Netsanet: የቀድሞውን የኢትዮጵያ ጦር ባልደረባ መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ ከቤተሰቦቹ ጋር ለማገናኘት የተደረገ ጥረት ተሳካ !

Freitag, 11. April 2014

የቀድሞውን የኢትዮጵያ ጦር ባልደረባ መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ ከቤተሰቦቹ ጋር ለማገናኘት የተደረገ ጥረት ተሳካ !

Aprl 10/201
4ሰሞኑንን በውስጥ መስመሬ የድረሱኝን መረጃዎች መስረት አድርጌ ሁለቱንም ወገኖች ከስልክ አንስቶ በአካል ለማገናኘት ያደረኩትን ሙከራ ዝርዝር መረጃ ከማቅረቤ በፌት ጥረቱ ጥረቱ የስመረ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የተጠቀሰውን የአፈላልጉኝ መለዕክት ህሊናቸው በብሄር ፣ በሃይማኖት ፣ በፖለቲካ ፣ ጽንፈኝነት ሳይታወር መልዕክቱን ሊንክ በማድረግ ወገናዊ ሀላፍነታቸውን ለተወጡ የፌስ ቡክ ተሳታፊ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ በ መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ ስም ከልብ የመነጭ ምስጋናዬን አቀራበልሁ ።
ከተጠቀሱት ግብረ ሰናይ የፌስ ቡክ ተሳታፊ ወገኖቼ በውስጥ መስመሬ ከአዲስ አበባ ፣ አስመራ ፣ ጀርመን ፣ ኖርዌይ ፣ ጣሊያን እና ሲውዲን «እስቶኮሆልም» ያሉ የፌስቡክ ወዳቾቼን ትበበር እና ድጋፍ አጊቻለሁ በዚህም መስረት ሱዳን ካርቱም ውስጥ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ ፎቶዎቸው ከተቀመጠው የመጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ ልጆች ጋር በእናት የምትገናኝ ታላቅ እህት እንዳላቸው ጥቆማ ደርሷኝ ፌቴን ወደ ካርቱም አዞርኩ ብዙም ሳይቆይ በውስጥ መስመሬ በድረስኝ ስልክ ቁጠር ባይታዋሩን የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ባልደረባ መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ቤተሰቦች በህይወት መኖር ለማጣራት ወደ ተጠቀሰቸው እህት ደወልኩ ። ለስልኬ እንግዳ የሆነባት እህት «ማንክበል» አለቺኝ ትግርኛ መሆኑ ነው እኔም ግራ እንዳትጋባ ያሉትን ነገሮች በሚገባት ቋንቋ እይተኮላተፍኩ በዝርዘር ገልጬ ስለራሷ እና ከ23 አመት በፊት ከባልተቤታቸው ተለየተው 3 ህጻናት ያለአባት የማሳደግ ሃልፌነት ስለተጣለባቸው ወላጅ እንቷ እና በእህት ወንድሞቾ ዙሪያ መረጃ ትሰጠኝ ዘንድ ጠይኳት ። ትግርኛ እንደማልቸል የተረዳቸው እህት አማርኛ ትንሽ ትንሽ እንደምትሞክር ገልጻልኝ በሚጣፍጥ የተኮለታተፈ አንደበት ታወጋኝ ጀመር ። ስሞ ወ/ሮ ናዝሬት መሆኖን ገልጽችልኝ እህት በአሁኑ ሰዓት ሱዳን ካርቱም በተለምዶ « ሃየል ሰሃፋ» እይተባለ የሚጠራ አካባቢ እንደምትኖር ገልጻ ደስታውንም ሃዘኑንም ጉንጮቼ በእምባ እኪሞሉ ሁሉንም ነግር ዝርዘር አድርጋ ሳትፈራ አጫወተችኝ ።
መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ በጣም የምትወዳቸው የእንጀራ አባቷ መሆናቸውን የምትናገርው ወ/ሮ ናዝሬት ኢትዮጵያን ለሁለት ገምሶ እናት አባትን ያለልጅ ልጀን ያለወላጅ አስቀርቶ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ካደረገው የኤርትራ ሪፈረደም በሃላ እንደተራራ የገዘፈውን የኤርትራ የኑሮ ወድነት ያለ አባት ለመግፋት መገደዳቸው ሳያንሳቸው ተዘርዝሮ የማያልቅ ስቃይ እና መከራ እንዳስለፉ ተነገረኝ ። አዎ ከአሰመራው ሪፈረደም በሃል አስመራ የኖሩ የነበሩ በሻዕቢያ ጸጉረ ልወጥ ተበለው የተፈርጁ ኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጸም የነበረውን ግፍ እና በደል በ1983 ኢ.አ የማየት እድሉ ገጥሞኝ ስለነበር ከ 23 አመት በፌት በወገኖቻን ላይ አስመራ ላይ የተፈጸመውን አስቃቂ ድርጊት ለሰዓታት ቆም ብዬ ለማስታወስኩ ተገደድኩ ።ብቻ ከዛ እልቂት መትረፍ እድል ነበር እና ከዚህ ሁሉ ሰቆቃ ያመለጠቸውን ህይወት « እሱ የፈጠራትን ነፍስ …..» እንዲሉ ተፍጨርጭረው አይናቸውን የግለፁት የመጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ልጆችን በአካል ባላውቃቸውም ከተነገረኝ አሳዛኝ ታሪክ አንጻር ከዛ እልቂት ተርፈው አሁን ላሉበት መብቃታቸው ለኔ ትገርት ሆነብኝ ። ለባለ ታሪኮቹ ደህነት ሲባል እዚህ ገጽ ላይ ሁሉንም ነገር ዘርዝሮ ማስፈሩ ተገቢ መስሎ ስላታየኝ ሙሉ ታሪኩን ባለማቅሪቤ እያዘንኩበዚህ አጋጣሚ አንባቢያንን ከወዲሁ ይቀርታ እጠይቃለሁ ።
ከመጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ልጆች መሃከል ሚኬኢል ጉርሜሳ የሚባለው አስመራ ውስጥ ካለው የኑሮ ውድነት እራሱን እና ቤተሰቡን ለመታደግ በኢትዮጵያ አድርጎ ሱዳን ካርቱም አብሯት እንደበር የምትናገርው ታላቅ እህታቸው ወ/ሮ ናዝሬት ህግወጥ በሆነ መንገድ ውቅያኖስ አቋርጦ አውሮፓ ለመግባት ከጓደኞቹ ጋር ወደ ሊቢያ ማቅናቱን ከስማት ውጭ ያለበትን ሁኔታ በግልጽ እንደማታውቅ ባቀረበችልኝ መረጃ ልቤ ክፉኛ ቢደናገጠም ያለአባት ያደገቸው ህጻን ምህረት ጉርሜሳ ዛሬ ወልዳ ከብዳ ወ/ሮ የሚል መአረግ ታክሎላት ከወላጅ እናቷ ወይኒቱ ወንድዬ ጋር አስመራ ከተማ ውስጥ አብረው በህይወት መኖራቸውን በማረጋገጤ ልቤ በደስታ ሃሴት ተሞልቷል ፡፤ ከዚህ ባሻገር ህጻን ገመቹ ጉርሜሳ ከአባቱ ከተለየ ወዲህ ስሙን ተወልደ መድህን ጉርሜሳ በሚል ለወጦ አስመራ ከተማ ውስጥ በህይወት መኖሩን የሚያሳይ መረጃ እጄ በመግባቱ ደስታዬ እጥፍ ድረብ አድርጎታል ፡ ፤ በአጠቃ ላይ የተጠቀሱትን ቤተሰቦች ከመጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ በስልክ አሊያም በአካል ለማገናኘት እየተደረገ ያለው ሙከራ ባይሳካም ጥረቱ ይቀጥላል ። በዚህ አጋጣሚ መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ የተጥቀሱትን ቤተስቦቾን የአስመራ ስልክ ቁጠር በፌስ ቡክ የውስጥ መስመር ማግኘት የሚችሉ መሆኖን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ !

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ « ከዚህ በታች የተመከተው ፎቶ 1 ) ሚኬኢል ጉርሜሳ እና ገመቹ ጉርሜሳ ወይም ተወልደ መድህን ጉርሜሳ መሆኑንን ገልጻለሁ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen