Netsanet: የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪውን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ

Mittwoch, 3. September 2014

የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪውን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ


ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ “ኮ/ል አለበል አማረ የድርጅቱ መስራችና ሊቀመንበር ሆነው
ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ ውጭ አገር ከሄዱም በሁዋላ ድርጀቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን” ካወሳ በሁዋላ፣ ድርጅቱ መስዋትነት
እየከፈለበት ያለው የነጻነት ትግል በቶሎ ግቡን እንዲመታ መሬት ላይ ወርዶ መታገሉ የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ ስላሚታመን በተደጋጋሚ
እንዲመጡ ቢነገራቸው ሊመጡ ባለመቻላቸውና አሁን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን ውጭ ሃገር ተቀምጦ መምራት ስለማይቻል ከድርጅቱ ሊ/መንበርነት
ወርደው በአባልነት እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምጽ ወስነናል “ብለዋል።
ድርጅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እንዲሰጠውም ጠይቋል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 በቅርቡ
ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen