Netsanet: ከታሰሩት የአንድነት አባላት ሁለቱ ሲፈቱ ቀሪዎቹ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

Donnerstag, 10. April 2014

ከታሰሩት የአንድነት አባላት ሁለቱ ሲፈቱ ቀሪዎቹ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

April 9/2014
መጋቢት 28/2006 ሊደረግ ለነበረው ‹‹ የእሪታ ቀን›› ሰላማዊ ሰልፍ ለህዝብ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጩ ከተያዙት አምስት የአንድነት አባላት መካከል ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የነበሩትና የርሃብ አድማ የመቱት ወርቁ እንድሮና አክሊሉ ሰይፉ ፖሊስ በትናንትናው ዕለት ያለምንም ዋስትና ሲለቅ የካ ፖሊስ ጣብያ የታሰሩት መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን፣ ሃብታሙ ታምሩና አሸናፊ ጨመዳ ዛሬ ማለዳ የካ ምድብ ችሎት ቀርበው ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡
የየካ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ያለ ፓርቲው ፈቃድ ወረቀት በመበተን አመጽ እንዲነሳ አድርገዋል፣ሌሎች ተባባሪዎቻቸውም ስላልተያዙ እነርሱን በመያዝ ምርመራዬን እንዳጠናክር ተጨማሪ የሰባት ቀን ቀጠሮ ይፈቀድልኝ ››ብሏል፡፡ችሎቱን ለመከታተል በቦታው ተገኝተው የነበሩት የአዲስ አበባ የአንድነት ዋና ጸሐፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ‹‹እነዚህን ሰዎች ወረቀት እንዲበትኑ አመራር የሰጠናቸው እኛ ነን፡፡ፖሊስ እነርሱን ፈትቶ እኛን ይሰር ››ከማለታቸውም በላይ‹‹የአዲስ አበባ መስተዳድር ላቀረብንለት የእውቅና ጥያቄ የዘገየ ምላሽ በመስጠቱና ቀኑ እየተቃረበ በመምጣቱ ህዝብ የማስተባበር ስራ እንዲሰራ አድርገናል፡፡መስተዳድሩ የሰልፉን ቀን እንድንቀይር የጠየቀን አርብ ዕለት ነው፡፡አባላቶቻችን ግን የታሰሩት ሐሙስ ዕለት ነው ፡፡ወረቀቱ ከደረሰን በኋላ የቅስቀሳ ስራችን አቁመን ህጉን አክብረናል፡፡ፖሊስ ግን ወገንተኛ ሆኖ አባላቶቻችንን አስሮ እያጉላላ በመሆኑ ያለምንም ዋስትና እንዲፈቱልን እንጠይቃለን››ብለዋል፡፡
ዳኛ ማሞ ሞገስ ፖሊስ ከአዲስ አበባ መስተዳድር የተጻፈውን ደብዳቤ በመመልከት እንዲወስን አመጽ እንዲነሳ ስለመስራታቸው መረጃ አለኝ የሚል ከሆነም ለነገ እንዲያቀርብ አዘዋል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen