Netsanet: ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ 250 ስደተኞች ሰጠሙ

Montag, 15. September 2014

ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ 250 ስደተኞች ሰጠሙ

ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ እንደገና በሚያሰቅቅ ሁኔታ 250 ያህል ስደተኞች ሳይሰጥሙ እንዳልቀሩ ተነገረ። ከሊቢያ ባህር ኃይል በኩል እንደተገለጠው ከሆነ 250 ያህል አፍሪቃውያን ስደተኞችን ያሣፈረ ጀልባ ሰጥሟል። እስካሁን የ26 ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ተችሏል። የባህር ኃይሉ ቃልአቀባይ እንዳለው፣ የብዙ ሰዎች አስከሬን ባህር ላይ ሲንሳፈፍ ታይቷል።

Flüchtlinge Mittelmeer 28.11.2013
በሌላ ዜና ፣ ዓለም አቀፉ የፈላስያን ጉዳይ ተመልካቹ ድርጅት (IOM) እንዳለው በ መርከቦች አደጋ ሳቢያ 700ያህል ወደ አውሮፓ ለመጓዝ በመንገድ ላይ የነበሩ ስደተኞች ሳይሰጥሙ አልቀሩም ።በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ቃል ድርጅቱ ጠቅሶ እንዳመለከተው፤ ባለፈው ሳምንት ፣ሰዎችን ከቦታ ቦታ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያሸጋግሩ ቡድኖች 500ሶሪያውያን፣ ፍልስጤማውያን፤ ግብጻውያንና ሱዳናውያንን ያሠፈረ ጀልባ ሆን ብለው እንዲሰጥም አድርገዋል። ይህም የሆነው ተሣፋሪዎቹ ባህር ላይ ወደሌላ አስተማማኝ ወደአልሆነ ጀልባ እንዲሸጋገሩ ተጠይቀው ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ነው ተብሏል። ሊቢያ ጠረፍ 200 ያህል ሰዎች የመስጠመቸውን ዜና IOM በማጣራት ላይ መሆኑን አያይዞ ገልጿል።
ተክሌ የኋላ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen