Netsanet: ቤታቸው እንዲፈርስ የወጣውን ትዛዝ በመቀዋወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች አደባባይ ወጡ

Montag, 21. April 2014

ቤታቸው እንዲፈርስ የወጣውን ትዛዝ በመቀዋወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች አደባባይ ወጡ

April 21, 2014

ነገረ ኢትዮጵያ – ፍኖተ ሰላም፡- በጃቢጠህናን ወረዳ የሆዳንሽ ቅዱስ ገብርኤል ቀበሌ ኗሪዎች የሆኑ ከአምስት ሺህ በላይ ሠልፈኞች ህገ-ወጥ ግንባታ በሚል ቤታቸው እንዲፈርስ የወጣውን ትዛዝ በመቀዋወም አደባባይ ወጡ፡፡ የወረዳው ከፍተኛ ባለስልጣናት ሚያዝያ 5 2006 ዓ.ም የቀበሌውን ህዝብ ሠብሰብው ከ808 በላይ ህገወጥ ቤቶች ይፈርሳሉ በማለት ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ የተቀሰቀሰ መሆኑ ሠልፈኞቹ ተናግረዋል፡፡ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው ያሉት ሠልፈኞቹ በስንት መስዓውትነት የገነባናው ቤት በመንግስት ትዕዛዝ እንደዋዛ ሊፈርስ አይገባም ብለዋል፡፡
መንግስት መመሪያውን በወቅቱ ባለማውጣቱና የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጉ በፈጠረው ስህተት ቤቶቻችሁ ሁሉ ይፈርሳሉ የሚል ትዛዝ ለምን አስተላለፈ? በበርሀ አረን ከስለንና የደም እዳ ከፍለን የገነባናው መኖሪያ ቤታችን ከላያችን ላይ ሲፈርስ መንግስት ለእኛ ለዜጎቹ ምን አማራጭ ይዞልን ነው? ልጆቻችንንስ የት እናድርሳቸው? ከዚህ ክልል ወጭ ሁሌም ተፈናቃዮችና ስደተኞች በዚህ ከልል ውስጥ ሁሌም ተፈናቃዮችና ስደተኞች ለመሆኑ በነፃነት ቤት ሠርተን የምንኖርበት ሀገር ወዴት ነው? ህግ ወደ ኋላ ዞሮ በእኛ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ የተፈለገውስ ከምን አንፃር ነው? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱት ሠልፈኞቹ ከዞንና ወረዳ ባለስልጣናቱ ጋር ሳይግባቡ ተለያይተዋል፡፡
ህገወጥ ሠላማዊ ሠልፍ በማድረግ ሽብርና ሁከት ፈጥራችኋል በሚል በዞንና ወረዳ ባለስልጣናት ዛቻና የማስፈራራት ምላሽ ያልተደናገጡት ሠልፈኞቹ ጉዳዩ በህጋዊ መንገድ ትክክለኛ መፍትሄ እስከሚያገኝ እንታገላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen