Netsanet: ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን፡፡

Dienstag, 15. April 2014

ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን፡፡

April 15/2014
ሠማያዊ ፓርቲ እሁድ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት የሚቆይ ከፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ጃል ሜዳ የሚደርስ ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ያዘጋጀ ሲሆን የሠላማዊ ሰልፉን ቀንና ሰዓትም በአዋጅ ቁጥር 031983 መሠረት ለሚመለከተው አካል በደብዳቤ በማሳወቅ ሰልፉን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን፡፡
ሰላማዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈጽሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶች የሠብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ለመንግስት አካላት በተደጋጋሚ ጊዜያት ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡
ይሁን እንጂ መንግስት እነዚህን ተከታታይ ጥሪዎች ተቀብሎ የማሻሻያ እርምጃ ከመውሰድና ችግሮችን ከመቅረፍ ይልቅ ጉዳዩን ችላ በማለት ችግሮቹ የበለጠ እየተባባሱ እንዲሄዱ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም እነዚህ ችግሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ለማድረግ ሠማያዊ ፓርቲ እሁድ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት የሚቆይ ከፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ጃል ሜዳ የሚደርስ ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ያዘጋጀ ሲሆን የሠላማዊ ሰልፉን ቀንና ሰዓትም በአዋጅ ቁጥር 031983 መሠረት ለሚመለከተው አካል በደብዳቤ በማሳወቅ ሰልፉን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይም ከዚህ ቀደም ተነስተው የነበሩ መንግስት በእምነት ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም፣ ዜጎች ከቀያቸው ማፈናቀሉ እንዲቆምና ዜጎቹ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ የሚሉ ጥያቄዎች የሚነሱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በገዢው ፓርቲ ስልጣን እንጅ ለህዝብ የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራታቸው ሕዝብ ለከፈለው ክፍያ አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም እያገኘ አለመሆኑም የውቅቱ አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን በተለይ የውሃ የመብራት የቴሌ ኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ሕዝብን እያመማረረ መሆናቸው በሠላማዊ ሠልፉ ላይ የሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
ለመሆኑ ይህን ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ ዘንድ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሲቪክ ማህበራትና ሚዲያው ከሚደረገው ጥረት ጎን መቆም ሀገራዊ ግዴታ እንዲወጡ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡
ሚያዚያ 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen