልፆአል፡፡ ጦርነቱ ከተጀመረም በኋላ አንደኛው ወንድሙ በክብር ሲሰዋ፤ ሌላኛው ደግሞ የደረሰበት በመጥፋቱ ትንሹ ልጅ ከዋናው ሠራዊት ተገንጥሎ፣ ወደ 200 የሚጠጉ ትዳር ያልመሰረቱ ጎበዝ ተዋጊዎችን ብቻ አስከትሎ ጠላትን በመብረቃዊ ፍጥነት መድረሻ ማሳጣቱ ተተርኳል፡፡ በወቅቱ ንጉሠ ነገሥቱ የሰላሙ መንገድ ገና አልተቋጨም በሚል የኢትዮጵያ ጦር ከመከላከል በቀር እንዳያጠቃ ትዕዛዝ አስተላልፈው ስለነበር፣ አቢቹ የሚፈፅማቸው ጀብዶችን አቁሞ ወደእናት ጦሩ እንዲመለስ ግፊት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም፡፡ በዚህም ንዴት የመንግስት ጦር እንዲዘምትበት ስለመወሰናቸው የሰላሌው ደጃዝማች አበራ መልክተኛ ልኮ ስላሳወቀው፣ ድንገት አቢቹ ወደ ጦሩ ሠፈር በመምጣት ከአቋሙ ፍንክች እንደማይል መግለፁን መጽሐፉ ይተርክልናል፡-
‹‹ደጃዝማች፣ ገና ከሰላሌ ስንነሳ ታማኝነቴን በምኒሊክ ስም ቃል የገባሁት ላንተ እንጂ ለሽማግሌዎቹ ወይም ለንጉሡ አይደለም፡፡ እኔ ንጉሥ አይደለሁም፤ ተራ ወታደር እንጂ፡፡ እና እኔ ሁለት ሶስት ወር ደሴ ተጎልቼ ጣሊያኖች እጄን እስኪይዙኝ አልጠብቅም፡፡ ላንተ ግን አሁንም በምኒሊክ ስም፣ በምኒሊክ አምላክ በድጋሚ ቃሌን እሰጣለሁ፡፡ …ተመለስ ላልከው ግን፣ የት ነው የምመለሰው? ምንስ መመለሻ ቤት አለኝና? እዚህም እዚያም እሳት እየነደደ እንዴት ቁጭ ልበል? …የሀገሬ ታማኝ ወታደር እንደሆንኩ አስረዳልኝ፡፡›› (234)
ከዚህ በኋላም ጦሩን፡- በሀብቶም የሚመራ የሀማሴን (የኤርትራ) ልጆች ጦር፣ በተስፋፅዮን የሚመራ የትግራይ ልጆች ጦር፣ በጋሹ የሚመራ የጎጃም ልጆች ጦር እና በወርቁ የሚመራ የሰላሌ ልጆች ጦር በማለት ከፋፍሎና በዕዝ አዋቅሮ ሲያበቃ፤ ጠላት ካምፕ ድረስ ዘልቆ በመግባት አያሌ ጀብዶችን አከናውኗል፡፡ መላው ዘማች ሠራዊት ከእነ አዛዡ ‹‹የልጁ ጦር›› እያለ አድናቆቱን ሲገልፅለት፤ ንጉሡ ራሳቸውም ‹‹ይቺ አንድ ፍሬ ደጃዝማች ከኛም በላይ ትልቅ ጀብዱ እየሰራች እንደሆነ እንሰማለን›› (288) እስከማለት ተገድደዋል፡፡ በዘመቻው ላይ የተሳተፉ አዝማሪዎችም ከዋናው ባለታሪክ ተገንጥሎ ዛሬም ድረስ ተወዳጅ መሆን በቻለች ዜማ እንደሚከተለው ያወድሱት እንደነበር የቼኩ ሰው ነግሮናል፡-
‹‹አቢቹ ደራ ደራ
አቢቹ ደራ ደራ››
የመጽሐፉ ደራሲ በዛው በጦር ሜዳ አንድ የከንባታ ልጅ አጫወተኝ ብሎ ያሰፈረው ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-

‹‹የከንባታው ጦር በጣሊያን ሠራዊት ተከቦ፣ መውጫው ጠፍቶት፣ አጥፍተህ ጥፋ አይነት ውጊያ ላይ እያለ ከየት መጡ ሳይባል እነዚያ የአቢቹ ፈጥኖ ደራሽ ደቦል አንበሶች ከጣሊያኑ ጦር ብብት ውስጥ ገብተው ሲኮረኩሩት፣ ደመሰስኩ ብሎ የሚኩራራው የጣሊያኑ ጦር ሳያስብ አደጋ ደርሶበትና በተራው ሲያፈገፍግ የከንባታውን ጦር ከዚያ ካለቀለት ውጊያ ውስጥ እነአቢቹ መንጥቀው አወጡት፡፡››
 (289-290)
በማይጨው ጦርነትም ቢሆን በምኒሊክ ስም ምለውና ፎክረው ለሀገር አንድነት ከወደቁ ስም የለሽ ጀግኖቻችን መካከል የሰላሌ ተወላጆችን በተመለከተ ከመጽሐፉ ላይ አንድ ሃሳብ ልጥቀስ፡-
‹‹በዚህ ጦርነት ሶስት አራተኛው የሰላሌዎቹ አሉ የሚባሉት ቆራጦች፣ ጀግኖቹና ደፋሮቹ ልጆች ከማይጨው የጦር ሜዳ ከአምባ በሆራ አልተመለሱም፡፡ እስከ መጨረሻው ድረስ ከጠላት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው በየምሽጉ ወድቀዋል፡፡›› (296)
እነሆም ላለፉት ሁለት አስርታት ከራስ ጎበናና ባልቻ ሶፎ፤ ከአብዲሳና አቢቹ ኢትዮጵያዊነት ይልቅ የዘውግ ማንነት ቅድሚያ ተሰጥቶት፣ አባቶችን ከታሪክ ባህረ-መዝገብ የማሰናበት ተልዕኮው ከጫፍ እየደረሰ ነው፡፡ በርግጥም ይህች ሀገር ከሰቅጣጭ ሞት ፊት ደጋግማ በቆመችበት ጊዜ ሁሉ፣ በመስዋዕትነት የታደጓት እልፍ አእላፍ ኢትዮጵያውያን አባቶች ቢሆኑም፣ ዛሬ ልጆቻቸው በማንነት ብያኔ እንዲነጣጠሉ እየተገፉ ስለመሆኑ በድፍረት መናገር እችላለሁ፡፡ ሌላው ቀርቶ አንዳንድ የሥርዓቱ ፅንፈኛ ተቃዋሚዎች የህወሓት መጠቀሚያ የሆነው ኦህዴድን ያህል፣ በዚህን መሰሉ የኑፋቄ ታሪክ ተወስውሰው ጥላቻን ሲሰብኩ፤ ልዩነትን ሲቀሰቅሱ መመልከቱ ምን ያህል ከአባቶቻችን እንደተነጠልን ያረዳናል ብዬ አስባለሁ፡፡
ዘጽአት…
(ከ2 ሺህ ዓመት በፊት ቀይ ባሕርን ተሻግረው፣ ሞትን ተራምደው፤ ከግብፃውያን የባርነት ቀንበር ነፃ የወጡ ዕብራውያንን በተመለከተ ቅዱስ መጽሐፍ በ‹‹ኦሪት ዘጽአት›› ላይ በስፋት ያትታል)
ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያችን፣ የአገዛዙን የሥልጣን ዕድሜ ለማረዘም ሆን ተብሎ ዘውግን ሰበብ አድርጎ ለተቀነባበረው የመበታተን አደጋ ተጋልጣለች፡፡ እናም ይህንን ሀገሪቷን በደም ውቅያኖስ የማጥለቅለቅ አቅም ያለው ከባድ ችግር ለማምከን፣ በቅድሚያ ከተጫነብን የታሪክ ሒሳብ ማወራረድ መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ልንላቀቅ ይገባል፡፡ ከመቶ ዓመት በፊት የአንድ ሀገር ሕዝብን በማዕከላዊ መንግስት ሥር ወደ አንድነት ለማምጣት የተደረገውን ታላቅ ተጋድሎ አኮስሶ፣ ተያይዘው የተከሰቱ ዘመኑና ነባራዊ ሁኔታዎች የፈጠሯቸው ስህተቶችን ነጥሎ ማስጮሁ፣ ‹‹ዜግነት-ኢትዮጵያዊ›› በሚል ፓስፖርት ከሀገር ሀገር የሚዘዋወሩ የግንባሩንም ሆነ የተቃዋሚውን ጎራ ልሂቃን የማንነት ቀውስ ከትቶ ከንቱ እንዳያስቀራቸው እሰጋለሁ፡፡ በአናቱም የህወሓት፣ የኦሮምኛና አማርኛ ቋንቋ ክንፍ ሆነው የሚያገለግሉት ኦህዴድና ብአዴንም በትውልድ ፊት በ‹አድርባይነት› የሚያስከስስ ታሪክ ተጋርተው እስከመጨረሻው በሕዝባዊ ማዕበል እስኪጠረጉ ድረስ መጓዛቸው በምንም መልኩ ስርየት የማያገኝ ጥፋት እንደሆነ በአፅንኦት ላሳስባቸው እፈልጋለሁ፡፡
ስለሆነም ከሀገሪቱ ቀጣይ ሕልውና ፊት የተጋረጠውን ይህን የመበታትን አደጋን ያዘለ የእርስ በእርስ ግጭትን ተሻግሮ፣ የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለማቆየት ብሎም ልጆቿ በዕኩልነት ይኖሩባት ዘንድ ለማመቻቸት፣ ዘመኑን ካለፈ ታሪክ ይልቅ ጊዜው በሚፈቅደው የሠለጠነ ፖለቲካ መዋጀት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ በይበልጥ ወደ ፍጥጫው እየተገፉ ያሉት ሰፊ ቁጥር ያላቸው የኦሮምኛና አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከአኖሌ መታሰቢያም ሆነ፤ በቅርቡ በተማሪዎች የስፖርት ውድድር ላይ በባሕር ዳር ስታዲዮም ከተሰማው ዘውግ-ተኮር ነውረኛ ቅስቀሳ ጀርባ ያደፈጠውን ዕኩይ የፖለቲከኞች ሴራ ለመበጣጠስ ፊት-አውራሪ መሆን ይኖርባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ የተቀደሰ ተግባር ከትውልድና ከታሪክ ተወቃሽነት ብቻ ሳይሆን ከዘገየ ፀፀትና መብከንከንም መታደጉ በግልፅ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲና ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች›› በሚል ርዕስ ባለፈው ዓመት ባሳተመው መጽሐፍ ላይ በግንባር ቀድምትነት ኦሮምኛ፣ አማርኛ እና ትግርኛ ተናጋሪዎች ሀገሪቱን ከአይቀሬው ሞት ይታደጉ ዘንድ በማለት ያሰፈረውን ለዘጽአት ሃሳብ ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ እንደሚከተለው እጠቅሳለሁ፡-
‹‹በተቃዋሚው ጎራ፣ ብዙ ሲንቀሳቀስ የማላየው የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖለቲካ ነው፡፡ የሁለቱም ልሂቃን ፖለቲካ በዋናነት በሁለት ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጓተት ወደ መሐል መጥቶ የጋራ ዲሞክራቲክ አጀንዳ መቅረጽ አልተቻለውም፡፡ ብዙዎቹ ሂሳብ የመወራረድ ፖለቲካን የዛሬ 30 እና 40 ዓመታት ብቻ ሳይሆን፤ የዛሬ 130 እና 140 ዓመታት በፊት የነበረውም ጭምር እንተሳሰብ የሚሉ ይመስሉኛል፡፡ የኦሮሞ ልሂቃን ዋናው ችግራቸው የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ለመቅረጽ ከመጣር ይልቅ ለብቻ የሚደረገው ትግልን የመንግስተ-ሰማያት አስተማማኝ መንገድ አድርገው ማምለካቸው ነው፡፡ የአማራው ልሂቃን በሽታቸው በዋናነት በአማራ ልሂቅ የተፈጠረች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደዛው ትቀጥል ነው፡፡ እምነታቸው መቀጠልም ትችላለች ነው፡፡ …በመጽሐፌ መደምደሚያ ላይ ለታሪክም ለሕዝብም አስቀምጬ ማብቃት የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ፣ አብዛኛው የትግራይ ልሂቃን ‹ሥልጣን ወይም ሞት› ብለው ሥልጣን ላይ የሙጥኝ እስካሉ ድረስ፤ አብዛኛው የአማራ ልሂቃን በአፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነት መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፤ ብዙሃኑ የኦሮሞ ልሂቅ ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ የምትወጣ አይመስለኝም፡፡›› (ገፅ 261፣ 262 እና 263)
እንደ ዶ/ር መረራ ያሉ ልሂቃን ሀገርና ህዝብን ለመታደግም ሆነ አባቶቻችንን አሰናብተን ወደ እልቂት እንዳናመራ ለሚያራምዱት ከታሪክ ጥላቻ የፀዳ ሃሳብ ባርኔጣዬን ከፍ አድርጌ አክብሮቴን እገልፃለሁ፡፡ ይህንን አጀንዳም በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ጃ ያስተሰርያል›› ዜማ ጥቂት ስንኞች እቋጨዋለሁ፡፡
‹‹ዘጽአት ለኢትዮጵያ ወደ ተስፋ ጉዞ
ባሕሩን የሚያሻግር አንድ ሙሴ ይዞ
ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጵ ያ ትንሳኤ
በአንድነት ከገባን የፍቅር ሱባኤ!››
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የእስር እርምጃ እንዳሣሰበው ሲ.ፒ.ጄ ገለጸ።

April 29/2014

ሚያዚያ ፳፩ (ሃያአንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለማቀፉ የጋሴጠኞች ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ)  ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን በ9 ጸሀፍያን ላይ የወሰደው የእስር እርምጃ፤ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ከተቃጡ የከፉ እርምጃዎች አንዱ ነው ብሏል።

“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን መግለጽን እንደወንጀል እየቆጠሩት ነው” በማለት ነው -የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪቃ ወኪል-ቶም ሩድስ-እርምጃውን የኮነኑት።
እሁድ ዕለት የመንግስት አቃቤ ህግ በ አዲስ ጉዳይ ዋና አዘጋጅ በ አስማማው ሀይለጊዮርጊስ፣ በፍሪላንስ ጋዜጠኞቹ በተስፋለም ወልደየስ እና በ ኤዶም ካሣዬ፣ እንዲሁም በጦማርያኑ በ አቤል ዋቤላ፣በ አጥናፍ ብርሀኔ፣በማህሌት ፋንታሁን፣ በዘላለም ክብረት እና በበፈቃዱ ሀይሉ ላይ  ከውጪ ድርጅቶች ጋር ይሠራሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀምም በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ይንቀሳቀሳሉ.. የሚል ክስ እንደመሰረተባቸው ሲፒጄ አውስቷል።
ተስፋለም፣አስማማውና ዘላለም ለፊታችን ሚያዚያ 28 ቀሪዎቹ ደግሞ ለሚያዚያ 29 እንደተቀጠሩ ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የደረሰውን መረጃ ዋቢ አድርጎ የጠቀሰው ሲፒጄ፤ በታሳሪዎቹ ላይ እስካሁን መደበኛ ክስ እንዳልተመሰረተ ጠቁሟል።
ሲፒጄ በመግለጫው-ፀሀፊዎቹ ዞን ዘጠኝ ተብሎ የሚጠራ የገለልተኛ አክቲቪስቶች ስብስብ አባል ሆነው የተለያዩ ዜናዎችንና ጽሑፎችን ይጽፉ እንደነበር  አመልክቷል።
“ዞን ሰጠኝ የተሰኘው ስያሜ ከቃሊቲ የተገኘ  መሆኑና  የጸሐፊዎቹ  መሪ ቃል፦”ስለሚያገባን እንጦምራለን” የሚል  መሆኑ በሲፒጄ መግለጫ ተመልክቷል።
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከደህንነቶች በሚደርስባቸው ወከባ ምክንያት ላለፉት ሰባት ወራት ዘግተውት የቆዩትን የፌስቡክ ገፃቸውን ዳግም በከፈቱ ማግስት መሆኑን እንደተረዳም የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ተቋሙ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ፦”የታሰሩት ጋዜጠኞች አይደሉም፤ እስሩ ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር የተገናኘ አይደለም። ከከባድ ወንጀል ጋር የተገናኘ ነው” ማለታቸውን ሲ.ፒ.ጄ ጠቁሟል።
“በጋዜጠኝነት ወይም ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ የቃጣነው በትር የለም። ሆኖም ማንም ቢሆን ሙያውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ለመፈፀም ሲሞክር በህግ ይጠየቃል” ሲሉም አክለዋል-አቶ ጌታቸው ረዳ።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደለየለት ፈላጪ ቆራጭ አገዛዝ  ማዘንበላቸውን እንዲገቱና በሀገሪቱ  ነፃ ሀሳቦች ይንሸራሸሩ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል-ሚስተር ቶም ሩድስ።
የታሰሩት 9ኙም ጸሀፊዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ድርጅቶችም የ ኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጦማርያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የወሰዱትን እርምጃ በማውገዝ ፤ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡት የ አሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ  እስረኞቹን እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
የተለያዩ ዓለማቀፍ የሚዲያ ተቋማትም ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በ9ኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደውን የማሰር እርምጃ ሽፋን ሰጥተውታል።
ከሚዲያ ተቋማቱ መካከል ኤ.ቢ.ሲ ኒውስ፣ ሲ ኤን.ኤን፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ሬውተርስ፣ እና አልጀዚራ ይገኙበታል።
እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በጉብኝታቸው ስለታሰሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አጠንክረው እንደተናገሩ  የኒውዮርክ ታይምሱ ታዋቂ አምደኛ  ኒኮላስ ክሪስቶች ለሰጣቸው አስተያዬት፤ “ በጣም  ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ዩናይትድስቴትስ  በመላው ዓለም ላይ የፕሬስ ነፃነትን በመደገፍና ከጥቃት በመከላከል ባላት ጠንካራ አቋም ትቆያለች” በማለት ምላሽ ሰጥተውታል።

ሠማያዊ ፓርቲ የነፃነት ትግልና የሃበሻ ጀብዱ

April 29, 2014

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
በቅርቡ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ በተደረገ የሩጫ ዝግጅት ወቅት የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆችነ ነን ያሉ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች “አትለያዩን! አትከፋፍሉን! ነፃነት እንሻለን! ለድሃው ይታሰብለት! ኑሮ ከበደን! ውሃ ጠማን! መብራት ናፈቀን!” በማለት በጣም ሰብዓዊና እናታዊ ጥሪ ጮክ ብለው አሰምተው ነበር። ይህም መልካም ድርጊታቸው ለፍትህና ለአንድነት የሚደረግ ህዝባዊ ጥሪ በሚያስበርግጋቸው የወያኔ ባለስልጣናት ሁከት ፈጠራ ተብሎ ተወነጀሉ። ፕሮፌሰር አልማርያም በተቆጣው ብዕራቸው

… ያገሬ ወይዛዝርቶች በምህረት አልባ ጨካኞች ሲንገላቱና ሲወገሩ ከዳር ቆሜ ማየትን ህሊናዬ ፈጽሞ አይፈቅድልኝም። ይልቁንም የእንግልታቸው ምክንያት ሰብዓዊ በሆነው መብታቸው ድምፃቸውን ስላሰሙ በመሆኑ የነሱና የመሰሎቻቸውን ጥሪ በዚህም ሳቢያ የሚደርስባቸውን አበሳ ሁሉ ለአለም አሳውቅ ዘንድ ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ…

ብለው ነበር። ከርሳቸው ድምጽ ጋር በማበር የሚያስተጋቡ ድምጾች ይኖሩ ዘንድ እውነት ነውና የኔንም ድርሻ እነሆ እጮሃለሁ። ጩሀቴም ቀደም ሲል በግፍ ለታጎሩ የህሊና እስረኞችና ሰሞኑን ለታፈሱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች አንዲሁም ለጎበዞቹ የዞን ዘጠኝ የሕዝብ አፈቀላጤዎችም (ብሎገሮችም) ነጻነት ያለኝ ጽኑ ፍላጎት መገለጫ ነው።
ሁከት ማለት የሌሎችን ሰላም ማደፍረስ፥ አምባጓሮና ጸብ ማንሳትና ማነሳሳት፥ የንብረት ጥፋትና በሰዎች ላይ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ማስከተል ነው። እኒህ ወጣት ሴቶች ግን ከዚህ በተቃራኒው የተንገላቱት ሰላም አንዳይደፈርስና ህዝብ እንዳይጎዳ በስልጣን ላይ ያሉት መንግስታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ሰላማዊ ጥሪ ነበር ያቀረቡት። የሀሰት ፕሮፖጋንዳው ሰለባ ያልሆነ በሙሉ ወጣቶቹ በአንድነትና በፍትህ የጸናች ሀገር ለመረከብ ከዚህ የበለጠ ቢያደርጉም ተገቢ ነው የሚል ይመስለኛል። የነርሱ አሳሪዎች በነርሱ እድሜ ጠመንጃ አንስተው መጥፎ ነው ብለው የፈረጁትን መንግስት ለመዋጋት ጫካ መግባታቸውን አለመርሳት ብቻ ሳይሆን እንደትልቅ ገድል በየመድረኩና በየመጽሀፉ ሲናገሩና ሲያስነግሩ እንሰማለን። ታዲያ የዛሬው ትውልድ ያውም እንደነሱ ሰው ለመግደል ጠብመንጃ ሳያነሱ ፍትህ አይጉዋደል ብለው በሰላም መጠየቃቸው እንዴት መጥፎ ሁኖ ነው ለእስርና እንግልት የሚዳርጋቸው? ማሰርንና አፈናን እንደ የስልጣን ዘመን ማራዘሚያ አማራጭ አድርጎ መውሰድ ከሚያስብ አእምሮ ሳይሆን በፍርሃት ከተዋጠና ለውጥ አይቀሬ መሆኑን መቀበል ካቃተው ደካማ ጭንቅላት የሚመጣ ነው። በአንጻሩም ነገ የነርሱ የሆነው ወጣቶች በፍርሀት ተገንዘው አረመኔዎች ሀገራቸውንና ተስፋቸውን ሲያጠፉባቸው በዝምታ ሊያዩ አይቻላቸውም።
ለዚህም ነው በወጣቶቹ የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎች ላይ ያለኝን ጽኑ እምነት መግለጽ የምሻው። የወጣቶች መነሳሳት ለሁሉም ወገን ብርታትን የሚሰጥ ነው። የለገመ፣ የሰነፈና ተስፋ የቆረጠ ወጣት የሞላበት ሃገር ሕዝብ መቃብር አፋፍ እንደቆመ ለቀስተኛ ነው። ለቀስተኛ መቼም ቢሆን ስለሚቀብረው ሰው ከሚሰማው ሀዘን ባሻገር እርሱም ነገ ሙዋች መሆኑን እያሰበ ሙዋቹን አፈር እራሱን ትካዜ አልብሶ ተስፋን ሳይሆን ፍርሀትን ሰንቆ ይመለሳል። ሀገር ተስፋ በቆረጠና ሽንፈትን በጸጋ በተቀበለ ወጣት ከተሞላች ቀብርዋ ተቃረበ ማለት ነው። ስለዚህ የሀገራችን ወጣቶች ተስፋ የሰነቁ፣ የበረቱና በእውቀትና ስነምግባር የታነጹ እንዲሆኑ ሁላችንም የየአቅማችንን ማድረግ ይኖርብናል። የሀገራችን ሰዎች “እናት የሞተች ቀን በሀገር ይለቀሳል… ወንድም የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል…. ሀገር የሞተ እንደሁ ወዴት ይደረሳል?” ይሉ የነበረው ያለምክንያት አልነበረም። እናም የዛሬን ወጣቶች ድርጊት ከቀድሞው የሃበሻ ጀብዱ (የሀበሻ ጀብዱ ከሚለው መጽሀፍ) ጋር ጣምራ ቅኝት ላደርግበትና ወጣቶችን ላደንቅበት መርጫለሁ።
ስለምን የሃበሻ ጀብዱን እንደመረጥኩ ግን እመለስበታለሁ። የጣልያኑም ወረራ ሆነ የባንዳ መራሹ ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ የሚበጅ አይደለምና ሀገሪቱን ወደተሻለ መንገድ ለመውሰድ የሚደርገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ነን ለሚሉ ሁሉ የህልውናና የነፃነት ፍልሚያ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ይገባል። የሠማያዊ ፓርቲና የትግራይ ተገንጣይ ነን የሚሉትን አቅም በመፈተሽ መንደርደርያውን ማጎልበት ያስፈልግ ይሆናል። ይህም መድፍ ተኳሽና በአውሮፕላን መርዝ የሚርጭን የግራዚያኒን ጦርና ነጠላ ለባሽ ባለጎራዴ እግረኛን እነደማወዳደር ማለት ነው። ምንና ምን ታወዳድራለህ የሚሉ እንዲህ ብለው ሊሞግቱኝ ይችላሉ።
ሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች፣ ተገንጣዮቹ እድሜ ጠገቦች ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ባዶ ኪስ፣ መንግስት ነን የሚሉት ደግሞ የሀገሪቱን ሃብት የግላቸው ያደርጉ ዲታዎች አዎ ምንና ምን? ሰማያዊ ፓርቲ ብእርና ወረቀት ፣ ወያኔዎች ባለታንክ፣ አውሮፕላን መድፍና መትረየስ ታጣቂዎች። እናም የማይቻል የሚመስለውን ይቻላል የሚሉ ወጣቶችና ሰው እንደዘበት መፍጨት የማይገዳቸው ‘ተራራ አንቀጥቃጮች’ እንደምን አድርገው መጋጠም ይችላሉ? በዚህ አይነት ንፅፅር ተስፋ የቆረጡት ወገኖች “ይቻላል!” ብለው የተነሳሱትን ወጣቶች “እንዲያው አርፈው ቢቀመጡ ነው የሚሻለው። በአጉል ወኔ ተነሳስተው ማለቅ ብቻ ሳይሆን እኛንም ያስጨርሳሉ። ጊዜው አሁን አይደለም” የሚል ምክር ቢጤ ሲሰጡ ይሰማሉ። የፖለቲካ መሪና ጠቢብ ነን የሚሉም “ለአሁኑ ወያኔ ስልጣን ላይ ቢቆይ ይሻላል” ሲሉ ተደምጠዋል አሉ።
እውነትም ብቸኛ ሃይል መመዘኛ ሁኖ የሚታየው የጠብመንጃው ቁጥርና የመግደል አቅም ከሆነ ያስፈራል። እውነታው ግን የሀይል ምንጭ የጠብመንጃና የጦር ጋጋታ ብቻ አይደለም። ከጠብመንጃ በላይ የዘላቂ ሀይል መሰረቱና የመጨረሻ ድል አጎናጻፊው እውነትና ፍትሀዊ ምክንያት ነውና።
ጊዜው ዛሬ አይደለም የሚሉትም መካሪዎች ጊዜው መቼ እንደሚመጣ ቢያሳውቁንም ደግ ነበር። ኬይንስ የሚባለው የምጣኔ ሀብት ምሁር እንዳለው “ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ሁላችንም ሙዋች ነን።” ስለዚህም የዛሬውን ነጻነታችንን ተነፍገን በነገ ተስፋ ብቻ ተሸንግለን ግፍን በፀጋ እንድንቀበል መመከራችን ደግም አይደለም። ነፃነት ተነፍጎ፣ ፍትህን አጥቶ፣ በደልን ተሸክሞ ተስፋ ቢስም ሆኖ መኖር አይቻልም። በደል ሲበዛ በቃኝ ማለት የሰው ልጅ ትክክለኛ ባህርይ ነው። ቢሆንም በርካቶች “እግዜር ያመጣውን እግዜር እስኪመልሰው” ሲሉ ይደመጣል። እግዜር የሌለውን አመል አውጥቶ ጥላቻ ቢለማመድ እንኳን እነዚህ አረመኔ ወንበዴዎች ለዚህን ያክል ጊዜ አናታችን ላይ ሁነው እንዲጨፈጭፉን አያዝብንም።
ፍትህና ነጻነት የሚገኘው በፀሎትና ልመና ብቻ ቢሆንማ ኖሮ አውሮፓውያን ሰሜን አሜሪካ ዘልቀው ሀገሬውን በበሽታና ረሀብ ሲጨፈጭፉት፣ እግዜሩ ዝም አይልም ነበር። አዎን እሱ መሬት ወርዶ ፍርድ የሚሰጥ ቢሆን አውሮፓውያን ጥቁር አፍሪካን ባርያ አድርገው በገዛ ምድሩ ላይ የግፍ ግፍ እየፈጸሙበት የእግዜርን ስም እየጠሩ መስቀልና መጽሀፍ ቅዱስ ይዘው ሲያስገበሩት ዝም ባላለ ነበር። ስለዚህም ነው ለነጻነት ሲባል ታንኩንም መትረየሱንም እንደነ አቡነ ጴጥሮስ መጋፈጥ የግድ የሚሆነው። ጸሎት ለብርታት ጥሩ ነውና ባይሆን እመብርሃን ለልጅሽ በደሌን እንደኔ ሆነሽ ንገሪልኝ ማለት፣ አላህንም ልጆችህ መከራችንን ከትከሻችን አሽቀንጥረን እንጥል ዘንድ ጉልበትና ብልሃት ጀባ በለን እያሉ መለማመን ጥሩ የሚሆነው። ግን ለብቻው በቂ አይደለምና ወጣቶች እንደ የግል ሀይማኖታቸው እያመለኩ እንደ እምነታቸው በጋራ ለነፃነት መታገላቸው የሚያበረታታንም ለዚህ ነው።
አሁን የሃበሻ ጀብዱን ለምን እንደጻፍኩ ላስረዳ አዎን የጣልያን ጀነራሎችን ሹምባሾችና አስካሪዎችን አስታውሼ መሆን አለበት። ታንኩንም፣ አውሮፕላኑንም መድፉንም መትረየሱንም ጭምር። የባንዳ ውርንጭሎችን፣ ልጆችና የልጅ ልጆችንም እንዲሁ አስቤያቸው ነው።
እነዚህ ነጠላ ላባሽ ባዶ እግር ተጓዥ ኢትዮጵያውያን በጣም የሚገርሙ ነበሩ። ኩራታቸውና በራሳቸው የመተማመን አቅማቸው ለውድድር አይመችም። እንደ ሀይል አሰላለፍ ቢሆን ከጣልያን ጋር ደፍሮ መጋጠም ከሞኝነት አይቆጠርም ትላላችሁ? ካላቸው የመሳርያና የወታደር ብዛት፣ ሰልጥኛለሁ የሚለው የነጩ ዓለም ያለው ጉልበትና ስልጣኔን የሚያውቅ ሰው በባዶ እግሩ ታንክ መግጠም ሞኝነት ነው ቢባል ማመን ብዙም ላይከብድ ይችላል። ለነርሱ ማን አልተንበረከከምና? ማንስ ቅኝ ግዛት አልሆነምና! ግን ኢትዮጵያ ምድር ላይ ታንክ በጎራዴ ድል ሆነ። አንዴ ቢሆን እድል እንለዋለን ሁለቴ ሶስቴም ሆነ። ሁለቴም ሶስቴም ነጠላ ለባሽ በባዶ እግር የሚጓዝ እግረኛና ቆመህ ጠብቀኝ ምንሽር ባለአውሮፕላንና ባለታንኩን ድል ነሱት። ግን ይህ አሸናፊነት እውን የሆነው ትክክለኛ ስነልቦና፣ አልገዛም አልንበረከክም የሚል እምቢ ባይነት ስለነበረ ነው። ለነፃነቱ ቀናዒ መሆን ከዚያም በላይ ወንድም የወንድሙ ተበቃይ መሆኑን ነበር። አይዞህ ባይና አጋር አብራ በረሃ ለበረሃ የምትጓዝ ጓድም ነበረችው። እሷን ማሳፈር ለባርነትም አሳልፎ ከመስጠት ሞቱን ይመኝ ስለነበር ነው። ሴቲቱም ብትሆን እርሱ ለነጻነቱ ሞቶ ግን የርሱን የጀግናውን ስም ይዘው ትውልድ የሚቀጥሉት ልጆቻቸው በነፃነት ቢኖሩ ምርጫዋ ስለነበረ ነው። የሴቶቹ ጀግንነትና ድፍረት ለወንዶቹም መነሳሳትና መበረታት ምክንያት ይሆናቸው ስለነበረ ነው የሚል ሃሳብን ነበር የሃበሻ ጀብዱን የጻፈው ፈረንጅ አዶልፍ ፓርለሳክ የዘገበው። “እነዚህ ነጠላ ለባሽ እግረኞች ይላል አዶልፍ ፓርለሳክ በጠላት መትረየስ አስሩ ሲወድቁ ሃያው ወደፊት ይገፋሉ ሃያው ሲወድቁ ሃምሳው ወደፊት ይገፋሉ ለሞት እየተጋፉ ወደፊት ይገሰግሳሉ እናም ያሸንፋሉ” ብሎ ሺህ ጊዜ አድናቆቱን መሰከረላቸው። እርግጥም ፍርሃቱን ያሸነፈ ጀግና ነው! እንዲያውም ነገስታቱ ወይም መሪዎቹ እየገቷቸው እንጂ ጣልያንን ድባቅ እየመጡ ቀይ ባህር ሊከቱ የሚችሉ ጎበዞች እንደሆኑ ሲጽፍ ገድላቸው በዐይነህሊናው የሚታየው ይመስላል። ታድያ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ምን አገናኘው ሰማያዊ ሰላማዊ ትግል ነው ታንክና ጎራዴን ምን አገናኘው? ለሚሉ በሚከተለው አስተያየት የተነሳሁበትን ለመደምደም እሞክራለሁ።
ልክ ይህንን ታሪክ አስቀምጠው የነገሯቸው አዛውንቶች ያሉ ይመስል ባዶ እጃቸውን ነፃነት ወይም ሞት ያሉ ቆራጦች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጀግነው ተነስተዋል። ይህንን መነሳሳት ደግሞ በሚገባ አሳይተዋል። አምስት ሲታገትባቸው አስራ አምስት ሆነው ይተማሉ፣ አስራ አምስት ቢታገት አምሳ አምስት ይሆናሉ። ስለዚህ የነጻነት ፍላጎታቸው ካልሞተ ለነፃነት የሚያደርጉት ትግል እንደማይቆም ግልጽ ነው። አዎ በጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ በባላባት በባላባት ተጠራርቶ የወጣው ጀግና እንደዚያ ነበር ነፃነትን የተቀዳጀው። ሰማያዊ ፓርቲም መሪው ሲታሰር ሽባ የሚሆን ጥቂት አባላት ቢታገቱ የሚሽመደመድ እንዳይሆን ሆኖ የተደራጀ ይመስላል። እንደዚያ ሆኖ ሊጠናከርም ይገባዋል። ወጣት ወጣት የሚሸት እንቅስቃሴ ተስፋ ይሰጣል። ነቅተው ሌሎችንም የሚያነቁ፣ ጎብዘው ሌሎቸንም የሚያበረታቱ በዘርፈ ብዙው ትግል ውስጥ ብዙሃኑ እንዲሳተፉ ያበረታታሉ። ለዚህም ነው ታስረው ታስረው የማያልቁ… ከጎንደር መልስ አዲሳ አበባ፣ ከአዲስ አዋሳ እያሉ ሺህ ሚሊየን ወጣቶች ለነፃነትና ለክብር ሲቆሙ የምናየው። ያኔ በጠላት ወረራ ጊዜ አቢቹ የሚባል ለጋ ወጣት ነበር በወንድሞቹ ሞት ማግስት ጨርቄን ማቄን የማይሉ 200 ጎበዞች ብቻ ስጡኝ በማለት የራሱን ጦር ሊመራ ወሰነ። የርሱ የነበሩ በሬዎችን አሳርዶ የወንድሞቹን ተዝካር አወጣና ወደ ደፈጣ ውጊያም ገባ። ያ ወጣት ለጣልያን ያደሩ የትግራይ ሽፍቶችን ጨምሮ ጣልያኖችን አርበደበዳቸው። የ16 አመት ወጣት ምንም የጦር ስልጠና ያልነበረው ጀግና ሰልጥነናል ያሉትን መግቢያ መውጫ አሳጣቸው። ምንም እንኳ ከጀግኖቹ ተርታ ስሙን ሊናገሩ ያልፈለጉ ቢኖርም እንኳ ዛሬ ታሪኩ ታውቆ ወደፊትም ሲነገርለት ይኖራል። የዛሬዎቹ ወጣቶች በውል የሚያውቁት ወያኔን ብቻ ነው። ወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳውን በሚነዛበት ሀገር ነው ያደጉት። ይሁን እንጂ የማይሞተው ኢትዮጵያዊነትና የነጻነት ጥያቄ አነሳስቷቸዋል። ዛሬም ብዙ አቢቹዎች ይኖሩናልና የወጣቶች መነሳሳት የነፃነት ብስራት ነው ስንል ከጎናችሁ አለን እያልናቸውም ነው። ሞት እስርና እንግልት ሌሎችን ወደፊት ያመጣል። ትግሉ ስልጣን መያዝ አይደለም ስልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚያዝበትን የእኩልነት የነፃነት ብስራት የሚሰበክበትንና በተግባርም የሚረጋገጥበትን ጎዳና መቀየስ ነውና ለዚህ ቅዱስ ዓላማ አሁን ተመሳሳይ ዓላማ አለን የሚሉ በተለያየ የትግል ስልት ግን ለነፃነት ለሚታገሉ ሁሉ ብርታትና መነሳሳትን ይፈጥራሉ። ኢትዮጵያ ከጎጠኛ ወራሪዎችና አገር አፍራሾች ነፃ እስክትሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ።
biyadegelegne@hotmail.com

ፖሊስ የጣይቱ ልጆችን ለማሸማቀቅ እየጣረ ነው

April 29, 2014

ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ለተደረገው ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ፖሊስ ‹‹የእውቅና ደብዳቤው አልደረሰኝም፣ ህገ ወጦች ናችሁ!›› ብሎ ያሰራቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት (የጣይቱ ልጆች) ላይ ፖሊስ የተለያዩ የማሸማቀቂያ ስልቶችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ በዛሬው ቀን ፖሊስ ታሳዎቹን በተለይም ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንዲፍራውን ‹‹እስር ቤቱን በመረበሽ›› በሚል ሌላ ክስ ከግቢ አስወጥተው ቃል ተቀብለዋቸዋል፡፡ በወቅቱም ማስፈራራትና ዛቻ እንደደረሰባቸው ታሳሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
የጣይቱ ልጆች በታላቁ ሩጫ ላይ በፖሊስ በተያዙበት ወቅት ፖሊስ የተለያዩ በደሎችን ለመፈጸም ሲጥር መብታቸውን ለማስከበር ባደረጉት ጥረት ፖሊሶች ሌሊት ከግቢ አስወጥተው የድብደባና ሌሎች ማስፈራሪዎችን እንዳደረጉባቸው ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ምግብ እንዳይገባላቸው፣ ቤተሰብ እዳይጠይቃቸውና ሌሎችንም መብታቸውን የሚጋፉ በደሎች እየተፈጸሙባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያYoung semayawi party female activists

በአዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ዮናስ ከድር የዩኒቨርስቲ ፈተናውን እንዳይፈተን በፖሊስ ተከለከለ::

April 28/2014
በአዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ዮናስ ከድር የዩኒቨርስቲ ፈተናውን እንዳይፈተን በፖሊስ ተከለከለ::
ዮናስ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከሌሎች የፓርቲው አባላት ጋር በቅስቀሳ ላይ እያለ ባሳለፍነው ሳምንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ፈተና እንዳለበትና በፖሊስ ታጅቦ ሄዶ መፈተን ህጋዊ መብቱ መሆኑን ለፖሊስ ቢገልፅም እንዳይፈተን ተወስኖበታል::
በአንድ ወቅት ፕ/ር መስፍንን ሳዋራቸው ስለ ትምህርት እንዲህ ብለውኝ ነበር
"በመማሬ ካገኘሁት ጥቅም መካከል ዋነኛው የኢህአዴግ አባል ከመሆን መዳን ሲሆን ያጋጠመኝ ደግሞ እስር ነው"
ልክ ብለዋል ፕ/ር የምሁር ቤቱ በመሀይማን በሚመራው እስር ቤት ነው

Montag, 28. April 2014

በአራት ዪኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላኑን በመቃወም ተቃዉሞውውቸዉን አሰሙ።

April 28/2014



በአራት ዪኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላኑን በመቃወም ተቃዉሞውውቸዉን አሰሙ።
በዉጭ አገር የሚገኘውና በቅርቡ የተቋቋመው የኦሮሞ ሜዲያ ንቴዎርክ ማስተር ፕላኑን በመቃወም ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ የነበረና የሚገኝ ሲሆን፣ በዶር መራራ ጉዳናን የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨመሮ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች ፕላኑን አዉግዘዋል።
የኦሮሞ ተማሪዎች ም በአምቦ፣ በወለጋ፣ በጂማና በሃረማያ ሰላማዊ በሆነመንገድ ተቃዉሟቸውን ለማሰማት የሞከሩ ሲሆን፣ በአጸፋው የፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ደብደባ በተማሪዎች ላይ እንዳደረሰ ለማወቅ ችለናል።
በወላጋ ፖሊስ ጥይት የተኮሰ ሲኦሆን በርካቶች እንደቆሰሉ የተቀረኡትን በአካባቢዉ ወዳለ ጫካ እንደትበታተኑ ለማወቅ ተችሏል። በጂማ 11 በአምቦ ደግሞ 15 ተማሪዎች ታስረዋል።
ተማሪዎቹ «ቡራዩ አይሸጥም፣ ሱሉልታ አይሸጠም፣ ለገጣፎ አይሸጥም፣ ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች ብቻ ! ፊንፊኔ የኦሮሚያ ናት..» የመሳሰሉ መፈክሮችን ሲያሰሙም ነበር።
በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል እንደሆነች በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን፣ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ማግኘት እንደሚኖርባትም ይደነግጋል። የኢትዮጵያ ግዛት ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ብሄረ ብሄረሰቦች እንደሆነ የሚደነግገው ሕገ መንግስቱ፣ ብሄር ብሄረሰቦች ራሳቸው በራስ የማስተዳደር መብት ያዉም እስከመገንጠል እንደሚፈቅድም ይታወቃል።
አገሪቷ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌዴራል አወቃቀር እንዲኖራት የተደረገ ሲሆን፣ ይሄም አወቃቀር ያል ሕዝብ ፍቃደ በኦነግ፣ በሕወሃት እና በሻቢያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንደሆነ ይታወቃል።
የኦሮሚያ ሕግ መንግስት የኦሮሚያ ባለቤት ኦሮሞ ብቻ እንደሆነ በአንቀጽ ስምንት ባስቀመጠዉ መሰረት፣ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን በኦሮሚያ ዉስጥ እንደ እንግዳ እንደሚታዩም የሚገልጹ በርካታ ክስተቶች አሉ።
በኦሮሞ ተማሪዎች ሲባሉ የነበሩት «ኦሮሚያ የኦሮሞውች ናት። አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት» የሚሉት መፈክሮች፣ አገዛዙ ራሱ በሰነድና በወረቀት የሚቀበለውና የሚስማማበት እንደመሆኑ፣ ተማሪዎች ሰላማዊ በህነ መንገድ በኦሮሚያ ሕግ መንግስት ዬትቀመጠዉን በመድገማቸው መደብደባቸው ፣ አሳፋሪ እና አዛዝኝ እንደሆነም ብዙዎች እየተናገሩ ነው።
ዜጎች በኢሕአደግ ባለስልጣናት ከቅያቸው የሚፈናቀሉት በሁሉም ክልሎች እንደሆነ የገለጹት ያነጋገርናቸው አንድ የፖለቲክ ተንታኝ ፣ በልማት ስም በኦሮሞዎችም ሆነ በማንም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርስን ግፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መቃወም እንዳለበት ይናግራሉ። አዲስ አበባን በተመለከተ « አዲስ አበባ ማደጓ አይቀርም። እድገቷ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ይፈጸም መባል ነው እንጂ ያለበት፣ የኦሮሚያ ሬፑብሊክ ወደፊት ለመፍጠር ከሚኖር ፍላጎት የተነሳ የኦሮሚያ ክልል ለምን አነሰች የሚል ጠባብ መከራከሪያ የትም አያደርስም።» ሲሉ ተማሪዎቹም ሆነ በዉጭ ያሉ የኦሮሞ ብሄረተኞች ያለዉን ተጨባጭ እዉነታ እንዲገነዘቡም ይመክራሉ።



በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

April 28/2014

(አዲስ ጉዳይ) ፖሊስ ለምርመራ 10 ቀናት ጠይቋል ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር
የዋሉት 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች ዕሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን
ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል።

 በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በማዕከላዊ እስር ቤት የቆዩት ተጠርጣሪዎች ሰኞ ለፍርድ እንደሚቀርቡ የተጠበቀ ቢሆንም ባልተለመደ ሁኔታ ዕሁድ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን የክሱም ሃሳብ በአጭሩ “ሀገሪቱን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሃሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማምተው የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል” የሚል ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ተመሳሳይ ክስ የቀረበባቸው ቢሆንም በ3 የተለያዩመዝገቦች ተከፋፍለው ነው ፍርድ ቤት ቀረቡት፡፡ የአዲስጉዳይ ጋዜጠኛ አስማማውኃይለጊዮርጊስ፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆነው ዘላለም ክብረት እና የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጠኛና በአሁኑ ወቅት በአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ላይ የሚሰራው ተስፋለም ወልደየስ በመዝገብ ቁጥር 118722 የተጠቃለሉ ሲሆን፤ አጥናፉ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ኤዶም ካሣ በመዝገብ ቁጥር 118721 እንዲሁም በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው።


በመዝገብ ቁጥር 118721 እና መዝገብ ቁጥር 118722 የተካተቱት ተጠርጣሪዎች ለሚያዝያ 29 ቀን 2006 ተቀጥረዋል።ጉዳያቸው በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተተው ተጠርጣሪዎች ደግሞ ለሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓመተምህረት ተቀጥረዋል።

Sonntag, 27. April 2014

ጥቂት ስለ ማዕከላዊ!

April 27/2014
ማዕከላዊን በከፊል አውቀዋለሁ፡፡ ትናንት ሰባት የሚሆኑ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮችና አክቲቪስቶች መታሰራቸውን ተከትሎ ወደ ማእከላዊ መወሰዳቸውን ሰምተናል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ጨለምተኛ ልመስል እችል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይኸው ነው፡፡
መጀመሪያ ክሱ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጊ ጥያቄ ነው፡፡ ይህን ለማወቅ ወሳኝ ፍንጭ የሚሰጠው የቤት ፍተሻው ነው፡፡ የታሰሩትን ሰዎች ቤት የሚፈትሹት ፖሊሶችና መርማሪዎች ቤቱን የሚፈትሹት ለጥቂት ሰዓታት (ቢበዛ ለሁለት ሰዓታት) ከሆነና በጣም ብርበራ ያልበዛበት ከሆነ አለቆች በጸረ ሽበር ሕግ ለመክሰስ እንዳላሰቡና አስፈራርተው ብቻ በዋስ ለመልቀቅ እንዳሰቡ ፍንጭ ይሰጣል፡፡ በተቃራኒው ፍተሻው በትንሹ ከስድስት ሰዓታት በላይ የሚረዝምና በቤቱ የተገኘውን ወረቀት፣ መጽሐፍ፣ ሲዲ፣ ኮምፒውተርና ሞባይሎች ምንም ሳይስቀሩ ሰብስቦ የሚያስኬድ ከሆነ ጉዳዩ በጸረ ሽብር ሕግ ከመክሰስ ጋር የተያያዘ እንደሆነ መጠርጠር ያሻል፡፡
ይሄ የቤት ፍተሻ የቤቱን ኮርኒስ መቅደድና ወለሉን እስከመቆፈር ይደርሳል፡፡ በዚህ ጉዳይ ውስጥ ዋናው ግንዘቤ መወሰድ ያለበት ነገር ሰዎቹ የሚያስሩት ማስረጃ በመያዝ ሳይሆን፤ ማስረጃ ሊሆን የሚችል ማንኛውም ነገር በፍተሻው አግኝቶ እሱን ቀባብቶና አሳምሮ መክሰስ መቻላቸው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መርማሪዎች፣ አቃቢ-ሕጎችና ተሰያሚ ዳኞች ተገናኝተው እንዲያወሩ ስለሚደረግ ነገሩን ፍርድ ቤት አድርሶ የሚፈለገውን ውሳኔ ለማስወሰን መንገዱ ጨርቅ ነው፡፡
በማእከላዊ ከተወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለሦስት ቀን ያህል ከቤተሰብም ሆነ ከማንም ጋር መገናኘት የማይተሰብ ነው፡፡ ይህ ታሳሪዎቹንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን የበለጠ ለማደናገጥና የሥነ-ልቦና ጫና ውስጥ ለመክተት ወሳኝ ነው፡፡ ታሳሪዎቹ በቀጥታ የሚወሰዱት ‹‹ጣውላ ክፍል›› ወደሚባሉ የእስር ክፍሎች ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚታሰሩ ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ለ15 ደቂቃ ያህል የሚቆይ ጸሀይ መሞቂያና መጸዳጃ ቤት መሄጃ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህ ከፍሎች በግምት አራት በአራት ስፋት ያላቸውና ወለላቸው ከጣውላ ጣሪያና ግድግዳቸው ከኮንክሪት የተሠራ ሲሆን፤ ቦታው ሻል ካለው የእስር ኮሪደር ‹‹ሸራተን›› እጅግ ያነሰ ነጻነት ያለውና፤ በጣም ከባሰው ጨለማ ክፍል ‹‹ሳይቤሪያ›› የተሻለ ቦታ ነው፡፡ ምርመራው ለእስር በገቡበት ምሽት ይጀመራል፡፡ የኢ-ሜይልና ሌሎችም አካውንቶች ፓስወርዶች በግድ እንዲሰጡ ይደረግና የኮምፒውተር ሀ ሁ በማያውቁ ‹‹መርማሪዎች›› አካውንታቸው ይበረበራል፡፡
ከዚሁ ጎንለጎን ቀለል ያለ ምርመራና ጥያቄና መልስ ይካሄዳል፡፡ በቀጣዮቹ አምስት እና አስር ቀናት ‹‹ጠቃሚ ውጤት በምርመራ አላገኘንም›› ብለው ካሰቡ ወደ ሌላኛው የእስር ክፍል ወደ ‹‹ሳይቤሪያ›› ያዘዋውሯቸዋል፤ በዚህ ወቅት የምርመራ ስልቱና አጠቃላይ ሁኔታውም ይለወጣል፡፡ ታስረው መቆየት ‹‹አለባቸው›› ወይም ‹‹የለባቸውም›› የሚለውን የሚወስኑት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ውሳኔው ይፈቱ ከሆነ ወደ ‹‹ሸራተን›› የእስር ክፍል ያዘዋውሯቸዋል፡፡ ይህ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት የሚያስችል የእስር ቦታ ሲሆን፣ በጊቢው ካሉት የእስር ክፍሎች ሁሉ የተሻለ አንጻራዊ ‹‹ነጻነት›› ያለው ነው፡፡
በጥቅሉ ሳይቤሪያ ከአንድ ሜትር ስኩዌር ብዙም የማይበልጥ፣ ጨለማ፣ በጣም ቀዝቃዛና አምስት ቀናት ቢቆዩቡት መላው አካልን ወደ አመድነት (ነጭነት) የሚለውጥ ዘግናኝ ቦታ ነው፡፡ በዚህ እስር ክፍል ውስጥ ሰዎች የሚታሰሩት ያላደረጉትን ነገር አድርገናል ብለው እንዲያምኑ ወይም የያዙትን ‹‹ሚስጥር›› ‹‹እንዲያወጡ›› ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚታሰሩ እስረኞች አንዳንዴ ያልተቋረጠና እስከ 14 ሰዓት የሚደርስ ምርመራ በፈረቃ በሚቀያየሩ መርማሪዎች ይደረግባቸዋል፡፡ በምርመራው እንደ እስረኛው ሁኔታ የሚላላና የሚጠነክር ድብደባና ቶርች መጠቀም የተለመደ ‹‹አሠራር›› ነው፡፡ ቶርች የተደረጉ ሰዎች ቁስላቸው እስከሚያገግም ከቤተሰብም ሆነ ጠበቃ ጋር ማገናኘት የማይታሰብ ነው፡፡ በእነዚህ ሁሉ ወቅቶች ቤተሰብ ምግብ ለማድረስ፣ ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ለማግኘት የሚደርጉት ጥረት ውጤት አልባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይቺ ነች፡፡
By Akemel Negash

Ethiopian to Demand John Kerry Raise Human Rights Issue

April 26, 2014

Demonstration to demand Secretary Kerry raise Human Rights Violations during his upcoming trip to Ethiopia and to show solidarity for jailed Semayawi (Blue) party members, Zone 9 independent Journalists and all Political Prisoners.Demonstration head of Secretary John Kerry's scheduled visit to Ethiopia.
A protest demonstration has called for Monday April 28, 2014 in Washington, DC in front of the State Department ahead of Secretary John Kerry’s scheduled visit to Ethiopia. The protest rally is planned to show our solidarity with detained Semayawi Party members, recently arrested independent journalists and bloggers from Zone 9 group and political prisoners and to urge Secretary Kerry to make human rights and freedom of expression as one of his main topics of discussion during his stay in Addis Ababa.
It’s to be recalled that in the last few days, the TPLF lead Ethiopian regime has arrested over 50 Semayawi ( Blue) Party members ahead of their planned peaceful and legal protest rally on Sunday April 27. The regime is also tightening its suffocating grip on freedom of expression in a major crackdown with the arrest of numerous members from independent blogger and activist group ( Zone 9). With still a year to go before the “general elections”, the regime is tightening the screws on its iron curtain on freedom of speech, opinion and thought.
We urge Ethiopians and friends of Ethiopians in Washington DC metro and surrounding areas to join us to express our outrage at TPLF lead governments spiteful action against peaceful political party members, independent journalists and to demand release of political prisoners and to urge Secretary Kerry to make human rights and freedom of expression as one of his main topics during his upcoming visit to Ethiopia.
For more information contact
Semayawi Support-North America
P.O.Box 75860, Washington, DC 20013
semayawiusa.org
info@semayawiusa.org

አዲስ አበባ፥ ጆን ኬሪ ሦስት የአፍሪቃ ሃገራትን ይጎበኛሉ

April 26/2014
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ለአንድ ሳምንት ያህል ሦስት የአፍሪቃ ሃገራትን እንደሚጎበኙ ተገለጠ። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መግለጫ ዛሬ እንዳስታወቀው ኬሪ የሚጎበኙዋቸው ሦስት ሃገራት ኢትዮጵያ፣ አንጎላና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ናቸው። ኬሪ የፊታችን ማክሰኞ በሚጀምረው የአፍሪቃ ጉብኝታቸው ሠብዓዊ መብትንና ዲሞክራሲን ማጠናከር ዋነኛ የንግግር አጀንዳቸው እንደሚሆንም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታውቆዋል። ጆን ኬሪ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝንና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቴድሮስ አድሃኖምን አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚያናግሩ መግለጫው አትቷል። ንግግሩም በአፍሪቃው ቀንድ ሠላም ለማስፈን ስለሚደረገው ጥረትና ከኢትዮጵያ ጋ ግንኙነቱን ስለማጠናከር እንደሚሆን መግለጫው አክሎ ጠቅሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሠማያዊ ፓርቲ ሦስት ከፍተኛ አመራር አባላት እንዲሁም ስድስት የኢንተርኔት ጦማሪያንን ጨምሮ አንድ ጋዜጠኛ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ መታሰራቸው ተዘግቧል።

Ethiopia detains bloggers and journalist

April 26, 2014

Al Jazeera
Security forces arrest six bloggers and a journalist in latest crackdown on opposition voices.
The Ethiopian government has arrested six independent bloggers and a journalist in what human rights group Amnesty International has called a “suffocating grip on freedom of expression”.Ethiopian government has arrested six independent bloggers
Six members of independent blogger and activist group ‘Zone 9’ and a prominent Ethiopian journalist were arrested on Friday in the capital Addis Ababa.
All six bloggers were arrested at night by armed security forces and taken from their homes to the Federal Police Crime Investigation Sector ‘Maikelawi’, where political prisoners are alleged to be held in pre-trial, and sometimes arbitrary detention.
The Zone 9 group who are said to be very critical of government policy and have a strong following on social media had temporarily suspended their activities earlier this year after accusing the government of harassing their members.
Journalist Tesfalem Waldyes who writes independent commentary on political issues for a Ethiopian newspaper was also arrested.
According to Ethiopian journalist Simegnish Yekoye, Waldyes is being denied visitation by friends and family and it’s unclear what prompted his arrest and what charges he is being held under.
Simegnish Yekoye told Al Jazeera she was unaware of why the government had clamped down on journalists and their was growing fear on the future of a free press.
“I am very scared, I don’t know what’s going to happen next,” she said.
Ranked 143 in the 2014 Reporters Without Borders press freedom index, media watchdogs say 49 journalists fled the country between 2007 and 2012 to evade government persecution.
Human rights group Amesty International criticised the arrests, saying “these arrests appear to be yet another alarming round up of opposition or independent voices”.
“The Ethiopian government is tightening its suffocating grip on freedom of expression in a major crackdown which has seen the arrest of numerous independent, critical and opposition voices over the last two days”, Claire Beston, Ethiopia researcher at Amnesty International, said.
Al Jazeera’s Mohammed Adow reporting from Bahir Dar said it was unclear what will happen to the detained journalists.
“There are scores of journalists currently serving between 14 and 27 years in prison with some charged on terrorism offences.”

Samstag, 26. April 2014

ሰበር ዜና • የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኛ በፖሊስ ታሰረ

April 26/2014

• ምክንያቱ እስካሁን ግልጽ አልተደረገም
የአዲስጉዳይ መጽሄት ከፍተኛ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እስካሁን ለመጽሔቱ ባልደረቦች ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ዛሬ ሚያዝያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማለዳ በፖሊስ ታስሯል።
በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ በከፍተኛ አዘጋጅነት የሚሰራው ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ ማለዳ ከቤቱ ሲወጣ በመኪና ሲጠብቁት በነበሩት ፖሊሶች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
አዲስ ጉዳይ ስለባልደረባው የእስር ምክንያትና ሁኔታ ለማጣራት ባደረገው ሙከራ የተገነዘበው ነገር ቢኖር ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ ፖሊስ ክበብ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ወጥቶ በሰላም ወደስራው በመሄድ ላይ ሳለ በመኪና ቆመው ሲጠብቁት በነበሩትና ከማዕከላዊ ምርመራ እንደመጡ በተናገሩ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋሉን ብቻ ነው።
ቤተሰቦቹ እንደተናገሩት የፖሊሶቹ ቁጥር 9 የሚደርስ ሲሆን ከመካከላቸው አንዱ ብቻ ነው ዩኒፎርም ያደረገው። በብርበራው ወቅት ፖሊሶቹ ወደጋዜጠኛው ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት ማንም ሰው እንዳይገባም ሆነ እንዳይወጣ ከልክለዋል ብለዋል።
የአዲስ ጉዳይ ባልደረቦች ከቤተሰቡ እንደተገነዘቡት ከሆነ ጋዜጠኛ አስማማውን ፖሊሶቹ ማለዳ ላይ ይዘውት ከሄዱ በኋላ ረፋድ ላይ መልሰው ወደቤቱ ይዘውት መጥተዋል። ከዚያም መኖሪያ ቤቱን ከማለዳው 4 ሰዓት እስከ10 ሰዓት ድረስ ሲበረብሩ የቆዩ ሲሆን አራት ፌስታል የተለያዩ ጋዜጦችና መጽሄቶችና ጋዜጠኛው የሚጠቀምበትን ላፕቶፕ ይዘው ሄደዋል።
በብርበራው ወቅት ቤተሰቦቹ ለጋዜጠኛው ምግብ ለመስጠት የጠየቁ ቢሆኑም ፖሊስ ግን ፍቃደኛ አለመሆኑን ተናግረዋል። ጋዜጠኛ አስማማው ብርበራው በተካሄደበት ወቅት በፖሊሶች በካቴና ታስሮ ቤት ውስጥ ነበር ብለዋል ቤተሰቦቹ።
በመጨረሻም ፖሊሶቹ ለምርመራ ወደማዕከላዊ ይዘውት እንደሄዱ ለቤተሰቦቹ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አዲስ ጉዳይ የደረሰው መረጃ የለም።
አዲስ ጉዳይ ጋዜጠኛውን ፖሊስ አነጋግሮ ይለቅቀዋል የሚል ተስፋ ይዞ እስካሁን ሰዓት ድረስ ቢጠብቅም የጋዜጠኛው ከእስር መለቀቅ አጠራጣሪ በመሆኑ ይህንን ሰበር ዜና ይፋ አድርጓል።
ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ በሮዝ መጽሄት (በአሁኑ አዲስ ጉዳይ) ከቅጽ 1 ቁጥር 1 ህዳር 1999 ዓ.ም የመጀመሪያ እትም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ7 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት ሙያው በመጽሄቱ ከፍተኛ አዘጋጅነት እያገለገለ የሚገኝና ጋዜጠኝነትን የሚሰራ የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኛ ነው።
አዲስ ጉዳይ በእስር ላይ የሚገኘውን የመጽሄቱን ከፍተኛ አዘጋጅ የእስር ምክንያት ከሚመለከታቸው አካላት በማጣራት ተከታትሎ መረጃውን ለህዝብ የሚያቀርብ መሆኑን ለማሳወቅ ይወድዳል።

ዞን ዘጠኞች ...... በምንሊክ ሳልሳዊ ..... ዝም አላልንም ..... ለማስፈታት እየተራባረብን ነው።ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው .... የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፕሮፓጋንዳ ይረጫሉ .... በነጻነት አይንቀሳቀሱም ....በዲያስፖራው ቻርጅ ይደረጋሉ ......

April 26/2014
ዞን ዘጠኞች ...... በምንሊክ ሳልሳዊ ..... ዝም አላልንም ..... ለማስፈታት እየተራባረብን ነው።ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው .... የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፕሮፓጋንዳ ይረጫሉ .... በነጻነት አይንቀሳቀሱም ....በዲያስፖራው ቻርጅ ይደረጋሉ ......

" እንፈታቸዋለን .. መረጃ ፈልገን ነው። " በማእከላዊ ቢሮ የመሸጉ የደህንነት ሹም
ወያኔ መወንጀያ ምክንያት አታጣም... የፍረጃ ፋብሪካ ብንላት አያንስባትም ።........
ከተወሰኑ ወራቶች በፊት የዞን ዘጠኝን እንቅስቃሴ አስመልክተን ከ ማህሌት MahiFantish Wube ጋር ወግ ቢጤ ይዘን ነበር ... ውስጣቸው መጥራት እንዳለበት እና በንጹህ ብዕር ስም የተመሳሰሉ መርዘኞች ወያኔ በደምወዝ እያስተዳደረ እንደሆነ ( አልዝለቅበት) ሆኖ ከወቅቱ እይታ አንጻር ከኔ መረጃ ግብአት ጋር ወደ መስመራችን ላይ ጠልቀን ነበር .... ይህንን የሰሙ የገዢው መደብ ቅጥረኞች አይንህን ላፈር .... እና የዛ መነሾ የዞን ዘጠኝ ዘብጥያ ..... ውጤቶች ስለላዎች ... ምናምኖች ...... ብቻ የወራት በፊት ንግግሮች ... የወለዱትን ወልደው ........
ትላንትና ከምሳ በኋላ ሁኔታዎች መልካም እንዳልነበሩ እና የወያኔ ደህንነት ሃይሎች እየተራወጡ እንደሆነ ተባራሪ የሚሳኤል መወንጭፎችን ተከትሎ ከወደ አዲስ አበባ እና አምቦ የደፈረሱ ወሬዎች ሰማን ... እስኪ የአምቦውን እናጣራው ስንል ልክ ከመሆኑም በላይ በሾርኒ የዳበስናቸው የአምቦው ዩንቨርስቲ ምክትል ቻንስለር በተዘዋዋሪያችን ነገሩን ..... አዲስ አበባ አፈናው ደርቶ ጀንበር ልታዘቀዝቅ ስትል አጠቃለሏቸው ተባልን.....
አሁንም ዝም አላልንም ወደ ኢሳት ቤት አመሻሽተን ጎራ አልን ወዳጄ ደረጀ Dereje Habtewold እንዴት ነው ስለው የሚያውቀው እንዳሌለ እና በአዲስ አበባ ወኪላቸው በኩል ሊያጣረው ዘመተ..... የመረጃ ፍጥነታችን አዝጋሚ መሆን ባያደርሰንም ደረስን፡፤
አሁን ዞን ዘጠኞች በመርዛም የወያኔ መርፌዎች ሳይጠቀጠቁ በፊት ከማእከላዊ መዳፍ ፈልቅቆ ለማውጣት የየራሳችንን ጥረት እያደረግን ነው። በግልም ይሁን በቡድን የምናነጋግራቸው ባለስልታናት ይህንን ጉዳይ አዲስ ነገር ይሉናል የማንደርስባቸው አውሬዎችን በአቋራጭ ለማግኘት ሞክረን ፊት ነሱን አሉን አቋራጮቻችን .. ወጣም ወረደ ግን ዞን ዘጠኞች ይፈታሉ፡፤ ወያኔ ተደናብሯል። እኛ ያልደረስንበት ግን ሊይዘው የሚፈልገው ሰው አለ ወያኔ እና .. እሱን ለማግኘት እያደነ ማሰር ቀጥሏል። የሕወሓት ከፍተኛ ጄኔራሎች ይተቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ቢሮ የ መረጃ እና የስለላ ደህነንት ቢሮ የፖሊስ ደህንነት ዲፓርትመንቶች የሚሰታቸው ትእዛዝ ከየት እንደሚወርድ የት እንደሚወጣ አያውቁትም የአንዱን አንዱ ያራውጠዋል ዜጎች በመሃል ይሰቃያሉ ይሞታሉ ይገረፋሉ .....
አሁንም ከቃል በተጨማሪ በጽሁፍ "የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከ እስር እንዲፈቱ አጥብቀን እንጠይቃለን!!"
ምንሊክ ሳልሳዊ