Netsanet: ሕጋዊነትን ያልተከተለ ስርጭት

Mittwoch, 17. September 2014

ሕጋዊነትን ያልተከተለ ስርጭት


ማክሰኞ መስከረም 6፡ 2007
ቀደም ሲል (ሰባ ደረጃ) በሚል ርዕስ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በኦፊሻል ድረ ገጱ ላይ አዲስ ሙዚቃ መልቀቁ ይታወቃል። ነገር ግን የዚህን ስራ መዉጣት ተከትሎ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ከአርቲስቱ እዉቅና ዉጪ በሶሻል ሚዲያዉ ላይ የተሰራጨ ሕጋዊነት የሌለውና ከዘጠኝ አመት በፊት አርቲስቱ በሆላንድ አገር መድረክ ላይ የተጫወተዉን ጥራቱን ወይም ደረጃዉን ያልጠበቀ ሙዚቃ ባልታወቁ ወገኞች እንዲሰራጭ ተደርጓል። ይህ እንዲሆን ያደረጉት ወገኞች ምክንያትም ሆነ ምንጭ ለጊዜዉ ባይታወቅም፡ ጉዳዩ ከአርቲስቱ የኮፒራይት መብት አንጳር ሲታይ ሕጋዊነትን ያልተከተለ በመሆኑ እዉቅና የሌለዉ ስርጭት መሆኑን ለአርቲስቱ አድናቂዎችና ወዳጆች በሙሉ ለመግለጵ እንወዳለን።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen