Netsanet: የሚሊዮኖች ድምጽ – ሲያትሎች ከደብረ ታቦር ጎን በመቆም የሚሊዮኖች አንዱ ሆኑ !

Donnerstag, 10. April 2014

የሚሊዮኖች ድምጽ – ሲያትሎች ከደብረ ታቦር ጎን በመቆም የሚሊዮኖች አንዱ ሆኑ !

April 9/2014
የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በአገሪቷ ዉስጥ ባሉ አሥራ አራት ከተሞች፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። እንቅስቃሴ በደሴ ሰላማዊ በማድረግ የተጀመረ ሲሆን፣ በሌሎች ከተሞች ከአንድነት ጽ/ቤቶች ወደ አደባባይ በሚሄድ ትይንተ ሕዝቦች በማድረግ ይቀጥላል።
በደሴ ከተማ የተደረገዉን እንቅስቃሴ በደንቬር የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ስፖንሰር ያደረጉት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚደረገዉን የመጀመሪያው እንቅስቅሴን ላስ ቬጋሶች፣ ሃዋሳ አትላንታዎች፣ ድሬደዋን የደብተራ ፓልቶክ ክፍል፣ ቂጫን ደግሞ የቃሌ ፓልቶክ ክፍል፣ ስፖንሰር እንደሚያደርጉ መግለጻችን ይታወቃል።
ሲያትል ዋሺንግተን ከደብረ ታቦር (ደቡብ ጎንደር ዞን) ከተማ ጋር ሶሊዳሪቲ በመመሰረት ፣ በደብረ ታቦር የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሚሊዮኖች ድምጽ ዘመቻ በከተማቸው ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ወጭ ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን የተዘጋጁ ሲሆን፣ ሲያትሎች እኛም «ከሚሊዮኖች አንዱ ነን» እያሉ ነው።
ይህ የሚሊየነሞች እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው። ነጻነት ርካሽ አይደለም። ዋጋ ያስከፍላም።
በዳያስፖራ የሚሊየነሞች ግብረ ኃይል፣ በሲያትል ያሉ ኢትዮጵያዉን ላሳዩት አኩሪና ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴ ያለዉን አድናቆት እየገለጸ፣ በሌሎች ከተሞችም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸውን እያደራጁ ፣ አገር ቤት ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ካለው ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ፣ ትግሉን እንዲቀላቀሉና ከሚሊዮኖች አንዱ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል። በባህር ዳር የታየው፣ በደሴ የተደገመው ፣ የሕዝብ መነቃቃት በየቦታዊ ሲሰራጭ፣ ያኔ የአምባገነኖች ፍጻሜ ይሆናል።
በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይል ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ፣ በሚከተሉት አድራሻ ቢያገኙት ጥያቄዎችትን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን። የአንድነት ፓርቲ ድህረ ገጽ በመሄድ፣ ( http://www.andinet.org )፣ ከላይ በስተቀኝ በኩል በፔይ ፓል፣ ካሉበት ቦታ ሆነው፣ የአቅምዎትን ድጋፍ ማድረግም ይችላሉ። ይችላሉ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
millionsforethiopia@gmail.com
404- 518-7858

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen