Netsanet: በትግራይ መቀሌ የሚደረገው የመምህራን ስብሰባ በመጀመሪያው ቀን ተቃውሞ ገጠመው

Freitag, 19. September 2014

በትግራይ መቀሌ የሚደረገው የመምህራን ስብሰባ በመጀመሪያው ቀን ተቃውሞ ገጠመው

                                    
(ፍኖተ ነፃነት) መምህራኑ በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ የተለያዩ አዳራሾች ተሰብስበው በ3 አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያዩ የተገለጸላቸው ሲሆን አጀንዳዎቹም፡-
1 . ስለተሃድሶ መስመራችንና የኢትዮጵያ ህዳሴ
2 . ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችንና ፈተናው
3 . የትምህርት ጥራትና ማነቆዎቹ የሚሉ ሲሆን ስብሰባው የሚቀጥለው ለ 7 ቀን እንደሆነና ቅዳሜና እሁድንም እንደሚጨምር ከመድረኩ መሪዎች ተገለጸላቸው፡፡ መምህራኑም እኛ ቅዳሜና እሁድ መሰብሰብ አንፈልግም ማረፍ አለብን በተጨማሪም እናንተ እየዞራችሁ ስትሰበስቡ አበል እንደምትወስዱት እኛም አበል ያስፈልገናል አበል አለው ወይ? የሚል ጥያቄ መምህራኖቹ አንስተዋል፡፡ ከመድረኩ መሪዎች አቶ ወልዳይ አሰፋ የመቀሌ ዞን ፀጥታ ኃላፊ እና አቶተካላይ የአዲሃውፂ ክፍለከተማ አስተዳደር የተሰጣቸው ምላሽ እኛ ወንድሞቻችን በረሃ ወጥተው ለሰላምና ዲሞክራሲ ብለው ታግለው ህይወታቸውን ሰውተዋል እናንተ ግን ለአንድ ሳምንት ለሚቆይ ስልጠና አበል ትጠይቃላችሁ እኛ አስተማሪዎችን፣ የፍትህ አካላት፣ አነስተኛና ጥቃቅን እና ሌሎችንም እንሰበስባለን ስብሰባው አገር አቀፍ ነው፣ ለዚህ ሁሉ አበል ሰጥተን እንዴት እንችላለን፣ ዓላማችን አንድ ነው ለምንድን ነው አበል የምትጠይቁት በማለት ሊያሳምኑ ሞከሩ ነገር ግን መምህሩ እኛ ጋ ሲደርስ ነው በጀት የሚያጥራችሁ እናንተ ግን በሀገሪቱ ሀብት እንደፈለጋችሁ ትጠቀማላችሁ በማለት የተቃወመ ሲሆን ነገ መምጣት አለባችሁ በሚል ኃይለቃል ከመድረኩ ቢገለጽም ስልጠናው ባለመስማማት ተበትኖዋል ሲል የመቀሌ የዜና ምንጫችን ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጾዋል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen