Netsanet: September 2014

Dienstag, 30. September 2014

በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ስም ከሚካሄደው ወንጀል ራስን ማራቅ የስደተኛ ወገኖቻችን ሃገራዊና ህዝባዊ ግዴታ ነው።


መስከረም 20/2007
እንደ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አይነት ገዳይ አናሳዎች በሚገዙት ሃገር ዜጎች ሰላም ስለሌላቸው፣ ጠዋት ወጥተው ማታን ለማየት ማረጋገጫ በማጣታቸው፣ የበይ ተመልካች ሆነው ለደናቁርት ሃጥዓን የወረደው የሃብት ማዕበል ከደጃቸው እንኳ ሲያልፍ ማየት እድል ባለማግኘታቸው፣ በከፋቸው ቁጥር የሚተነፍሱባት አደባባይ ተነፍገው ቁጭት በየቤቱ ሲያንገበግባቸው፣ የባሰባቸውም “ምን ይመጣል?” ብለው ለብሶት ብቅ ሲሉ መታነቅ ስለታከታቸው ፣ባህር ኣቋርጠው ከማያውቁት ሃገር ዜጋ እግር ስር መውደቃቸው በአጠቃላይም ስደት ለሚባለው አዋራጅ ስምና ህይወት መዳረጋቸው አይቀሬ ነው።
ቢርበዉም ቢጠማውም በታሪኩ ስደትን የማያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በመሪሩ የአምስቱ አመት የፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ዘመን እንኳ ሃገር ጥሎ አልጠፋም። በዱር በገደሉ ተሰዶ አርበኝነትን ወለደ፣ ለአርበኛው ነጻ ኣውጭ ደጀን ሆኖ አገለገለ እንጂ። ዛሬ ዴሞክራሲ በአሸንዳ በሚንቆረቆርባትና ህዝቦቿ በቀን ስድስት ጊዜ በልተው በሚያገሱባት አዲሲቷ የወያኔ
ኢትዮጵያ ተርቦና ተበድሎ የመኖር መብቱን ተነፍጎ መቀመጥ የታከተው ዜጋ፣ የባሰም ቢመጣ ሃገሬን ልልቀቅ ብሎ በባዕድ ሃገር የስደት ካምፖችን አጣቦት እንደሚገኝ ቢታወቅም፣ በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ስም ወገኔ ናቸው በሚላቸው ዘመን አመጣሽ ብልጣ ብልጥ በላዔ ብሮች እጅ መውደቁ ግን የበለጠ ታሪካችንን ያበላሸውን ያህል ይሰማናል።
በብዙሃኑ ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ የስደተኛ ገንዘብ የራሳቸውንና የመኪናዎቻቸውን ቀፈት ሞልተው የሃሰትን ተስፋ በየመንደሩ በመነስነስ ተራ እውቅናን ለመሸመት የሚሯሯጡትን ወንጀለኛ ግለሰቦች እናውቃቸው ስለነበረ ይህ ወገናችን በቀላሉ የነኝህ ሃሳዊ መሲሆች ሰለባ ሊሆን መቻሉ የበለጠ አሳስቦናል።
EPPF GUARD በሚል እያጭበረበረ የሚገኘው ልዑል ቀስቅስ እና ራሱን ሙሴ ተገኘ እያለ የሚጠራው ግለሰብ ሲሰሩት ከኖሩበት ደረቅ ወንጀል በተጨማሪም በሃሳዊ ፖለቲከኛነታቸውና በድርጅታችን ስምና በሌላቸው የአርበኝነት ገድል በመነገድ የእውነተኛ ሰፋሪ ስደተኞችን የጥገኝነት ማመልከቻ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ብሎም ለወደፊቱ ከጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ላይ መሆናቸው ለእውነተኛው ስደተኛ የብርሃን ግርዶሹ ይታየናል ። እነኝህ ከድርጅታችን ገረገራ ስር የነበሩ ግለሰቦች አለማዊ እንጂ ሃገራዊ ራዕይ ስላልነበራቸው ሰራዊታችን እንዳይደርሱብን ብሎ ያስወገዳቸው ሲሆኑ ሁሉም ሲወገዱና ወደፈለጉበት ሃገር እንዲሄዱ ሲሰናበቱ “ከኤርትራ ለቀን ወጥተናል” በማለት በየአጋር ድረ-ገጾቻቸው ላይ የሃሰት መረጃዎችን በትነዋል። የዜጎችን ትጥቅ ለማስፈታት ሞክረዋል፣ ባገኙት አጋጣሚ ከኛ ያገኙትን መረጃ በየድረ ገጾቻቸው ሳይቀር በመለጠፍ ለወያኔ የእጅ መንሻ አድርገውናል፣ የምንቀሳቀስባቸውን ስፍራዎች ሳይቀር በሳተላይት አስደግፈው ለጠላት ሰጥተውብናል።
ዛሬ በጥቂት ስደተኛ ወገኖቻችን ታጅበው “አባብዬ!” እስከመባል የደረሱት አባይ አዋቂዎች፣ በታሪካቸው አንድም የተሳካ ነገር አከናውነው የማያውቁና የምስኪን ስደተኛ ወገኖቻችንን ፎቶግራፍ በየድረገጾቻቸው ላይ በመለጠፍ መለመኛ እስከማድረግ የደረሱ፣ እርጉዝ በሚያስወርደው ገጻቸውና ገጸ ባህርያቸው በየኢንተርኔቱ የታጋይ ዜጎችን ስም በማጉደፍ ለጠላት ኢላማ ማስደረጋቸው፣ ያስቆጣናል። እየሞትን ባለንበት ድርጅታችን ስም እነዚህን ስደተኛ ወገኖቻችን በማታለል፣ የሃሰት ሰነድ በማዘጋጀት የነዋሪነት ፈቃድ ለማግኘት የሚደረገው ነውር ያሳስበናል። በተሰዉት እውነተኛ የህዝብ ልጆች ደም በመቀለድ አርበኝነትን ለጊዜያዊ የግል መጠቀሚያና ስሜት ማርኪያ መዋሉን ስንመለከት ውስጣችንን ያመናል። በመሆኑም፣ በጀርመን፣ በሲዊስ እንዲሁም በመላው አውሮፓ የምትገኙና፣ በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ስም በሚነግዱ ግለሰቦች ተወናብዳችሁ፣ ከእጃቸው የወደቃችሁ ስደተኛ ወገኖቻችን በሙሉ በትግል ተፈትኖ፣ የህዝብን ደም ደምቶና ሞቱን ሞቶ፣ ዛሬም ለመኖሩና መስዋዕትነትን እየከፈለ ለመሆኑ የተመሰከረለትን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርን በመደገፍና በመከተል ታሪካዊ ኢትዮጵያዊ ድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
________________________________________
የኢህአግ ዓለም አቀፍ ኃይል
EPPF international Force
የኢህአግ ዓለም አቀፍ ኃይል ኢሜል ይጠቀሙ
EPPF International Force contact email :-
eppf.international.committee@gmail.com
www.arbegnochginbar.org
በሌላቸው ድርጅት ድርጅት አለን፣ ባልታዩበት አውድማ ጦር አለን፣ እያሉ ዋሽተው የሚያስዋሿችሁንና ለውርደት ሊዳርጓችሁ ታጥቀው የተነሱትን የኢንተርኔት አርበኞች በመታገል የህዝባዊ ትግሉ አካል ትሆኑ ዘንድ ልባዊ መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
በወንጀለኛ ግለሰቦቹ ላይ እየተሰበሰበ ያለው የሃቀኛ ኢትዮጵያውያኑ ፔቲሽን እናንተን ፈጽሞ የማይመለከት በመሆኑ በጋራ ለሚደረገው አለም አቀፍ የተባበረ ትግል ሙሉ ተሳትፏችሁን ታበረክቱ ዘንድ በወደቁት ሰማዕታትና ዛሬም በየእስር ቤቱ ፍዳቸውን እየበሉ ባሉት ወገኖቻችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። 
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አዲስ ባደራጀው አለም አቀፍ ኮሚቴ ጥላ ስር ተሰባስባችሁ፣ ራሳችሁን፣ ድርጅታችሁንና ሃገራችሁን ትታደጉ ዘንድም ስንጠይቅ ማናቸውንም የድርጅታችንን ጉዳይ መወያየት እንዲችሉ ውክልና በሰጠናቸው ከሚከተሉት የየአካባቢው ተወካዮች ጋር በመወያየትና በመገናኘት የህጋዊው ድርጅታችን አካል ትሆኑ ዘንድም በአክብሮት
እንጠይቃለን። በተጨማሪም በምናገኛት ጠባብ ጊዜ ከምናዳብራት ድረ ገጻችንwww.arbegnochginbar.org ብቅ በማለት ገድላችንን፣ ወቅታዊ ዜናችንና መልክታችንን ትከታተሉ ዘንድ እንጋብዛለን።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
አንድነት ሃይል ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
መስከረም 20/2007

ሰበር ዜና መምህራንን ከስራ ቦታችው ማፍናቅል ትጀምሯል፡፡


የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ
ከሰሞኑ በተካሄደው ስልጠና እናተያያዥ ጉዳዮች ከመምህራን ጋር መስማማት ያልቻልው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎቸ በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ የተለያዩ ወጣት መምህራንን ስልጠናው በተሳካ ምክንያት እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቸ ውስጥ ድብቅ አጀንዳ ይዛቹህ ስትንቅሳቅሱ ተገኝታቹሀል በሚል ምክንያት የተነሳ ህወሀት መራሹ መንግስት የሚከተሉትን መምህራን ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ያለፍላጎታችው ተነስተው ወደ ገጠራማ ስፍራዎች እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባገኘው መረጃ መሰረት በግዴታ ዝውውር የተሰጣቸው መምህራን የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. መ/ር ይማም ሐሰን
2. መ/ር ሙለታ ዲንቃ
3. መ/ር ኤርሚያስ ተገኝ
4. መ/ር ሐይለ አምላክ ይገዙ
5. መ/ር ደምስ ግዛቸው
6. መ/ር አንዳርጋቸው ምህረቴ
7. መ/ር አንተነህ ንጉሱ
8. መ/ር ይስሀቅ ጉደታ
9. መ/ር መላኩ አበበ
10. መ/ር ዮሐንስ ካሳሁን
11. መ/ር ዳዊት የሺጥላ
12. መ/ር ዘሪሁን አላምረው ሲሆኑ ከትላንትናው እለት ማለትም 19/01/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ያለፍቃዳቸው መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በተመሳሳይ መንገድ በርካታ መምህራን ከስራ የመባረር እና ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መመደባቸው ይታወሳል

ሰበር ዜና መምህራንን ከስራ ቦታችው ማፍናቅል ትጀምሯል፡፡

                                     የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ
ከሰሞኑ በተካሄደው ስልጠና እናተያያዥ ጉዳዮች ከመምህራን ጋር መስማማት ያልቻልው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎቸ በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ የተለያዩ ወጣት መምህራንን ስልጠናው በተሳካ ምክንያት እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቸ ውስጥ ድብቅ አጀንዳ ይዛቹህ ስትንቅሳቅሱ ተገኝታቹሀል በሚል ምክንያት የተነሳ ህወሀት መራሹ መንግስት የሚከተሉትን መምህራን ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ያለፍላጎታችው ተነስተው ወደ ገጠራማ ስፍራዎች እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባገኘው መረጃ መሰረት በግዴታ ዝውውር የተሰጣቸው መምህራን የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. መ/ር ይማም ሐሰን
2. መ/ር ሙለታ ዲንቃ
3. መ/ር ኤርሚያስ ተገኝ
4. መ/ር ሐይለ አምላክ ይገዙ
5. መ/ር ደምስ ግዛቸው
6. መ/ር አንዳርጋቸው ምህረቴ
7. መ/ር አንተነህ ንጉሱ
8. መ/ር ይስሀቅ ጉደታ
9. መ/ር መላኩ አበበ
10. መ/ር ዮሐንስ ካሳሁን
11. መ/ር ዳዊት የሺጥላ
12. መ/ር ዘሪሁን አላምረው ሲሆኑ ከትላንትናው እለት ማለትም 19/01/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ያለፍቃዳቸው መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በተመሳሳይ መንገድ በርካታ መምህራን ከስራ የመባረር እና ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መመደባቸው ይታወሳል

የዋሽግተኑ ተቃውሞ ኢሳትን በዓለም ዓቀፍ ስመጥር የዜና አውታሮች ዝናው ገንኖ እንዲወጣ አደረገ፣ኤምባሲው ጉዳዩን ለፖሊስ አሳውቆ እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ አራት ኪሎ ያለ ይመስል ዋሽግተንን በተኩስ መናጡ አሜሪካኖችን ማናደዱ አልቀረም (የዋሽግተኑን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተመለከተ የጉዳያችን አጭር ዘገባ)

 

ፎቶ www.csnwashigton.com 

''መሣርያውን ወደሚከራከሩት ሰዎች ደገነ እና ተኮሰ'' ''He points the weapon at others who argue with him and fires'' ሮይተርስ ከዋሽግተን ዲሲ ዛሬ የዘገበው። 

ዛሬ መስከረም 19፣2007 ዓም ዋሽግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተቃዋሚ ኢትዮጵያውያን ቁጥጥር ስር ውሎ ባለ ኮከቡ ሰንደቅ ዓላማ በነፃው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተቀይሯል። ተቃውሞውን አስመልክቶ ኢሳት ዘግይቶ በለቀቀው ተጨማሪ ዘገባ ተቃዋሚዎቹ በኢምባሲው ውስጥ ዘልቀው የአቶ አንዳርጋቸውን እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ''ነፃነት! ነፃነት!'' ሲሉ አሳይቷል።

ቀደም ብሎ አምባሳደር ግርማ ብሩ በሸሚዝ እንደሆኑ ከሌሎቹ የኢምባሲው ሰራተኞች ጋር ቆመው ሲመለክቱም ሌላው የታየው ትዕይንት ነበር።ተቃውሞውን ተከትሎ የዓለም ስመጥር የዜና አገልግሎት ድርጅቶች ሮይተርስ  እና የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤ ኤፍ ፒን ጨምሮ የቪድዮ ምንጫቸው ኢሳት የኢትዮጵያውያን ቴሌቭዥን መሆኑን ከመጥቀሳቸውም በላይ የኢሳትን ሰበር ዜና የያዘ ቪድዮ በቀጥታ ለጥፈው ታይተዋል።በመሆኑም በዛሬው እለት ኢሳት በመላው ዓለም የዜና አውታሮች የመወሳቱን ያህል ከእዚህ በፊት በእዚህ አይነት ስፋት በመላው ዓለም በሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች የተጠቀሰ አይመስለኝም።

በሌላ በኩል በአሜሪካን ሕግ ሽጉጥ ተኩሶ ማስፈራራት አይደለም በአንደበቱ ለማስፈራራት የሞከረ የሚደርስበት ቅጣት ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል።ሆኖም ግን የኢምባሲው ሰራተኛ በተኮሰው ጥይት አካባቢውን በማሸበር እና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙ ዜጎችን በማስፈራራት ሕግ መጣሱን ለማወቅ ተችሏል።በአሁኑ ሰዓት ግን ግለሰቡ በቁጥጥር ስር መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየጠቀሱ ይገኛሉ።ሆኖም ግን ግለሰቡ የዲፕሎማቲክ ከለላ ካለው አሜሪካ በአጭር ጊዜ ከሀገር እንዲወጣ ልታደርግ ትችላለች።በመሆኑም NBC የዜና አገልግሎት የተኮሰው የኢምባሲ  ሰራተኛ መታሰሩን ገልጧል።ዜናውን ይህንን  በመጫን ማንበብ ይችላሉ።

ጉዳዩን ተከትሎ በነገው እለት ከኢትዮጵያ የሚወጣው  መግለጫ ይዘት ከወዲሁ መገመት አያስቸግርም።ሆኖም ግን ምንም አይነት መግለጫ እና ማብራርያ ቢሰጥ በአሜሪካውያንም ሆነ በምዕራቡ ዓለም ፅንሰ ሃሳብ አንፃር  ከጠቅላላ ጉዳዩ ውስጥ የኢምባሲ ሰራተኛው  ምንም አይነት የጦር መሳርያ  ባልያዙ በባዶ እጃቸው ተቃውሞ ባሰሙ ኢትዮጵያውያን ላይ  የጦር መሳርያ በመደገን የማስፈራራቱ እና በኃላም የመተኮሱን ያህል የጎላ እና አናዳጅ ነገር ነጥሮ አይወጣም። በመሰረቱ ዜጎች የሀገራቸውን ኢምባሲ ሲቃወሙ ይህ አዲስ አይደለም።እራሷ አሜሪካ የእራሷ ዜጎች ባልሆኑ ግን በሌሎች ሀገሮች ዜጎች ኤምባሲዋ ተውሯል።

በዲፕሎማሲው ዓለም ደግሞ አንድ ኢምባሲ በራሱ ሀገር ተወላጆች በተቃውሞ ቢናጥ ጉዳዩ የዓለም ዓቀፉን የቬና ስምምነት ከመመልከት  ይልቅ የአንዲት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ገንፍሎ የመውጣት አይነተኛ አመላካች ጉዳይ ከመሆን አያልፍም።ከእዚህ በዘለለ ኢምባሲው ጉዳዩን ለፖሊስ ደውሎ እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ አራት ኪሎ ያለ ይመስል ዋሽግተንን በተኩስ መናጡ ነው አሜሪካኖችን የሚያናድደው።

በመጨረሻም አንድ ነገር ማንሳት ይቻላል።ባራክ ኦባማ ከአቶ ኃይለማርያም እና ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ቁጭ ብለው ካወሩ ገና  ሳምንት ሊሆነው ነው።የዛሬው በመዲናቸው ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቃውሞ ያሰሙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ለኦባማም ጭምር የሚያስደነግጥ ነው። የኦባማ የአፍሪካ ፖሊሲ ዕውን በጥናት ላይ የተመሰረተ ነው? ላለመሆኑ ማሳያው የዛሬው ጠንካራ ተቃውሞ ነዋ!

ጉዳያችን
መስከረም 20/2007 ዓም (ሴፕቴምበር 30/2014)

Fox News: Shots fired outside Ethiopian Embassy in DC

በሰሜን አሜሪካ የሚገኝ ፎክስ የተሰኘው የቴሌቢዥን ጣቢ እንደዘገበው የኢትዮጵያን ሳተላይት ቴሌቢዥንን ( ኢሳት) በዋቢነት ተቅሶ በምስል አስደግፎ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በሀገር ቤት በወገን ላይ የሚፈፀመው ግፍና መከራ ለመቃወም በኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ ሰላማዊ ተቃውሞ አደረጉ ።
Fox News: Shots fired outside Ethiopian Embassy in DC
WASHINGTON – Shots were fired outside the Embassy of Ethiopia in D.C. on Monday afternoon. Fox News: ESAT TV an Ethiopian television network caught the shooting on camera while they were covering a protest at the embassy

Montag, 29. September 2014

ሰበር ዜና በዋሽንግተን ዲሲ የ ኢትዮጵያን ኢንባሲ ኢትዮጵያኖች ተቆጣጠሩት ባለ ኮከብ ባንዲራውን አውርደው ኮ ከብ የሌለበትን የ ኢትዮጵያን ባንዲራ ሰቀሉ

ሰበር ዜና  በዋሽንግተን ዲሲ የ ኢትዮጵያን ኢንባሲ ኢትዮጵያኖች ተቆጣጠሩት  ባለ ኮከብ  ባንዲራውን አውርደው  ኮ ከብ የሌለበትን የ  ኢትዮጵያን ባንዲራ  ሰቀሉ

ESAT Breeking News Ethiopian Embassy in DC Sept 29 2014

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ጨምሮ በርከት ያሉ የአረና አባላት የነበሩ አንድነትን ተቀላቀሉ

ፍኖተ ነፃነት
10468445_1563151703908775_2362047875547912265_n1. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ የዓረና ማ/ኮሚቴ ነበር
2. መምህር ገብሩ ሳሙኤል የዓረና ቁጥጥ ኮሚሸን አባል ነበር
3. ኦቶ ሺሻይ አዘናው የዓረና ማ/ኮሚቴ አባል ነበር
4. አቶ አስገደ ገ/ስላሴ የዓረና ሥራ አስፈፃሚ አባል ነበር
5. ኢንጂነር ዓብደልወሃብ ቡሽራ ማ/ኮሚቴ ነበር
6. ወ/ት ዘቢብ ተሰማ ማ/ኮሚቴ ነበር
7. አቶ ሰለሞን አባይ
8. ይልማ ይኮኖ እና ሌሎች የአረና አባላት ነበሩ በትናንትናው ዕለት አንድነት ፓርቲን በይፋ 
የተቀላቀሉ ሲሆን፤ የመቀሌ አንድነት ዞን ባዘጋጀው የእንኩዋን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ላይ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ ፀጋይ አላምረው፣ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት አቶ አሻግሬ መሸሻ እና አስራት አብርሃም ከአዲስ አበባ በእንግድነት ተገኝተዋል።በዚህ ወቅት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከዓረና ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተቻለ መጠን ሰላማዊና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ ማንም ሰው የፈለገውን ፓርቲ መልቀቅም ሆነ መቀላቀል መብቱ ቢሆንም ከአላስፈላጊ ሰጣ ገባ መጠንቀቅ እንደሚስፈልግ መተማመን ላይ ተደርሰዋል።
ትግሉ መተጋገዝና መተባበር ግድ የሚል በመሆኑ እንደከአሁን በፊቱ በዓረና ካሉት ጓዶች ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግኑኝነት ይኖረን ዘንድ በጣም አስፈላጊ ነው። ምንም ጥርጥር በሌለው ሁኔታ ነገር ተመልሰን የምንገናኝ፤ አንድ ሆን የምንቀጥል በመሆኑ፤ ከሁለቱም ወገን አብሮ የመስራቱ ጉዳይ መታሰብና መግባባት አስፈላጊ ነው።

10622825_1563151770575435_8226973651818742831_n

የታጋይ አንደርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።


የታጋይ አንደርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።

Sept 28, 2014
ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በአምባገነኑ ወያኔ እጅ ወድቆ መሰቃየት ከጀመረ 3 ወራት አልፈዋል። ባለፉት ቀናት የአውሮፓ ህብረት የሰበአዊ መብት ም/ቤት በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ውይይት አደርገዋል ። አንዳርጋቸው የፖለቲካ እስረኛ እና ለዲሞክራሲ፣ ለነጻነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ሰበአዊ መብት መከበር የሚታገል የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ሲሆን ባስቸኮይ ተለቆ ወደ እንግሊዝ እንዲመለስ ኮሚሸነር ተናግረዋል፡፡
የተከበሩ አና ጎሜዝ አንዳርጋቸው ብቻ አይደለም በርካታ ኢትዮጵያኖች ታስረዋል ብሎግ ዘጠኝ፣ ጋዜጠኞች፤ ፖለቲከኞች ሁሉም ካለ ምንም ምክንያት መፈታት አለባቸው። የኢትዮጵያን ፓርላማ ባለፈው ሂጄ አይቸዋለሁ በጣም የሚገርም ነው የፖለቲካ እስረኛ ሳይሆን ሽብርተኞች ናቸው ያሉን ሲሉ ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ነው። እስክንድር ነጋ ሽብርተኛ ሳይሆን አለም አቀፍ የብእር ተሸላሚ ነው። ብሎግ 9 ጸሃፊያን፣ ጦማሪያን ናቸው። አንዳርጋቸው ጽጌ የፍትህ ታጋይ ነው። ታዲያ እንዴት ነው የኢትዮጵያ መንግስት ህግን የሚተረጉመው ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በሁለት ወር ውስጥ ይህን ጉዳይና የኢትዮጵያን ሰበአዊ መብት በተመለከተ እና የአንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ የሚመለከት ኮሚቴ እንዲሰየም እና እንደገና እንደሚወያዩበት የወሰኑ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ አሳሳቢ በመሆኑ ከእንግሊዝ መንግስት ጋር በመሆኑ ለብቻ በሚቀጥሉት እናየዋለን ሲሉ ዘግተዋል።
በዚሁ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ቀርበው አሁንም የተለመደ ማስተባበያ ሰጥተዋል። እኛ ምንም አይነት ህግ አልጣስንም ብለዋል።

Sonntag, 28. September 2014

ኢትዮጵያዊያንና ትግላችን፤ (ትግሉ ወደፊት እንዲሄድ ምን ማድረግ አለብን? )

እስከመቼ ቅፅ ፲፯ ቁጥር ፲፯
አንዱ ዓለም ተፈራ
መስከረም ፲፭ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት  ( 9/25/2014 )
በስታቲስቲክስ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ዘገባ ማቅረብ ባልችልም፤ ባካባቢዬ ያለውን ሀቅ ተከታትዬ የሚኖረኝ ግንዛቤ፤ መንገዱኝ ይከፍትልኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ሰብስቤ፤ ይሄ ነው ብዬ የማቀርበው የጥናት ዘገባ የለኝም። ውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ስለሚፈልጉት ወይንም ስለሚያደርጉት ተጨባጭ ማስረጃ ያጠራቀምኩት ዝርዝር የለኝም። ነገር ግን፤ በመጀመሪያ እኔ ራሴ የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን አካል በመሆኔ፤ በዙሪያዬ ከምገናኛቸው እንደኔው የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ጋር ስለሀገራችን ሁኔታ እወያያለሁ። ለጥቆም በየድረ ገጹ የሚጻፈውን አነባለሁ። ባጠቃላይ በማንኛውም የዜና መለዋወጫ መንገዶች ሁሉ የሚካሄደውን የሀገሬ ጉዳይ ሳላሰልስ በቀን ሳይሆን በየሰዓቱ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ እከታተላለሁ። ከሞላ ጎደል ሁላችን በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ መለወጥ እንዳለበት እናምናለን። ከዚያ አልፎ እያንዳንዳችን ለዚህ ለውጥ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት እንዳለብን እናምናለን። እናም ዝግጁ ነን። ታዲያ እንዴት አድርገን ነው ይኼን ኃላፊነት፣ ፍላጎትና ዝግጁነት፤ በትክክለኛና በተሰባሰበ የአንድነት መንገድ ለትግሉ እንዲሠለፍ የምናደርገው?
በተከታታይ፤ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ በሀገራችን ያለው ምን ዓይነት መንግሥት እንደሆነና ምን ዓይነት ትግል እንደሚያስፈልገን በዚሁ ድረገጽ አስፍሬያለሁ። ( የጎደለና ያላነበቡ ካሉ፤ nigatu. wordpress.com  በመሄድ ሙሉ ጽሑፎችን መመልከት ይቻላል። ) በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል የማቀርባቸው ነጥቦች፤ ሀ) ይህ የወራሪ መንግሥት ሀገራችንንና ሥልጣኑን ወዶ እንደማይለቅ፤ ለ) ከዚህ መንግሥት ጋር የሚደረገውን ትግል፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ለስኬት እንደሚያበቃው፤ ሐ) ትግሉ በአንድ ማዕከል መመራት እንዳለበት፤ መ) ትግሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የነፃነት ንቅናቄ እንደሆነ፤ ሠ) ትግሉ የግድ የሰላም ትግል እንደሆነ እናረ) አሁን የተያዘው አወቃቀሩ የተሣሣተ የድርጅቶች መንገድ መሰረዝ እንዳለበት በመዘርዘር፤ ምን ማድረግ እንዳለብን አመላክታለሁ።
Tensaye
ሀ)      ይህ የወራሪ መንግሥት ሀገራችን እና ሥልጣኑን ወዶ አይለቅም።
አንዳንዶች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪውን መንግሥት ስለማይወደው፤ “በምርጫ አቸንፈነው ሥልጣኑን ይለቃል”፤ብለው ያምናሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪውን መንግሥት ስለማይወደው የሚለው፤ ትክክል ነው። ቀጥሎ ያሉት ሁለት ነጥቦች ግን አጠያያቂ ናቸው። በመጀመሪያ በምርጫ አቸንፈነው! የሚለውን እንመልከት። ምርጫን ማቸነፍ የሚቻለው፤ ትክክለኛ የሕዝብ ወኪልነትን ለማግኘት ትክክለኛ መፍትሔ መያዝ ቅድሚያ ያለው ሆኖ፤ ትክክለኛ የምርጫ ቅንብርና አስተማማኝ የአመራረጥ ሂደት ሲኖር ነው። የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም መንገድ ትክክለኛ የምርጫ ቅንብር እንዲኖር አይፈልግም። እንዳልነው ሕዝቡ አይወደውምና! ምርጫ የሰላም የፖለቲካ ትግልን መሠረት ያደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ፤ መንግሥቱ የኢትዮጵያ ሆኖ፤ የሚያስተማምን ሕጋዊ መንገድ ሲኖር ነው። ይኼ የለም።
ሰላማዊ ትግልን በተመለከተ፣ ያልተስተካከሉ ሁለት አፅናፋዊ አመለካከቶች አሉ። የመጀመሪያው “ሰላማዊ ትግል አይሠራም!” ብሎ አጠቃሎ የሚኮንነው ክፍል ነው። ሌላው ደግሞ “ሰላማዊ ትግሉን እንደ እንቁላል ተሽቆጥቁጦ አቅፎ መጓዙ!”ን ያመነበት ክፍል ነው። ሰላማዊ ትግል፤ በነዚህ መካከል ነው በተግባር የሚካሄደው። ሰላማዊ ትግሉን የሚያምኑ ታጋዮች፤ ባለው ሕገ መንግሥት ተገዝተው ማጌጫ፤ ያንገት ጌጥ የሚሆኑ አይደሉም። ማኀተማ ጋንዲ ወራሪ እንግሊዞችን፤ ፓርላማ እንዲያስገቡት ከምርጫቸው ውድድር አልገባም። በጥቅማቸው ላይ ተነስቶ አመጽ ነው ያካሄደው። እሰሩን እንጂ አናደርግም ብሎ ነው ያመጸው። “የናንተን ጨው ከምንቀበል፤ በእግራችን ረጂም መንገድ ተጉዘን የራሳችን እናገኛለን!” ነው ያሉት። ማርቲን ሉተን ኪንግና አፍሪቃዊ አሜሪካዊያን ሰላማዊ ታጋዮች ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ፤ ፕሬዘዳንቱና አቃቤው “እባካችሁ ታገሱን፤ እስካሁን ያገኘነውን ድል ያስተጓጉልብናል!” ሲሉ፤ “ያ የናንተ ጉዳይ ነው። ለኛ ከነፃነታችን የበለጠ የናንተን አቋም አክብደን ቦታ አንሠጠውም!” በማለት ሰልፋቸውን ቀጠሉ።
ሰላማዊ ታጋዮች እንግዲህ ዋና ዓላማቸውን ለማግኘት፤ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እያወቁ፤ እምቢታን ማስቀደማቸው ነው ትግሉ። ይህ ወራሪ መንግሥት ነው። በሱ ፓርላማ መግባትና አለመግባት፣ በዚህ ምርጫ ቁጥር ማግኘትና አለማግኘት፤ ዋጋ እንደሌለው ታሪኩ አስተምሮናል። ይህ ወራሪ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ ምንም ዓይነት የመግባባትና አብሮ ነገሮችን የመመልከት አእምሮ የለውም። ስለዚህ የምርጫ ጉዳይ ለሱ ጌጥ ከመሆን ሌላ ምንም ትርጉም የለውም።
ወራሪው መንግሥት የፈለገውን ገደብ ቢያደርግም፤ የሕዝቡ ታጋይ ክፍል ባንድነት የሚነሳበትን መንገድ ማበጀት አለብን። ለሕዝቡ የሚቀርቡት ምርጫዎች፤ ወራሪው በሚያዘጋጃቸው የሱ መደነቂያ መድረኮች ሳይሆኑ፤ ታጋዩ ክፍል በሚያዘጋጃቸው የራሱ መድረኮች መሆን አለባቸው። የራሱ መድረኮች በሙሉ ለራሱ የተዘጋጁ ናቸው። እኒህን ማስወገድና ከኒህ መራቅ አለብን። በታጋዩ ክፍል ለሕዝቡ የሚቀርቡት፤ ኢትዮጵያዊነት ወይንም የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆን አለባቸው። በዚህ ታጋዩ ራሱ በሚያዘጋጀው ምርጫ፤ ወገን ይለያል። አንድም ከሕዝቡ ጋር መቆምን፤ አለያም ከወራሪው ጋር መቆምን። ትግሉ በኢትዮጵያዊነት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆን አለበት። ይህ እንዳይሆን ወራሪው መንግሥት ሰማይ ይቧጥጣል፣ ይለምናል፣ ያስፈራራል፣ ጦር ይቀስራል፣ የማያደርገው ነገር የለም። እኛም ተመችተንለታል። ስለዚህ ራሳችንን ካላስተካከልን፤ ወደፊት መሄድ አይቻለንም። እናም በምርጫው ለሱ ጃኖ አልባሽ ከመሆን ይልቅ፤ የመውደቂያው አለት ድንጋይ እንዲሆን ማድረግ አለብን። በሱ ድግስ እናቸንፋለን የሚለው ተቀይሮ፤ የምርጫውን ምንነት በማሳወቅ በራሱ ድግስ መውደቂያዉን ለማዘጋጀት እንጣር።
በሌላ በኩል ደግሞ ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሥልጣኑን ስለመልቀቁ ነው። ይህ እኮ ወራሪ ነው። ወራሪ በየትኛው ታሪክና ቦታ ነው ወዶ ሥልጣኑን የለቀቀው? ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግምባር እኮ ሥልጣኑን የሚለቀው፤ መቃብሩ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው። እናም በአንድነት እንግፋው። ወዶ ይለቃል ማለታችንን ትተን፤ አስገድደን ለማስለቀቅ ወስነን በተግባሩ እንሰማራ። የምናስገድደው ጦር መዘን ሳይሆን በሕዝብ የአንድነት እምቢታ ነው። ጠመንጃችን እምቢታችን ነው። ይህ ወራሪ ሕግ ያወጣል መልሶ ያፈርሰዋል። የሚያውቀው ቢኖር እሱ ዘለዓለም ገዥ ሆኖ መቀመጥ እንዳለበት ብቻ ነው። ስለዚህ ምንም መያዣ መጨበጫ ስነ ሥርዓት የለውም። እናም በዚህ ወይንም በዚያ የሚለው መንገድ አይሠራም። ራሱ የገነባቸውን ሕጎች የሚያፈርስ መንግሥት፤ ለማናቸውም የሕዝቡ አቤቱታ ፈቱን ሠጥቶ ያስተናግደዋል የሚል፤ ራሱን መመርመር አለበት። የራሱን ሕጎች በማፍረሱ፤ ሕጎችን ማፍረስ ትክክል ነው! እያለ እኮ ነው። ሕዝቡ ለምን የሱን ሕጎች መከተልና ማከበር ይገደዳል? ይህ መንግሥት በምንም መንገድ ሥልጣኑን ወዶ አይለቅም።
አንዶንዶች በውጭ መንግሥታት ተገፍቶ ትክክለኛ ምርጫ ያደርጋል ብለው ያምናሉ። የውጭ መንግሥታት እኮ የቆሙት ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ነው። ለኢትዮጵያዊያን የተመሠረተና የቆመ የውጭ መንግሥት የለም። ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሎሌያቸው ሆኖ፤ የነሱን ጥቅም እስካስጠበቀላቸው ድረስ፤ በምንም መንገድ እንዲወግድባቸው አይፈልጉም። እኛኮ ዳር ደንበራችንን እናስከብራለን፣ ለሙን የሀገራችን መሬት ለራሳችን አራሾችና የመሬቱ ባለቤቶች እናስመልሳለን፣ ይህ ወራሪ መንግሥት ያለእውቅናው ያደረጋቸውን ሀገር የማስገንጠል፤ ወደብ የማሳጣት፣ የአባይን ዕድል በሌሎች እጅ የማስገባትና የመሳሰሉትን ዓለም አቀፍ ውሎች ልናፈርስ የተነሳን ነን! ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ብለን የተነሳን ነን! እንዴት ብለው እኛን ይደግፉ? ወይንስ የዋህነት ውጦናል? ስለዚህ፤ ለውጭ መንግሥታት አቤቱታ ማቅረባችንን ትተን፤ በአንድነት በመሰባሰብ፤ ጠንካራ ሆነን በመገኘት፤ ወደኛ እንዲመጡና እንዲለምኑን እናደርግ።
አንዳንዶች ዴሞክራሲያዊ አሠራር ሊከተል ይችል ይሆናል ብለው ያምናሉ። ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዲፈለፈል እንጠብቃለን ወይ? ምንነቱና የሕልውናው ምሰሶ የሆነውን ፀረ-ኢትዮጵያዊነት እንዴት አድርጎ ይገፈዋል? ምኞት ጥሩ ነው። ምኞት ገሃድ ሆኖ በራሱ ይቆማል ብሎ መጠበቅ ግን የዋኅነት ነው። ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም ተዓምር ዴሞክራሲያዊ አሠራርን ይጎራበታል ማለት ቅዠት ነው። በታሪኩም ሆነ ዛሬ፤ በዛሬው ዕለት በሚያደርገው ተግባር፤ ዴሞክራሲያዊነትን ከአጥሩ ወዲያ በጎሪጥ በጠላትነት የሚያይ ነው። የአዲስ አበባን መሬት እንዳሻው ከሕዝቡ እየነጠቀ ለራሱ ጄኔራሎችና ደጋፊዎች የሠጠ ድርጅት፤ ምን ይከተላል ብሎ ነው ዴሞክራሲያዊ አሠራርን የሚቀበል? ዴሞክራሲን ሊማረውም የማይችለው ጉዳይ ስለሆነ፤ በፀረ-ዴሞክራሲያነቱ እንደዳቆነ በዚያው ቀስሶ ይቀበርበት።
ለ)      ይህን ትግል፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ለስኬት የሚያበቃው።
የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከፋፈልና ይሄንን ክፍፍል ዘለዓለማዊ ለማድረግ፤ የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያልፈነቀለው ደንጋይ፤ ያልገባበት ጉድጓድ የለም። የዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን እምነቱ፤ “ደጋግሜ ካሰቃየኋቸውና ጊዜ ከወሰደ፤ የኔ ፍላጎትና ተግባር ዘለዓለማዊ ሆኖ ይቀመጣል።” ነው። “ኢትዮጵያዊነትን አጥብቀው የሚሟገቱለትን ግለሰቦች በማሰቃየትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠብቁ ድርጅቶችን መፈናፈኛ በማሣጣት፤ ደፍረው ወደ ኢትዮጵያዊነት የሚመጡትን ቁጥራቸውን እቀንስና፤ ያለትክ የሚያልፉት ሲያልቁ፤ ለኢትዮጵያዊነት ቋሚ አይኖርም።” ብሎ ነው። ይህ መንግሥት ምንም ዓይነት ጠንካራ እምነት በዚህ ላይ ቢኖረውም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን በነጠላው ጫፍ ቋጥሮ የያዛት ዕቃ ሳትሆን፤ በልቡ ውስጥ ያለ የደሙ ቀለም፣ የእምነቱ ማሠሪያ ስለሆነ፤ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ሕዝቡን ይዞ ይኖራሉ። የሚጠፋው፤ ጊዜ ያበቀለው የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከነመንግሥቱ ነው።
አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለው የወራሪና የተወራሪ ግዛት ነው። ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ አይደለም። ይህ እኔ በዚህ ተበድያለሁ ብሎ የራስን በደል የሚቆጥሩበት አይደለም። ይህ ርስ በርስ የምንወዳደርበት የቁንጅና ምርጫ ዝግጅት አይደለም። ይህ የወገን ደራሽ የሀገር አዳኝ ትግል ነው። ይህ ትግል እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊና እያንዳንዷን ኢትዮጵያዊት በአንድነት የሚያሰልፍ ትግል ነው። እናም ኢትዮጵያዊነት ነው። ስለዚህ ትግሉ ለድል የሚበቃው መላ ኢትዮጵያዊያን የኔ ብለን አብረን ስንነሳ ነው። ለዚህ ደግሞ የሁላችን ፍላጎትና እምነት የያዘ የትግል ራዕይ መቀመር አለበት። ባሁኑ ሰዓት ይህ ራዕይ አራት የትግሉ ዕሴቶችን ያካተተ ይሆናል።
አንደኛ፤           የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ መሆኑንና ሉዓላዊነቱን መቀበል ነው።
ሁለተኛ፤                  የኢትዮጵያን አንድ ሀገር እና አንድ ብሔር መሆን መቀበል ነው።
ሶስተኛ፤           የየአንዳንዱ/ዷ/ን ኢትዮጵያዊ/ት/ የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር መቀበል ነው።
አራተኛ፤                    በሀገራችን በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን መስፈን መቀበል ነው።
እኒህ ናቸው ሁላችን የምንጋራቸው አሁን የኢትዮጵያ መታገያ ዕሴቶቻችን።
ሐ)     ይህ ትግል በአንድ ማዕከል መመራት አለበት።
አሁን በፊታችን የተዘረጋው አንድ ትግል ነው። አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያን ወጥሮ የያዛት፤ ወራሪው መንግሥት በሕዝቡ ላይ የሚያደርገው በደል ነው። በዚህ በደል የሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በትግል ላይ ነው። ይህ ትግል በኢትዮጵያ ሕዝብና በወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መካከል ያለ ትንቅንቅ ነው። ትግሉ፤ ሕዝቡ ነፃ ለመውጣት፤ ወራሪው የፈለገውን በሕዝቡና በሀገሩ፣ በሕዝቡ ነፃነትና በሕዝቡ እምነት ላይ የሚያላግጥበትን ሁኔታ ለመቀጠል፤ እያደርጉ ያሉት ግብግብ ነው። ስለዚህ ያለው የትግል ሠፈር፤ ሁለት ብቻ ነው። አንዱ የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሠፈር ሲሆን፤ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠፈር ነው። እናም ትግሉ አንድና አንድ አጥር ብቻ ነው ያለው። የሚቻለው አንድም ከአጥሩ ወዲህ ሆኖ ከሕዝቡ ጋር መቆም ነው፤ አለያም ከአጥሩ ወዲያ ሆኖ ከወራሪው ጋር መቆም ነው።
ይህ በግልፅ የሚያሳየው የዚህ የወራሪ መንግሥት ጠላትና ድራሹን አጥፊ፤ ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሣሪያ ነው። ለዚህ የሚያስፈልገው ደግሞ አንድ ማዕከል ነው። ኢትዮጵያዊ ማዕከል። የትግሉ ማጠንጠኛ በሆነው ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ አንድ ማዕከል ማበጀት ነው። ይህ ሕዝባዊ ንቅናቄ ብቻ ነው፤ ሕዝቡን ለድል የሚያበቃው። ይህ ማዕከል ነው ትግሉን መምራት ያለበት።
መ)     ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቅናቄ ነው።
የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር ለማጥፋት፤ ድርጅት መመሥረትና መታገሉ አንድ ነገር ነው። መዋቅርና በዚህና በዚያ ማስፋፋቱ አንድ ነገር ነው። ቆም ብሎ፤ እያንዳንዱ የድርጅት አባል፤ ድርጅታችን ከተመሠረተ አንስቶ ምን ሠራን? ከጀመርንበት ነጥብ እስካሁን ምን ያህል ፎቀቅ አልን? ተሳክቶልናል? ወይንስ አልተሳካልንም? አደግን? ወይንስ ደከምን? የዚህ ሂደት ዕድገታችን መመዘኛው ምንድን ነው? ባገኘነው ስኬትስ ጠግበናል ወይ? እያልን መለካት አለብን። በዚህ ምርምራችን ደስተኞች ከሆን መቀጠሉ ተገቢ ነው። ካልተደሰትን ደግሞ፤ አንድም ድርጅቶቻችንን መቀየር አለያም ግባችንን መቀየር ይኖርብናል። አለያ ትግሉን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ተዘጋጅተናል ድርጅታችንም ጌጣችን ነው፤ ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ጊዜም በሚደርስበት በደል አንገቱን ደፍቶ አልተቀመጠም። በየወቅቱ በደሉን በመቃወም የተለያዩ ትግሎችን አድርጓል። ከነመንግሥቱ፣ ግርማሜ ንዋይና ወርቅነህ ገበየሁ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀምሮ፤ በተማሪዎች እንቅስቃሴ፤ በየክፍለ ሀገሮች የገበሬዎች መነሳሳትና በየካቲት ፷ ፮ቱ የታየው ሕዝባዊ እምቢታ የዚህ ምስከር ነው። በየጊዜው የተደረጉት መነሳሳቶች በተለያዩ ምክንያቶች ለስኬት አልበቁም። ይኼንን መርምረን ትምህርት መውሰድ አለብን። ሀገራዊ ውይይቶች የተደረጉባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ያማረ ውጤት ያስከትላሉ። ይሄን ለማድረግ ግን ጥረቶች አልታዩም። ለምን?
አሁንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች አሉ። ችግራቸው ምንድን ነው? ብለን አልጠየቅንም። ለምን? ለምሳሌ፤ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችን ለረጅም ጊዜ እየታጋሉ ነው። ይህ እንቅስቃሴያቸው በአብዛኛው የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት አለው። ታዲያ ለምን ግቡን አልመታም? በተጨማሪ፤ በኤርትራ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ እናደርጋለን ብለው የተነሱ ብዙ አሉ። እኒህም ለረጅም ጊዜ መግለጫዎችን ሲያወጡ ስምተናል። ለምን ከፍተኛ ደረጃ ላይ አልደረሱም? እንቀጥል። በውጭ ሀገር ያለን ኢትዮጵያዊያን ነፃነት፣ ጊዜ፣ ንብረት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ለወገን ተቆርቋሪነት ሞልቶናል። ታዲያ ለምን በአንድነት ተሰልፈን አልተነሳንም? ልጨምርበት። በሀገር ቤት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ። ለምን እንቅስቃሴያቸው ወደፊት አልተራመደም? በማዕከላዊነት ደግሞ፤ የየድርጅቶቹ መሪዎችና የትግሉ ልሂቃን፤ ለምን ይሄን ማድረግ እንዳልቻልን ጥናት አድርገን መፍትሔ ለምን አላቀረብም? ይሄ በተደጋጋሚ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።
ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልስ የግድ መኖር አለበት። እንግዲህ ሁሉም በያሉበት ያነሱት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎችን ነው። አንዱ ከሌላው የሚለየው፤ በራሳቸው ዙሪያ ብቻ ያለው ላይ ማተኮራቸው ነው። ቁም ነገሩ ግን የያዳንዳቸው ጥያቄዎች የሁሉም ጥያቄዎች ናቸው። የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የጠየቁት የመብት ጥያቄ ነው። መምህራንና ተማሪዎች የጠየቁት ይኼኑ ነው። ነጋዴዎች የጠየቁት መብትና እኩልነትን ነው። ይህ የሁሉም ጥያቄ ነው። ቤት ተከራዮችና ቤት ለመሥራት የተዘጋጁት የጠየቁት መብታቸውን ነው። ይሄ የሁሉ ጥያቄ ነው። በደቡብ የተፈናቀሉት ኢትዮጵያዊያንና በኦጋዴን የሚሰቃዩት ኢትዮጵያዊያን የጠየቁት ኢትዮጵያዊ መብታቸውን ነው። ይህ የሁሉ ጥያቄ ነው። ስለዚህ የጎደለው እኒህን ጥያቄዎች በማያያዝ የሁሉም ማድረግና ሁሉም በአንድ ላይ የሚነሱበትን ማዘጋጀቱ ነው። ሁሉም የመብት፣ የነፃነት፣ የሕግ፣ የእኩልነት ጥያቄዎችን ነው ያነሷቸው። ሁሉም የሁሉም ጥያቄዎች ናቸው። ስለዚህ ሁሉም በአንድ ላይ ሁሉንም ማንገብ ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው። የድርጅት ሚና ይሄን ማድረግ ነው። ድርጅት የራሱን መርኀ-ግብር ብቻ አንግቦ ለራሱ ሥልጣን ማግኛ መንገድ ማስላት ሲይዝ፤ ፉክክር ይነግሳል። በርግጥ ነግሷል። እናም ቁጥር ለማብዣ ያለው እሽቅድድም፤ ዋናው ቁም ነገር ሆኗል። ከዚህ መውጣት አለብን። ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳሳት ነው። የሕዝቡ ንቅናቄ ነው።
ሠ)     ይህ ትግል የሰላም ትግል ነው።
አሁን ያለንበትን የደበዘዘ የትግል እንቅስቃሴ ሕይወት ሠጥተን ወደፊት ለመጓዝ፤ ማመንና መከተል ያለበን የትግል ቅደም ተከተል ዝርዝር፤ በግልፅ መስፈር አለበት። ነፃነት የመጀመሪያው ነው። ወራሪውን፤ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ማስወገድ አለብን። የተለያዩ ክፍሎች በተለያየ መንገድ በትግሉ ተጠምደዋል። የተለያዩ ድርጅቶች በመድረኩ ተጋግረዋል። በትጥቅ ትግል ላይ “ተሰማርተናል” የሚሉም አሉ። እንግዲህ ማን ከማን ጋር እንደሚታገልና ድሉ በምን እንደሚተረጎም ግራ የተጋባበት ሀቅ በመካከላችን ሰፍኗል። ይህ ትግል ወራሪውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፤ ከዚያ ቀጥሎ ለሚመጣው ሥርዓትም ጭምር ነው። ወራሪውን ማስወገድ ብቻ የትግሉ ዋና ማውጠንጠኛ ማድረግ አጓጉል ነው። ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣው ሥርዓትም በእኩል ደረጃ መቀመጥ አለበት። አንድን ትግል በሌላ ትግል የመተካት አባዜ በሺታ ነው። ይህ ለኔ ብቻ ብለው በራሳቸው ድርጅት ተጎናንፈው የተቀመጡ ክፍሎች አጀንዳ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጀንዳ አይደለም። ስለዚህ የዚህ ትግል ባለጉዳዮች መላ ኢትዮጵያዊያን ነን። እናም ትግሉ አሁን ባለበት ደረጃ፤ ሰላማዊ ነው። የትግሉን ተሳታፊዎች መሰባሰብ እና አንድነትን መፍጠር፤ ዋና የቅድሚያ ተግባሩ ነው። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤት ነው፣ ሕዝቡ ሉዓላዊነቱ መጠበቅ አለበት፣ ሕዝቡ ትግሉን ይምራ ስንል፤ በአንድነት ሆነን ትግሉን ሁላችን እንቀላቀልበትና የሕዝቡን መብት እናስከብር ማለት ነው። “የኔ ድርጅት ሲያቸንፍ መብቱን ለሕዝቡ እሠጣለሁ።” የሚለው የቁጮ አባባል፤ ትናንት አልፎበታል። የዛሬ ሰዎች ነን። የዚህ ትርጉም፤ በቀጥታ ሲቀመጥ፤ “እኔ ገዥ መሆን እፈልጋለሁን በኔ ሥር ሆናችሁ እኔን ለማንገሥ ታገሉ።” ማለት ነው።
ረ)      አወቃቀሩ የተሣሣተው የድርጅቶች መንገድ መሰረዝ አለበት፤
አዎ! ሳይደራጁ ትግል የለም። ጣሊያን ፋሽስቱን የተጋተሩት ጀግኖች አርበኞቻችን፤ በየጎጡና በየመሪያቸው ከመንደር እስከወረዳ፣ ከወረዳ እስከ አውራጃ፣ ከአውራጃ እስከ ንጉሣቸውና ከንጉሣቸው እስከ ንጉሠ ነገሥታቸው ባንድ ሀገር፤ ባንድ መንግሥት ስም ተደራጅተው ነው። በየግሉ የሚደረግ እንቅስቃሴ ለድል አያበቃም። ከራሳችን ከዚህ ታሪክ የምንወስደው ትምህርት፤ ድርጅት ለወቅታዊ ጥያቄው መልስ የሚሆን መሣሪያ ነው። አሁን ደግሞ የሚያስፈልገን መሣሪያ፤ መላ ኢትዮጵያዊያንን በኢትዮጵያዊነት አሰብስቦ፤ በወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ላይ የሚያስነሣና፤ ለድል አብቅቶ የሽግግር መንግሥት የሚያቋቁም ነው። ይህ የሀገር ነፃነትን ለማስገኘት የሚደረግ መደራጀት ነው። ይህ መደራጀት የሚያስከትለው የሽግግር መንግሥት፤ ሕገ መንግሥት ተረቆ የሚጸድቅበት፤ ሕገወጥ በሆነ መንገድ የተደረጉት የወራሪው መንግሥት ዓለም አቀፍም ሆነ የሀገር ውስጥ ውሎችና ሕጎች የሚሰረዙበት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ምዝገባ ተደርጎ፤ እኒህ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትና ተቀባይነት የሚያገኘው ወገን ሥልጣኑን የሚያስረክብበት ወቅት ነው።
ለዚህ ሂደት የሚያስፈልገን ኢትዮጵያዊ የሆነ አንድ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ክፍት ነው። “ጉዳዬ ነው” ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግሉ ገብቶ የሚሳተፍበት ንቅናቄ ነው። መደራጀት ለሆነ ተግባር የሚደረግ የሰዎች መሰባሰብ ነው። አሁን በኢትዮጵያ የትግል ምኅዳር፤ ለዚህ ንቅናቄ ተወዳዳሪ ሌላ ድርጅት አይኖርም። ያሁኑ ሰዓት መደራጀት ሀገርን ነፃ አውጥቶ የሕዝቡን የበላይነት ለማስከበር ብቻ ካልሆነ፤ ኢትዮጵያዊም ሕዝባዊም አይደለም። ከዚህ ይልቅ የራሴን ድርጅት ነው የማጠናክረው ብሎ የሚሯሯጥ ድርጅት፤ ከወራሪው የትግሬዎች ነፃ ወጪ ግንባር የተለዬ አጀንዳ የለውም። አሁን ቅድሚያ ቦታ ያዥነት ኖሮኝ፤ ሌሎችን ዘግይተው ሲመጡ አቸንፋለሁ የሚል ድርጅት፤ ከመርኀ ግብሩና ከቆመለት ዓላማ ይልቅ ብልጣ ብልጥነትን የተካነ፤ ድርጅቱን ከሀገሩ ያስቀደመ፤ ግለኛ ድርጅት ነው። ይህ የሕዝብ ወገን አይደለም። ይህ ኢትዮጵያዊ አይደለም። እናም ይኼን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ንቅናቄ በአንድነት እንመሥርተው። ሃሳብ ላለው በ eske.meche@yahoo.com እገኛለሁ።

Samstag, 27. September 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ የዝግጅት ክፍል ባልደረባ መስከረም 18/2007 ዓ.ም (መስቀልን) ቃሊቲ ከሚገኙ ታሳሪዎች ጋር አሳልፈዋል፡፡


በወቅቱም አቶ በቀለ ገርባን፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳን፣ አዛውንቱን ሲሳይ ብርሌን፣ አቶ ጉታ ዋቆንና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን አግኝተዋል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ ከታሰሪዎቹ መካከል የተወሰኑትን መልዕክት እንደሚከተለው አቅርባለች፡፡ 

‹‹ህብረ ብሄር ፓርቲዎች ተጠናክረው የብሄር ፓርቲዎችን ማጥፋት አለባቸው›› አቶ በቀለ ገርባ

ከዝዋይ ወደ ቃሊቲ ከመጣሁ 11 ወራት ሆኖኛል፡፡ በህዳር ወር 2006 ዓ.ም ነው ወደ ቃሊቲ የመጣሁት፡፡ በአሞክሮዬ መሰረት ጥር 11 ቀን 2006 ዓ.ም መፈታት ቢገባኝም አሁንም ድረስ እስር ቤት ውስጥ እገኛለሁ፡፡ በወቅቱ በአሞክሮዬ መሰረት መፈታት እንዳለብኝ ለእስር ቤቱ ኃላፊዎች ደብዳቤ ጽፌ ነበር፡፡ ሊፉቱ ሲፈልጉ አስጠርተው ያነጋግሩሃል፡፡ ካልፈለጉ ደግሞ ዝም ይሉሃል፡፡ እኔ ደብዳቤ ብጽፍም አልተጠራሁም፡፡ ምክንያታቸውን ባላውቅም ሊፈቱኝ አልፈለጉም ማለት ነው፡፡ ግን በአሞክሮዬ ባለመፈታቴ አልተጎዳሁም፡፡ በርካታ ነገሮችን ተምሬበታለሁ፡፡ እንዲያውም የሚጎዱት እነሱው ራሳቸው ናቸው፡፡ በርካታ ታሳሪዎች አሳሪዎቹ ለቃላቸውም ሆነ በህጉ ተገዥ እንዳልሆኑ በእኔ ጉዳይ ተምረዋል፡፡ አሁን በመጋቢት ወር ዋናውን ፍርድ ጨርሼ እፈታለሁ ብዬ እጠብቃለሁ፡፡

እኔ የማምነው በባለሙያነቴ ነው፡፡ ፖለቲከኛ ነኝ ብዬ አላምንም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን እንደ ግለሰብ ፍትህን እሻለሁ፡፡ ስልጣን ላይ ማንም ይምጣ ማን ፍትህን የሚሰጥ ከሆነ ችግር የለብኝም፡፡ በሙያተኝነቴ ነው መቀጠል የምፈልገው፡፡ ነገር ግን ክፍቶች አሉ፡፡ ወደ ፖለቲካው የገባሁትም ክፍተቶችን በማየቴ ነው፡፡

ህብረ ብሄራዊ የሚባሉ ፓርቲዎች ለአብዛኛው ህዝብ ተደራሽ አይደሉም፡፡ የህብረ ብሄር ፓርቲዎች ድክመት ደግሞ የብሄር ፓርቲዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡ በእነሱ መዳከም ነው የብሄር ፓርቲዎች በየ ቦታው ለመመስረት እድል የሚያገኙት፡፡ ህብረ ብሄር ፓርቲዎች የአንድን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት አቅም የላቸውም ብሎ ያሰበ አካል/ሰው እወክለዋለሁ በሚለው ማህበረሰብ ስም ፓርቲ ያቋቁማል፡፡ እኔም በዚህ ክፍተት ነው ወደ ፖለቲካው የገባሁት፡፡ ይህ ችግር ባይኖር ማህበረሰብን ከፋፍሎ ‹‹ይህኛው ፓርቲ የዚህ፣ ያንኛው ደግሞ የዚህኛው ማህበረሰብ ፓርቲ ነው›› ተብሎ እንዲከፋፈል ፍላጎት የለኝም፡፡

ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች ቢጠናከሩ በአንድነት መታገልን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ከአንዱ ዓለም አራጌ ጋር በታሰርንበት ወቅት ‹‹እናንተ ከተጠናከራችሁ እኛ እንጠፋለን፡፡ እናንተ ተጠናክራችሁ በብሄር የተደራጀነውን ማጥፋት አለባችሁ፡፡ ተጠናከሩና እኛን አጥፉን፡፡ ያኔ ሁላችንም በአንድነት እንታገላለን፡፡ ችግሮችም ይፈታሉ›› እለው ነበር፡፡ የህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች አለመጠናከር እንጅ ለዚህኛው አሊያም ለዛኛው ህዝብ ብዬ መስራት አልፈልግም፡፡ በአንድነት መስራትን የመሰለ ነገር የለም፡፡

ህብረ ብሄር ፓርቲዎች በአንድ በኩል በመረጃ እጥረት፣ በሌላ በኩል በስህተት፣ አሊያም አይቶ በማለፍ የአንድን ማህበረሰብ ችግር ችላ ይሉታል፡፡ ይህ ነው ተነጣጥሎ ለመታገል፣ ለብሄር ፓርቲዎች መበራከት ምክንያት የሆነው፡፡ ህዝብ መብቱ እስከተከበረለት ድረስ ማን መጣ ማን ትኩረት አይሰጥም፡፡ ህብረ ብሄር ፓርቲዎች መዳከም ግን የብሄር ፓርቲዎች ተደማጭነት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗል፡፡ አሜሪካን ለምሳሌ ብንወስድ ህዝቡ መብቱ እስከተከበረለት ድረስ ጥቁር መራ ነጭ ችግር የለበትም፡፡ የእኛ አገርም ጉዳይ ተመሳሳይ መሆን ይችላል፡፡ በዚህ ላይ እኛ ወንድማማቾች ነኝ፡፡

እኔ ህብረ ብሄር ፓርቲዎችን እወቅሳለሁ፡፡ እነሱ ከተጠናከሩ በየቦታው በተናጠል የሚደረገው ትግል ወደ አንድ ጠንካራ ትግል ይመጣል፡፡ እነሱ ከተጠናከሩ በተናጠል የሚደረገው ጭቆና ይቀንሳል፡፡ ክፍተት ባይኖርና ህብረ ብሄር ፓርቲዎች ለሁሉም ህዝብ መድረስ ቢችሉ እኔ በሙያዬ በቀጠልኩ ነበር፡፡ እንዲህ የምንታሰረውም እኩ ከድክመታችን የተነሳ ነው፡፡ ጠንካራ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ቢኖረን እኮ እኛም አንተሰርም ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የአገራችንን ችግር መፍታት አንችልም፡፡ በተናጠል ለጭቆና እንዳረጋለን፡፡ በተናጠል እንታሰራለን፡፡ በሂደት ጭቆናውን እየለመድነው እንሄዳለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ለውጥ ማምጣት አንችልም፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ጭንቅ ላይ እንዳለች እርጉዝ ሴት ነች›› አቶ ሲሳይ ብርሌ

የተፈረደብኝ 13 አመት ነው፡፡ ከታሰርኩ አራት አመት ሆኖኗል፡፡ እድሜየ 65 ደርሷል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ችግር አለ፡፡ የእስር ቤቱን ኃላፊዎች የምናገኛቸው ህክምና ስንፈልግ ነው፡፡ ነገር ግን የህክምናው ጉዳይ ባይወራ ይሻላል፡፡ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በእርግጥ ውጭ ያለው ህዝብም በሰፊው እስር ቤት ውስጥ እንዳለ ነው የሚቆጠረው፡፡ ልዩነቱ የተሻለ ነፋስ ስለምታገኙ፣ ስለምትዘዋወሩና የፈለጋችሁትን ሰውም ስለምታገኙ ነው፡፡

እኛ እያረጀን ነው፡፡ ከእድሜያችን አንጻር በትግሉ ሂደት ብዙም የምንጨምረው ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ እናንተ ወጣቶች ናችሁ፡፡ ለትግሉ መሰረት የምትጥሉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ወጣትነት ለትግል ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ አባት ያላወረሰውን ልጅ ሊያስቀጥል አይችልም፡፡ እናንተ አሁን ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለልጆቻችሁም ጭምር ነው የምትታገሉት፡፡ እናንተ በርትታችሁ ካልታገላችሁ ልጆቻችሁ ምንም የሚወርሱት ነገር አይኖርም፡፡ አባት ያላወረሰውን ደግሞ ልጅ ምንም ነገር ሊያስቀጥል አይችልም፡፡ በመሆኑም እናንተ ከአሁኑ ለእውነት በመቆም ልጆቻችሁ የሚያስቀጥሉት ነገር መስራት አለባችሁ፡፡

ጭቆና እስካለ ድረስ እኔም ሆንኩ እናንተ ባንታገልም ጭቆናውን ለማስወገድ የሚነሳ ሰው አይጠፋም፡፡ እናንተን እድለኛ የሚያደርጋችሁ ጭቆናውን ለመግታት ፈልጋችሁ፣ በራሳችሁ ተነሳሸነት በመጀመራችሁ ነው፡፡

ጭንቅ ላይ ያለች እርጉዝ ሴት ካላማጠች አትገላገልም፡፡ ለእኔ ኢትዮጵያ ጭንቅ ላይ እንዳለች እርጉዝ ሴት ነች፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ከሚደርስባት ስቃይ ለመገላገል ማማጥ አለባት፡፡ ያኔ ትገላገለዋለች፡፡ ለዚህ ደግሞ ትግል ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶች መታገል አለባችሁ፡፡ ትግሉ ጥንካሬን ይጠይቃል፡፡ መጠንከር አለባችሁ፡፡

‹‹ተቃዋሚዎች በምርጫው ካላመኑበት ሁላችንም አንገባም ማለት አለባቸው›› አቶ ኦልባና ሌሊሳ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ ምርጫው ቀድመው መስራት አለባቸው፡፡ ምርጫ ስለመግባት አለመግባት ከመወሰናቸው በፊት ጠንክረው መስራት ይገባቸዋል፡፡ ውሳኔውን ከመወሰናቸው በፊት ውሳኔውን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ነገር ማሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ጉዳይ ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ ለውሳኔያቸው ደግሞ ተገዥዎች መሆን አለባቸው፡፡ አንዴ ከተወሰነ በኋላ ጠንካራ አቋም መያዝ አለበት፡፡ በህዝቡ አመኔታ ለማግኘት በውሳኔያቸው መጽናት አለባቸው፡፡ መወላወል አይገባም፡፡ ጊዜው እስኪደርስ ጠንክረው መስራት አለባቸው፡፡ በአንድ ወቅት 33 የሚባል ስብስብ ነበር፡፡ አሁንም ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለምርጫው በጋራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ተቃዋሚዎች በምርጫው መሳተፍ ለህዝብ የማይጠቅም መሆኑን ካመኑ እና መግባት የማያስፈልጋቸው ከሆነ በአንድነት ኃይልን አሰባስቦ ከምርጫው መውጣት ይቻላል፡፡ በምርጫው ካላመኑበት ሁላችንም አንገባም ነው ማለት ያለባቸው፡፡ በተናጠል ከምርጫው ራስን ማግለል ጥቅም አይኖረውም፡፡ በእርግጥ ይህ መወሰን ያለበት ጊዜው ሲደርስ ነው፡፡ እስከዛ ግን ጠንክረው መስራት አለባቸው፡፡

መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን በጣም እናመሰግናለን፡፡ ውጭ ያለውን የቤት ስራችሁንም ጠንክራችሁ መስራት አለባችሁ፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጊዜያትም እስር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ኢትዮጵያውያን መልዕክት ለማቅረብ ትጥራለች፡፡

እንኳን ለልማታዊው የደመራ አከባበር አደረሳቹ!

ከባህር ማዶ ነኝና ዛሬ የመስቀል በዓል እንደመሆኑ የአገር ቤት የደመራን በዓል በቀጥታ ለመከታተል እያቅለሽለሸኝም ቢሆን የወያኔን የቀጥታ ስርጭት መከታተል ጀመርኩ። ብዙም ሳልቆይ ግን ከወትሮው በተለየ አለባበስ ሁኔታ ለበዓሉ ድምቀት ከሚሰጡት ወትሮ ከምናውቃቸው የስንበት ትምህርትቤት መዘምራን በተጨማሪ የሃኪም ፣የኢንጅነር፣ የገበሬ፣ የተማሪ፣ የአስተማሪ፣የወዛደር... ምን የቀረ አለ?... ልብስ የለበሱ በርካታ ሰዎች በመዘምራኑ ተከበው ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመለከትኩ። መልዕክቱ ወዲያው ገባኝ። እንደገባኝም አልቀረ ካድሬው ጋዜጠኛ የኢትዮጲያ ቤተክርስቲያን ልማቱን ትደግፋለች፣ የሚደረጉትን ልማቶችን ትባርካለች፣ የመነኮሳት ልብስ ተላብሰው የሚታዩትም ስለልማቱ ሲጸልዩና ሲባርኩ ነው እያለ ሲደሰኩር... ሐይማኖታዊው የመስቀል ስርዓት መሆኑ ቀርቶ በደንበኛው የወያኔ እጅ የተቦካና የተጋገረ ልማታዊ የደመራ በዓል ስለሆነ ከዛ በላይ ማየት አላስፈለገኝም። ውስጤ ባዶ ሲሆን ተሰማኝ።
አማራና ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አከርካሪውን እንሰብራለን ሲሉን፣ አይ አማራም አደለሁ እምነትም በልብ ስለሆነ አይጠፋም ብዬ ዝም አልኩ። አማራም እየታደነ ከነህይወቱ ወደገደል ተጨመረ፣ተገደለ፣ከቀየው ተፈናቀለ፣ ዘሩም አንዲመክን ተደረገ። አድባራትም ተቃጠሉ፣መነኮሳትም ተዋረዱ፣ ቤተክርስቲያንም ተሰደደች። በመቀጠል ኦሮሞው ላይ ዞሩ።
የኦሮሞ ግንባር ሲፋቅ ኦነግ ነው እያሉ ገደሉት፣ አገር ጥሎ እንዲጠፋ አደረጉት፣ እስር ቤቶችን በኦሮሞ ልጆች ሞሉት። ኦሮሞ አይደለሁምና ዝም አልኩ። ማነው ባለሳምንት ብለው ደግሞ ሙስሊሙ ላይ ዞሩ።
የተሻለና ዘመናዊ የሆነ እምነት አመጣንልህ ተቀበል፤ ካልተቀበልክ ደግሞ እየተባለ በየመንገዱ ደበደቡት፣ እንደውሻ አሳደዱት፣ ሽብርተኛ ብለው አሰሩት። ሙስሊም አደለሁምና ምን አገባኝ አልኩ።
ማን ቀረ ከቶ፧ የጋምቤላና የሱማሌው ጭፍጨፋ፣ የአፋሩ፣ የደቡቡ ሁሉም በየተራ ተወረደበት። ከፋፍለውና ነጣጥለው መቱን፣ እርስ በርስ አባሉን፣አዳከሙን።
አንድ የቀረችኝ የማንነቴ መለያ የሆንችው እምነቴና እምነቴን የማሳይበት ባሕላዊ እሴት ብትኖረኝ እሷንም ዛሬ ተነጠኩ። ሲጀመር የጋራ የሆነውን የማንነት ታሪክ አበላሹት፣ ታሪክ አልባ አደረጉን። በመቀጠል ህዝብን ከህዝብ በማነሳሳት አለመተማመንን አብቅለው አንድነታችንን በማኮላሸት ነጣጥለው መቱን። ከዛ አቅም እንደሌለን ሲያውቁ አገሩን ለባዕዳን ቸረቸሩት። በገዛ አገራችን የበይ ተመልካች ሆነን ቁጭ አልን።
ከንግዲህ ምን ቀረኝ ? አገሬን፣ እምነቴንና ታሪኬን አጣሁ ማለት ነው። እንግዲህ እኔ ማነኝ ? የሚጣልለትን እየበላ የሚኖር እንስሳ ወይስ ከወደኩበት አቧራዬን አራግፌ በመነሳት እንደኔው ከተረገጠው ጋር ዘር ሃይማኖት ሳልል እጅ ለእጅ ተይይዤ ማንነቴን መመለስ፤ በተባበረ ክንድ የወያኔን ስርዓት አሽቀንጥሮ በመጣል በጋራ፣ በእኩልነትና በመቻቻል መርህ ኢትዮጲያችንን ከፍ በማድረግ ተከብረን መኖር ? ለመሆኑ ለመኖርና ላለመኖር ምርጫ ያስፈልገዋል እንዴ ?
ዋ... ኢትዮጲያዬ!
መጽሐፈ ሄኖክ፣ መስከረም ፩፮፣ ፪ሺ፯

Freitag, 26. September 2014

የአንድነት ፓርቲ የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳግም ተሰማ ተሰወሩ

September 26,2014

የአንድነት ፓርቲ የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳግም ተሰማ ከትላንት መስከረም 15 ቀን ጀመሮ መሰወራቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። « ዳግም፣ ድህንነቶች መኖሪያ ቤቱድረስ (ኦሎምፒያ) ሰሞኑን በዲኤክስ መኪና መጥተው ያነጋሩትንና ያስፈራሩትን አውግቶን ነበር፡፡ ይህንን ሲያወጋን ግን በራስ መታማመኑ እና ድፍረቱ ከራሱ ጋር ሆኖ ነው፡፡ ለዛሬጥዋት ፖሊስ ጋር ተጠርቶ ቀጠሮ ቢኖርበትም እሱ ግን ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ ሃሳብ ያካፍለን የነበረው በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች ነበር፡፡ ዳግም ጎበዝ፣ ረጋ ያለ፣ አስተዋይና ራሱንበዕውቀት ለማበልጸግ የሚጥር ወጣት መሆኑን አውቃለሁ» ትላንት ከአዲስ አበባ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እንደጦመረው ፖሊሲ በአቶ ዳግም ላይ ከፍተኛ ማስፈራራትና ክትትል ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያደርግ ነበር።
አቶ ዳግም ታስረው እንደሆነ ለማጣራት በተደረገው ሙከራ፣ አቶ ዳግም ቢያንስ አዲስ አበባ ባሉ እሥር ቤቶች መታሰራቸውን የሚያረጋገጥ ምን መረጃ አልተገኝም።
አቶ ዳግም መሰወራቸው እንጂ መታሰራቸው ገና ባይታወቅም፣ በፖሊስ መጠራታቸዉና ወከባ በርሳቸው ላይ መፈጸሙ ፣ አገዛዙ በአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ ጥንካሬ መደናገጡን  ፣ ይደረጋልተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የተመታና የተሰባባረ፣ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የማይችል፣ የአንድነት ፓርቲ እንዲኖር ለማድረግ ፣ የአመራር አባላቱን ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ፣  ከወዲሁ ሆን ብሎእየስራ መሆኑን አመላካች ነው።
አቶ ዳግም ተሰማ የሚመሩት የኦዲት ኮሚቴ፣  በቅርቡ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ሪፖርት አቅርቦ የነበረ ሲሆን ፣ ኮሚቴው ያቀረበዉን ሪፖርት ምክር ቤቱ እንዳጸደቀው፣ በስፋራውየነበሩ የአንድነት አመራሮች ይናገራሉ።
ከዚህ በፊት በነበራቸው  ሃላፊነት ተገምግመው  “ኤፍ” ያገኙትን ኢንጂነር ዘለቀ ረዲን፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ሌሎች በርካታ ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮች እያሉ፣  ለምንምክትል ሊቀመንበር አድርገው እንደሾሙ በመጠየቅ፣  የኦዲት ኮሚቴው ከፍተኛ  ትችት በሊቀመንበሩ ላይ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩም በኦዲት ሪፖርቱ ደስታኛ እንዳልነበሩም የደረሰን ዜናያመለክታል።
በአቶ ዳግም ላይ ፖሊስ ክትትል ማድረግ የጀመረዉም፣ የሚሰበስቡት ኮሚቴ የኦዲት ሪፖርት ካቀረበ በኋላ እንደሆነ ፣ ከዚያ በፊት ብዙ በፖሊስ ራዳር ያለነበሩ የአንድነት አመራር አባል እንደሆኑም ለማወቅ ችለናል።
ከሶስት ወራት በፊት የታሰሩት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ንቅናቀ ሰብሳቢ፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣  በአንድነት ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ዉስጥ ፣ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ የዉጭግንኙነት ስራቸውን መስራት እንዳልቻሉና መቀየር እንዳለባቸው ሐሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ፣ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ከስህተቶቻቸው ተምረው ሥራ  ላይ እንዲያተኩሩከማድረግ ይልቅ፣ ጭራሹን  አቶ ሃብታሙ አያሌውን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊያባርሩ እንደነበረም ለመረዳት ችለናል። ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት «የሚሰራና የሚንቀሳቀስ አመራር እንዴትእናስወጣለን ? » በሚል የኢንጂነር ግዛቸው ዉሳኔ እንዲቀለበስ አደረጉት እንጂ፣ አቶ ሃብታሙ ከአንድነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊባረሩ ይችሉ ለማወቅ ችለናል።
እንደዚያም ሆኖ ብዙም አልቆየም ፣ ከኢንጂነር ዘለቀና ኢንጂነር ግዛቸው ጋር ክርክር የገጠሙት አቶ ሃብታሙ አያሌው በሕወሃት/ኢሕዴጎች ለመታሰር መብቃታቸውም የሚታወቅ ነው።
በአንድነት የምክር ቤት ስብሰባ ኢንጂነር ግዛቸውና ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ያልተደሰቱበትን  ሪፖርት ፣ አቶ ዳግም ተሰማ የሚመሩት የኦዲት ኮሚቴ ባቀረበ በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ፣ አቶ ዳግም ተሰማመታሰራቸው፣  ብዙዎች በኢንጂነር ዘለቀና በኢንጂነር ግዛቸው ላይ ጥያቄ እንዲጠይቁ እያደረጋቸው ነው።
በተያያዘ ዜና የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ፣ ትግሉን ወደ ኋላ እየጎተቱት በመሆናቸው፣ ለአገርና ለትግሉ ሲሉ፣ ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው እንዲለቁ፣  በፓርቲዉ ዉስጥ ባሉ አባላትእንዲሆም ከፓርቲው ዉጭ ባሉ ለፓርቲው ቅርበት ባላቸው የተከበሩ ምሁራን ተማጽኖ እየቀረበላቸው እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።
ኢንጂነሩ በተለያዩ ሜዲያዎች «ለወጣቶች ሃላፊነቴን ነገ ለማስረከብ ዝግጁ ነኝ። የስልጣን ጥማት የለኝም»  በአንድ በኩል እያሉ፣ በሌላ በኩል ግን አብረዋቸው በታገሉ፣ አብረዋቸው ቃሊት ታስረውበነበሩ አንጋፋ ምሁራን ሲለመኑም «ከስልጣኔ  ፍንክች አልልም» የሚል አቋም እንደያዙም ለማረጋገጥ ችለናል።
ኢንጂነር ግዛቸው ሃሳባቸውን ካልቀየሩ በፍቃዳቸው በክብር የማይለቁ ከሆነ፣ በድርጅቱ ሕግና ደንብ መሰረት፣ በምክር ቤቱ ዉሳኔ ከሃላፊነታቸው ሊነሱ የሚችሉበት ሁኔታም እንዳለም የሚገልጹአንዳንድ ምልክቶች እየታዩ ነው።