Netsanet: የግንቦት ሰባት አመራር አባል በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ዙሪያ ኢትዮጵያ ሪቪው ያቀረበውን ሪፖርት አጣጣሉ

Mittwoch, 10. September 2014

የግንቦት ሰባት አመራር አባል በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ዙሪያ ኢትዮጵያ ሪቪው ያቀረበውን ሪፖርት አጣጣሉ

ኢትዮጵያ ሪቪው በቅርቡ ባወጣው ረፖርት፣ በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ዙሪያ የሻእቢያ እጁ እንዳለበት መዘገቡ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ ለኢትዮሜዲያ አስተያየት የሰጡት፣ የድርጅቱ አመራር አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ፣ ሪፖርቱን ልብ ወለድና የፈጠራ ወሬ ብለዉታል።
የኢትዮጵያ ሪቪው ዋና ኤዲተር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ፣ ሪፖርቱን ከማውጣታቸው በፊት አስቀድመው እርሳቸዉን ሆነ ሌሎች የግንቦት ሰባት አመራር አባላትን ቢያነጋገሩ ኖሮ ጥሩ ይሆን እንደነበረ የገለጹት አቶ ነዓምን፣ “ይህ ሪፖርት መዉጣቱ በኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ የሚደረግገዉን እንዲመጣ የሚደረገዉን ትግል ጎድቶታል” ሲሉም የተሰማቸውን ቅሬታ ለኢትዮሜዲያ ገልጸዋል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen