Netsanet: ቤቱ ሲፈርስበት ‹በዓሉን ብቻ ልዋል› ብሎ የሚለምን ከኢትዩጵያ ውጪ የት ይገኛል?

Samstag, 12. April 2014

ቤቱ ሲፈርስበት ‹በዓሉን ብቻ ልዋል› ብሎ የሚለምን ከኢትዩጵያ ውጪ የት ይገኛል?

April 12/2014

ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በሳምንቱ መጨረሻ ከመኖሪያ ቤት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ሰምተናል፡፡ቤታችን ከፈረሰ ለጎዳና እንዳረጋለን በማለት‹‹በህግ አምላክ››ያሉ ዜጎች የጥይት መልስ ተሰጥቷቸው ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸው ያሳዝናል፡፡ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ የክልሉ አስተዳደር ለአመታት ሰዎቹ በመኖሪያነት ሲጠቀሙበት ለነበረው ቤት ውሃ፣መብራት፣ስልክ እንዲያገኝ አድርጎና ህጋዊ ከለላ ሲሰጥ ቆይቶ በአንድ ጀምበር ቤቱን ላፍርስ ብሎ መነሳቱ ነው፡፡በወቅቱ ነዋሪዎቹ ለአፍራሽ ግበረ ሀይሉ ‹‹መጪው ዓመት በዓል በመሆኑ ቢያንስ በዓሉን እንድናከብር ቤቱ የሚፈርስበትን ቀን አራዝሙልን››ነበር ያሏቸው፡፡
በአዋጅ ቤት ከመፍረሱ በፊት 90 ቀን የመስጠት ግዴታ ያለበት አካል ጨዋ ህዝብ ቢያጋጥመውም ጨዋነቱን እንደ ፍርሃት መቁጠሩ ህይወት እንዲገበር ምክንያት ሆኗል፡፡ግን እናንተዬ ‹‹በዓሉን ልዋል እንጂ ታፈርሱታላችሁ››የሚል ህዝብ ከኢትዩጵያ ውጪ ከቶ ከወዴት ይገኛል፡፡ለእንዲህ አይነቱ ጨዋ ህዝብስ እንዲህ አይነት አስተዳደር መገኘቱ አያስደንቅዎትም፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen