Netsanet: አንድነት የአዲስ አበባ መስተዳድርን ሰነድ ጠየቀ

Dienstag, 8. April 2014

አንድነት የአዲስ አበባ መስተዳድርን ሰነድ ጠየቀ

April 7/2014

---
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አስገብቶት ለነበረ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ የማሳወቂያ ክፍሉ ኦፊሰር በጻፉት የመልስ ደብዳቤ ‹‹የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ››የሚል ቃል ተጠቅመው ነበር፡፡
ፓርቲው ፓርላማው ካወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት አዋጅ ውጪ በኦፊሰሩ የተጠቀሰውን የስነ ስርዓት ደንብ ባለማግኘቱ የሰልፍና የስብሰባ ጥያቄ በሚያቀርብበት ወቅት ስነ ስርዓቱን እንዲያውቀው፣ መስተዳድሩ ያወጣው የስነ ስርዓት ደንብም ፓርላማው ካወጣው አዋጅ ጋር መቃረን አለመቃረኑን ለመመልከት ይረዳው ዘንድ ዛሬ ለሚመለከተው አካል ሰነዱን ይሰጡት ዘንድ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen